“ለኤርትራ መገንጠል ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ናቸው” ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ፡፡

  “ለኤርትራ መገንጠል ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ናቸው” ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ፡፡

ልባም መንግስት ከመጣ ኢትዮጵያና ኤርትራ በኮንፌደሬሽን ሊተሳሰሩ ይችላሉ
የኢሳያስን መንግስት የማውረድ ኃላፊነት የኤርትራ ህዝብ ብቻ ነው
በድርድር በአሰብም በምፅዋም የመጠቀም መብት አለን
የቀይ ኮከብ ዘመቻ ቢሰምር ኖሮ፣ ይሄን ቃለ ምልልስ ማድረግ ባላስፈለገን ነበር …

የኤርትራ ችግር የሚጀምረው የፌዴሬሽኑ መፍረስን ተከትሎ ነው ይላሉ – በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረጉት ዕውቁ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ፡፡ እንዴት? ለአዲስ አድማስ በዝርዝር አብራርተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በ25ኛ ዓመት የነፃነት በዓላቸው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ለወርቃማው በዓል ያገናኘን” ማለታቸውን ያስታወሱት ፕሮፌሰሩ፤ ከዚያ በፊት ግን ሁለቱ አገራት በኮንፌደሬሽን ሊተሳሰሩ የሚችሉበት ዕድል ይኖራል” ባይ ናቸው፡፡ የኤርትራን መንግስት በኃይል ስለማውረድ ተጠይቀውም የሶማሊያ አልሻባብና የኤርትራ ብሄራዊ መንግስት ለየቅል ናቸው ብለዋል፡፡ የአሰብና የምፅዋ ወደቦች ያለ ኢትዮጵያ ፋይዳ እንደሌላቸው የታሪክ ምሁሩ ያስረዳሉ፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ችግር እንዴት ነው የሚፈታው? ምሁሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ መኖሪያ ቤት (ለቡ) ተገኝቶ በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ከታሪካዊ ዳራው አንስቶ በስፋት አነጋገሮአቸዋል፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ለመገንጠሏ ታሪካዊ ተጠያቂ የሚሆነው ማን ነው?
ይሄን ለማብራራት የቅኝ አገዛዝንና ኤርትራ እንዴት ነፃ ወጥታ ከኢትዮጵያ ጋር ተዋሃደች የሚለውን ማየት ያስፈልጋል፡፡ ፌደሬሽኑ ለምንና እንዴት ፈረሰ የሚለው ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡ አፄ ዮሐንስ 4ኛ ከወደቁ በኋላ አፄ ምኒልክ ስልጣኑን ሲይዙ ከጣሊያን መልዕክተኛ ጋር የውጫሌ ውል ይፈራረማሉ፡፡ እንደሚታወቀው 17ኛው አንቀፅ ልዩነት ይፈጥራል፡፡
ብዙ ሰዎች ለአድዋ ጦርነት መንስኤ አድርገው የሚያቀርቡት ይሄን የውጫሌ ውል ነው፤ ግን የውጫሌ ውል ምክንያት አይደለም፡፡ የውሉ 17ኛው አንቀፅ ክብሪት ይጫር እንጂ ዋናው ምክንያት የኢጣሊያ የመስፋፋት ፍላጎት ነው፡፡ ጦርነቱ በዚህ መነሻ ከተካሄደ በኋላ አፄ ምኒልክ መረብን ተሻግረው ለመግፋት አልሞከሩም ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ጣልያን የያዘችውን ከመረብ ወዲያ ግዛት ኤርትራ ብላ ሰይማ ማስተዳደር ያዘች፡፡ የቅኝ ግዛት ያኔ ነው የሚጀመረው፡፡ ለ50 ዓመት በዚህ ሁኔታ ኤርትራ ቅኝ ግዛት ሆነች፡፡ ቀጥሎ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጣ፡፡ በዚህ ግዜ ጣሊያን ከጀርመን ጋር ወገነች፡፡ ከነሱ በተቃራኒ የተሰለፈችው እንግሊዝ፤ ኢትዮጵያ ነፃ እንድትወጣ ታደርግና ጃንሆይ ከስደት ተመልሰው መንግስታቸውን እንደገና ይመሰርታሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ኤርትራ ከጣሊያን አገዛዝ ወደ እንግሊዝ ወታደራዊ አገዛዝ ትዞራለች፡፡ ለ10 ዓመታት ኤርትራ በእንግሊዝ ስር ነበረች፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኤርትራውያን የነፃነት ታጋይ ድርጅቶች ብቅ ይላሉ፡፡ በሶስት ጎራም ይከፋፋሉ፡፡ አንደኛው “ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ አለብን፤ ጠላቶቻችን ናቸው ቀድሞ የለዩን እንጂ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት” የሚሉ የአንድነት ሃሳብ አራማጆች ናቸው፡፡ ሁለተኞቹ ነፃነትን፣ መገንጠልን የሚፈልጉ ሲሆኑ በአብዛኛው በዚህ ስብስብ ውስጥ የነበሩት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ይሄ ንቅናቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘንድ ይደርሳል፡፡ አቶ አክሊሉ ሃ/ወልድ ያኔ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ እሳቸው ግሩም የሆነ የፖለቲካ ጨዋታ ይጫወታሉ፡፡ ሶስተኞቹ መዋሃድ አለብን ግን ውል ልናስር ይገባል የሚሉ ናቸው፡፡ በመጨረሻ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ በውል የሚለው ሃሳብ አሸነፈ፡፡ ኤርትራ መስከረም 1946 ዓ.ም በፌደሬሽን ትዋኃዳለች አንዱ የተመድ ተልዕኮ የኤርትራ ህዝብ ፍላጎት ባገኘው መሰረት ኤርትራ ነፃ ወጥታ የራሷን ውስጥ አስተዳደር መስርታ ከኢትዮጵያ ጋር በፌደሬሽን እንድትዋሃድ ይደረጋል፡፡
ከመጀመሪያውኑ የወቅቱ መሪ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ይሄን አለመፈለጋቸው እንግዲህ አንዱ የችግሩ መነሻ ነው፡፡ ለምን አልፈለጉም? ከተባለ፣ በኤርትራ ገና በመቋቋም በማደግ ላይ ያለ ቢሆንም ዲሞክራሲያዊ ስርአት ነበር፡፡ መድብለ ፓርቲ ያቆጠቆጠበት፣ የመናገርና የመፃፍ መብት ያለበት፣ ጠንካራ የሰራተኞች ማህበር የነበረበት ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያለው ደግሞ ፍፁማዊ ዘውዳዊ አስተዳደር ነው፡፡ ያ በህዝብ የተመረጠ ነው፡፡ እዚህ ያለው በመለኮታዊ ቅብአት የሚያምን ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለት መልክ ያላቸው ስርአቶች አብረው እንደማይሄዱ ዘውዳዊ ስርአቱን እንደሚያናጋው ጃንሆይ ተገንዝበውታል፡፡ ከመጀመሪያውኑ ፌዴሬሽኑን ለማፈራረስም ተንቀሳቀሱ በዚህ የተነሳ ፌደሬሽኑን ጠሉት፡፡
ይሄን የጃንሆይን ፍላጎት በተግባር ለመለወጥ ያገዟቸው ሁለት ኤርትራውያን ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት እንደራሴ የነበሩት ቢትወደድ አስፋው ወ/ሚካኤልና ቄስ ደሜጥሮስ ገ/ማርያም ናቸው፡፡ ይህን አቶ ዘውዴ ረታ በኤርትራ ጉዳይ መፅሃፋቸው ድንቅ አድርገው አስፍረውታል፡፡ የቢትወደድ አስፋው ዋና መከራከሪያቸው፤ “ፌደሬሽን ከኛ ልምድና የፖለቲካ ስርአት ጋር የሚጣጣም አይደለም፤ ቅኝ ገዥዎች የጫኑብን ነው፤ ስለዚህ መወገድ አለበት” የሚል ሲሆን ሌላው መከራከሪያቸው ደግሞ ፌደሬሽኑ በተራዘመ ቁጥር የኤርትራውያን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እየተዳከመ ይሄዳል የሚል ነበር፡፡ ስለዚህ ይሄን ፌደሬሽን ማስወገድ አለብን የሚለውን አቋም አንፀባረቁ፡፡ እኚህ ሰው ዋና ተቃውሞአቸው የኤርትራ ዲሞክራሲያዊነትን ነበር የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኚህ ሰው፤ “ይሄን ስናደርግ ጃንሆይ ይሄን አድርጉ ሳይሉን በራሳችን ተነሳሽነት ያደረግነው ቢሆንም የጃንሆይ ድጋፍ አልነበረንም ማለት አይደለም” ይላሉ፡፡ አቶ ዘውዴ ረታ ይሄን መነሻ አድርገው፣ ፌደሬሽኑን በማፍረስ ጃንሆይ ሊወቀሱ አይገባም፤ ተጠያቂው የኤርትራ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡
