ፀረ-ወያኔ የጋራ ብሔራዊ ትግል ጠንቅ ጠባብ ብሄርተኝነት ብቻ አይደለም

ማሳሰቢያ፤ከዚህ በታች የቀረበው ጽሁፍ የተለያዩ አወዛጋቢና አናጋጋሪ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው ከራሳቸው ዕይታ አኳያ የተመለከቷቸውን ጉዳዮች እያነሱ ግምገማዎችን ያቀርባሉ። በጽሁፉ ውስጥ ስለተጠቀሱት ነጥቦች ትክክለኛነትም ሆነ ስህተት ኃላፊነቱ የጸሃፊው መሆኑንን እያጠቆምን እኛ ነጻ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን እንደመሆናችን መጠን ሃሳባቸው ለአንባቢ አድርሰንላቸዋል።

ከዮናስ ተክለማርያም

ማሳሰቤያ- ለአንባቢያን

-ይህ ጽሑፍ ትውልደ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ጠባብ ብሄርተኞችና ጠባብ ብሄርተኝነትን አይዳስስም

-ይህ ጽሑፍ በአገር ቤት በቅርጽም ሆነ በይዘት ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተዛማጅነት ያላችውን ይሁንታዎችና ትርምሶችን አይዳስስም

-ይህ ጽሑፍ በዲያስፖራው/በውጩ ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያተኮረ ነው

-ፀሃፊው በሚኖርበት የባዕድ አገር ካየውን ፣ ከተከታተለውን ፣ ከቃኘውን፣ ከተገነዘበውን፣ ካሳሰበውን – ከሌሎች ኢትዮጵያውያንም እይታና አስተያየት ተመርኩዞ ነው የጻፈው

– ይህ ጽሑፍ  ሁልእንትናዊ ግድፈቶች እንዳሉት ፀሃፊው ያውቃል ፤ ፀሃፊው ለይዘት እንጂ ለቅርጽ እምብዛም አይጨነቅም ፣ ጓደኛ ወይም ዘመድ ከተወደደ ከነ-ንፍጡ እንደ ሚባለው – የፀሃፊው ዋና ፍላጎት የዚህ ጽሑፍ መልዕክት ከነግድፉ ለሌሎች ማሳወቅ፣ለሌሎች ማጋራ ትና እንዲገነዘቡት ማድረግ ላይ ነው ።

ወያኔ በጠመንጃ ሃይል የደርግ ቁንጮ መንግሥቱን ፈንቅሎ የአዲስ አበባው የገዢዮቻችን ቤት ከተረከበበት 1983 ዓ.ም አንስቶ – ከፋፍሎ ለመግዛት፣ የኢትዮጵያውያን አገራዊና ሕዝባዊ ስነልቦና ለማኮላሸት/ለመበረዝ ፣ አገራዊና ሕዝባዊ ኅልውናችንን ለማዳከምና ለመበጣጠስ ያላሴረው ሴራና ያልነደፈው ስልት የለም ። ከእነዚህም አንዱ የጠባብ ብሄርተኝ  ነት ወይም የጎሰኝነት ፖለቲካ ፖሊሲው ነው ። ከህብረ-ብሄረሰባዊ ኢትዮጵያዊነት ወይም ከዜጋዊ ኢትዮጵያዊነት ይልቅ የጠባብ ብሄርተኝነት ሰሜትና የጠባብብ ሄርተኝነትፖለቲካ መኮትኮቱና ማጠናከሩ ነው ።

የወያኔ የጠባብ ብሄርተኝነት ፖለቲካ በተመለከተ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በበርካታ ኢትዮጵያውያን ስለተጻፈ ለአርእስቴ መግቢያ እንዲሆነኝ ጨለፍኩት እንጂ ይህንኑ ለመውቀ  ውቅጥ ወይም እዚሁ ላይ ለመሞዘዝ አይደለም ። የምፈልገውን መልእክት የማስተላለፍበትን ጽሑፌ የሚያተኩረው  በሌሎች ለብሄራዊ ትግላችን እንቅፋት ወይም  ጎጂ ናቸው በምላቸው ነጥቦች ላይ ነው ። እነዚህም (የተለቪዥን ፣ የሬዲዮ ዜናና የኅትመት ስርጭት ድረገጽ አውታሮች ሚዲያ ኢ-ዲሞክራሲያዊነት) ፣ የተቋሚ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች መከፋፈልና አቅመቢስ መሆን ፣ (ጎሰኝነት ፣ጎጠኝነትና ፣ጭፍን ጥላቻ) ፤ የምዕምናን መከፋፈልና የቤተክርስቲያናት መሰነጣጠቅ ፣የኮምኒቲ ዎችና የእስፖርት ተቋማት መከፋፈልና መዳከም ናቸው ። እነዚህ ነጥቦች እንዴት ‘ፀረ-ወያኔ የጋራ ብሄራዊ ትግል’ እንቅፋት እንድሆኑና እንድሚሆኑ ም እየነጠልኩ ለእኔ የሚታየኝን ለአንባቢ ያን ለማስጨበጥ እሞክራለሁ ።

የሳት ቲቪና ሬዲዮ

ለተራቡ ምግብ፣ ለተጠሙ  ወሃ፣ ለታመሙ ኅክምና ወዘተ..ሲሰጣቸው ምን እንደሚሰማቸው ለማውቅ እነሱ ባለፉበት ማለፍ ወይም እነሱ መሆን ነው። የእሳት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲጀመር -ለዘመናት ስንመኘውና ስንታገልለት የነበረውን ‘ነጻ ሚዲያ’ እውን ሆነልን አልን፤ ፈነጠዝን ፤ ለኢትዮጵያውያን – አዲስ ውጋጋን፣ አዲስ ጮራና አዲስ ተስፋ ፈነጠቀ እያልን በአካልም በስልክም ተነጋገርንበት ፤ተወያየንበት። ነጻና የማን ም ተጽኖ የሌለበት፤ በፀረ ወያኔ ተሰልፈው  ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ ለፍትህና ለእኩልነት ለሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩልነት የሚያገለግል ሚዲያ ነው ተብሎ ተወራ ። የኢትዮ-ዴያስፖራ ኮምኒቲዎች፣ የሲቪክ ፣ የሃይማኖትና የፖለቲካ ድርጅቶች -በአገራችን ብሄራዊ አጀንዳዎች ላይ በተናጥልም ሆነ በጋራ እንዲወያዩ   መድረክ የሚሰጥና የሚያስተናግድ ሚዲያ እንድሚሆንም ታመነበት ።በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩበት አካባቢዮች ሁሉ- የሳት ማጠናከሬያ ገንዘብ ማዋጣት ተቀጠለ ፤ እኔም ከአንዴም ሁለቴ የገንዘብ አስተዋጾ አድርጌያለሁ።

እሳት ከተመሰረተበት እ.አ.አ ጁላይ 14/2010 ዓ.ም ጀምሮ -የሳት ተወካዮች በዓመት ሦሥቴ ወይም ሁለቴ እኔ ያለሁበት አውስትራሊያ አሁጉር እየመጡ – በያንዳንዱ ጉዞዋቸው ከ $70-100 ሺ የአውስትራሊያ ዶላር ይዘው ይመለሳሉ ። ኢትዮጵያውያን ተበድረውም ቢሆን ለእሳት ገንዘብ የሚያዋጡበት ምክንያት እሳት ለሃቀኛ  ተቃዋሚ ድርጅቶች ሁሉ በእኩልነት የሚያገለለግል እየመሰላቸው ነው ።

በአንድ በማውቃቸው እቁብተኞች እቁብ ቀንና ቦታ ተገኝቼ ስለእሳት አገልግሎት ስናወራ የሳት ባለቤት ግንቦት 7 ነው ይባላልና – እንዴት ታዩታላችሁ ብዬ ስጠይቃቸው ሁሉም በአንድ አፍ- “አይ የሳት ባለቤት ራሱ እሳት ነው አሉኝ፤ በማስከተልም እሳት ማንም ከማን ሳያዳላ የሚሰራ ነጻ ሚዲያ ነው” አሉኝ ። የቀጥታ የግንቦት 7 አባላት እና የእጅ አዙር የግንቦት 7 አባላት ማለት የሳት አባላትም-እሳት የግንቦት 7 እንዳልሆነ ምለውና ተገዝተው ይከራከራሉ ።

እውነትም እሳት ነጻ ሚዲያ ነውን? እሳት የነጻ ሚዲያ መስፈርትና መተክል አለውን ? እሳት ነጻ ሚዲያ ከሆነ ለምን ሁሉንም የተቃዋሚ- የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች በእኩልነት መድረክ ሰጥቶ አያስተናግድም?  እ.አ.አ ከ 26- 27 ማርች 2016 በእሳትና በግንቦት 7 አጋሮች በተዘጋጀው (Ethio-vision) የኢትዮጵያ ራዕይ በተሰኘው  የውይይት መድረክ – የሸንጎ የፖለቲካ አቋም ይዘው የቀረቡትን የአቶ አክሊሉ ወንዳፍራው ን ንግግር ብቻ ነጥሎ -አደባብይ ወጥቶ ሕዝብ እንዳይሰማ – ው እሳት ለምን አፈነው? ወይስ ጥሪው እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ዓይነ   ት ነበርን? እሳት የግንቦት 7 ካልሆነ ለምን የሳት ጋዜጠኞች እስከ ኤርትራ በረሃ እየሄዱ የግንቦት7 ናቸው የሚባሉትን ሠራዊት ፎቶ አንስተው የሚያስተዋውቁትና የሚቀሰቅሱት ?ለምድነው  የንጉስ ኢሳያስን ቤተመንግሥት ድረስ ገብተው ኢሳያስ   ን ሲያነጋግሩና ቃለመጠየቅ ሲያደርጉ  የተነሱትን ፎቶዎች በእሳት ተሌቪዥን ለኢትዮጵያውያን የሚያሻሽጡት ? ለምንድ ነው የእሳት ጋዜጠኞች ግንቦት7 በሻቢያ እርዳታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊያመጣ ይችላል ባዮችን ደግመው ደጋግመው ሲያወያዩ የሚታዩት? ከእነህም አንዱ የፋሽቱ መንግሥቱ አጎትና የሥልጣኑ ቀኝ እጅ የነበረት ዶ/ ካሳ ከበደ ነው ። ለምንድ ነው የሳት ጋዜጠኞች በየቦታው የግንቦት7 ሰብሰባዎችና መድረኮች የሚያመቻቹትና የሚዘግቡት? በዚህ አንቀጽ ያሰፈርኳቸው ጥያቄዎች – የግንቦት7 እና የሳት አባላት ውሸታምና አጭበርባሪ መሆናቸውን ለመንገርና የፖለቲካ የዋህ ኢትዮጵያውያንን ለማስገንዘብ እንጂ የፖለቲካ  በሳሎችማ -ገና ከጅምሩ እሳት የግንቦት7 የፕሮፓጋን ዳ መሳሬያ/ማሽን መሆኑን ቢረዱም እንደዚህ ኢ-ዲሞክራሲያዊና መድሎአዊ ይሆናል ብልው አላሰቡም ነበር ፤ ሰለሆነም እርዳታቸውን ለገሱ ።

እ.አ.አ 7 feb 2016 “On media jamming and mass uprising in Ethiopia” “የሚዲያ አፈናና ሕዝባዊ አመጽ” በሚል አርእስት አሜሪካ ውስጥ በተደረገው የውይይት መድረክ ፤ ፕሮ/ጌታቸው በጋሻው የሳት ነጻ ሚዲያነትና አገልግሎት አድንቀው ‘እሳት ባይኖር ኖሮ’ የሚል ግጥም እንደተጻፈም ጠቅሰዋል ። ያ ማለት እሳት ባይኖር ኢትዮጵያው ን ስለአገራቸው ወሬ የሚያሰማ ሚዲያ አይኖርም ነበር ለማለት ይሆን?እሳት ለኢትዮ ጵያውያን ብቸኛ የዜና መሳርያ ነው ለማለት ይሆን? እሳት በመኖሩ የኢትዮጵያ  የፖለቲካ ሁኔታ ተቀይረዋል ለማለት ይሆን? እሳት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ -ጆሮ፣ ዓይንና አንደበት ነው ለማለት ይሆን? ወዘተ..

