ኢሕአፓ ለጎንደር ሕዝብ ትግል ሙሉ ድጋፉን ያረጋግጣል !!!

ኢሕአፓ ለጎንደር ሕዝብ ትግል ሙሉ ድጋፉን ያረጋግጣል !!!
#Ethiopia #Amharaprotests #EPRP #Gonderprotests #MinilikSalsawi
በኢሕአፓ የትግል ታሪክ ውስጥ ጎንደርና የጎንደር ሕዝባ ያላቸው ቦታ ከፍተኛ ነው ። የጎንደር ሕዝብ ኢሕአፓንም ሌሎች ሀገር ወዳድ ድርጅቶችንም ደግፎ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍሏል ። አራጁ መላኩ ተፈራና አረመኔው ደርግ ፤እንዲሁም ዘረኛውና ጸረ አማራው ወያኔ ይህን ታጋይና ሀገር ወዳድ ሕዝብ በተለየ ደረጃ አጥቅተውታል ። የጎንደር የሰማዕት ታሪክ የኢሕአፓ ታሪክ ማዕክል ሆኖም ቆይቷል ።
ኢሕአፓ በጎንደር እየተካሄደ ያለውን ጸረ ወያኔ ትግል ሙሉ በሙሉ ይደግፋል ። ወያኔም ማጥቃቱ፤ንብረታቸውን በእሳት ማጋየቱ፤ መሬትና ማንነትን ለማስክበር ቆርጦ መነሳቱን ያደንቃል ። የሕዝብ ቁጣ ሊያበርዱና ሊያሰናክሉ፤ ሰላም በሚል ቀረርቶ ትግልን ሊያኮላሹ፤ በፖለቲካና ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ማበር መደራጀት ሲገባ የጎጥ ሰልፍና ልማት ተብዬውን ሊሰብኩ የተነሱትን ሁሉ ኢሕአፓ ያወግዛል ። ወቅቱ የመራራና የቆራጥ ትግል ወቅት ነው ። ወያኔ ሕዝብን በጅምላ በመፍጀት ትግሉ ለማፈን መጣሩ የሚጠበቅ ነው ። በግድ ወደ ትግራይ የተጠቃለለው መሬትና ማንነቱ የተካደውም ሕዝብ ቆርጦ መነሳቱ የሚመሰገን ነው ። የአፍራሽና የቅጥረኞች አዞ እንባ ረግጦ ትግልን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ትግልን ለሚያውቀው የጎንደር ሕዝብ ሊያስተምር የሚቃጣ ሊኖርም አይችልም ።
ከጎንደር ሕዝብ ጎን በተጨባጭ መቆም ጊዜው አሁን ነው ። ሀገርን ማስመለስና ድንበርን ማስከበር፤ ማንነትን ማስረገጥ ለነገ የሚባል ትግል አይደለም ። በመሆኑም ኢሕአፓ በአካባቢው ያሉትን አባላትና ደጋፊዎች የትግሉ አካል ሆነው እንዲሰለፉ ጠርቷል ። በሰበብ አስባቡም ከወያኔ ጎን ቆመው የነበሩትም በጊዘ ከሕዝብ ጎራ እንዲቀላቀሉም ጥሪ ያደርግላቸዋል ። ይህ ጸረ ወያኔ ትግል መጠቃት የለበትምና ሀገር ወዳድ ሀይሎች ሁሉ– በያሉበት–ሊታደጉት፤ሊረዱት፡ሊያጠናክሩት መነሳት አለባቸውም ይላል ።
ከዚህ ተያይዞ መነሳት ያለበት ዋናው ጉዳይ ግን የጎንደር ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ባእዳን ዝምታን መምረጣቸውን ነው ። ጸረ አማራው የወያኔ ፖለቲካ ከእነዚህ ክፍሎች ከድሮ ጀምሮ ሲደገፍ የቆየ ነውና የሕዝቡ ትግል ማስተጋባትም ሆነ ለድል ማብቃት የኢትዮጵያውያን ግዳጅ ሆኖ ይገኛል ። የጎንደር ሕዝብ አመጽ ወያኔ ሊል እንደሞከረው የባዕድ ታጣቂ ሀይሎች እርምጃ ሳይሆን፤የማንም ድርጅት ድርጊት ሳይሆን የሰፊው ሕዝብ የእምቢታ ውጤትና አመጽ መሆኑ መታወቅም ያለበት ነው ።
ኢሕአፓ ከጎንደር ሕዝብ ጎን ተሰልፏል !!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
EPRP
P.O.BOX 73337 Washington DC, 20056 USA
Tel. 202 291 4217 Fax: 202 291 7645
Email [email protected]
Website www.eprp.com
EPRP
BP 30022
92276 Bois Colombes cedex
France