በወቅቱ ቢትወደድ በኤርትራ ፓርላማ ቀርበው፤ “ይሄ ውስጣዊ አስተዳደር የሚባል ነገር የለም፤ አንድ መሪ አንድ መንግስት ነው ያለን” ብለው ፌደሬሽኑን አፈረሱት፡፡ ጉዳዩ ይፋ ሲደረግ ግን የኤርትራ ፓርላማ በስምምነት እንዳፈረሰው ተደርጎ ነው የቀረበው፡፡ የኤርትራ ችግር የሚጀምረው የፌደሬሽኑ መፍረስን ተከትሎ ነው፡፡ የመጀመሪያውና ትልቁ የኢትዮጵያ መንግስት ስህተት ይሄ ነው፡፡ ተመድን ሳያማክሩ በግላቸው ማፍረሳቸው ጥፋት ነው፡፡ ጃንሆይ በወቅቱ “ይሄ ነገር አይሆንም ተው” ያሏቸውን አማካሪዎቻቸውን የፀሐፊ ትዕዛዝ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሐንስና የአቶ አክሊሉ ሃ/ወልድን ምክር ቢሰሙ ኖሮ ለራሳቸውና ለመንግስታቸው፣ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ይበጅ ነበር፡፡ እኔ በማላውቀው ከፍተኛ ፖለቲካ ፌደሬሽኑ ይፍረስ ከተባለ ወሳኙ የኤርትራ ህዝብ ነው ይሄም ታዛቢዎች ባሉበት በሪፈረንደም ሲረጋገጥ ነው ይህ አልሆነም የኤርትራ ፓርላማም ፌደሬሽኑን ለማፍረስ የህዝቡ ይሁንታ አልነበረውም ፌደሬሽኑን በማፍረስ ተጠያቂው ንጉሰ ነገስቱ ናቸው፡፡ በዚህ መነሻ ነው እንግዲህ በኤርትራ የመገንጠል ሃሳብ ያነገቡ ድርጅቶች የተቋቋሙት፡፡
የማታ ማታ … ደርግን ለሽንፈት፣ አማፅያኑን ለድል ያበቃቸው ሚስጥር ምንድን ነው?
የሰላሙ በር ሲዘጋባቸው ኤርትራውያኑ ወደ ትጥቅ ይገባሉ፡፡ ኤርትራውያኑ በራሳቸው ሜዳ መዋጋታቸው፣ መልክአምድሩ (ኮንቬንሽናል) ለሁለገብ ጦርነት አመቺ አለመሆኑ፣ አማፅያኑ የውጭ ድጋፍ በተለይ ከኢራቅና ከሶርያ ያገኙ የነበረ መሆኑ እንዲሁም የሽምቅ ተዋጊዎቹ እምነት፣ ዲሲፕሊንና፣ የታጋይነት መንፈስና የአመራሩ ብስለት… ተጣምረው አሸናፊ አድርጓቸዋል፡፡
በኦጋዴን ጦርነት ጊዜ አማፅያኑ ሀገሪቱን ነፃ ለማውጣት የቀሯቸው 4 ከተሞች ብቻ ነበሩ፡፡ አስመራ፣ አሰብ፣ ምፅዋና ባሬንቱ ብቻ ነበሩ የቀሩት፤ ሌሎቹን ይዘዋቸው ነበር፡፡ በ1974 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግስት ሁለገብ ዘመቻ ያካሂዳል፡፡ በሶስት አቅጣጫ ሶስት ከባድ እዞች አሰልፎ አማፅያኑን ናቅፋ ላይ ለመጨፍለቅ ነበር አላማው፡፡ ሻዕቢያ መጨረሻ ላይ ከፍተኛ ፍልሚያ ያደረገው ናቅፋ ላይ ነበር፡፡ ከናደው እዝ ጋር ነበር የተፋለሙት፡፡ በወቅቱ ደርግ ናቅፋን 2 ኪ.ሜ ነበር ለመያዝ የቀረው ይባላል፡፡ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ “Red Tears” በሚለው መፅሃፉ ይሄ ተልዕኮ ስለከሸፈበት ሁኔታ ሲያብራራ፤ ዋናው ኢታማዞር ሹም ጀነራል ኃይለ ጊዮርጊስ ኃ/ማርያም (ዋናው ኢታማዦር ሹም) (መንግስቱ ቀደም ብሎ የ3ኛው ክ/ጦር ስለነበር) መንግስቱ ኃይለማርያምን ለማስደሰት ብሎ 17ኛ ክ/ጦር በያዘው ቦታ ቀድሞ 3ኛ ክ/ጦር እንዲገባ ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፤ ያቺን የጊዜ ክፍተት ተጠቅሞ ሻዕቢያ ይመታቸዋል፡፡ ይሄ ነው ሻዕቢያን ያተረፈው፡፡ ስለዚህ ሚስጥር በሚገባ ሊነግረን የሚችል የናደው ጦር አዛዥ የነበረው ውበቱ ፀጋዬ ብቻ ነው፡፡
ደርግ እንደ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ከፍተኛ ኃይል አሰልፎ አያውቅም፡፡ የአየር ኃይል፣ የምድርና የባህር ኃይሉን ነበር በጋራ ያሰለፈው፡፡ የዕዝ ማዕከሉ ሁሉ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ ዞሮ ነበር፡፡ በሻዕቢያ በኩል ፍርሃት ይፈጠርና ከመደናገጥ ተነሳ ይመስላል ለታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ የያነጋግሩን መልዕክት ይልካል፡፡ ጁሊየስ ኔሬሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ወደ ኢትዮጵያ ይልኩትና ኢሳያስ እርቅና ንግግር እንደሚፈልግ ለመንግስቱ ይነግሩታል፡፡ ያኔ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ የነበሩ ሣሊም ሣሊም ነበሩ መልዕክተኛው፡፡ እኔም ይሄን ጉዳይ ለማጣራት አንዴ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ለ2 ሰዓት ያህል አነጋግሬያቸው ነበር፡፡ በወቅቱ የእርቅ መልዕክቱን ለመንግስቱ እንዳደረሱና መንግስቱ እንዳልተቀበላቸው ነገሩኝ፡፡ “ጦሩ በተጠንቀቅ ተሰልፏል፤ አሁን ተው ብንለው ሞራሉ ይሰበራል፤ ስለዚህ በጦርነት ነው የምንፈፅመው አለ መንግስቱ፡፡ ከጦርነቱ ፍፃሜ በኋላ ከአማፅያኑ ጥቂቶቹን በጦር በሰራዊታችን ውስጥ ልናስገባ እንችላለን አለኝ” አሉኝ፡፡ እንደኔ በወቅቱ በድጋሚ አንድ ወርቃማ እድል አምልጦናል፡፡ እንግዲህ በወቅቱ ጦርነቱ ተካሂዶ ውጤት አልባ ሆኗል፡፡ ሻዕቢያን የመጨፍለቅ አላማ ተሰናክሏል፡፡ ይሄ ለሻዕቢያ እንደ ድል የሚቆጠር ነው፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ቢሰምር ኖሮ ለኢትዮጵያ የተለየ የታሪክ አጋጣሚ ይኖር ነበር፡፡ የነፃነት እንቅስቃሴው ላይቆም ቢችልም ቢያንስ በብዙ ዓመታት ወደ ኋላ ይጎትታቸው ነበር፡፡
ኢሣያስ በወቅቱ ለደርግ የእርቅ ጥያቄ ያቀረቡት ለጊዜ መግዣ ብለው ሊሆን አይችልም?
ጥሩ ግምት ነው፡፡ ሊሆን ይችላል፡፡ አይሆንም ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን መንግስቱ ውጊያውን እንደሚያሸንፉ እርግጠኛ ስለነበር ያንን ጥያቄ አለመቀበሉ የሚያስገርም አይደለም፡፡
እንዲያ ከሆነ … ደርግን እንዴት መውቀስ ይቻላል?
በእርግጥ ጦሩ ከማይመለስበት ደረጃ ደርሷል ተብሏል፡፡ በቀይ ኮከብ ዘመቻ ብቻ በመሃል ያለቀው ወታደር ከ10 ሺህ በላይ ነው፡፡ 4 ወር ሙሉ ፅኑ ውጊያ አድርገዋል፡፡ ምንድን ነው ያከሸፈው የሚለውን ሊመልስልን የሚችለው፣ የጦሩ መሪ የነበረው ውበቱ ፀጋዬ ብቻ ነው፡፡ ይሄን ሃቅ ይዞ ከተቀበረ የኢትዮጵያ ታሪክ ተወቃሽ ሊሆን ይችላል፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ቢሰምር ኖሮ ይሄን ቃለ ምልልስም ማድረግ ባላስፈለገን ነበር፡፡
የሻዕቢያና የህውሓት የትግል አጋርነት ምን ይመስል ነበር?
እንደሚታወቀው ህወሓት ከኤርትራው ትግል ተለይቶ አያውቅም፡፡ የኤርትራን ትግል እንደ ደጀኑ ነው ሁልጊዜ የሚያየው፡፡ ህውሓት፤ “ኤርትራ የኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ነች” ብሎ ሲነሳ ነው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የተፃረረው፡፡ በወቅቱ የህውሓት ህልውና የተቆራኘው ከኤርትራው እንቅስቃሴ ጋር ስለነበር ነው “ቅኝ ግዛት ነች” ያሉት፡፡ በአንፃሩም ያለ ህውሓት ድጋፍ ሻዕቢያ ሙሉ ለሙሉ ድል አይጎናፀፍም ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ተጋግዘው ነው “ኤርትራ ነፃ ወጥታለች” ያሉት፡፡
ኤርትራ ነፃነቷን ካገኘች በኋላም በሁለቱ ሀገራት መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ግጭቶች ያልቆሙት ለምንድን ነው?