የኢሳት- ቲቪና ሬዲዮ አውንታዊ ሥራዎች

የአንድን ማኅበራዊ/ሕዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ሞያተኛ -ግለሰብ፣ ቡድን፣ ድርጀት ወዘተ..ሥራ <የሚለካው> ሌሎች ተመሳሳይ አገልግሎት ከሚሰጥ/ጡት ሞያተኛ/ኞች ጋር ነው ። ስለሆነም እሳት-በቅድመ እሳት ከነበሩት- በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማርኛችን የሬዲዮ ዜና ሥርጭት አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩትና ከሚሰጡት -ቪኦኤ/VOA ፣ ዶችቬሌ/ DW ፣ (ኤስቪስ/ SBS እና አዲስ ድምጽ/ADDIS DIMS) ሲነጻሰር የሳት አውንታዊ ወይም ከእነዚህ ሚዛን የደፋ  የሚዲ አገልግሎቱ/ሥራው ላይ ነው የማተኩረው ። ይኸውም እሳት ወያኔ የሚፈ–ጽማቸውን-ግፍች፣ በአገር ቤት በየጊዜው የሚነሱትን ፀረ-ወያኔ / ሕዝባዊ አመጾች ፣ በተለያዩ የአገራችን ምድር በረሃብ የተጠቁትን ወገኖቻችን፣ በድርቅ ምክንያት ስለሚሞቱቱ የቤት እንሣት፣ በዓልም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሚደርጉትን ፀረ-ወያኔ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ የኢትዮጵያውያን ሥደተኞች ገጠመኞችን ፣ ከመሬታቸው  ስለተፈናቀሉትን ኢትዮጵያውያን፣ የሳት እርዳታ ማሰባሰቤያ መድረኮች ወዘ..ምስል/ ፎቶግራፍ እያስደገፈ ለኢትዮጵያውያን ይፋ አድርጓል፤ እያደረግም ነው ። የመለስ ዜናዊ ሞት ተከታትሎ ይፋ አድርጎዋል ፣ በወያኔ ሠራዊት መካከል ያለው የሥልጣ ን/የማዕረግ ተዋረድ ጎሳዊና አድሎአዊ መሆኑን በጭብጥ አጋልጧል ፣በኢትዮጵያ እስር ቤቶች በዕሥረኞች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ እና አልፎ አልፎ ወያኔ በሰብሰ  ባ የተወያየባቸውን ሚስጥሮች አጋልጧል ። እሳት ከሚያስተናግዳቸው ሎሎች ፕሮ  ግራሞች በትምህርት ሰጪነቱ ፋይዳ ያለው ‘የትምህርት ብልጭታ’ ሲሆን በአዝናኝ ነቱ ‘ዋዛና ቁም ነገር’ ነው – የቀረ ካለ አንባቢ ይሙላበት ።

የሳት-ቲቪና ሬዲዮ አሉታዊ ገጽታዎች

ሁላችንም  እንድምናውቀው  ሚዲያ ኃይል ነው ፤ ሚዲያ የጥፋትም የልማትም መሳርያ ነው ። ስለሆነም ይህ የሳይበር ሚዲያ (እሳት) ቀደምትና አበይት ሥራው መሆን የነበረበት – ለረዥም ዓመታት የትግል ልምድ ያላቸውን ፣የሀገራችንን ተጨባጭ-ፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወዘተ..ሁኔታዎችን ለማስተማር -ልምድ፣ በቃትና ችሎታ ያላቸውን ፣ ሕዝባቸውና አገራችወን ለሚወዱ ፣ ለእውነተ ኛና ለሃቀኛ ተቃዋሚዮችን- ሰፊ መድረክ  ሰጥቶ በአገራችን ብሄራዊ አጀንዳዎች ላይ በተናጥልም ሆነ በጋራ የሚወያዩበት፣ የተራራቁትን የሚቀራረቡበት ፣ የተጣሉ ትን ፣የሚታረቁበት መድረክ መሆን ነበረበት ። የእሳት አስተዳዳሪና የእሳትጋዜጠኞ ች ያንን ሚና መጫወት ነበረባቸው ።

ነገርግን እሳት ትኩረትና ቅድሜያ የሰጠው ከዚህ በተቃራኒ ለተሰለፉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ነው ።ይኸውም እሳት ተመስርቶ ሥራ ላይ ከዋለበት ሰዓት አንስቶ፤ ከኢትዮጵያ ጋር በጉርብትና እንጂ አብረን አንኖርም ፣ ኢትዮጵያዊ ሥነል-ቦና የለንም ፣የኢትዮጵያ ሃገራዊ አንድነት አንቀበልም ፣እኛ የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዢዎ ች ነን ወዘተ..ባዮችን ከየተደበቁበትን- ጫካ፣ መንድር ፣ ጉራንጉር ወዘተ.. በባትሪ በመፈለግ  ኢትዮጵያዊ ማስክ አልብሶ ወደ አደባባይ በማውጣት ሥራ ላይ ተሰማ ሩ።  ሰፊ መድረክ ሰጥቶ አስተዋወቋቸው ፣ አሻሸጧቸው/ፕሮሞት አደረጋቸው፤ ጎላ ብለው እንዲታዩ ይህ ቀረ የማይባል ጥረት አደረጉላቸው ። የሳምንቱ እንግዳ በተሰውኘው መረሃግብሩ/ፕሮግራሙ  ሲያሳትፋቸው ከሚታዩት አብዛኞቹ የደርግ ና የፋሽስቱ መንግሥቱ ጽረ-ሕዝብ ባለስልጣንና ካድሬ የነበሩ ናቸው ።ለምንይሆን? በ 1983 ዓ.ም በለደን የተደረገውን ዓይነት የሥልጣን ድርድር -በአሜሪካና በአውሮ ፓ ማኅበር (E.U) ግፊት ከተደረገ -ግንቦት 7 እነዚህን ሃይሎች በዙርያው አሰልፎ  ና ሁለተኛ ኢህኣድግ (EPRDF) ፈጥሮ ሥልጣን ላይ ለመውጣት ከማሰብ ይሆን? ወያኔ መጣል የሚቻለው  ከጠባብ ብሄርተኞች ጋር በመሰለፍ ነው ከማለት ይሆን? ለተገንጣይነት የሚታገሉት ላቅ ያለ የፖለቲካ  -ብስለት ፣ ብቃት ፣ስልት ፣እስትራ ተጂ ወዘተ..አላቸው ከማለት ይሆን?

ሌሎች የሬዲዮ ዜና ስርጭት አውታሮችና የኅትመት ሥርጭት ድረገጽዎች በተመለከተ

እነዚህ በባዕዳን አገራት ለሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የሚያገለግሉ ሬዲዮኖችና ድረገጽዎች ቁጥር በጣም ብዙ ስለሆኑ – እያንዳንዳቸውን -ተግባር፣ አውንታዊና አሉታዊ አገልግሎት ምን እንድሚመስል ለመመስከር አልሞክርም። ነገርግን ከራሴ ገጠመኝን፣ ካስተዋ ልኩትና ከሌሎ ች ከሰማኋቸውን አስተያየቶች ተመርኩዤ የእነዚህ መዲያ-አድሎአዊ ነት፣ ኢ-ዲሞክራሲያዊነ  ትና ሙስናዊነት – ጠቅለል ጠቅለል ባለመልክ ለማሳየት እሞክራለሁ ። አብዛኞቹ በሚዲያ ሥራ ላይ ያላቸው አስተሳሰብ /ማይንድ ሴት እና አሠራር ተመሳሳይ ነው ። የሚዲያን መተክሎች/ፕሪንስፕልስ ተከትለው የሚሰሩ  ‘ኢትዮጵያን ያማአከልና ያስቀደመ’ የሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ኢትዮጵያዊ/ት የሚዲያ ሞያተኞች እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው ። እጅግ በጣም በርካታዎቹ የሚያስቀድሙት የግል ጥቅም ፣ የድርጅት ታዛዥነት ፣ ተክለሰውነ ት፣ ወዳጅነት ወዘተ..ነው (1 ) አንድ የአገርና የኅዝብ ጉዳይ የሚመለከት/መልዕክት ያለው ጽሁፍ ሲላክላቸው ፤ ጽሑፉን -አንድ የገንዘብ ድጎማ የሚያደርግላቸው  ወይም የተወዳጁትን – የፖለ ቲካ ፣ የሲቪክ ፣ የሃይማኖት ወዘተ..ድርጅት ወይም ድርጅት መሪ የሚነካ ከሆነ ጽሑፉ አደባባይ እንዳይወጣ ያፍኑታል  (2) አንድ ጽሁፍ ሲላክላቸው -ጽሑፉን የሚለኩት- በጽሑፉን ይዘትና መልዕክት ሳይሆን በጸሃፊው ነው ። ጽሁፉ -በፕሮፌሰር ፣ በዶክተር ፣ በፖለቲካና በሕዝባዊ መድረክ  በሚታወቅ ፣ አንድ ትንሽ መጽሃፍ ጽፎ በአንድ ድረገጽ በለጠፈ ሰው ወዘተ.. የተጻፈ ከሆነ ወዲያውኑ በድረገጻቸው ይለጥፉታል ። በአገር ጉዳይ ላይ ለቃለ መጠየቅም ለውይይትም  የሚጋብዙዋቸው ከሞላ ጎደል እነዚሁ ናቸው (3) በጓደኝነት ፣ በዝምድና ፣ በትው ውቅ ፣በትውልድ አካባቢነት ፣ በአምቻ ጋብቻ  ወዘተ.. የሚላኩ ጽሑፎችም በደምብ ይስተናገዳሉ ።

