የክብር ዶክትሬት ክብሩን እያጣ ነው ተባለ

የክብር ዶክትሬት ክብሩን እያጣ ነው ተባለ

 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ለተመረጡ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል Addis Admass

በሀገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዓመቱ ለሁለትና ሶስት ሰዎች የክብር ዶክትሬት መስጠትን እንደ ልማድ መያዛቸው ከክብር ዶክትሬት መሰረታዊ አላማዎች ጋር የሚፃረርና ክብሩን የሚያራክስ ነው ሲሉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ፡፡
የክብር ዶክትሬት የሚሰጥባቸው መስፈርቶች በመርፌ ቀዳዳ ግመል እንደ ማሽሎክ ያህል ናቸው ያሉት ምሁራኑ፤ በአሁን ወቅት አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር ፉክክር በሚመስል መልኩ ዶክትሬቱን የሚሰጡበት አካሄድ በአስቸኳይ ሊታረም እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
የክብር ዶክትሬቱ የተሰጠባቸው ግለሰቦችም ለስም መጠሪያነት መጠቀማቸው ተገቢ አይደለም ያሉት ምሁራኑ፤ መገናኛ ብዙኃን የክብር ዶክትሬት የተሰጠውን ግለሰብ፤ “የክብር ዶክተር” እያሉ መጥራታቸውም አግባብ ባለመሆኑ ማረም ይኖርባቸል ብለዋል፡፡
የቋንቋና ስነ ፅሁፍ ምሁሩ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ፤ ከሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ለተለያዩ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት የሚሰጥበት ሁኔታ፤ ከማዕረጉ መሰረታዊ አላማ ጋር የተቃረነ መሆኑን አለማቀፍ ልምዶችን በማጣቀስ አስረድተዋል፡፡
በአሁን ወቅት በትምህርት በቅተዋል ተብለው ዶክትሬት ዲግሪ የሚሰጣቸው ምሁራን ምን ያህል ችግር ፈቺ ምርምር ሰርተዋል የሚለው ራሱ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ የጠቆሙት ዶ/ር በድሉ፤ የክብር ዶክትሬት የሚሰጠው አንድ ግለሰብ ተምረው ዶክተር ከሆኑት ባልተናነሰ ሁኔታ ማህበረሰባዊ አስተዋፅኦ ሲያበረክትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡
“ማዕረጉ በመደበኛ ትምህርት ከሚገኘው ዶክትሬት ይበልጣል” ያሉት ምሁሩ፤ በዋናነት ከራሱ ማህበረሰብ ባለፈ ለዓለም ህብረተሰብ ያበረከተው አስተዋፅኦና በአለማቀፍ ደረጃ ያለው ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከግምት ገብቶ ነው የክብር ዶክትሬቱ የሚሰጠው ብለዋል፡፡ “ማንም ሰው ከተማረ ዶክትሬቱን ያገኘዋል፤ ማንም ሰው ግን “የክብር ዶክትሬትን” ሊያገኝ አይችልም ያሉት ዶ/ር በድሉ፤ በኛ ሀገር ግን ክብሩን እንዲያጣ ተደርጎ እየተቀለደበት ነው ብለዋል፡፡
የክብር ዶክትሬት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ መስፈርቶች የጠቆሙት ዶ/ሩ፤ ግለሰቡ ከትውልድ  ሀገሩ አልፎ እንደ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ አበበ ቢቂላ እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት ምስረታና ከሊግ ኦፍ ኔሽን ምስረታ ጋር ተያይዞ ስማቸው የሚነሳው አፄ ኃይለ ሥላሴ አይነት አለማቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሲሆኑና ለአለም ያበረከቱት አስተዋፅኦ ለሌላው አርአያ ይሆናል ሲባል ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመረው አካሄድ ግን ወደ አካባቢ ተወላጅነትና ጎሳ እየወረደ መምጣቱን በመጥቀስ፤ ምን አስተዋፅኦ እንዳበረከቱ በጉልህ ያልተገመገሙ ግለሰቦች ጭምር  እየተሰጣቸው መሆኑ የክብር ዶክትሬቱን ከአላማና መርህ ውጪ አድርጎታል ብለዋል፡፡ አብዛኞቹ የክብር ዶክትሬቱ የተሰጣቸው ግለሰቦች ይገባቸዋል የሚል እምነት እንደሌላቸው የጠቆሙት ምሁሩ፤ በሙዚቃው ዘርፍ ከጥላሁን ገሰሰና ከአስቴር አወቀ ውጪ ሌላ ይገባዋል ብዬ የምቀበለው ሰው የለም ብለዋል፡፡ የዶክትሬት ዲግሪ መርሃ ግብር የሌላቸው ዩኒቨርሲቲዎችም የክብር ዶክትሬት መስጠት እንደማይችሉ ዶ/ር በድሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የዶ/ር በድሉን ሃሳብ የሚጋሩት የህግ ምሁሩ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ በበኩላቸው፤ ጉዳዩ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኗል ይላሉ፡፡ በሁለት