ሻዕቢያና ወያኔ ተባብረው ነው የኢትዮጵያን ጦር ኃይል የደመሰሱት፡፡ ከዚያ በኋላ ጦሩ እንደ ትቢያ ነው የተበተነው፡፡ ከድላቸው በኋላ በ1983 አዲስ አበባ ላይ የሽግግር መንግስት ሲቋቋም ኢሣያስ በታዛቢነት ነበር የተቀመጠው፡፡ ሻዕቢያና ወያኔ በትግሉ ጊዜ ብዙ ልዩነት ነበራቸው፡፡ ከጦርነት አፋፍም የተመለሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ከድሉ በኋላ በተለያዩ መስኮች ስምምነት መፈራረም ጀምረው ነበር፡፡ እስከ 7 ዓመት የሚዘልቅ የኢኮኖሚ፣ ወታደራዊ ፖለቲካዊ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡
የድንበሩ ጉዳይ ምን ይሁን ሲባል የጋራ ኮሚሽን አቋቁሙ፡፡ ኮሚሽኑ ስራውን እየሰራ ሳለ የኤርትራ መንግስት በታንክና በመድፍ የታጀበ ሰራዊት ልኮ ባድመንና ሽራሮን በከፊል ያዘ፡፡ የጦርነቱ መንስኤ ይህቺ ብትሆንም ለ1991 የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ባድመ እንደ ምክንያት ሆነች እንጂ ምክንያቶቹ ሌሎቹ ናቸው፡፡ ከነፃነታቸው በኋላ … ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራቸው የንግድ፣ የመግባብያ ገንዘብ፣ የኤርትራውያን ዜግነት ጉዳይ የመሳሰሉትን መፍትሄ አላበጁለትም ነበር፡፡
የናቅፋ ገንዘብ ጉዳይ፣ የወደብ ጉዳይ ብዙ ችግር ነበረበት፡፡ ለዚህ ቀውስ እንደ እሳት ማቀጣጠያ ክብሪት የተጠቀሙት ባድመን ነበር፡፡ እንግዲህ በዚህ ጦርነት ከ70-100 ሺህ የሚገመት የሰው ህይወት ጠፍቷል ይባላል፡፡ በጦርነቱ አሸነፈና ባድመን ተቆጣጠረ፡፡ ጉዳዩም ወደ አልጀርስ ሄዶ የአልጀርስ ስምምነትን ይፈራረማሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በራስ መተማመኑ አይሎ ይመስለኛል … “የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ይግባኝ እንቀበላለን” ብሎ ፈረመ፡፡ ይሄ ትልቁ ስህተት ነበር፡፡ ባድመ ለኤርትራ ተፈርዳ ሳለ፣ የኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በግልፅ ሳያጣሩ፤ “በጡንቻችን ያስመለስናትን ባድመን በህግ አረጋግጠነዋል” አሉ፡፡ በኋላ ባድመ ለኤርትራ መሰጠቷን የኢትዮጵያ መንግስት ሲረዳ ባድመን አልለቅም አለ፡፡ ድንበሩን ከማስመራችን በፊት ባሉት ችግሮች ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መነጋገር አለብን የሚል አቋም የኢትዮጵያ መንግስት ያዘ፡፡ የኤርትራ መንግስት በበኩሉ፤ “የለም መጀመሪያ ከባድመ ውጡና በጠረጴዛ ዙሪያ እንገናኛለን” ይላል፡፡
ይሄ ነው እንግዲህ ላለፉት 18 ዓመታት መቋጫ ያላገኘው ንትርክ መንስኤ፡፡ አሁን ያለው ቀዝቃዛ ጦርነት የዚህ ውጤት ነው፡፡ ሀገራቱ ይሄ ግትርነት እስካለ ድረስ ተፋጠው ነው የሚቀጥሉት፡፡ በቅርቡ የተፈጠረው ትንኮሳም የዚሁ ውጤት ነው፡፡
ከሰሞኑ የኤርትራ መንግስት ትንኮሳ ተፈፀመብኝ ብሎ ለተባበሩት መንግስታት በቅድሚያ አቤቱታ አቅርቧል … በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
መልሴ እንግዲህ ግምታዊ ነው የሚሆነው፡፡
ምንም የተጨበጠ ነገር የለም፡፡ ሁለቱም መንግስታት በዝርዝር የሚገልፁት ነገር የለም፡፡ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኩል የኤርትራን መንግስት በተመለከተ ሪፖርት መውጣቱ፣ እንደገና “የኢትዮጵያ መንግስት ሊወረኝ ነው” የሚለው ጩኸት ከየት መጣ ብለን መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የሆነ የተቀናበረ ነገር ያለ ይመስላል፡፡
እናንተም ያነጋገራችኋቸው ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት፤ ኤርትራ ገብተን ኢሣያስን ማስወገድ አለብን ነው ያሉት፡፡ እኔ ይሄ አማራጭ ሊሆን አይገባም ባይ ነኝ፡፡ አልሻባብን እንደወጋነው ኢሳያስንም ማስወገድ እንችላለን ማለት … አሸባሪ ቡድንና ብሄራዊ መንግስትን ነጥሎ ያለማየት ይመስለኛል፡፡
የኤርትራ ብሄራዊ መንግስት ነው፤ በሶማሊያ ያለው አሸባሪ ቡድን ነው፡፡ የአንድን ሀገር ብሄራዊ መንግስት እንዴት እናስወግድ ይባላል፡፡
እንኳን ብሄራዊ መንግስትን ለማስወገድ ይቅርና ከ10 ዓመት በፊት እናስወግደዋለን ያልነውን ተራ አሸባሪ ቡድን እንኳ ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ አልተቻለም፡፡ አልሻባብ ዛሬም በሶማሊያ ህይወት አለው፡፡ የኤርትራን መንግስት እናስወግድ ስንል ምን አዘጋጅተን ነው? የኤርትራ ተቃዋሚዎች አሉ ከተባሉ ደካማዎች ናቸው፤ ወጣቶቿ በስደት መከራ የሚበሉ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የሻዕቢያ መንግስት ምን ያህል ነው የሚያሰጋን? ጠንካራ አይደለም፤ ስለዚህ በኢትዮጵያ ላይ ጥይት ለመተኮስ አይደፍርም ባይ ነኝ፡፡ ከተኮሰም መቃብሩን ቆፈረ ማለት ነው፡፡ ከአሁን በኋላ በአካባቢው ጥይት ተተኮሰ ከተባለ መጀመሪያ ሊተኩስ የሚችለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡
የኤርትራ መንግስት ጠንካራ አይደለም ከተባለ ለምንድን ነው ታዲያ በቀላሉ ማስወገድ የማይቻለው?
የኤርትራ ህዝብ መንግስቱን ቢጠላ ሀገሩን አይጠላም፡፡ ሀገሩን ይወዳል፡፡ ሀገሩ በሌላ ጦር ስትወረር ዝም ብሎ አያይም፡፡ ሁለተኛው እናስወግድ ቢባል እንኳ በሀገሪቱ ስልጣን ተረክቦ ሊመራ የሚችል ጠንካራ ተቃዋሚ ባለመኖሩ ሀገሪቱ የአሸባሪዎች መናኸሪ ልትሆን ትችላለች፡፡ ያን ጊዜ ደግሞ ኢትዮጵያ በሁለት በኩል ትወጠራለች ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መንግስቱን የማስወገድ ኃላፊነት የኤርትራ ህዝብ ብቻ ነው፡፡ ድጋፍ ግን አያስፈልጋቸውም ማለት አይደለም፡፡ በኃይል ሳይሆን በሌላ ነገር መደገፍ ይቻላል፡፡ ከታሪክ እንደምናውቀው መንግስታት የሚጠቀሙት ስልት ነው፡፡
ከኤርትራ ጋር በተያያዘ በአሁን ወቅት ለኢትዮጵያ አሳሳቢ የሚሆነው ምንድን ነው?
ኤርትራ እንደሚታወቀው ህገ መንግስት የሌላት ሀገር ነች፤ የመናገርና የመፃፍ፣ የመሰብሰብ መብት የሌለባት በአንድ ሰው ፍፁማዊ አገዛዝ ስር ያለች ሀገር ነች፡፡ ኢኮኖሚዋ የደቀቀ ነው፡፡ መንግስቷ ከዓለም ማህበረሰብ የተገለለ፣ በአንድ እግሩ የቆመ መንግስት ነው፡፡ ይህ አይነቱ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ይከፍታል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ለራሱ ደህንነት ሲል የሚያደርግ አይመስለኝም፡፡ በአንፃሩ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ አንፃር ሲታይ ጠንካራ መንግስት ነው፡፡ በኢኮኖሚው፣ በወታደራዊ ኃይሉ የተሻለ ነው፡፡ ከአፍሪካ ቀንድ ጡንቸኛው ሰራዊት ነው፡፡ ስለዚህ በኔ ግምት የመጀመሪያዋን ጥይት ሊተኩስ የሚችለው የኤርትራ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡ የውስጥ ችግሩንም ለማርገብ የኢትዮጵያ መንግስት ይሄን አማራጭ ሊጠቀም ይችላል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል “ሰላምም ጦርነትም” አለመኖሩ ለመንግስታቱ የሚጠቅመው ነገር ይኖር ይሆን?
በኤርትራ በኩል መንግስታቸው “ህዝቡን ልትወረር ነው፣ ሀገር ልትደፈር ነው፣ ሉአላዊነትህ ሊጣስ ነው” በማለት እያስፈራራ የፖለቲካ ህይወቱን ያስቀጥልባታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ውስጣዊ ውጥረቶች አሉበት፡፡ እነዚህን ለማርገብ እየፎከረ የህዝቡን ቀልብ ይስብባታል፡፡
ከዚህ ችግር መውጭያ መፍትሄው ምንድን ነው?