የተቋሚ የፖለቲካና የሲቭክ ድርጅቶች መከፋፈልና አቅመቢስ መሆን

ከጥር ወር 2008 መጀመርያ ጀምሮ በዋናነት የኦሮሞ ብሄረስብ ወጣቶች በተከታታይ ያደረጉትን ጠመንጃ አልባ አመጾች የፈጠረው ሁኔታ – የፖለቲካና የሲቪክ ተቃዋሚ ድርጅቶች የተጓዙበትን የተናጥል ትግል ውጤቱ (outcome) ምን እንደሚመስል ደግመው ደጋጋመው እንዲያስቡብትና እንዲመረምሩ ያስገደዳ ቸው ይመሰል ነበር ። ለሃያ አራት ዓመታት ለኅብረት ትግል ጥሪ፣ አቤቱታና ውት  ወታ ጆሮ ዳባ በማለት ፤ ከማን አንሼ-ብቻዬን ታግዬ ለሥልጣን እበቃለሁ ባይነት፣ የፖለቲካ የዋኅነት/ናይቪቲ ፣ ባጭር አቋራጭ  ሥልጣን ለመጨበጥ -ሃቀኛ ታጋዮ ችን አግልሎ ከባንዳዎች ጋር መሰለፍ ወዘተ..ለጥፋት እንጂ ለየትኛውም አገርና ሕዝብ አድን ፖለቲካ ግብ እንደማያደርስ ትምህርት ያገኙበት ይመስል ነበር ። አመጹ ቀድሞ ከተደረጉት አንጻራዊ አመጾች ሁሉ ለየት ያለ ስለነበረ የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዮች በጣም እንዳስደነገጠ -ለተለያዩ ኢትዮ/ድረገጾች ከጻፉዋቸው ጽሁፎች፣ ለተለያዩ ኢትዮ/ዜና አውታሮች ከሰጡትን የቃለመጠይቅ መልሳችውና አስተያይታቸውን መረዳት ችዬአለሁ ። ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ወድቃለች! ኢትዮት- ጵያ አደጋ ላይ ናት! ኢትዮጵያ በመፍረስና ባለመፍረ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛ-ችለ! ኢትዮጵያ እየፈረስች ነው ! ስለሆነም የህብረት ትግል በአስቸኳይ መጅመር አለበት! ወዘተ.. የተሰኙ መፈክሮች አሰሙ ፤ ደሰኮሩ ።

ያንን-ለኢትዮጵያም ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ፣ ለወያኔም አደጋ ይዞ መጥቷል የተባለው አመጽ እውን ከሆነ እነሆ መንፈቅ ሆኖዋል ፤ ታዲያ የትአለ ህብረቱ ?  ምነው እነዚያ መፈክሮቹ ሁሉ የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ? ከስሜታዊነት ያለፈ ሥራ መስራት አንችልም ማለት ነውን? ለሃያ አራት ዓመታታ ተቃዋሚዮችን አቅመቢስ- (inadequate) ያደረገው የተናጥል ትግል አሁንም ተቀጠለበት፤ ለምን ?

ለድክመታችንና ለውድቀታችን የታገልነው ያህል – ለምን ለጥካሬያችንና ለአሸና ፊነት አንታገልም ? ማለት ለድክመታችንና ለውድቀታችን መሠረታዊና ዋንኛ ምክን ያት ‘በኅብረት’ ያለመታገል መሆኑን -ኅብረት ኃይል መሆኑን፣ ኅብረት ለኢትዮጵያ ሕዝብም አለኝታ መሆኑን ወዘተ..ከታወቀ -ኅብረት ፈጥሮ ለመታገል ምን አስፈራን?

ለመሆኑ ሁሉም ፀረ ወያኔ ኢትዮጵያዊ  ተቃዋሚዮች የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር የጋራ ችግር ነው የሚሉ ናቸውን? በፀረ ወያኔ የተሰለፉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዮች ሁሉ- ብሄራዊ ስሜትና ሥነልቦና እኩል ነውን?   በፀረ ወያኔ የተሰለፉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሁሉ- ኢትዮጵያና የኢትዮጵ ሕዝብ ያስቀደም ትግል ይታገላሉን ? ሁሉም የኢትዮጵያ ሃገራዊና ሕዝባዊ ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መሆኑን የሚያስጨንቃቸው ናቸውን ? ወዘተ..መልሱ  -አው ከሆነ  ‘ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ’ እንደ ሚባለው -ዛሬ ያልተፈጠረ ኅብረት፣ ዛሬ ያልተገኘ አንድነት፣ ለዛሬ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ሥነ-ልቦና ፣ ለዛሬ ያልሆነ የአገርና የሕዝብ ፍቅር ፣ ለዛሬ ያልሆነ ትምህርትና የፖለቲካ እውቀት ወዘተ..ለመቼ ሊሆኑ ነው ? ለሰማይ ቤት ወይስ ለመቃብር ?

ከላይ ያሰፈርኳቸውን ጥያቄዎች በቅርጽ እንጂ በይዘት የማያሟሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች አሉ የምንል ከሆነ ፤ የኅብረት ትግል የማይፈሉጉበት፣ የኅብረት ትግል የሚፈሩበትና የሚያሳቡቡበት ምክንያቶች ምንና ምን ይሆኑ?

– የካፒታል ፣ የሚዲያ ተቋም ፣ የደፈጣ ውጊያ ግንባር ወዘተ አለኝ ፣ አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት ከእኔ ጋር ናቸው ፣ ተቃዋሚ ተብዮች ሁሉ በእኔ ሥር ካልተሠ ለፉ ኅብረት አያስፈልገኝም ፤ ብቻዬን ታግዬና ወያኔን ጥዬ ሥልጣን መጨበጥ የሚያስችል አቅም አለኝ የሚል/ሉ የፖለቲካ ድርጅት/ቶች ስላለ/ሉ ። ስለድርጅቴ  አትወያዩ፣ አትተቹ ፣ አትጻፉ ፣  አስተያየት አትስጡ ፣ በድረገጻቹህ አትለጥፉ ወዘተ .. በማለት የኢትዮጵያውያንን ፖለቲካዊ አንደበትና የሚዲያ ነጻነት ለማፈን የሚቃጡ/ጣ  አምባገነን የፖለቲካ ድርጅችት/ቶች ስላለ/ሉ ።እ.አ.አ  በ2015 አጋማሽ አካባቢ የአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ባለቤትና አስተናጋጅ አቶ አበበ በለው የግንቦት 7 ወደ ኤርትራ መሄድን አስመልክቶ በአየር/ሳይበር መድረክ/ፎረም ኢትዮጵያኖችን -ስለአወያየ በከረንት አፌርስ በፓልቶክ ሚዲያ የደረስበትን የስድብና የዘለፋ ውርጅብኝ  ፣ ይህንኑ አስመልክቶ -በኢትዮሚዲያና በቪኦኤ ላይ <VOA>  ላይ ተጽኖ ለማድረግ የተደረጉትን ሙከራዎች የፍላጭ ቆራጫዊ አምባገነንነት (አብሶሊት ዲክታቶሪያል) ባህሪ በቂ ማስረጃዎች ናቸው ።

-በሚፈጠረው ኅብረት ውስጥ ከኔ የተሻለ ችሎታ ያላቸው ስዎች ስላሉ -ሊ/መምበ ርነት፣ ዋና ፀሃፊነቴ ፣ ገ/ያዥነቴ ወዘተ..አጣለሁ/እነጠቃለሁ ከሚል ፍርሃት

-ያንን ድርጅት አልወደውም ፣ እነእገሌ ያሉበት ድርጅት እጠላዋለሁ ፣ ከእነሱ ጋር ኅብረት ከመፍጠር ከወያኔ ጋር ህብረት መፍጠር ይሻላል የሚሉ ስላሉ ። እንደ እነ  ዚህ ያሉትን ድርጅት መሪዮች- ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ያሉበትን የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ድርጅቶች አይወዱም ይሆናል ። ከሃቀኛ የተቋሚ ድርጅት/ቶች ጋር ለመሥራት ምቹ ያልሆኑበት የመደብ ፣ የፀረ ህዝብነት ፣ የመጥፎ ባህሪ ወዘተ.. ጀርባ ይኖራቸው ይሆናል ።

-እውነት ይሁን እውሸት ባይታወቅም -ድርጅቴ ለስበዓዊ መብት የቆመ ድርጅት ስለሆነ ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ኅብረት ከፈጠርኩ- ካለሁበት አገር መንግሥት የሚሰጠኝ ን ድርጎ/ፈንድ አጣለሁ ከሚል ሰበብ ። ሌሎችም በርካታ ውሃ ቀጠነ ፀረ-ኅብረት ምክንያቶችና ሰበቦች ይኖራሉ ። እንደ እነዚህ ዓይነት ተቋዋሚ ተቢዮች ‘ትግል’ -ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስቀደመ አይደለም ፤ በኅብረት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ መንጋጋ  ከማላቀቅ- የሚያስቀድሙት እየድርጅታቸውና እየራሳቸውን ጥቅም ፣ ፍላጎትና ሥልጣን ነው ፤ ስለሆነም የኅብረት መሰናክል ናቸው ።

ጎጠኝነት

እገሌ ጎጠኛ ነው ሲባል-ያ ስው ጎሠኛ ነው፣ መንድርተኛ ነው ፣ አድሎአዊ ነው ፣ ኢ-ፍትኃዊ ነው ፣ ዘመድተኛ ነው ፣ ጓደኝተኛ ነው ወዘተ..እንድማለት ይመስለኛ ል ።ጎጠኝነት በተለያዩ ሥውርና ይፋ መንገዶች ይንፀባረቃሉ ወይም ይተገበራሉ ።

1) አንድ ሰው በፖለቲካ ፣ በሃይማኖት ፣ በሞያ ፣ በማኅበራዊ ፣ በመንግሥታዊ ወዘተ..ድርጅት/ቶች የያዘውን የበላይነት ወይም ሁነኛ ሥልጣን ተጠቅሞ  የእኔ ናቸው  ፣ ለሥልጣኔ ይጠቅሙኛል የሚላቸውን -ዘመዶቹ ፣ ጎሳዎቹ ፣ ጓደኞቹ ፣ ከትውልድ ሠፈሩ እስከ ትውልድ ክፍለ ሃገሩ የሚያወቃቸውን በይፋም ሆነ በሥውር ከሾመ ወይም ከቀጠረ ፤ ያ ሰው ጎጠኛ ነው ።

2) ልማታዊ ጎጠኝነት፦  መንግሥት ማድረግ ያልቻለውን የትውልድ አካባቢ ለማልማት/ለመገንባት የመሰባሰብ ጎጠኝነት ።ይህንን ዓይነት ጎጠኝነት አውንታዊ ጥቅም እንዳለው አሉታዊም ጎን አለው። ይኸውም ኢትዮጵያዊነትን ያማአከል/ያስ  ቀደመ ሥራ እንዳይሠራ ያደርጋል ፤ በኢትዮጵያዊነት አጀንዳ ላይ እንዳይተኮር ያደርጋል/ እንቅ ፋትይፈጥራል (የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ኅልውና ለመታደ ግ ወይም ለማዳን ከምናደርግው የጋራ ትግል አኳያ ማለቴ ነው) ። ሁሉም ለጎጡ ብቻ እንዲያስብ ፣ ሁሉም ወደ ጎጡ እንዲሄድ ይጋብዛል ። የብሄርተኝነት ጽንሰ ሃሳብ ፣ የብሄርተኝነት ይዘትና ትርጉም /ኮንቴክስት ባይኖረውም – በቅርጽ የብሄር ተኝነት አካሄድ ይጋራል ። በተለይም የአሁኖቹ ገዢዮቻችን ለከፋፍለህ ግዛ ሥራዓ ታቸውን ሊጠቀሙበት ይችላሉ ፤ ለምን ሌሎችን ጠባብ ብሄርተኛ ትላላችሁ  እናንተም  ጎሳዊ ሳይሆን ጎጣአዊ ጠባቦች ናቹሁ ሊሉ ይችላሉ ።

