የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው?
ተሻለ መንግሥቱ
በብሂለ ግዕዝ “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” ይባላል። አንዳንድ ነገሮችን በአፍ ወለምታም ይሁን በቴሌፓቲክ የነገሮች አፈጻጸም ሂደት ቀድመው ይጠቀሳሉ። መለስ ዜናዊ ስለአክሱም ሐውልት የይገባኛል ጥያቄና የባለቤትነት ይዞታ ሲናገር መረንን በማያውቀው ስድ አንደበቱ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ከፋፋይ ሃሳብ በገሃድ ተናግሯል። ለነገሩ መለስ ያልተናገረው ጠያፍ ነገር የለም። የአንዲት ሀገር መሪ ሆኖ ራሱን ሾሞ ሲያበቃ ሌሎችን እንደጨርቅ እርሱ የወጣትበን ጎሣ ግን እንደወርቅ መመሰሉን በአደባባይ ገልጾ እርሱና እርሱን መሰሎች ሀፍረትን ባያውቁም እኛ ስለነሱ አፍረናል።