መፍትሄው ጦርነት ሳይሆን ንግግርና ውይይት ነው፡፡ ይሄን ለማድረግ ደግሞ በሁለቱም ሀገራት የዲሞክራሲ መስፋፋትን ይጠይቃል፡፡ የሚደረገው ስምምነት እንደ አልጀርሱ ሳይሆን ዜጎችን ማሳተፍ አለበት፡፡ አገራቱን ከጦርነት የሚታደጋቸው ሌላ አካል አይኖርም፡፡ በተለይ የምዕራባውያን መንግስታት፣ ኤርትራና ኢትዮጵያን የቼዝ መጫወቻ እንዳያደርጓቸው መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
የመጨረሻው መፍትሄ የሰላም ድርድር ብቻ ነው፡፡
የሁለቱ ሀገራት ህዝብ፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ በኢኮኖሚ የተሳሰረ ነው፡፡ የቻይና ግንብ በመገንባት መለየት አይችልም፡፡
ልቦና ያላቸው መንግስታት ከመጡ የፈረሰው ፌደሬሽን ተመልሶ ይገነባ ይሆናል፤ ካልሆነም በኮንፌዴሬሽን እንደምንተሳሰር እኔ ተስፈኛ ነኝ፡፡ ይሄ እንደኔ ሩብ ክፍለ ዘመን የሚፈጅ አይመስለኝም፡፡ ኢሣያስ 25ኛ ዓመት የነፃነት በአላቸው ላይ ባደረገው ንግግር፤ ለወርቃማው በዓል ያገናኘን ብሏል፡፡ ለኔ ይሄ ከቅዠት ያለፈ አይደለም፡፡ 25 ዓመት ባልሞላ አጭር ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ሀገራት በኮንፌደሬሽን ሊተሳሰሩ ይችላሉ፡፡ ዋናው አዕምሮና ብልህነት ያለው መንግስት መምጣቱ ነው፡፡
በኛ ሀገር ያለው የተቃውሞ ፖለቲካ ብዙ ጊዜ ኤርትራ መገንጠል አልነበረባትም ከሚል ቁጭት መነሳቱ ለኤርትራውያን የሁልጊዜ ስጋት አይሆንባቸውም? በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
አንዳንዱ ኤርትራዊ የኢሳያስን ቃል እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ቃል ያምናል፡፡ ብዙው ደግሞ ይሄ ነገር እየተደጋገመ ሲነገር ሲሰማ ስጋት ያድርበታል፡፡ ያገኘነውን ነፃነት ልናጣ ነው ብሎ ይሰጋል፡፡ የኤርትራ ብሄርተኝነት ከፍ ያለ ነው፡፡ ኤርትራ ነፃ የወጣችው በኢትዮጵያ መንግስታት ስህተት ነው፡፡ መጀመሪያ  ፌደሬሽኑን በማፍረሳቸው ጦርነት ውስጥ ተገባ፡፡
ደርግ ደግሞ የቀረበለትን መልካም እድል ገፍቶ ሄዶ ተሸነፈ፡፡ ስለዚህ ኤርትራውያኑ ነፃነታቸውን ያገኙት በጡንቻቸው ነው፡፡ ታዲያ በጡንቻቸው ያገኙትን ነፃነት ስናናንቅባቸው ስጋት ሊገባቸው ይችላል፡፡ ይሄ ደግሞ አሁን ያለውን መንግስታቸውን ሊያጠናክረው ይችል ይሆናል፡፡ የኤርትራ መንግስት የትግሉ ዘመን ወኔ እየደቀቀ ቢሆንም፣ የኤርትራዊነት ስሜት ግን ከህዝቡ ተሸርሽሯል ማለት አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ ያለ ወደብ መኖር አትችልም፤ የአሰብ ወደብም ይገባታል የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ይሄን ወደብ መልሰን የራሳችን የምናደርግበት እድል ይኖራል ብለው ያስባሉ?
እኔ በወደቡ ጉዳይ አሰብ የኛ ነች ከሚሉት የተለየ አቋም ነው ያለኝ፡፡ እሱ የኛ ነች ይላል፡፡ የመጠቀም መብት አለን ከሆነ ያስኬዳል፤ ትክክል ነው የመጠቀም መብት አለን፡፡ ከወደቦቹ ባለቤት ጋር የኢትዮጵያ መንግስት መስማማት አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ተዘግታ መኖር የለባትም፡፡ በአሰብም በምፅዋም የመጠቀም መብት አለን፡፡ ኢትዮጰያ ካልተጠቀመችባቸው ደግሞ እነዚህ ወደቦች ለኤርትራ ጥቅማቸው እምብዛም ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው ኮንፌደሬሽን መምጣቱ አይቀርም የምለው፡፡
አሰብን በመጀመሪያ ለጣሊያን የሸጠው የዚያው አካባቢ ሰው ነው፡፡
ከዚያ ጣልያን ከኤርትራ ጋር ጠቅልሎ ያዛት፡፡ ለብቻዋ የቀረች አልነበረችም፡፡ ታዲያ እንዴት ነው አሰብን ብቻ ነጥለን አውጥተን የኛ ነች ማለት የሚቻለው፡፡ ይሄ በአለማቀፍ መርሆች አያስኬድም፡፡ የመጠቀም መብት እንዳለን ሜ/ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት በሰላም መጠቀም እንችላለን ባለው ሃሳብ እስማማለሁ፡፡
የመጠቀም መብት አለን ሲባል እንዴት ነው? እንደ ጅቡቲ ወደብ ማለት ነው?
ለዚህ ሁለቱ መንግሥታት የሚያደርጉት ስምምነት ነው የሚወስነው፡፡ ውላቸው ወሳኝነት አለው፡፡ በኪራይ ነው? በጥቅማጥቅም ነው…? የሚሉትን የሁለቱ አገራት ድርድር ይወስነዋል፡፡
ኢትዮጵያ የመጠቀም መብቷን፣ ኤርትራም የወደቦቹን የባለቤትነት መብት ተጠቅመው የሚሰሩበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፡፡ የመብትና ግዴታ ጉዳይ ሁለቱ ሀገራት በውይይት ሊጨርሱት ይገባል፡፡
ሁለቱ አገራት አሁን ያላቸውን የጦር አሰላለፍ እንዴት ይገመግሙታል?
አሁን ያጠናሁት ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ከማነበው ተነስቼ ብናገር፣ የኢትዮጵያ ጡንቻ ይበልጥ ፈርጥሟል፡፡ የኤርትራ በአንፃሩ የተዳከመ ይመስላል፡፡
ወጣቶቹ እየተሰደዱ ነው፡፡ እንግዲህ የሳዋው ስልጠና ፋይዳ ቢስ እየሆነ ነው ማለት ነው፡፡
“ለኤርትራ መገንጠል ተወቃሾቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ናቸው” ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ይሄ ቢሆን ኖሮ ማለቱ ምንድነው ጥቅሙ? የፌደሬሽኑ መፍረስ የመሳሰሉት ጉዳዮችን ማንሳቱ ምንድነው ፋይዳው?
ይሄ ታሪክ የምንማረው ለምንድነው እንደ ማለት ነው፡፡ ከየት ተነስተን እዚህ ደረስን? እዚህስ ያደረሱን እነማን ናቸው? በዚያ ሂደት አቀበት ቁልቁለት ነበረበት፡፡ የታሪክ ዘገባ የሚፃፈው ሀገር ተረካቢው እሱነቱን እንዲያውቅና ስለሚረከባት ሀገር ማወቅ ስላለበት ነው፡፡ ደርግና ኢህአፓ ለምንድን ነው እንደዚያ የሆኑት? ጃንሆይስ የሰሩት ስህተት ምንድን ነው? የመሳሰሉትን መጪው ትውልድ ማወቅ አለበት፡፡
የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት በሰሜኑና በደቡብ፤ በፌደራሊስትና በኮንፌደራሊስት፣ በአንድነት ባዮችና በተገንጣዮች መካከል ነበር፡፡
4 ዓመት ሙሉ ተዋግተዋል፡፡ የጠፋው 1 ሚሊዮን ህዝብ ነው ይባላል፡፡ ሰሜኑ ድል ተጎናፀፈ፡፡
ከዚያ በኋላ ግን እዚህ እንደሚደረገው ይሄን ድል 21 መድፍ በመተኮስ አይደለም የሚዘክሩት፡፡
ወንድማማቾች ናቸው የተጋደሉት፡፡
በየሸንተረሩ በየአፈሩ የተቀባበሩት ወንድማማቾችና እህትማማቾች ናቸው፡፡ በየዓመቱ 21 መድፍ መተኮስ ለእርቅና ለሰላም የሚበጅ አይደለም፡፡
ይሄን መንግስት ማወቅ አለበት፡፡ አንዱ ሲደሰት የሌላውን ወታደር ቤተሰብ ቁስል እየቦረቦረ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ ስለዚህ እኔ ይሄ መድፍ ትኮሳው መቆም አለበት ባይ ነኝ፡፡
የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት አብቅቶ አንድ ከሆኑ በኋላ የአሜሪካ የታሪክ ፀሐፍት የሚስማሙበት አንዱና ዋነኛው ጉዳይ፤ የእርስ በእርስ ጦርነቱ አሜሪካን ፈጥሯል የሚለውን ነው፡፡
ዛሬ ላይ ያለችውን ሃያሏን አሜሪካን የፈጠረው ያ ጦርነት ነው፡፡ የኛ የእርስ በእርስ ጦርነት ውጤቱ፡- ኤርትራን አስገነጠለ፤ ወደብ አልባ አደረገን፡፡ ቢሆንም የተመሰረተው የፌደራል ስርአት በኔ በኩል ለህዝቦቿ ለሀገሪቱ ጠቃሚ ነው፡፡
ይሄ እምነቴ ነው፡፡ የደርግ የመሬት አዋጅ የደርግ መልካም ቅርሱ ነው፡፡ የዚህ መንግስት ዋናው ቅርሱ ደግሞ አሁን ያለው የፌደራል መዋቅሩ ነው፡፡ ስለዚህ ታሪክ የምንማረው ያለፈውን አውቆ ያሁኑን ተረድቶ የወደፊቱን ለማለም ነው፡፡ የታሪክ ዋናው ፋይዳው ራስን ለማወቅ ስለሚረዳ ነው፡፡