መንገድ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ የጠቆሙት ፕ/ር ጥላሁን፤ በስነ ፅሁፍና በኪነ ጥበብ አለማቀፍ ተፅዕኖ የፈጠሩና በአገር አቀፍና በአለማቀፍ ደረጃ በተሰማሩበት ሙያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሰዎች ናቸው ለማዕረጉ የሚመረጡት፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት ፀሐፊ ሆነው ማገልገላቸውን የሚያስታውሱት ፕ/ር ጥላሁን፤ በደርግ ዘመን የክብር ዶክትሬት መሰጠት ቆሞ እንደነበርና ዳግም ካስጀመሩት አንዱ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በስነ ፅሁፍ ለደራሲ ከበደ ሚካኤልና ኋላም ለደራሲ ሀዲስ አለማየሁ መሰጠቱን ያስታውሳሉ፡፡
የክብር ዶክትሬት የሚሰጠውን ግለሰብ ለመምረጥ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ እንደሚደክሙና ምናልባትም ለበርካት አመታት መስፈርቱን የሚያሟላ ግለሰብ ላይገኝ እንደሚችል የተናገሩት ፕ/ሩ፤ አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ጉዳዩን የፉክክርና የባለስልጣናት እጅ መንሻ እያደረጉት ይመስላል ብለዋል፡፡ በአካባቢ ተወላጅነት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል ያሉት ምሁሩ፤ ከሰሞኑ እየተሰጡ ያሉ የክብር ዶክትሬቶች ፖለቲካ ፖለቲካ የሚሸቱ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ መስፈርት ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸው ግለሰቦች ማዕረጉን ፈፅሞ ለመጠሪያነት ሊጠቀሙበት እንደማይገባ ሲናገሩም፤ “የክብር ዶክተርም” ሆነ “ክቡር ዶክተር” የሚለው አጠራር ፈፅሞ ስህተት ነው ብለዋል – ፕ/ር ጥላሁን፡፡
በንጉሡ ዘመን እንደ ሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ሴዳል ሴንጎር ላሉት የነፃነት ታጋዮች የክብር ዶክትሬቱ መሰጠቱን ያስታወሱት ምሁሩ፤ በወቅቱ ክብሩ ተጠብቆ እንዲቆይ እንደ ብርቅ ነበር የሚታየው፤ የአሁኑ አካሄድ ግን ልጓም ያጣ ሆኗል፤ በአስቸኳይ ሊስተካከልና ሊታረም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ሌላው አስተያየታቸውን የሰጡት የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፤ ዩኒቨርሲቲ ማለት “ዩኒቨርሳል” ከሚለው ቃል እንደመሰየሙ አለማቀፍ ባህሪ እንጂ አካባቢያዊ ባህሪ እንደሌለው አውስተው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዘርና ጎሳ እየወረደ መምጣቱ ክብሩን አሳጥቶታል ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ለግለሰቡ ሲሰጥ ዩኒቨርሲቲውንም የሚያስከብር ይሆናል ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ ዩኒቨርሲቲዎቻችን አካባቢያዊ በመሆናቸው ከዚሁ የአካባቢያዊ ስሜት በመነጨ ለየአካባቢያቸው ተወላጆች ለመስጠት መሽቀዳደማቸው አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ ከክብር ዶክትሬት አሰጣጥ አላማና መርህ ጋርም ፈፅሞ የሚሄድም አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በዛሬው እለት በተለያዩ የትምሀርት ዘርፎች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች የሚያስመርቀው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ለተመረጡ ግለሰቦች የክብር ዶክትሬትን እንደሚሰጥ ጠቁሞ የክብር ዶክትሬትን ለመጠሪያነት መጠቀም አግባብ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሚሰጠውም አንድ ግለሰብ “እኔ የክብር ዶክትሬት ይገባኛል” ብሎ ሲያመለክት ወይም ሌላ አካል ጥቆማ ሲያቀርብ፤ የግለሰቡ አስተዋፅኦ ተገምግሞ መሆኑን የገለፀው ዩኒቨርስቲው፤ በተቋሙ ይገባቸዋል የሚባሉ ግለሰቦች ሊመለመሉና ማዕረጉ በሴኔት ውሳኔ ሊሰጣቸው ይችላል ብሏል፡፡
ሰሞኑን ተማሪዎቻቸውን ያስመረቁት የወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ለአቶ አዲሱ ለገሰና ለሙዚቀኛዋ ማሪቱ ለገሰ የክብር ዶክትሬት ሠጥቷል፡፡ አክሱም ዩኒቨርሲቲም ለአቶ ስብሃት ነጋ የክብር ዶክትሬቱን ሲሰጥ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፤ ለሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ መስጠቱ ታውቋል፡፡

