በጎንደር ብአዴን እና ሕዝቡ ያደረገው ስብሰባ ተጠናቀቀ

ሐምሌ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከሰሜን ጎንደር ሕዝብ የተወጣጡ ሽማግሌዎች ከብአዴን ባለስልጣናት ጋር ዉይይት ማድርጋቸው ይታወሳል። በዚህ ወይይት ሐምሌ 17 ቀን በጎንደር ሰልፍ እንደሚደረግ ሽማግሌዎች ባሳወቁት መሰረት የብአዴን ባለስልጣናት ሰልፉ ለ10 ቀናት እንዲራዘም መጠየቃቸውም ተዘግቧል።

ሰልፉ ለሐምሌ 24 ቀን እንዲሚደረግ ዘገባዎች በስፋት እየጠቆሙ ሲሆን አቶ በረከት ስምኦንን እና የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ያካተተ የብአዴን አመራር ከሕዝቡ ጋር በጎንደር ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት መወያየታቸዉንም ለማወቅ ተችሏል።

ከስፍራው የደረሱ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በስብሰባው የሕዝቡን አቋም ያንጸባርቁ የነበሩ ሲሆን፣ አቶ በረከትም ከሕዝቡ የተነሱ ብሶቶችና ጥያቄዎችን በማስታወሻ ደብተራቸው ላይ ማስፈራቸዉን ጠቁመዋል። አቶ በረከት የሕዝቡን ጥያቄ ይዘው እንደሚቀርቡና ተመልሰው መጥተው ለሕዝቡ ሪፖርት እንደሚያደረጉም ቃል ገብተዋል። “አንድ ደብተር ሙሉ ጥያቂያችሁን ፅፌ ይዤያለሁ ፣ ለሚመለከተው አካል ወስጄ አንድም ሳልቀንስ አቀርብና እንወያይበታለን። ከዛ መልሱን ይዤ ወደ እናንተ ተመልሼ እመጣለሁ” ነበር ያሉት።

ሕዝቡ ጌታቸው ረዳ የተባለው ግለሰብ እና ኢቢሲ በአማራው ክልል ህዝብ ላይ ሲያሾፉና ስድብ ሲዘነዝሩ እንዴት ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ሲሉም የብአዴን አመራር አባላትን አፋጠዉም ነበር። “ እንዴት ጌታቸው ረዳ የተባለ ጅል የአማራው ክልልን ህዝብ ሲሰድብ ዝም አላችሁ? እንዴት ብትንቁን ነው ይህን ትንሽ ሰው ሚኒስትር አድርጋችሁ የሾማችሁብን? ..” የሚሉት በጌታቸው ረዳ ላይ ከቀረቡት አቤቱታዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ነበሩ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጌታቸው ረዳና በኢቢሲ ሲቀርቡ የነበሩ ዘገባዎች አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸው ሕዝቡን በአሰቸኳይ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባቸው የገለጹ ሲሆን ፣ አቶ በረከትም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ እየቀረበ ያለው ነገር ብዙ እንደማይጥማቸው ለሕዝቡ ገልጿል።

ሌላው የብአዴን አመራር አቶ ብናልፍ አንዷለም የተባሉኢ ግለሰብ ሲናገሩ ላዳመጠ የትግራዩ አባይ ወልዱ የሚናገር ነበር የሚመስለው። የክልሉን ህዝብ እንደሚወክሉ ፖለቲከኛ ሳይሆን በጥቅም የተገዙ፣ የለየለት የህወሃት ካድሬ መሆናቸዉንም ነበር ያረጋገጡት። እንደ ወንበዴ በሌሊት መጥቶ ዜጎችን ለማፈን የተንቀሳቀሰውን አሸባሪ ቡድን በማሞገስ ” የፌድራል ፖሊስ ህጋዊ ነው…” የሚል የመሳሰሉትን ፍሬከርስኪ አስተያየት ለመስጠት ሲሞክሩም በተሰብሳቢው ጩኸት ንግግራቸው በተደጋጋሚ ተቋርጧል። ሰዉዬ በተናገሩ ቁጥር ሕዝብ እያስቆማቸው ምናምንቴ ነበር የሚመስሉት።

ከሕዝቡ ይሰጡ ከነበሩ አስተያየቶች መካከል፡

“ ይሄን ሁሉ ግፍ በሰፊ ትዕግስታችን ችለን ተቀምጧል ።አሁን ግን ትግስታችን ተንጠፍጥፎ አልቋል”
“ ህወሓት አንዳች እርምጃ እወስዳለሁ ብትል የሚመጣው አፀፋ የከፋ እንደሆን የጎንደር ሕዝብ መልክቱን በብአዴን በኩል ልኮላታል”
“ የህወሓት የበላይነት እስከ መቼ? ከአሁን በኋላ ኢህአዴግ አብቅቶለታል ፣ ኢህአዴግ የጎንደር እናቶችን ደም እምባ ያስነባውን የመላኩ ተፈራን ስራ በሕወሓት አማካኝነት በጎንደር ሕዝብ ላይ ደጋግሞ እያደረገው ነው “
“ወንድሞቻችንን ከወልቃይት ገፍታችሁና አባራችሁ፣ ጎንደር መጠው ቢጠጉ፣ ህዝብን ንቃችሁ አፍናችሁ ወስዳችሁ ፣ ህወሓት የጎንደር ሕዝብን በደንብ ታውቀዋለች እንግዲህ ይለይልናል ፣ “