16 Comments on ““ለኤርትራ መገንጠል ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ናቸው” ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ፡፡”

  1. Yih tera teret awri new.
    Yih bedn mhur tebyew ye chigru mnci itali ena engliz keziyam areboch beteleym gbx mehonachewn enkua ayawqm..
    Lederg meshenef ye sotializm. komunizm mefres, ye u.s/ c.i.a. ye inglizna ye awropa xret, sierana sra wana wosañ mekniyatoch mehonachewn ayawqm.
    Etiopian eyawodemat yalen ye yismula ena yegosa kfflosh/ federalism mednequ mn yakl bado qefo mhur tebeyo mehonun agalxual.
    Glesebu tedebqo sixexa yenore sekaram yimeslal.
    Etiopia be worari, wonjeleña ye tgrie woyanie yewsx qñi gzat sr wodqa megeñetuan ayawqm.
    Agerachn ye tgrie woyanie eyaferesat ena ye tgrie yebelynet eyasfafabat megeñetuan altegenezebem.

  2. Senu yemil tefa gmat gebreab ke eritrea new.
    Yih homosexual luxi fnafnt moralu bcha sayhon yewodemew, angolum cimr wodmual.
    Xere-tgrie woyanien ena woyanien meleyet tesnotal. Wordual, tewardual.
    Xnb neh.