3) ማኅበራዊ ጎጠኝነት፦ በአንድ መንድር/ሠፈር ተወልዶ – ከህጻንነት ዕድሜ አንስቶ አብሮ (በልተው ጠጥተው ፣ተጫውተው ፣ ጨፍረው ፣ ት/ቤት ሄደው ወዘተ..በማደግ) ፣ ቤተሰብ ከቤተሰብ በመተዋወቅ ምክንያቶች ተገናኝቶ አብሮ (መብላት፣ መጠትና መጫወት) ጤናማና ሶሺዮሎጂአዊ ይሁንታ ነው ። ነገር ግን አብሮ በማድግና ቀድሞ በመተዋወቅ ብቻ ሳይሆን – በአንድ  አካባቢ፣ ወረዳ ፣ አውራጃ ፣ ክፍለ ሃገር ወዘተ.. ወተወላጅነት  ብቻ -ጎ.ሜ ፣ወ.ዬ  ፣ ወ..ቴ ወዘተ.. በሚል ሰያሜ በይፋም ሆነ በሥው ር ተሰባሰቦ -የመብላት ፣ የመጠጣት፣ የመጨ ፈር ወዘተ ፣ ለአከባቢ ልማትም ሆነ ለአገራዊ ፖለቲካ ምንም አስተዋጾ  የማያደር ግ/ጉ ጎጠኝነት ። ድግሳችንም ፣ ግብዣችንም ፣ ሠርጋችንም ፣ ጋብቻችንም  ወዘተ.. እኛው በእኛው  የሚል ዝንባሌ የሚታይባቸው -የሌላ አካባቢ ተወላጅ ኢትዮጵያ ውያንን አግላይ ማኅበራዊ ጎጠኝነት-ፋሽን እየሆነ የመጣ ይመስላል ። እንደውም የአንዱ ክ/ሃገር አማራ የሌላውን ክ/ሃገረ አማራ የሚጠላበትና የሚቋሽሽበት ጎጠኝነ ት እየተደመጠና እየተስተወለ ነው ።

የምእምናን መከፋፈልና የቤተክርስቲያናት መሰነጣጠቅ

በክርስትና ሃይማኖት እምነት መሰረት- ቤተክርስቲያን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በስብስብም ሆነ በተናጥል የእግዛብሄር ቃል የሚሰሙበትና የሚጸልዩበ ት የክርስቲያኖችም የእግዚአብሄርም ቤት ነው ። ነገር ግን በአገር ቤትም ሆነ በባ ዕዳን አገሮች የሚገኙት የዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያዊ የዕምነት ድርጅቶች በቅርጽ ሃማኖታዊ ይምሰሉ እንጂ በይዘት ፖለቲካዊ ናቸው  ። ስለሆነም -ሃይማኖታዊ ጎሰኝነት ፣ሃይማኖታዊ ጎጠኝነትና ጭፍን ጥላቻ በባዕዳን አገሮች በፀረ-ወያኔ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናትም ሆነ በእንድገና መወለድ/ቦርን አጌን ቤተክርስቲያና ት -የምእምናን መከፋፈልና የቤተክርስቲያናት መስነጣጠቅ አበይት ምክንያቶች ናቸው ። እንዴት?

<ሃይማኖታዊ ጎሰኝነት> ፡- ለምን ለወያኔ ሰነዶስ አቡን አይፀለይለትም ፣ ስሙ ለምን አይነሳም ያ ካልሆነ ይህ ቤተክርስቲያን አንፈልገውም ብሎ ጥሎ መሄድ ወይም ተገንጥሎ ሌላ ቤተክርስቲያን መመሥረት ።

<ሃይማኖታዊ ጎጠኝነት> ፦ መሠረቱ- ወሎዬ ፣ጎጃሜ ወዘተ.. የሆነ አንድ ቄስ ወይም መነኩሴ በጥፋቱ ከተወቀስ ወይም ከተባረረ ፤ ጥፋቱ ምንድነው ? እንዴት እንፍታው ? ብሎ መጠየቅ ሲገባ ፤ ሁሉም ባይሆኑም በርካታዎቹ የዚያ ክ/ሃገር ተውላጆች ያንን ቤተክርስቲያን ይጠላሉ ፤ከዚያ ይርቃሉ ። የአንድ ቤተክርስቲያን ቄስና ዳቁን የአንድ አካባቢ ሰዎች ከሆኑ -እንበል ጎንደሬ ከሆኑ ፤ አይ ! ጎንደሬዎች የተጠራቀሙበት ቤ/ክርስቲያን ስለሆነ አንሄድም ብሎ መቅረት።

<ጭፍን ጥላቻ> ፦ የአንድ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ሊ/መምበር ፣ ጸሃፊ ፣ ገ/ያ ዥ ወዘተ.. ሰው አያከበርም ፣ ገላመጠኝ ፣ ይዋሻል ወዘተ.. ብሎ በመቀስቀስ  ቡድን አዘጋጅቶ ከዚያ ቤተክርቲያን መራቅ ። በአወስትራሊያ ፣ በኢክቶርያ እስተት ፣ በልሜርቦርን ከተማ  በጎሰኝነት፣ በጎጠኝነትና በጭፍን ጥላቻ ምክንያቶች- አንዲት  ፀረ-ወያኔ የኦርቶዶክስ ቤተክ ርስቲያን -እንድ ድመት ወይም እንድ ውሻ ሦስት ግልገል ቤተክርስቲያት ወለድች፤ ከራሷ ጋር አራት አካል ሆነች ። እነዚህ ችግሮች ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ሌሎች ባዕዳን አገሮች ሁሉ እንዳሉም እገምታለሁም ።

አምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለአምሳዎች ግን ጌጥ ነው እንደሚባለው ፤ አንድ ቤተክርስቲያን አይበቃንም ፣ በተለያዩ መላእክት ስም -በዚህና በዚያ ሰፈር ተጨ ማሪ ቤተክር ስቲያን ያስፈልገናል ተባብሎ ፣ ተመካክሮና ተፈቃቅዶ ቢሆን ኖሮ – ባህላችንና ልማዳችን የሚፈቅዱልንና የሚያስከብረን ሥራ ነበር ። በአገር ቤትም ሆነ በባዕዳን አገሮች የሚኖሩትን  ኢትዮጵያውያን አብሮ እንዳይኖሩ – ወያኔ በቀየሰው  -የጎሰኝነት ሰሜት ምክንያት መከፋፈልና መራራቅ የለመድነው  ቢሆንም ‘የጎጠኝነትና የጭፍ ን ጥላቻን’ ሥራ ሲተገብሩ የሚታዩት ፤ ወያኔ በዋና ጠላትነት ፈርጆ -ከሚገላቸው ፣ ከሚያስራቸው ፣ ከቄያቸው ከሚያፈናቅላችው ፣ ከሚያሳድ  ዳቸው ወዘተ.. ከአማራው ብሄርስብ ናቸው ። የአናሳ ብሄረሰቦች አባላት የዚህ ዓይነት ጽንፈኛ ሥራ ሲሰሩ አይታይም  ።

ኮምኒቲዎችና የኮምኒቲ እስፖርት ተቋማት መከፋፈልና መዳከም

-ከእናት አገራችን በብዙ ማይልስ እርቀን በምንገኝባቸው ባዕዳን አገሮች ወፍዘራሽና ባይተዋር እንዳንሆን

-ደስታችንም ሆነ ሃዘናችን ባህላችን በተከተለ በጋራ ተሳትፎ ለማስተናገድ

-የማንነት ቀወስ እንዳይደርስብን-ባህላችን ፣ ታሪካችን ፣ ቋንቋችን ፣ ወጋችን ወዘተ ተንከባክበን ለማቆየትና ለልጆቻን ለማስተላለፍ

-ከምንኖርባቸው ባዕዳን አገሮች ሕዝብ ባህልና ሥርዓት ተመሳስለን እንዳንኖር የሚገጥሙንን ችግሮች በጋራ ለመፍታት

– ብሄራዊ በዓሎቻችንና አውደ ዓመቶቻችን በጋራ ለማክበር

-ለአካል እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን በሁሉም  የእድሜ ደረጃ ያሉትን ኢትዮጵያውያን  – እንዲገናኙ ፣ እንዲተዋወቁ ፣እንዲወያዩና በጋራ እንዲዝናኑ     ወዘተ..በማሰብና በማቀድ  -በቅድመ ወያኔ በአንድ ኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር የተቆረ  ቆሩትን /የተመሰረቱትን ማኅበሮች (ኮሚኒቲዮች) እና በኮምኒቲ ሥር የተዋቀሩትን የእስፖርት ተቋማት- ወያኔ የሥልጣን ኮርቻ ላይ ከወጣ ጅምሮ – ‘በጎሰኝነት ፣ በቡድንተኝነትና  በጭን ጥላቻ’ ምክንያቶች ሲከፋፈሉና ሲዳከሙ ይታያሉ ።

አንድ ኢትዮጵያዊነትን ያማአከለ/ያስቀደመ ኮሚኒቲና የዚያ ማኅበረሰብ ማኅበረ የጋራ አንጡራ የእስፖርት ተቋም ቅርስ (the common or the collective good) ነጥቆ ወደ ቡድን ንብረትነት በማዛወር – የቡድን መጠቀሜያ ለማድረግ  የሚጥሩ ፣ ሃቀኛና ኢትዮጵያዊነትን እምብርት ያደረጉ ኮምኒቲዮችን የሚከፋፍሉና የሚያዳክ      ሙ ፣ ‘በጭፍን ጥላቻም ሆነ በጠላት ተልዕኮ’ – ሃቀኛ የኮምኒቲ መሪዮችን በመጥላ ት፣ በማስጠላትና በመከፋፍል ሥራ ላይ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን – በእኔ አካባብ   ቢ እንዳሉ ሁሉ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ባዕዳን አገሮችም እንደሚንሩ እገምታለሁሉ ።

ማጠቃለያ

የኢትዮ -ዴስፖራ የሚዲያ ምያተኞች፦ (1) የሞያ ነጻነት ባለበት ፣ በሞያቸው ምክንያት መታሰር ፣ መገረፍና መገደል በሌለበት ፣ የአካልና የአእምሮ ጉዳት ይደርስብኛል በማይባልበት (2) በሞያቸውም ባይሆን በማንኛወም የሥራ መስክ ሠርተው ራሳቸውና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር በሚችሉበት አገሮች እየኖሩ ፤

  • ኢትዮጵያ አገሬ ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ህዝቤ በለው የሚታገሉትን ሃቀኛና እውነተኛ የፖለቲካና የሲቭክ ድርጅቶች አግልልው – የኢትዮጵያ አገራዊ ና ሕዝባዊ ሉዓላዊነትን ፣ የኢትዮጵዊነት- ታሪክ ፣ ቋንቋ ፣ ባህል ፣ሥነል ቦና ወዘተ.. የማይቀበ ሉትን ወይም የእኔ ናቸው የማይሉትን  የፖለቲካ ድርጅቶች- ማደራጀት ፣ ማስተገድና ማስተዋወቅ/ፕሮሞት ማድረግ የመረጡና የሚመርጡ የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች እንዳሉ በዚህ ጽሁፍ ከላይ ጦቁሜያለሁ ። ከዚህ ዓይነት የሚዲያ ድርጅት/ተቋም  የሚሠሩ ጋዜጠኞች  – ለገንዘብ ፣ ለጥቅማ ጥቅም ፣ ለሽሞት  ወዘተ.. ብዬ ሞያዬን የሚያጎድፍ ፣ የአገሬና የሕዝቤን ኅልውና የሚጻረር ፣በታሪክ የምወቀስበት ወዘተ..ሥራ አልሰራም ለማለት ለምን አልደፈሩም ? እስካሁን ያጠፉትን ጥፋት ባለመገንዘብና ባለመንቃት ከሆነም ከአሁን ጀምሮ ራሳቸውን ከዚህ ዓይነት የሚዲያ ተቋም ማግለል ይጠበቅባቸዋል (የሳት ጋዜጠኞችን ይመለከታል) ።

(2) በቅንነት ፣ በዲሞክራሲያዊ መተክል ፣ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ  ጉዳዮችን ያማአከለና ያስቀደመ የጋዜጠኝነት ሞያ አገልግሎት ከመሥጠት ይልቅ የአንድ  የፖለቲካ ድርጅት ፣ የአንድ  የሲቪክ ድርጅት ፣ የዶክተር ፣የፕሮፌሰር  ፣ የደራሲ ፣ የወዳጅ ፣ የአካባቢ ልጅ ፣ የአምቻ ጋብቻ  ወዘተ.. የፖለቲካ ፍላጎ  ትች ማስተናገድና ማሻሻጥ – ለምን ይመርጣሉ ? ለምን ቅድሜያ ይሰጣሉ ?

ከግል ጥቅም ፣ ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ፣ከዶክተር ፣ ከፕሮፌስር  ከወዳጅ  ወዘተ.. ጥቅምና ፍላጎት – አገርና ሕዝብ አይቀድሙምን ? ለእነዚህ ተገዢ መሆን አጎብዳጅና አድርባይ መሆን አይደለምን ? የጋዜጠኝነት ሞያ ንቃተኅሊ የሚፈታተን አይሆንምን? ለተያያዝነው  ብሄራዊ ትግል አሉታዊ አስተዋጾ  አይኖረውምን ? ( በዲያስፖራ ለሚኖሩ የኢትዮጵዮ -ሚዲያ ሞያተኞችን ሁሉ ይመለከታል)

አምባ-ገነንነት ፦ በባዕዳን አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያ የሚዲያ ሞያተኞችን -የመናገር ፣የመጻፍ ፣ ኢትዮጵያውያንን የማወያየት ፣በድረገጻቸው  አንድን ድረጅት የሚተች ጽሁፍ የመለጠፍ ወዘተ.. ነጻነት ለማፈን የሚሞክሩ እንደ <ግንቦት 7> ዓይነት አምባገነን የፖለቲካ ድርጅቶች – በአገር ቤትሥልጣን ቢዙ (1) ተቃዋሚዮቻቸውን እንዴት እንደሚመቱ (2) ሕዝቡን እንዴት እንደሚያስተዳድሩት ከወዲሁ መገመት ይቻላል ።

ማኅበራዊ ጎጠኝነት ፦ በአንድ አካባቢ ተወላጅነት ተሰባስቦ -መብላት ፣ መጠጣት  መጨፈር ወዘተ..እንድ ሃይል ተደርጎ ይወሰዳል ፤ምቾትና ደስታ የሚያጎናጽፍ ይመ ስላል ፤ ከአብሮነት ልዩነት ይመርጣል ፣ ማለት እነሱ ከተወለዱበት-(አካባቢ ፣ወረ ዳ ፣ አውራጃ ፣ ክ/ሃገር) ያልሆነ/ነች አይፈለጉም ።ይህ ዶምስቲክ ወይም የውስጥ ዜኔፎቢያ  እንድ ማለት ነው ። “pond is the only world for frogs” “እንቁራ ቶች ከሚኖሩበት ጨፌ ሌላ ዓለም የላቸውም” እንድሚባ ለው -አስተሳሰባቸው  ከወፍ ጎጆ የጠበበ ፣ንቃተ-ኅሊናቸው እንቡጥ የሆነ ማኅበራ ዊ ጎጠኞች እያቆጠቆ ነው ።

ሃይማኖታዊ ጎጠኝነት ፦ ክእኔ አካባቢ የመጣ ቄስ ወይም ዳቁን በጥፋቱ ከተወቀስ ፣ ከተቀጣ ፣ከተባረረ ወዘተ..ቤተክርስቲያኑን ጥዬ እሄዳሉሁ የሚሉ ፣ እኔ ከተወለ ድኩበት አካባቢ ባልመጡ ቄሶችና ዳቁኖች አልገለገልም  ፤ ሁሉም የቤተክርስቲያኑ ምዕም ናን በራሳቸው አካባቢ ቄስ ወይም ዳቁን መገልገል አለባቸው የሚሉ፤ ለምሳ ሌ የአንድ ቤተክርስቲያን ምዕምናን-የጎንደር ፣የወሎ ፣ የጎጃም ፣የሸዋ ፣የጅማ- ተወ ላጆች ከሆኑ በቤተክርስቲያኑ ከአምስቱ ክ/ሃገራት የመጡ ቄሶችና ዳቁኖች መኖር አለባቸው  ዓይነት ግራየተጋባ ወይም አስተሳሰብ ያላቸው ወይም በጠላት ተልዕኮ የተቃኘ ‘ሃይማኖታዊ ጎጠኝነት’ – ከላይ እንደገለጽኩት የምዕምናንና የቤተክርስቲ ያናት አንድነት እያናጋና እያተራመሰ ነው ።

ጭፍን ጥላቻና የጠላት ሉዕኳን ፦ በጭፍን ጥላቻና በጠላት ሉዕኳን የሚሴርባ ቸው እነማናቸው ? ለምን ? የጭፍን ጥላቻና የጠላት ሉዕኳን ሰለባዎች – ሃቀኛ የኮሚኒ ቲ ፣ የቤተክርስቲያን ፣ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች መሪዮችና አባሎች ናቸው ። ለምን? ለ(አገራቸው ፣ታሪካቸው ፣ ባህላቸው ፣ ቋንቋቸው አንድነታቸው ፣ ማንነታቸው  ፣ ጥንታዊ  ሃይማኖታቸው ፣ ኢትዮጵዊነታቸው  ፣ ኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና ፣ኮሚኒቲያቸው  ወዘተ..) ስለሚታገሉ ፣የእነዚህን ሕልውና ስለሚንከባከቡ ፣ ለእነዚህ ሉዓላዊነት ስለሚከላከሉና ስለሚፋለሙ ።

ይህንን ጽሁፍ በመጻፍ ላይ እያለሁ -አንድ ለረዥም ዓመታት የማውቀው ኢትዮጵያዊ የተወሰኑ የአሜሪካ ግዛቶች ወይም እስቴትስ ጎብኝቶ ሲመለስ -<ወያኔ ሃያ አምስት ዓመታት ስለገዛን ለምን እንቆጫለን  -የወያኔ ወኪል ሆነን የምናገለግ እንመስላልን> አለኝ ። እኔም በአውንታ እንዴት እይታችን ተገጣጠመ አልኩት !

በዚህ ጽሁፍ ንኡስ አርስቶች ሥር የጻፍኳቸው  ድርጊቶች/ ይሁንታዎች ሁሉ ምክንያቶች ምንና ምን ይሆኑ ? የወያኔ እጅ ? ድንቁርና ? የንቃተ-ኅሊና ዝቅተ ኝነት ? የግልና የቡድን ፍላጎት ከአገርና ከሕዝብ ፍላጎት ማስቀደም ? እንድ እኔ እይታ ከላይ በዚህ ጽሁፍ ከገለጽኳቸው  ድርጊቶች ሁሉ በስተጅርባ  – ወያኔ ፣ድንቁ ርና ፣ የንቃተኅሊና-ዝቅተኝነት ፣ የግልና የቡድን ፍላጎቶች አሉበት ።

ይኸውም  በወያኔ ጥቅማ ጥቅም በመታለል ፣በድንቁርና ተጽኖ፣ ከንቃተ-ኅሊና ማነስ እንዲሁም ከአገርና ከሕዝብ ፍላጎት የግልና የቡድን ፍላጎት በማስቀደም   የሚከወኑ ተግባሮች ናቸው እላለሁ ፣ የእነዚህ ውጤቶች ናቸው ፣ ሌላ ሊሆን አይችልም ። በመሆኑም – በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ራሳችንን በማጥፋት ላይ እየዘመት ነው ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወያኔ ዕድሜ የሚያራዝም ሥራ እየሠራን ነው ። ስለሆነም ለሕዝባዊ አንድነታችን ፣ ለአገራዊ ሉዓላዊነታችን እና ዲሞክራሲያዊ የአስተዳደር ሥራዓት ለማምጣት ለምናደርገው  ‘ፀረ -ወያኔ የጋራ ብሄራዊ ትግል’ ጠንቅ ጠባብ ብሄርተኝነት ብቻ አይደለም ። በዚህ ጽሁፍ በንኡስ  አርእስት ያሰፈርኳቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች – ለተያያዝነው  ፀረ-ወያኔ ብሄራዊ ትግል ጎታች ፣ እንቅፋትና ሳንካ ናቸው  የሚል እምነት አለኝ ። ለመፍትሄው በጣም ሊታሰብበት ይገባል እላለሁ ። ከመፍትሄዎቹ አንዱ -የሰከነና ጥራት ያለው (ኦርጋኒክ) ውይይት ማድረግና ማንቃት ይሆናል ።

ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተነሱብንን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች በሃቀኛ የኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ይወድማሉ ! በቅርጽ ለኢትዮጵያዊነት የቆሙ የሚመስሉ ፤ በይዘት ግን በፀረ-ኢትዮጵያዊነት የተሰለፉ ሃይሎች ይጋለጣሉ !

ይህ ጽሑፍ አደባባይ እንዲወጣ በድረገጻችሁ የምትለጥፉልኝ የሚዲ ሞያተኞች ፤የኢትዮጵያ አድባር ይጠብቃችሁ ፤ ተፈጥሮ ይመርቃችሁ -ማለት ዕድሜያችሁ ይርዘም  ።

46 Comments on “ፀረ-ወያኔ የጋራ ብሔራዊ ትግል ጠንቅ ጠባብ ብሄርተኝነት ብቻ አይደለም”

  1. This year, the world will generate 2.6 trillion pounds of garbage — – Yonas’s scribble or rather rant is nothing but a GARBAGE…

  2. አሁን አተ ተቋሚለመምሰል ነው እንኳን የሰው የዝንብም ተጋራ እናውቅ አለን ድርብ ወያኔ?

  3. ESAT and PATRIOTIC GINBOT-7 have become a nightmare to TPLF/Woyane and all Tigre accomplices. The writer of the the above opinion, Yonas, is in the camp of the likes of Elias Kifle, Abraha Belay and Abebe Belew who are doing Woyane’s bait by spewing fear and hate for ESAT and other successful Ethiopian institutions. So Yonas continue with your lies, misinformation and better yet hallucination. So I say to you and the likes, the best you can do at this time is to crawl back to your Dedebit where you belong. The day of reckoning is fast approaching.

    Thanks to ESAT, the world now knows that TPLF/Woyane leadership consists of cunning, ruthless, vicious and stone-cold criminals who maintain themselves in power by force of arms only. TPLF/Woyane regime is far more brutal and cruel than the Italian Fascist army that invaded Ethiopia, and no different in its aims to completely destroy the social, economic and political fabric of the country.

  4. You are rotten looter tplf. Why do you have to pretend? Let me tell you this: your masters are preparing to fight with Eriteria and one of their strategies to win the war is to quell any possible uprising from inside and outside Ethiopia. Bad mouthing ESAT, Tamagne, Sisay, …. all these bulshit will not save you. You know what is good for you? Abondon woyane and stand with Ethiopians as the true tigrians did for centuries. Woyane is not Ethiopian.