32 Comments on “የክብር ዶክትሬት ክብሩን እያጣ ነው ተባለ”

  1. Diasporawoch besntu temqgnetachu
    Qentachu letmotu
    neaw ? Ine Dr. Sebhat Nega abatih
    sayweld Degree yenebrew neaw. EPRDF yalut TEGADALAYoch Satfeter Haile Selassies best
    Students yenberu
    nachew. Siyansachew
    neaw.

  2. ende !! Mehamud ye kiber Dr aygebawim ?????

    ke Aster aweke gar Mehamudn

    manetater

    Dubana qil ,, leye qil new !!!

    AYE ZEMENE mehayem weyane kkkk

  3. professor samora,professor addisu,professor Arkebe,professor sibhat, professor meles zenawi, Professor TPLF……

  4. The thing that struck me is about
    those hopeless and desperate thieves of Gim -7 supporters who demonized our hero
    Dr. Tilahun Gessese
    and spouse simply he was awarded
    as Doctor.
    KINA YALEW BENATU
    IMMES YEKENAL ALU

  5. Ginbot 7 hezbachin
    Tefto ketalw senbtoal. Aydelem
    Ande Esat 40 Esat bitkeftu waga yelachum Shabiam gizew siders yewerewurachoal.
    Minem Ethiopia Ethiopia atshetum

  6. Andandie siyasbut
    Ager yelelw kemehon
    yebelet frustrate
    Yemiyadrg yale aymeslegnem.
    Bihonm letelat banda barriya kemihon motin imertalhu Doctor
    negne yemilew Berhanu zemed kalew Memehir Girma ga betam Sybasebet
    biwesd yeshalal

  7. Andandie siyasbut
    Ager yelelw kemehon
    yebelet frustrate
    Yemiyadrg yale aymeslegnem.
    Bihonm yaflegw bihon bagerie lgenzb almotim.
    Yqum Mot.

  8. Adissu Legesse & Sibehat Nega Dr.yetebalut sewin selegedelu newe
    lela minseru ebakachihu be Ethiopia hizeb atikelidu ken esikeyalif.

  9. Inezh ye Neftegnas
    lejoch kalensu lelaw sibal aynachew yiqelal.
    Dr. Tilahun Gessesen inkuwan ye Gim -7 Slaves yadrgutin aytachhoal.

  10. Tikekel neaw yalkew Serbello
    Beinatachew —–
    yimiqenu yemiqegnant DNA
    bewustachw teqebroal. Yehie G7
    wust yetachequt
    bemulu Denqorowch bicha nachew?

  11. Alemash
    Tnsh qolo yizeh ke alemash ye xela asharo texega alelu.
    Ebaksh ke ewr biet andayna brq new yilual aynet new.

  12. Aferkuñ slenante new yetebalew.
    Ke secu teqebayu tewardwal.
    Be bado neger mekofes
    hod siyawq doro mata newnegeru

  13. Sle esat ena sle aberñoch gnbot7
    beyegiziew tgrie woyaniewoch saytaktu yawogzalu.
    Ahun limuaxex teqarbo yeneber tesfachn bejigu lemeleme.
    Ejig yekefa xelat bihonbachew new enezih tgrie woyaniewoch ereft axtew ahunm hualam yemiyawogzut.
    Ahun yager sew ciqunu, nexanetkn yetegefefk ges ybelh tlq tesfa alene be esat ena aberñoch gnbot7.

  14. Sle esat ena sle aberñoch gnbot7
    beyegiziew tgrie woyaniewoch saytaktu yawogzalu.
    Ahun limuaxex teqarbo yeneber tesfachn bejigu lemeleme.
    Ejig yekefa xelat bihonbachew new enezih tgrie woyaniewoch ereft axtew ahunm hualam yemiyawogzut.
    Ahun yager sew ciqunu, nexanetkn yetegefefk des ybelh tlq tesfa alene be esat ena aberñoch gnbot7.

  15. You convinced by Doctrate of only Tilahun G. and Astet A.
    Let me ask you some questions,
    What they did special?
    They have full right and support from the regimes,they use the language that of the regimed like to hear.So they simply sing in comfort zone.
    Now i want to ask you about Ali Birra,the iconic singer and activist for equality of language,let me remind you he was sing while the Ethiopian regimes declared that speakin Afan Oromo was guilty and shame.They have fun on him while he asked ghem to sing by Afan Oromo by saying that Afan Oromo may break microphone and Radio.With your ful respect,Can I correct you? Have it:The only man deserve honorable doctrate is Singer Ali Bira.Well done Jimma University to do that.