  3. የዘመኑ የዘር ልሂቃን ፕሮፊሰሮች ዶሮ ብታልም ጥሪዋን እንደሚባለው ተረት ህልማቸውን እንጂ የኢትዮፒያን ሃቅ እውነተኛ ታሪክ ሲተነትኑ አናይም ምክንያቱም ለነዚህ የዘር ልሂቃኖች ህልማቸውን የፋሺስት አሽከር ባንዳ የትግሪ ነጻ አውጭ ህወሃት ለማሳካት የኢትዮፒያን ፖለቲካ የውስጥ የውጭ ብቻ ሳይሆን ቀየርኩት ያለው የኢትዮፒያን እውነተኛ ታሪካን በማጥፋትም ጭምር ስለሆነ ይህንን ለማበረታታት የዘር ልሂቃኖቹ ፕሮፈሰር ዶክተር ነን ባዮች ህዝቡን ለማሳመን እኛ የታሪክ ስህተት አልሰራንም በኢትዮፒያ ላይ ስህተት የሰሩት ሚሊሊክ, አጺሃይለስላሲ, ደርግ እያሉ, እያሉ አሁን ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ ለትግሪ ህልውና በፋሺስት ኢጣሊያን ዘመን ያልተሳካለትን ኢትዮፒያን ለባእዳን አስረክበው የራሳቸውን አገር ለመመስረት እና የትግሪ ወረራ መስፋፋት ለማካሂድ የዘር ፊደሪሽን ከፋፍለህ አጥፋው ኢትዮፒያን እንደ ፋሺስት ኢጣሊያን ዘርፈው ታላቃን ትግሪ ለመገባት ኢትዮፒያን የኢኮኖሚ መሰረታቸው እና ምንጫቸው አድርገው ለማስቀጠል ምድረ የትግሪ ልሂቃን በዚህ ኢትዮፒያን ለመጠቀም በዚህ ወደብ የትግሪ እንጂ የኢትዮፒያ አይደለም በሚል ህልም ለኢርትሪያኑ ወደቡ የናተነው ግን እኛ ለናተ ነጻነት አስተዋጾ ያደርግነው ትግሪዎች ወደቡን መጠቀም መቻል አለብን ማለት ጀምረዋል ወደቡ የኢትዮፒያነው ለማለት የማይፈልጉበትን ምክንያት ልብ ብለን ማየት አለብን እንደኚህ የዘር ልሂቃን ፕሮፊሰር ከሆነ ለጣሊያን ወደቡን የሸጡት የዛው አገር ኢርትራዊያኑ ናቸው ስለዚህ እንዲት የኢትዮፒያ ይሆናል የሚል የወረደ አስተያየት ነው የሰጡት በዚህ የኢርትሪያ መገንጠል ተጠያቂዎቹ የኢትዮፒያ መንግስታቶች ናቸው ይላሉ ኢርትሪያን ለፋሺስት ኢጣሊያን አስረክበው ከኢትዮፒያ እናት አገራቸው የለዩት ዛሪ ኢትዮፒያ ቁንጮላይ የተቀመጡት የፋሺስት አሽከር የጣሊያን ህልም ይዘው የመጡ የባንዳ የትግሪ ነጻ አውጭዎች ህወሃቶች አባቶች ናቸው:: ጣሊያን ፋሺስት አዎ የመጣው ኢርትሪያን ብቻ ሳይሆን መላው ኢትዮፒያን ለመቆጣጠር ነው የነኚህ የባንዳ አባቶች እንካን ለሚሊሊክ አይደለም ከጣሊያን ጋር ተሻርከው አጺ ዮሃንስን በመካድ ሰሐጢ በረሃላይ አሰፍረው በጣሊያን ሃይል ስልጣን ለመያዝ የነበራቸው ህልም ነው :: አጺ ዮሃንስ ጣሊያኖችን እኮ ካገሪ ውጡ በማለት ተማጽነዋል ለመዋጋትም ተነስተዋል ጣሊያን ግን ለውጊያ ዝግጁ ባለመሆኑ አጺ ዮሃንስ በበረሃ ወታደሮቻቸውን እንዳያልቁ ተመለሱ :: ከተመለሱ በሃላ ደርቡሽ ባስነሳው ጦርነት ዘመቱ የዚን ግዚ የባንዳ ትግሪ የፋሺስት ኢጣሊያን አሽከሮች የጣሊያንን ህልም ባሽከርነት ለማስፈጸም ኢትዮፒያን በፋሺስት ጣሊያን ቁጥጥር ስር ለማዋል አጺ ዮሃንስን የበደሉ መስሎአቸው ወደ ደርቡሽ ሲዘምቱ ጣሊያንን እያደረደሩ አስመራ አመጡአቸው በዛን ዘመን የነበረ ከሃጂ ከነስሙ ደበብ ይባል ነበር:: አጺ ዮሃንስ ህይወታቸው ማለፉ ሲሰማ በትግሪ ሰው ሁሉ በየስፍራው ሽፍታ ሆነ እርስ በርሱም ይጋደል ስለነበር አጺ ሚሊሊክ ወደ ትግሪ ዘምተው ጣሊያንን ወደ አስመራ መምጣቱን ምነው ወዳጆች ነን ካላችሁ ከኒ አገር ምን ትሰራላችሁ ምን አመጣችሁ ብለው አገሪን ልቀቁልኝ ብለው ነው ያሉአቸው እንጂ ኢርትሪያ የኢትዮፒያ አይደለችም አላሉም:: እነሱም ምጥዋ ሃሩር ሆኖ ነጋዲዎችን ስላላስቀመጠልን እንጂ ቦታ እናሰፋለን አገር እናሰፋለን እንገዛለን ብለን አልመጣንም ለነጋዲዎች የሚሆን ቦታ ስጡን በማለት የባንዳ ትግሪ አስመራ ድረስ ያመጣቸውን ኢጣሊያኖች ሚሊሊክ ለንግድ ከሆነ ብለው ለነጋዲዎች ቦታ ቢፈቅዱም አገር እንዳያሰፉና እንዳያጠፉ በትግሪ ህዝቡ ከአጺ ዮሃንስ በሃላ ሽፍታ ሆኖ እርስ በርሱ ስለሚገዳደል ራስ መንገሻን ሾመው የትግሪ ሰዎች እንዳይጣሉም ከመካከላቸው የሸዋውን ደጃች መሸሻ ሰተው ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ መጡ በዚህን ግዚ ጣሊያኖች ከትግሪ ባንዳዎች ጋር ሆነው ደጃች መሸሻን አስረው ራስ መንገሻን አባብለው ሚሊሊክን እንዲክድ እና ከጣሊያን ጋር እንዲሰራ አደረጉት በዋናነት ለጣሊያን ኢርትሪያን አስረክቦ ድበር ተዋስኖ ተስማምቶ ሚሊሊክን ክዶ የተቀመጠው የትግሪው ራስ መንገሻ ነው በሃላ የጣሊያን መስፋፋት እየተጠናከረ ራስ መንገሻ ባላሰበው መንገድ ጣሊያኖች ቢተክርስቲያን የወታደር ማጎሪያና ሃይል ሲጠቀሙበት እና አድዋ ገብተው ዘረፋ ሲያካሂዱ ራስ መንገሻ ካገሪ ንጉስ ጋር እግዚአብሂር ከመረጠው ጋር ይሻለኛል በማለት የጣሊያንን መስፋፋት ሲገነዘብ ለአጺ ሚሊሊክ ይቅርታ አድርጉልኝ በማለት ተመጸነ ሚሊሊክም ላገራቸው ለኢትዮፒያ ሲሉና ለህዝባቸው ሲሉ የትግሪ ባንዳ ከሃጂዎች በኢትዮፒያ ላይ አጺ ዮሃንስ ቢሞቱ የክርስቲያንን መዲና ሊያጠፉነው በሚል መላው ኢትዮፒያን አሁንም አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሂር የወሰነልንን ባሕር አልፎ መጥታልና እኒም ያገሪን ከብት መሞት የሰዊን መድከም አይቺ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሪት ይቆረቁር ጀመር አሁን ግን በኢግዚአብሂር እረዳት አገሪን አሳልፊ አልሰጠውም የሸዋ ሰው ወራይሉ ከተህ ላግኝህ ብለው አዋጅ ነገሩ እንዲሁም መላው የኢትዮፒያን ህዝብ በሚሉ ላገሩና ለነጻነቱ እንዲነሳ አሳወጁ ከዚህ በሃላ እንግዲህ የኢትዮፒያ ህዝብ ኢትዮፒያን ዳር ድበራን አስጠብቆ ነጻነታቸውን ለመፋለም ላገራቸው የኢትዮፒያን ድበር ባህር ተሻግሮ የመጣውን ጠላት ለመደምሰስ የየአገሩ ጦር ዘምቶ የባንዳ ትግሪ የጣሊያን አሽከሮችን ጭምር ተፋልመው አድዋላይ ጣሊያን መስፋፋቱን እንዲያቆም ኢትዮፒያን ነጻነታን እንድታውጅ እና ኢርትሪያም ወደናት አገራ እንድትመለስ ነው የንጉሶቹ ስረአት የተዋዋለው ስለዚህ የኢትዮፒያ የንጉስ ስረአት መንግስቶችም ሆኑ ደርግ ኢትዮፒያን በየትኛውም በኩል የሚመጣ ጠላታን እየተፋለሙ የኢትዮፒያ አንድነታን ዳር ድበራን ጠብቀዋል ከሚሊሊክ ድል በሃላ የኢትዮፒያ ህዝብ አድዋላይም ደሙን ካፈሰሰ በሃላ የትግሪ ባንዳ የጣሊያን አሽከሮች መልሰው በራስ መንገሻ አማካይነት እኛ እናነግስሃለን በሚል የኢትዮፒያን መንግስት ለማፍረስ የሸዋ ሚሊሊክን መካድ እንዳለበት ደጋግመው ባንዳዎች ሞክረዋል እራስ መንገሻም በባንዳዎች ስልጣን ለመያዝ ጉጉት ስለነበረው የኢትዮፒያን መንግስት ለማፍረስ ሚሊሊክን ደጋግሞ ክዳል እቲጊ ጣይቱም እኛ የናተን ቢት ለማቆም ስንሰራ አንተ የኛን ቢት ለማፍረስ መንግስት ለማፍረስ ትጥራለህ በማለት የጣሊያን አሽከር ባንዳዎች ኢትዮፒያን አሁንም ለማፈራረስ እንዳልተኙ የገባቸው ሚሊሊክ ለየ አገሩ ሹም በማስጠንቀቅ እንዲሁም ለትግሪ ህዝብ በማስጠንቀቅ ኢትዮፒያን እየጠበቁ አጺ ሃይለ ስላሲ ዘመን ድረስ እንዲ ደርሱ በቅተዋል የባንዳ የፋሺስት አሽከር ትርጊዎች አሁንም በአጺ ሃይለስላሲ ዘመን ያለሙትን ኢትዮፒያን የማፈራረስ ሲራ ለማካሂድ ለጣሊያን በማበር ሚናቸውን በመጫወት ጣሊያን መልሶ ኢትዮፒያ በዘር ከፋፍሎ እንዲቆጣጠር አድርገዋል የኢትዮፒያ ህዝብም በፋሺስት ተጨፍጭፋል አጺ ሃይለስላሲ ይህ ሁሉ ታሪክ ሚስጥሩ ምን እንደሆነና ጣሊያን በትግሪ ባንዳ እየተመራ ኢርትሪያን እንደተቆጣጠረው አሁንም ህልሙን ለማሳካት ኢትዮፒያን ለመጠቅለል ማሰቡን ስለሚያውቁ ተሰደው የኢትዮፒያን ነጻነት መልሰው ለማስከበር አይደለም በባንዳ ትግሪዎች የሂደችውን ኢርትሪያን እንድትመለስ አድርገዋል ይህ እንግዲህ የትግሪ ባንዳዎች አልተመቻቸውም አጺ ሃይለስላሲ ከሚሊሊክ በሃላ የመጡ የተተኩ ንጉስ እና ከመሃል አገር ስለመጡ በሚል ጥላቻም ባንዳዎች አጺ ሃይለስላሲን ጠምደው ያዙ ለምን በጣሊያን ሃይል ዛሪ መላው ኢትዮፒያ እየታመሰች ሃብታን እየተዘረፈች የትግሪ የጣሊያን ሺማምንቶች ኢትዮፒያን መጠቀም አልቻሉም ስለዚህ ኢርትሪያን መልሰው አስገንጥለው በትግሪ ነጻ አውጭ ስም ኢትዮፒያን በፋሺስት ታክቲክ ለመዝረፍ እናየጣሊያንን ህልም ኢትዮፒያን ከፋፍሎ ገዝቶ ጣሊያንን የኢኮኖሚ ባለቢት በማድረግ መንግስቱን ለማጠናከር ያደረገውን እስትራቲጂ የባንዳ የትግሪ ነጻ አውጭዎች ህልም ሃይለስላሲን ለመጣል በሚስጥር መስለው ሲሰሩ ኖረው ሳይሳካላቸው ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ምድረ የባንዳ ትግሪ ነጻ አውጭ ፕላናቸውን ቀይረው ኢትዮፒያ ታሪክ እንደሊላት ኢትዮፒያዊነት በአምሃራ የተመሰረተ እና በሚሊሊክ የመጣ ሃይማኖት በሚሊሊክ እንደመጣላት አድርገው የኢትዮፒያ ህዝቦችን ጣሊያን ያልተሳካለትን የዘር መከፋፈል የሃይማኖት መከፋፈል ባንዳ የትግሪ ነጻ አውጭ የኢርትሪያ መገንጠል የትግሪ ነጻነት እና ህልውና ይከበራል በማለት በዘር ተሰባስበው ደርግን ለመጣል ጫካ የወጡት ከደርግ ጋር መስለው እንደሃይለስላሲም እየሰሩ ኢትዮፒያን ለማጥፋት እና እንደአገር እንዳትቆም ትግሪ የራሱን አገርና መንግስት እንዲያቆም ኢትዮፒያ የምትባል አገር ጎናችን መቆም የለባትም ብለው ያለሙ ሃይሎች መልሰው ኢርትሪያን ሃይለስላሲ ወደናት አገራ ያመጣትን ደርግ ያቆያትን ገንጥለው ነጻነታን አጸደቅን የባህር ወደብ የኢትዮፒያ ሳይሆን የኢርትሪያነው በማለት መጠቀም እንችላለን ባህር ኢትዮፒያ ካልተጠቀመችበት ምንም አይሰራም ስለዚህ መጠቀም አለብን የሚለው የትግሪዎች ህልም እያለሳለሱ እነሱ እና ኢርትሪያኖች አንድ የተቀረው ኢትዮፒያዊ ግን አያገባውም በማለት አሁንም ኢትዮፒያን አፍርሰው የትግሪ አገር እና መንግስት ለማቆም የኢትዮፒያን ህዝቦች በዘር አባልተው ዘር አጥፍተው አምሃራን አጥፍተው ትግሪ ተስፋፍቶ እነሱ የሚፈልጉት ያውም የዘር ፊዲሪሽን በኢትዮፒያ ቆሞ ኢትዮፒያን እየተጠቀሙ ሊላው የነሱ የበይ ተመልካች ሆኖ ህልማቸውን ሲያሳኩ እንዲያያቸው የሚያለሳልሱበት ታክቲክ ነው የኢትዮፒያ ነገስታቶች የኢትዮፒያ ድበርን አድርገው ሲገዙ የኖሩት ወሰን የሚሉት ባህሩን ነው ስለዚህ ባህሩን ኢርትሪያኖች ስለሸጡት የነሱነው የሚለው አስተሳሰብ እና የኢትዮፒያ አይደለም የሚለው አነጋገር ፈጽሞ አይሂድም አጺ ዮሃንስ አገሪን ነው ያሉት ሚሊሊክም አገሪን ነው ያሉት አጺ ሃይለስላሲም አገሪን ነው ያሉት ደርግም አገሪን ነው ያለው ስለዚህ የትግሪ ነጻ አውጭዎች እና የትግሪ ልሂቃኖች ኢትዮፒያን እየበዘበዛችሁ ባህር የኢርትሪያነው ትላላችሁ ለመሆኑ በጎንደር ለሱዳን ሸጦ ኢትዮፒያላይ ጉብ ያለው የትግሪ ነጻ አውጭ መንግስት ነኝ ባይ ነው ስለዚህ መሪቱ የኢትዮፒያ አይደለም ልትሉን ነው እናተ እኮ የማትሉት ነገር የለም አሁን ስለኢትዮፒያ ድበር እና ስለኢርትራዊያን የተለያዩ ናቸው ኢርትራዊያን ባባንዳ ትግሪዎች አማካይነት ጣሊያኖች ሊቆጣጠራቸው ችለዋል እንጂ ታሪካቸው መሰረታቸው ኢትዮፒያኖች በኢትዮፒያ በስተሰሚን የሰፈሩ ህዝቦች ናቸው አዎ የንጉስ ስረአት የኢትዮፒያን ህዝብ በታሪኩ አስተሳስሮ አገር አቆሞ ኢትዮፒያን ለኢትዮፒያኖች አድርጎ ያኖረ ስረአት ስለሆነ ኢርትሪያኖችም ከዚህ የተለየ ታሪክ የላቸውም የንጉሶች ስረአት ኢትዮፒያዊነት ስለሆነ ጣሊያን ኢትዮፒያን ለመቆጣጠር በዋናነት የንጉሶችን ስረአት ለመጣል እና ሃይማኖት ለማጥፋት ነው ከትግሪ ሽፍታ ወረበሎች ጋር የሰራው ለዚህም ነው ዛሪ ህወሃት የትግሪ ነጻ አውጭ በዋናነት ኢትዮፒያን ለመከፋፈል ኢርትሪያን ለማስገንጠል የትግሪ ነጻነት ለማስከበር ሊሎቹም በዘር እንዲከፋፈሉና ኢትዮፒያ እንደ አገር እንዳትቆም የንጉሶቹ ስረአት ኢትዮፒያዊነትን ያቆመ በመሆኑ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኢትዮፒያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የጥንት ታሪክ ያላትና የኢትዮፒያን ህዝቦች ያስተሳሰረች ሃይማኖት በመሆና ይህን ሁሉ ለማጥፋት በዋናነት የንጉሶቹን ስረአት እና ሃይማኖትን እንዲሁም አምሃራን ማጥፋት ብሎ የተነሳው :: ዛሪም የኢርትሪያ መገንጠል የትግሪ ነጻነት ብሎ የተነሳው የህወሃት የትግሪ ባንዳ ነው የኢትዮፒያም መፍረስ ነጻነት ማጣት ቀንደኛው ተጠያቂ ትግሪ ባንዳ ብቻ ነው ማንም አይደለም ገና የወረረውን መሪት በወረራ ያስፋፋውን መሪት ይመለሳል የዘር ፊደራሊዝም በነጻ አውጭዎች መከፋፈላይቻልም