  5. What a total waste?

    I never seen the TPLF PRists get such busy and desperate to write such garbage. The Good news for us the democracy and freedom hungry Ethiopians is that the end of the Banda TPLF is near us and we kinda feeling it more than anytime and enjoying to see how scared, desperate the Banda TPLF and in a state of complete lose they are.

    Death to Banda TPLF !
    Victory to all Ethiopian fighters for freedom and democracy, including those in Eritrea !
    Long live Ethiopia !

  6. ወዳጄ መልካም ብለሀል ስለ ኢሳትና እሳታዊ ስራው ይፃፍ ከተባለ የሳይበር ስፔስም አይበቃም። በኛው ገንዘብ እኛን የሚያጠፉ እኛን የሚያዋርዱ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠየፉ እየጋበዘ ኢትዮጵያውያነትን ያሰድባል። ችግሩ የነሱ ሳይሆን እኛ መሰደባችንን መገንዘብ ያለመቻላችን ነው። ሰሞንን ይህን ትከትሎ የኢትዮጵያ ጠላቶች የእሩምታ ተኩስ ያወርዱብሀል የአውስትራሊያ ቢራ እየጠጣህ መሳቅ ነው። በነገራችን ላይ በየቤተ ክርስቲያኑም የሚደረገውን አመጽም ዋናው አስተባባሪ ይሀው ኢሳትና ግምቦት ነው ግምቦት እና እሳት አቴቴ ነው ወይስ ጨሌ? ስለ መልካም ጽሁፍህ እና ለገጹ ባለቤቶች ደፍረው በማውጣታቸው ሊመሰገኑ ይገባል። እስቲ ይህ ጽሁፍ ኢትዮጵያውያን ስንገናኝ እየበገንን የምናወራው ነው እኔ አይደለሁም እሱ ነው ምን ያሰኛል? ለዛውም ጸሀፊው ስሙን ትቶ። በተረፈ ቪዥን ኢትዮጵያ ያልከውን ሺዥን ኤርትራ ብትለው መልካም ነበር። ኢሳት የጅ7 ነው በዚህ ቅሬታ የለኝም በጀቱን ግን አባላቶቹ፤ ሻቢያ፤ ኤርትራዉያን ግብጾች፤ አረቦች ያዋጡ። አገሬን ለማፍረስ ተባባሪ አልሆንም። ተንኮለኛ ወያኔዎች በዚህ አስተያየቴ ደስ አይበላችሁ ክጅ7 ተራ አባላት ጋር ችግር የለብንም በእይታቸው የተሻለ መስሉአቸው ነው አብረን ወደፊት እንደምንሰራ እትጠርጥሩ የናንተው ልዩ ነው ከምንም አይገጥምም።

  7. a courageous and truth full analysis of the state of diaspora Ethiopian politics. It really shows the budding of tribalism and dictatorship in the so called diaspora opposition.

  8. አንተ አድርባያ ባንዳ ነህ ከወያኔ በማያስ ጠላት ነህ የኤላያስ ክፍሌ ዘመድ ሆነህ ምን ልትረባ የኢትዩጵያ ህዝብ ይፋረድሀል ኢሳት ጀግና ነው አርበኞች ግንቦት 7 ያሸንፋል አንተና አንተን የሚመስሉ ለፍርድ ይቀርባሉ ባንዳ ወያኔ

  9. ዛሬ ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታማኝ በየነዎችንና ሲሳይ አጌናዎችን አፍርታለች!!

    ትግላችን በሁሉም የኢትዮጵያችን ምድር ላይ በመረረ ሁኔታ እየተካሂያደ ነው ያለው!!

    በወገኖቻችን ላይ እየተደረገ ያለው መጠነ ሰፊ የግፍ ሰቆቃ ከመጠን በላይ ስለሆነ ከዚህ በሁዋላ ተኝተን የምናድርበት ጊዜ አክትሟል!!
    ተነሱ ወገኖቼ ይብቃን !!
    ትእግስት ብሎ ነገር ከዚህ በሁዋላ አይሰራም !!

  10. You said right Yonas.but from the ethiopians nothing except mesadeb.no one ethiopian like the truth.Bls for ethiopinas mesadeb bahl new,lie,many many.so leave them if they want divided ethiopia in to 1000 villages.Habesha tenkay zer liers.yonas leave them ke habesha nothing good except mesadebbbbbb.dirty habesha.

  11. የትግራይ ህዝብ ሆይ!!!
    በስምህ ነፃ ሊያወጣህ የሚነግድብህን፣ ወልደህ፣አሳድገህ፣ቀልበህ ከዚህ ያደረስከው ፓርቲህን በቀደምትነት ታግለህ ማስወገድ ይጠበቅብሀል!!
    እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ የቤት ሥራ ተሸክመህ ነው ያለኸው!!
    የቤት ሥራህን ከሌላው ቀድመህ ማጠናቀቅ እጅግ ይጠበቅብሀል!!!!
    ትግል የጀግኖች ድል የእግዚአብሔር ነው!!
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክልን!! አሜን!!

  12. red color = qey qelem
    monday = seño = seNo,
    bandie 2tun symbol key+n=ñ
    buyer =geþ,
    bandie 2tun symbol key+t=þ
    page = gex
    poet = gxm gexami
    drink = mexex
    study = xnat
    breast = xut
    salt = cew
    fatty meat = coma sga
    shoes = camoch
    smoke = cis
    tortoise = ieli
    wrong = s-htet
    right = tkkl

  13. ኢሣት ከመቋቋሙ በፊትና በሁዋላ እንደ የሜልበርን ህዝብ ለኢሣት ብዙ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ የለም። ኢሣቶችም ራሳቸው የሚመሰክሩት ነው። ለምሣሌ፦ አቶ አበራ የላሊበላ ሬስቶራንት ባለቤት $30,000 ባንድ ግዜ ለኢሣት ማበርከታቸውን ሁላችን የምናስታውሰው ነው።
    ታድያ ህዝቡ በገንዘቡ ኢሣትን ሲደግፍ ውስጥና ውጭ የሚገኙ ኢትዮጽያውያን የወያኔ ተቋዋሚ መሪዎችን እያቀራረበ ያነጋግራል፥ ያወያያል ያደረጉት ውይይት ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልፅ ያስተላልፍልናል በሚል ነበር።
    ኢሣት ከትቋቋመ አንድ ዓመት በሁዋላ አቶ እሸቱ(በቪክቶርያ የኢትዮጵያ ማ/ሰብ ኮሙዩኒቲ አመራር) ኢሣት የግንቦት 7 እንደሆነና ከኢትዮጵያውያን እንደተጠለፈ፦ እነ ታማኝም ከአማራ ጠላቶች ጋር መስራታቸውን እንድያቆሙ፦ ምክርም ማስጠንቀቅያም ማስተላለፋቸውን አንዘነጋውም።
    ነገርግን መጀመርያ ሁላችን ያላወቅነው ነገር ቢኖር ኢሣት የግንቦት7 ሣይሆን የሻብያ መሆኑን ነው።
    አሁን ግን ሁሉን ኢትዮጵያዊ ነቅቷል። ማንም ሊሸውደው አይችልም።
    ከፈለጉ ሜልበርን መጥተው ፔትሽን ፈርሙ ብለው ይሞክሩና!።

  14. And bexlqet ena besfat metaseb yalebet tlq qumneger ale.
    Esum goseñanet, zereñanet, goxeñanet ena bhierteñanet yemibal new.
    Yihn guday betkkl meftie mesxet lemnfexrat dimokrasiyawit itiopia qulf meseret new.
    Goseñanet/bhierteñanet mexelatna mewegez yalebet lerasu yegosa yebelaynet woim lemegenxel yaleme kehone new.
    Neger gn begosaw lay gf/bedel, ciqona eyetefexemebet bemehonuna yan lemasweged alama adrgo kehone lidegefna liberetata gd new.
    Lemsalie amara xelatie new blo ye tgrie woyanie be amara lay mexene sefi yemaxfat xqat kefto aseqaqi gdya, esr, zrfiya, yemeriet worerana mafenaqel eyefexemebet yigeñal.
    Yihn lemasweged amara be bhieru bideraj ena yetgrie woyanie biyaxeqa tkkl new
    Alamaw tgrie woyanien masweged eskehonena le itiyopia andnet, ekulnet, xere-ciqonana le dimokrasi blo ketagel tkkl new.
    Liela msalie demo ye tgrie woyanie be oromo hzb lay eyederesebet yemigeñewn gfna bedel lemasweged biderajna tgrie woyanien biwega tkkl new.
    Neger gn enqsqasiew le itiyopiya andnet, ekulnet, dimokrasiyawinet mehon alebet.
    Yih be programm be tegbarm yemitay mehon alebet.
    Manñawm xere-tgrie woyanie tgl medegef yalebet megenxel kalhone, ye lielawn itiyopiyawi hlwna/ekulenet yemixarer kalhone new.
    Alamaw ye tgrie woyanien masweged bcha yehone tglm be ejgu yidegefal.
    Le ekulnet, le andnet, le dimokrasiyawinet, le nexanet ena le fth yemidergu tgloch bemanm beyetm bideregu medegef alebachew

  15. ኢሳት ከድቅድቅ ጨለማ አውጥቶ እዚህ አድርሶናል የተሻለ
    ብርሀን ለማግኘት መተቸት አይከፋም ተገቢም ነው ።ከሰው
    ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም እንደሚባለው ስህተትን
    ከማስገንዘብ ያለፈ ትችት ነው።

  16. ከሞላ ጎድል ፅሁፉ እውነታነት አለው! አውስትራሊያ የሚኖሩ ወገኖቻችን የበለጠ እንዲወያዩበት ያደርጋል በድህረገፅ በመለጠፍ ትብብር ያደረገው ኤልያስም ሊመሰገን ይገባወል የሚገርመው ግን አሁንም የግንቦት 7 ደጋፊወች ከተጋረደባቸው ግርዶሺ አይናቸውን ለመግለጥ አለመቻላቸው ነው ቢያንስ ሰሞኑን የተከሰተው የድርጅቱ መሪወች አቋም (ሻቢያነት) ታላቅ ማስረጃ ነበር። ግንቦት 7 ማለት ልክ ወያኔ የሚጓዝበትን መስመር ተከትሎ የሚጓዝና በአንድ ጎሳ ላይ ጥላቻ ያደረባቸው ደቡብ አካባቢ የተወለዱ ግለሰቦች በወያኔ አስታዋሺነት ተደራጅተው የሚመሩት ድርጅት ለመሆኑ ግልፅ ነው። ግንቦት 7 ለትግሉ ይጠቅማሉ ብሎ ያዘጋጃቸው ፖሊሲወች በሙሉ ከወያኔ የተኮረጁና በተዛዋሪ ግንኙነት ያላቸው ሲሆኑ ለአፈፃፀም እንዲያምች ተብሎ በዲሞክራሲዊ ስም ሺፋን የተበጀላቸው ናቸው።

