ራያ ሌላኛዋ ወልቃይት፤ በአሁኑ ሰዓት ህወሓት ራያ ውስጥ የአማርኛ ስያሜ ያላቸውን ቦታዎች ቶሎ ቶሎ ወደ ትግሬኛ በመቀየር ስራ ተጠምዷል

ራያ ሌላኛዋ ወልቃይት ሆናለች።  በአሁኑ ሰዓት ህወሓት ራያ ዉስጥ የአማርኛ ስያሜ ያላቸውን ቦታዎች ቶሎ ቶሎ ወደ ትግሬኛ በመቀየር ስራ ተጠምዷል። አቶ ጌታቸው ረዳ የራያ ህዝብ የአማራነት ማንነትን ጥያቄ ሲመሩ የነበሩትን የሃገር ሽማግሌዎች ወደ መለስ ዜናዊ ቢሮ የማድረስ ሚና ተጫውተውያውቃሉ። ሽማግሌዎቹ ያኔ በአቶ መለስ የተሰጣቸው መልስ መሬቱ የትግራይ ነው። እናንተ ትግሬ መሆን ካልፈለጋችሁ ለቃችሁ ወደ አማራዉ ሂዱ የሚል ምላሽ ነበር።ቡድኑን ይመሩ የነበሩት አቶ ንጉሱ ቸኮል ከጠቅላይ ሚኒሲትሩ ፅ/ት ቤት እንደወጡ ወድያውኑ ተመርዘው እንዲገደሉ ተደርጓል።

የራያ አርሶአደሮች አማራ አማራ ትሸታላችሁ እየተባሉ የማዳበሪያ ሂሳብ ወድያዉኑ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ። እጅ በእጅ መክፈል ያልቻሉ በሬዎቻቸውን እንዲሸጡ፣ ገዥ አጣን ሲሉ ደግሞ አርደዉ ስጋዉን እንዲሸጡ ይደረጋሉ። ይሄን አድርገው የማዳበርያ ሂሳብ ካልሞላላቸዉ ደግሞ ልጆቻቸውን አረብ ሃገር ልከዉ እንዲከፍሉ ይመከራሉ።

የራያ ልማት ማህበርን የህዉሓት ደህንነት ክፍል በዐይነ ቁራኛ የሚከታተለው ተቋም ነው። ለዚህ ማህበር አባላት እለት ከእለት ዛቻና ማስፈራርያ እየደረሳቸው ይገኛል። የራያ ወጣቶችም ቢሆኑ ትግሬኛን ለመጠቀም ፍላጐት እንደሌላቸው በተለያዩ መድረኮች እያንፀባረቁ ይገኛሉ ። የራያ ህዝብ የአማራ ብሔርተኝነት እንዲህ እንዳሁኑ ሳይፋፋም አማራነታችንን መልሱ ብሎ ቀድሞ የወጣ ህዝብ ሲሆን የዛሬው የወልቃይት ህዝብ ተጋድሎ ወጋገን አዲስ ተስፋ ጭሮበታል።