  16. Most of the above comments except one or two are written by the frustrated high officals of EPRDFmembers and their running dogs.

  17. Why Aster Awoke got a Doctrate Degree stil now? There is some thing behind it. All Ethiopian Universities should measure every one by their intensive work contribution for our motherland ratherthan selecting the socalled ordinary individual by un clear & invisible criteria.

  18. ማፈርያዎች የባንዳ ስብብስብ በነዚህ ነው ምንገዛው!!!

  19. to ‘Alemash’ banda, why not ‘Honorary Doctorate of Bandaism’ to all bandas like, afterary Nega (father of davil Sebhat Banda Nega), Zenawi Asres, and all selato’s and an Italian Askaris from Adwa?

    speaking of name ‘Alemash’ she was the wife of the cursed banda family in Adwa ‘Zenawi Asres’. Zenawi banda married to ‘Alemash’ then brought an all time greatest Banda son ‘Legesse Zenawi’ a.k.a. evil ‘Meles Zenawi’ Honorary Doctor of Mercenary Banda. he is now in hell.

    Long live Ethiopia !
    Victory to freedom and democracy fighters of Ethiopia, including those in Eritrea!

  20. አይ ጉድ በየጉሮኖው በጣቃና ድር ነጋዴዎች ሳይቀር በቀርከሀና በጭቃ የተሰሩት “የመቀሌውን አይጨምርም” ዩኒበርስቲ ተብዬዎች በጎሳ ላይ ተመርኩዘው ለመሰሎቻቸው ቢያድሉ ምን ይደንቃል? ጎሰኞቹ አገርን የሚያህል ክቡር ሀብት በጥቅም ማደል ብቻ ሳይሆን ቸርችረውት የለ!! ወያኔ አዲስ አበባና መቀሌ ላይ የክብር ዶክትሬት ሲቸረችር ሌሎቹም እንደ ጌታቸው መሸጣቸው እኮ ነው! ይቀጥሉ ይዋረዳሉ የተረዱት ቀደው ይጥሉታል ደናቁርቶቹ ተሸክመውት ይዙሩ ሞሮን የሰቢል ሰርቢስ ጋዜጠኞቻቸውም እውቀቱ ሳይኖራቸው ገዳዳ ከረባትና ጎልዳፋ ብእር ብቻ ይዘው ስለሆነ ለሆዳቸው የተሰለፉት አትደነቁ

  21. ye Shabia barriyawoch xncacu .
    Artra Slave masxeracuh ga hidu
    inkuwan Doctorate Degree lisex
    Univesity yemibal beagerum yelm.
    Ishi tadie ine Kassa Kebede , Neamin
    Zeleke , the blind Madebbo , and the
    Pathological liars Bonger & Abebe Gelaw .
    yemishet afelalegu . kkkkk

  22. Atsebha ante gimatam bedewin Shabiya
    anten bilo amxaci Fara. bante bet Ethiopia lememsl
    neaw indenant gegema alayhum .

  23. Ye Italian Mosoloni Chachutoch yemitalelachewn Frfari eyeleqaqemu beiquy Chinqlatachew weste Blich yemtlbachewn Krfatawi amelekaket bemaserachet Gmatam Kersachewn moltew yadralu. Tqit yeseqoqa gzeyachewnm lemarazem ytralu.
    Hlinachewn bemeshete newna yemitedaderut gizeyawi FNDEQACHEW yemitebeq new !!!!

    YEWESLATA LIJE WESLATA NEW !!!!

  24. The problem in Ethiopia is the government and/or institutions do not take formal corrective mechanisms for such kinds of confussions. Believe me we will keep talking this issue year after year using the title…even journalists…radios and TVs keep saying Hon Dr. somebody…

  25. Mnalbat ye kbr doktor/doktriet glx yalhonelachew kalu, yin kezih teketayun anbbu.
    Ye and universiti baleslxanat andn gleseb yemiyadenqut kehonu ye adnaqotachew megleca ye kbr doktor/doktriet (honorary doctor) yisexutal/yisexuatal.
    Gn yih keziya universti seci baleslxanat wuci trgum yelewm, phd aybalem/aydelem. Demoz ayasgeñm, teqebayu doktor teblo ayxerabetm, ye kbr doktor teblo ayxerabetm. Manm sew secum cimr betmhrt yemigeñew doktrate alemehonun yawqal.
    Lemnm mayxeqm new. Yeteshelamiw gleseb adnaqi baleslxanoci adnaqotachewn yegelexubut trkimrki neger new.
    Andandiem shelamiwochu adnqew sayhon yemishelmut tazew weim xqm lemagñet felgew lihon yichlal

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*