    እኛን የሚፈልጉን ለገንዘባችን እንጅ ወያኔን ታግለን ነፃነታችን እንድናስመልስ አይደለም ወያኔን በመደራደር የሞተችውን ኢትዮጵያ እንድንቀብራት ነው የሚፈልጉት። ተወደደም ተጠላም ወያኔና ሻቢያ ከአርባ አመታት በላይ ከፈፀሙት ግድያ ይልቅ ነፍሰገዳዮችን በአምሳላቸው አደራጀተው አገራችን እንዳጠፏ ተግባር ምስክር ነነው። የግንቦት 7 መሪወችም የለየላቸው ፀረ-ኢትዮጵያ ነፍሰበላውችን በኢሳት አማካኝነት እየፈለፈሉ የጥላቻ ካርታ እየሳሉ ያልነበረ ሰንደቅ አላማ እየሰቀሉ ከእስትራቴጀካዊ ጠላቶቻችን በወዳጅነት ስም እየተሞዳሞዱ ከጥፋት ወደጥፋት እየተረማመዱ በማጭበርበር ላይ የሚገኙ ግልብጥ ወያኔወች ናቸውና ፀሐፊው እንዳስቀመጠው ዲያስፖራው ማሰብ ያለበት ወያኔ የገደላትን ኢትዮጵያ ግንቦት 7 ሊቀብራት አይገባምና አስቸኳይ መፍትሔ መፈለግ ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ለማንኛውም ለፀሐፊው ምስጋና ይድረስልኝ

    ዳመናው ነኝ

  17. We know this websit working to tplf under groung this strugle is not about Esat g7 olf onlf this strugle is as human my feedomm stolen by tairant tigre tplf
    Death for tigre tplfk

  18. We know this websit working to tplf under groung this strugle is not about Esat g7 olf onlf this strugle is as human my feedomm stolen by tairant tigre tplf
    Death for tigre tplfk

  19. Arbeñoch-gnbot 7 ye tgrie woyanien lemedemses yetequaquame new.
    Esat be tgrie woyanie yetafenewn mereja le itiyopiyawiyan masaweq ena ye xere-tgrie woyanie enqsqasiewech bemasaweq magez new.
    Betegbar ag7 yasayew gulh dl yelem.
    Esat michlewn yahel mereja eyaqereb new. Le xere-itiyopiya hailoch mesariya mehon yelebetm. Hunoal yemil texebaci mereja yaqrb. Yalemerja esatn meqawom le tgrie woyanie mesrat new. Woim yetgrie woyanie sra new.
    Ag7n yemiqawomu hulet mkniyatoch aqerbewal.
    1. Ye eritrea meriwoch le itiyopiya bego amelekaket yelachewmna be eritrea dgaf nexanetachn magñet mihon aydelem yilunal.
    2. Beselamawi tgl enji betxq tgl mehiedu mexfo new yilunal.
    Gn enezih hulet mkniyatoch ag7n lemeqawomna lemawgez beqi aydelum. Nexanet felagiwech kehon, ye tgrie woyanien medemses yemnsha kehon mengedun cerq yaderglachuh bcha new malet minorbn.
    Xelatien lemn twegutalachuh blo meqawem yexiena aydelem.
    Awe and miyascenq neger ale. Esum wenie temoltew wede eritrea mihiedu jegnochachin eza mn hunita wusx gebtew new amerqi yetxq tgl yaladeregut yemil hasab new.
    Yihm bihon le gara nexanetachin lisewuln yetesemaru jegnochachin endnqawm mkniyat ayhonm.
    Leña slasebu lenesum bemasebachin axaru xnqaqie adrgu malet alebn.
    Ag7 amerqi tgl aladeregm blen meqawom woim mawgez yelebnm.
    Mkniyatum gleseboch yemichlutn lemadreg berasachew menged ye mehied mebtachew new.
    Aleqachew aydelenm.

  20. To my understanding
    G7 has lost so many of its supporters
    between the recent
    Shameful outright insult on Tilahun Gessese & his spouse and the G7 call for petition
    in support of the
    Killer Issaeias Afeworki. Still squeezing day by day.
    KAFERKU AYMELESGNE

  21. Yegema eniqulalli siseber tibesugni tibesutni yilali ende? Amtena yegema enqulali andi nachihuu.your stinky too woordy doesnot make you writer.becouse if you break stinky egg do you kook it?.you are stinqy egg.in the middke of no where ,you think what you wrote is fonna gwt people attention to it. No way.

  22. Gim -7 bemulu tesfachew yechelmbachew babarriyanet serat
    yalu nachew. Temehirt yaldefru yebtachinet yemisetachew asafariwoch nachew. Sewu indiet indetelachw baweku

  23. Esat and arbegnot ginbot 7 are gedayu deadly enemies for tgre woyane and alegnita/hope for all ethiopians.

  24. To start with G7
    isn’t an Ethiopian
    group. Its as a Crystal clear that they all are 100%
    Shabiea’s hired agents . All ETHIOPIANS knows
    these facts.
    High time to apologize the Ethiopian people.

  25. ለሁሉም ሰው የመስለውን አስታይት መስጠት
    መብቱ ነው።
    ጸሀፌው ወያኔ የሚያስብለው ምኑ ላይ ነው?
    ኢሳትን በመተቸቱ ከሆነ የዴምክራሲ ሀሁ አለመረዳት ነው።ማንም ሊተች ሊወቀስ ይችላል
    ሀሳብን በሀሳብ እንጂ በስድብ አይደለም
    ለእድገትም ሆነ ለለውጥ መማማር ነው
    ሚዲያ አስመልክቶ የራሱን ሀሳብ አቅርባል
    ትችት ስንዝራል መብት ነው
    በአጭሩ በጭፍን ድጋፍ እና በጭፍን ተቃውም ለውጥ አይመጣም

  26. Keep crying, ESAT is exposing your cousins unfathomable crimes against our people. An attack on ESAT is an attack on the people of Ethiopia. Tplf is sending it’s agents to discredit Esat, but it won’t happen because Esat established it’s credibility by know. The judge is not yonas teklemariam. There’s no kangaroo court here that tplf agents running. The judges are the Ethiopians. They love Esat. How do I know, cuz everyone of them are reporters by exposing the wicked regime. As for me, I will keep giving for Esat.

  27. አውስትራልያ እድለኞች ናችሁ። ለምን ብትሉኝ ሚዛናዊ የሆነ የSBS ሬድዮ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ አለላችሁ።
    ስለዚህ ይኼን ሃሣብህን በዛው መልቀቅ ትችላለህ። አቶ ዮናስ።

  28. bexam yemigrmw Gim 7 yalew beabzGNEW
    wegel sertw bemingest yetfrdebachw
    nachew . Gim 7 lemgbat mejemeria
    criminal honeh yemitflg mehon alenh.

  29. The writer has said what he has to say the point is we are not producing results by arguments,he she said, bla bla etc. One thing that is certain is that, if you are being misslead by few media or individuas, the problem is yours not the the one with the master mind. Hey who are we following anyway, and why is everyone is waiting for some leader, messiah to save him? We need to get up ourlazy behind and take charge of ourlife and destiny.

  30. መጀመርያ እኔ እንደማውቀው ኢሣት ከሻብያ በስተቀር የማንንም ድጋፍ እንደማይበቃው ነው። ለምሣሌ፦ መታሰብያ ቀፀላ (ምንአለሽ መቲ) አምና ሜልበርን የመጣች ግዜ የተገኘ የኢሣት ደጋፊ እኔን ጨምሮ ከሃምሣ ሰዎች የሚበልጥ አልነበረም። የተገኘው ገንዘብም ከስድስት ሺ የሚበልጥ አይደለም።
    ታድያ፦ የደርሶ-መልስ ጉዞ ትኬት ከለንደን እስከ ሜልበርን፣ የአዳራሽ ኪራይ፣ የPA system ኪራይ፣ የሆቴል እና ጥቃቅን ወጪዎች ቢሠላ ከገቢው ወጪው ይበልጣል። የካችአምናም እንደዚሁ አፈወርቅ አግደው የመጣ ግዜ። ስለዚህ ኢሣቶች ሙሉ ወጪያቸው እና ደመወዛቸው የሚሸፍኑላቸው የኢትዮጵያ አንድነት የማይፈልጉት አንዳንድ የአረብ ሃገራት በሻብያ አመካኝነት መሆኑን ነቄ ብለናል።

  31. የእስራኤሉ መሪ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 3 ሺህ አመታት አስቆጠረች ሲል ወያኔ እኮ 100 አመት አይሞላትም ሲሉ መልሳቸው ምን ይሆን ወይስ ኔታናሁን ስህት ነው ይሉት ይሁን ወያኔ ፀረ-ኢትዮጵያነቱን የሕዝብ ጠላት ዋናው ነቀርሳ ወያኔ የጋራ የኢትዮጵያ ጠንቅ ፣እባቦች ጠባቦች ድዊይዩ ናቸው፡፡

    ተዋበ

  32. Betam yemiyasqew irs bersachew ingda
    honew siqrbu neaw . sawu neqe beloal.
    Man yabde ale ke xelat media wust lemetayt
    yemifelgw . Yeferdbt Ermias Legesse bichnaw ina
    hule geb ye Eri-TV Analyst . Ye fugera metsehafun
    sewu inwnet meslot chebchebe lakas fistion mehonu
    yetawkw metsehafu publish yetdrgew be Shabis ye genzb
    degaf be esat crews betbebr mehonu inho yetawkew
    zegyto neaw . Sele gelesbu ye esatu Afework ( gigurgur )
    yetnagerw kebqi belay neaw.

  33. Luel alem bemil sm ye dehnnet mereja new blo yehone yehast mereja yemixf sew ale.
    Yih sew ye tgrie woyanie teqawami meslo new ke woyanie dehnnet yetegeñe mereja blo yemixf.
    Gn andum ewnet huno alayenm.
    Yih sew ye tgrie woyanie selay yemeslal.
    Ye woyanie teqawami meslo yehaset mereja eyexafe be teqawamiw gora lemetamenna sergo lemegbat yemimokr yimeslal.
    Be careful/Xnqaqie adrgu lemalet new.