ይገኙበታል።

ለ10 ቀናት ተላልፎ የነበረዉና እሁድ ሐምሌ 24 ቀን በጎንደር ክተማ ይደረጋል ተብሎ የታቀደው የሰላማዊ ሰልፍ ነገር፣ እነ በረከት በተገኙነት ስብሰብ ላይ ሳይነሳ ስብሰባው ተበትኗል። በእርግጥ ሰላማዊ ሰልፉ በታቀደለት ቀን እንደሚካሄድ ሕዝቡ የስማ እንደሆነ ከጎንደር የሚደርሱ መረጃዎች ሲጠቁሙ፣ በሶሻል ሜዲያም ቅስቀሳዎች በስፋት እየተደረጉ ነው።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሕዝቡ ወገን መሆናቸዉን አስመስክረዋል። አቶ በረከትም በርጋታና በአክብሮት ነበር ሕዝቡን ሲያዳምጡ የነበሩት። ምን ያህል ሕዝቡ እንዳከረረ በመረዳታቸው አቶ በረከት አዲስ አበባ ያሉ ጓደኞቻቸውን አሳምነው መሰረታዊ የፖለቲክ ለዉጥ እንዲመጣ በመጨረሻው ሰዓት የድርሻቸዉን አዎንታዊ ሚና ይጫወቱ ይሆናል የሚል ግምት ያላቸው ጥቂቶች ቢኖሩ፣ አቶ በረከት የተላኩት ጊዜ ለማራዘም እና ህዝቡን ለማዘናጋት ነው የሚለው አስተያእይት ግን አይሎ የሚሰማ አስተያየት ነው።

በኦሮሚያ የተነሳው ቀዉስ፣ ሰሞኑን የቀድሞ የሕወሃት ጀነራሎች ያቀረቧቸው ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎች ተደምረው፣ በኢሕአዴግ ዉስጥ ለዉጥ እንዲመጣ የማይፈለገውን አክራሪ ቡድን ወደ ጎን ተገፍቶ፣ ፔሪስትሮይካ በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚረዳ ሃይል ከኢሕአዴግ ዉስጥ ይወጣ ይሆን ? በቅርብ የምናየው ይሆናል። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው፤ ጨዉ ለራስህ ስትል ጣፍጥ እንደተባለው አራት ኪሎ ያሉ ባለስልጣናት ለራሳቸው ያስቡበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

8 Comments on “በጎንደር ብአዴን እና ሕዝቡ ያደረገው ስብሰባ ተጠናቀቀ”

  1. bua tekekle ya hewuahate ya blayenuate muakoume alubate!!! aye ato benalefe tasazenalahie!!! erasehene betatufa yeshalehale kua hezebe kuametelaye .

  2. Yes. It is up to the salt block to be teasty; otherwise, people will throw it as if it were a stone. But ANDM,like others, is already a living stone born from the womb of its mother- TPLF.So,nothing is expected from ANDM.They,too,are afraid, if change happens,of loosing their power and their illegally accumulated wealth from Amaras and of being accused of their wrong doings they committed on Amars for the last 20 years or so. So,we would raher rely on the people themeswlves than ANDM.

  3. ኮተታሞች ሽንታሞች ቅዘናሞች ወሬኞች ሁሌ ቁም ነገር የሌለው ውሬ? አንድ ቀን እንኳን እውነት አትናገሩም?

  4. በጎንደር ብአዴን እና ሕዝቡ ምንም አይነት ግንኝነት ያልነበራቸውና ወደፊትም ብአዴን አማራን የሚወክል ሳይሆን ወያኔን ብቻ ነው! አማራን ለቀቅ ወያኔን ጠበቅ ያድረግ እንጅ ብአዴን አማራን ከወያኔ አለቆቹ ጋር ተባብሮ ስንቱን የአማራ ልጅ አሳረደ፣አስገደለ፡፡
    አንድም ብአዴን ከአማራው ጎን መቆሙን የሚያሳይ ምልክት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም እና ለምን ስብሰባ ተቀመጠ
    አይሆንም ተው በሉት ብአዴን!
    ሳንጃው

  5. እኔ የምፈራው መሳሪያችሁን ያስፈቷችሁ እለት ጎንደር የደም ወንዝ ነው የምትሆነው አደራ አደራ እዚች ላይ በርቱ።

  6. ምላስ ምንም ዋጋ የለውም ሽንታሞች 1 ጎማ ቢፈነዳ ዱካቹ አይገኝም

  7. Hi Rubbish! Don’t insult one ethnic group. When people are starting stereotyping, they are starting dying and become moronic and Tazabi is one of them. If you are talking about heroism, please, please shut up. Please remember the recent history, even the war with Eritrean after independence. You know who rescue you. That war was waged with half heart as other Ethiopian were disappointed with the narrow politics the ruling party is exercising. Be mature and challenge issues don’t ethnics. If you sow, hate you will harvest very soon the reap.
    GOD BLESS THIS CONTRY and DEATH TO WOYANE! Zergaw

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*