  34. አሁን ለኢሳት ለ ግቦት7 ማዋጣት አለማዋጣት ምን የሚያጨቃጭቅ ነገር አለ የኢትዮፒያ ጠላቶች የትግሪ ነጻ አውጭዎች እንዲሁም ተገንጣይ አስገንጣዮች 17 አመት ኢትዮፒያዊነትን እና ኢትዮፒያን ሲወጉ እኮ በዲያስፖራ ያሉ የትግሪ ነጻ አውጭዎች እያንዳንዱ ገንዘብ እያዋጣ በተለያየ መንገድ እየሰበሰቡ የርዳታ ገንዘብ እየተቀበሉ አይደለሞይ ለአላማቸው ኢትዮፒያን እና ኢትዮፒያዊነት ጠላት ብለው የወጉት የደርግ ስራት ጋር እኮ ሳይሆን ችግራቸው ከኢትዮፒያዊነት ጋር እና የራሳቸውን አገርና ለዘሮቻቸው ነጻነት ማስከበር ትግሪን ከድህነት ማውጣት ነው ጠባብ ብሂርተኞች የምትላቸውንማ አጭበርብረው ፐውዘው አምሃራን እና ኦርቶዶክስን ካጠፋን ለየዘሮቻችን አገር እና ነጻነት እናስረክባለን በሚል 25 አመት ኢትዮፒያ ቁንጮላይ ተቀምጠው ትግሪ የሰፈረበትን ለማስፋት የአምሃራን ዘር ሲያጠፋ ሊሎች ተገንጣይ ሃይሎችን ከኢትዮፒያ ምድር አምሃራውን እንዲያጠፉ እንዲጨፈጭፉ የኛ ጠላት አምሃራ በቅኝ ግዛት የያዘን እንጂ ኢትዮፒያዊ አይደለንም ኢትዮፒያ ታሪክ የላትም ሚሊሊክ የፈጠራት ነች ሚሊሊክ ክርስቲያን እያለ ጨፍጭፎ አምሃራ በወረራ የመጣነው በማለት እነሱ ሲሰፍሩ የአምሃራ ዘር እንዳልነበረ እየተሰበከ ካድሪው በአምሃራ ጥላቻና በኢትዮፒያ አንድነት ጥላቻ እየተጠመቀ የብሂር ብሂረሰቦች መብት እስከ መገንጠል እየተባለ በህገ መንግስት አገር ለማፍረስ አንድ ላይ በኢትዮፒያ ስም የህዝብ አሰፋፈርን ዘር በማጥፋት እና ዘር በማጽዳት ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ ተጠቅሞባቸዋል ጠባብ ብሂርተኞች በዘራቸው ከረጢት ውስጥ ገብተው ሲፈራፈሩ የትግሪ ነጻ አውጭ ክልል ያለገደብ ለትግሪው የሰፈረበትን ካርታ ሲያሰፋ ወደተለያዩ የኢትዮፒያ አውራጃዎች ትግሪን በማጉረፍ የኢኮኖሚ ባለቢት በማድረግ ነጋዲው ፎቅ ሰሪው ባለሃብት ኢንቨስተር እየተባለ ሊላውን እየሰለዩ ሃብቱን ከባእድ ጋር ማእድኑን ,ወርቁን …እያውጡ ሲቸበችቡት እና አገሩን እና ማንነቱን ሲያጠፉት ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ እኮ ጠባብ ብሂርተኞችን ስለዘራቸው እያሰቡ ትልቃን ኢትዮፒያ ሲዘርፍና የትግሪ ተጠቃሚ ሲያደርግ አይናቸው እንዳያይ ጭቅላታቸው ከአገራቸው ይልቅ ዘራቸውን እያሰቡ እነሱን ማጥፊያ ሃይል የትግሪ ነፍሰ ገዳይ እያሰለጠነ እያለሳለሰ ጠባብ ብሂርተኞችን በቁጥጥሩ ስር በማስገባት እያከበከቡ ከጫካ አምጥተው በጫካ ህገ መንግስት እየተገዙ ኢትዮፒያዊ ነጻነታቸውን በፈቃደኝነት ለወያኒ አስረክበው በዘር ማንነታቸው ነጻነት አተው ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭን ዛሪ ይማጸናሉ ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ አሁንም በነጻ አውጭ ስም በግልጽ የትግሪ ነጻነት ህልውና የሚከበረው በትግሪነት የያዝነው ያለምነው አላማ ተሳክቶ እስካላረጋገጥን ድረስ በዘር ማንነታችሁ ነጻ መውጣት የለም ብሎ ክርችም አርጎ በገዛ አገራቸው በገዛ ሃብታቸው በጥባብ ብሂርተኝነት ነጻነታቸውን ያጡት ጠባቦችና ሃላ ቀሮች ናቸው:: ለምሳሊ አንድ የኦሮሞ ዶ/ር ከጃዋር ጋር ባውስትራሊያ እራዲዮ ቃለ ምልልስ ሲደረግለት ወያኒ የኦሮሞ ወገኖቻችንን በመጨፍጨፉ ምክንያት ነበር ቃለ ምልልሱ ዶ/ር የኦሮሞ ዘር ታጋይ ነው በወቅቱ ደግሞ ወያኒ የሱርማ ወገኖቻችንን በ 21ኛው ክፍለ ዘመን መሪታቸውን ለመሸጥ እንዲት በገመድ አስሮ ያየንበት ዘመን ልባችን የደማበት ወቅት ነው ዶ/ ር ስለነዚህ ሰዎች ሲናገር ወያኒ ይሂንን ሲሰራ በቃ እኛ እሩቅ ስላሉ አናውቅም በማለት ሲናገር በጣም ነው ያዘንኩት አንድ ዶ/ር እንዲህ የወረደ ነገር ሲናገር ያሳዝናል እነዚህ ሰዎች ኢትዮፒዊያን ናቸው ህወሃት የኢትዮፒያ ጠላት ስለሆነ እኮ ለመዝረፍና ለማጥፋት እንደነዚህ ጠባብ ብሂርተኛ ዶ/ር እና ፕሮፊሰር አይናቸው ተጨፍኖ ዘራቸውን ብቻ እያሰቡ ትግሪ ወያኒ ለነሱ አገር በዘር እንዲወስንላቸው ፕሮፓ ጋንዳ እንዲሰሩ በመጠቀም ሊላውን ዘር ነገድ ወያኒ ያለክልል ሲጎርፍና ሲዘርፍ አፋቸውን እንዲይዙና ባለህበት እርገጥ እንዲሉ ስላበቃቸው ነው ጭራሽ ዶክተሩ የሱርማን ብሂረሰብ እሩቅ ስለነበሩ አላወቅንም ሲል ያሳዝናል ወያኒ በመላው ኢትዮፒያ ጠባብ ብሂርተኞችን አይናቸውን እየጨፈነ እኮነው እየዘረፈ ያለው ስለዘሪ እንጂ ስለሊላው አያገባኝም እንዲሉ በማድረግና ዘራቸውንም ሆነ እነሱን ለማጥፋት ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ የመላ ኢትዮፒያን ሃብት ተቀራመታት በኢትዮፒያ ሃብት የትግሪው ነጻ አውጭ የኢኮኖሚ ባለቢት ሆነ ስለዚህ ጠባብ ብሂርተኞች አገርን እና ዘራቸውን ለማስገደል አገር አልባ ለማድረግ ትልቅ ሚና ለትግሪ ነጻ አውጭ ተጫውተዋል የ25 አመት ፖለቲካ ይህ ፖለቲካ አይደለም እንደ እንሥሣ ህዝብ ለህዝብ እንዲጋደል አብሮ እንዳይኖር በማድረግ ግዚ እያራዘሙ ለዘሪ ነጻነት እና አገር እምመሰርተው ትግሪን ከድህነት የማወጣው የትግሪ የበላይነት የሚከበረው በዚህ እስትራቲጂ ነው የሚለን ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭነው:: ዛሪ ከትግሪ በስተቀር እያንዳንዱ ኢትዮፒያዊ ነገድ አገሩን ያጣ በዘር ማንነቱ አገሩን ያጣ በዘር ማንነቱ የተጨፈጨፈ እየተጨፈጨፈ ያለ ወደ ትግሪ ስንሂድ ጥያቂአቸው የማንነት ጥያቂ አይደለም:: ሊላው ነገድ ወደ ትግሪ እየጎረፈ ትግሪን ስለወረረ በትግሪ ሃብት የኢኮኖሚ ባለቢት ስለሆነ አይደለም :: ትግሪነትንም ሆነ ኢትዮፒያዊነትን አልተነፈጉም ወያኒ ግን በኢትዮፒያስም ለትግሪ ነጻ አውጭነት በነጻ አውጭ ስም ጉብ ብላል የትግሪ ተቃዋሚዎች የሚቃወሙት ህወሃት በስማችን እየተጠቀመ አሁንም ትግሪ ከድህነት አልወጣም እያሉን ነው ይሂ ትልቅ ልዩነት አለው ከሊላው ጋር ሲተያይ ሊላው ከድህነት ለመውጣት አገር ያስፈልገዋል በህወሃት አገሩን እና ማንነቱን ነጻነቱን ስለተነፈገ በመጀመሪያ አገሩን እና ነጻነቱን ማስመለስ ግድ ይላል ከዛ ብሃላ ከድህነት ለመውጣት መስራት ይቻላል ስለዚህ የኢትዮፒያ ህዝብ ለአገሩና ለነጻነቱ በፈለገው መንገድ ለኢሳት ሆነ ለግቦት ሰባት ቢያዋጣ መብቱነው ለነጻነት እስከሆነ ድረስ ህወሃት ኢትዮፒያላይ ጉብ ብሎ የትግሪ ነጻ አውጭ ነኝ ይላል የህወሃት አባል የሆነ ሁሉ ያዋጣል አይደል እንዲ ? ዲያስፖራ ያለ የትግሪ ማህበረሰብ ለትግሪ ልማት በሚል ስም ገንዘብ ያዋጣሉ ስለዚህ በኢትዮፒያዊነት ለኢትዮፒያ ነጻነት ከዘራችን ይልቅ ላገራችን ብለው ኢትዮፒያኖች በፈለጉበት ተሰባስበው ግቦት 7 ይሁን ኢሳት ለአላማቸው ከሆነ ምንድነው ችግሩ እያንዳንዱ ለአላማው ነው ለነጻነቱ ነው ማውጣት ያለበት ስለዚህ ምነው ኢሳትንና ግቦት 7 ላይ ብቻ ችግር አበዛህ እንደዚህ አይነት ባንዳዎች ኢትዮፒያኖች የዘር ከረጢት ውስጥ ወተው አባቶቻቸው ለሞቱላት አገር ሲሰባሰቡ አይመቻችሁም

  35. እኔ የምጠይቀው ደግሞ ለምን ፕ/ር ብርሃኑ፣ ነዓምን እና ኤፍሬም ማዴቦ የአርበኛ ማእረግ ሲሰጣቸው ምነው? ለጋዜጠኞቹ ለፋሲልና ለመሣይ ? አሃ..!ለካ ማዕረግ ሰጪዎች እነሱ ናቸው!?። ኢሣቶች።

  36. Hulum ye ageritu habt, genzeb ke jibuti wode meqelie lemiseraw yebabur mesmer mewal ke jemere 2 amet honew.
    Ye skuar (sugar) projekt genzeb le meqeliew yebabur mesmer wlual.
    Yexefut kondomniyem genzebm endihu.
    Lemenge, le mekelakeya, le kll dgoma, wezete yemibalu genzeboch le meqelie babur menged wlewal.
    Zrfiyaw betolo woyanien kalawedmnew qexaynew
    hulun beteqemanbet seat bzu esatoch bzu ag7tochn enfelgalen ke zerafi worada yetgrie woyanie nexa endiyawexun.

  37. What do you think if you would like to be fucked with a huge dick, Writer ? Another Woyannie Banda ! Fuck Fuck Fuck You !

  38. የእሳትን ሚና በተመለከተ – ከዚህ ከፍ ብሎ የሚገኘውን አስተያየት ጻሃፊና የወንድም ዮናስ ማለት የዚህ ጽሑፍ ባለቤት አስተያየት ተመሳሳይ ነው ። ወንድም ዮናስ የሚለው እሳት የሚያገለግለው የወያኔ አቻ ጠላቶቻችንን – ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠላትነት ፈርጀው የሚታገሉን ሃይሎችን ስለሆነ ይህንን አቋሙን ይቀር ነው !!

  39. The writer raised the right questions many in the diaspora wishing to have answers for. He does not have answer, so do the many Ethiopian diaspora who share his concern. It is not going to be easy finding answers because usually illetrate Ethiopians in the diaspora are the one who are vocal while being suceptible to village poltics. The opportunist politicians already figured this out. They cater to their wish. I am not that old who is close to death. But I certainly believe of dying without seeing a matured political party operating from abroad. Nor do media

    outlet. As I said catering to the igorant villagers is the motto they worship.It has worked for the opportunist politicians. It will continue work. But Ethiopia loses.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*