  4. I dont know the prof, he seems to be pro-eritrean or he is eritrean.

    This =======> በድርድር በአሰብም በምፅዋም የመጠቀም መብት አለን is unacceptable !

    Ownership !

    The Asseb region belongs to Ethiopia, and neither TPLF nor ferenjis can permanently landlock Ethiopia !

    I have yet to read the article, but if he only blames Ethiopian governments for the landlocked status of Ethiopia and NOT satanic USA and ferenjis in general, we must assume that the prof, like money other educated Ethiopians, is bought by the CIA.

    Even a kid can see that TPLF and EPLF came to power ONLY (!!!) thanks to satanic USA support.

    I think that answers clearly who is responsible for the landlocked status of Ethiopia.

    Ethiopian governments (i mean only Haile Selassie and Derg) were neither angels or perfect, but so are all other governments in the world. But the countries ruled by those other governments didn’t end up landlocked like Ethiopia, why ?

    There is only one explanation, satanic USA (USA was not destructively engaged in those other countries) !

    The USA and ferenjis landlocked Ethiopia to make the country a WARNING EXAMPLE for other countries !

    Regarding the “WARNING EXAMPLE” matter, a short glance at the Ethiopian map suffices for other countries to get the “message”.

    Map of Ethiopia

    http://www.mapsofworld.com/ethiopia/maps/ethiopia-map.jpg

    Despite conventional views this landlocking was done by ferenjis, and it is one area that shows the ill-will the ferenjis harbour towards Ethiopia.

    A short glance at the world map (look at Jordan, Iraq, countries in West Africa and of course DR Congo) suffices to recognize the ill-will of ferenjis towards Ethiopia.
    As we can see on the map of DR Congo, the common practice in international law is to always ensure access to the sea when countries are formed, even by cutting corridors through other countries.

    We can see on the DR Congo map where a corridor was cut through Angolan territory, creating the Cabinda province north of the DR Congo at the Atlantic coast which is separated from the rest of Angola.

    Watch the map carefully, the mainland of DR Congo is hundreds of Kilometers away from the Atlantic Coast, still a corridor was cut through Angola to connect DR Congo to the sea.

    And then look at the map of Ethiopia, it lies so near to the coast, not even 100 km away from the coast, still the ferenjis, particularly the USA, decided to make Ethiopia landlocked because of ill-will !

  5. This prof appears retarded, or dishonest.

    Even a kid can see that if the USA had not supported EPLF and TPLF the situation we had in Ethiopia until May 1991 G.C. wouldn’t have changed today.

    That is so simple. What a shame that a professor cant see what a kid can see.

  6. ፕሮፌሰር ገብሩ፤
    ጥሩ ታሪክ አስተምረዉናል፣ የንጉስ ኃይለስላሴን አካሄድ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ስኅተት ነበር ብለውናል። መቼም ከበሮ ሲያዩት ያምር እንደሚባለው ሆኖ እንጅ፣ በእርሳቸው ቦታ በዚያን ወቅት ሆነው ቢሞክሩት አሁን የሚተቹትን ለማለታቸው እጠራጠራለሁ።
    ያም ሆነ ወደ መፍትሄው ሲኬድ አሁንም ልክ በሁለቱም አገዛዞች ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደሚፈልጉት ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያውቅ ሰው ይጠፋና፣ የሚቀረው ደንታ ቢስ የሆነ ትውልድ በተለይ በኢትዮጵያ እንዲፈጠር ካደረግን በኋላ ኤርትራ የኛ ናት የሚል አይኖርም በሚል የተሰላ ስሌት ይመስላል። እንደምናየው በኢትዮጵያም ዘርፊ፣ እርባና እና ደንታ ቢስ ትውልድ እየገነቡ ስለሆነ የተሳካላቸው መስሎ ይሰማቸው ይሆናል። ነገር ግን ገና ነው ነገሩ፣ ምክንያቱም ምን ይባላል ከሁኔታው ያኳኋኑ የሚባል አለ። ኢትዮጵያዊ ወዶና ፈቅዶ አገራችሁን መስርቱ፣ ወንድማማቾች ነን፣ እናንተም በሄዳችሁበት ይቅናችሁ እኛንም እንደዚሁ፣ ለናንተ ይሄ ድርሻችሁ ለኛ ይሄ ድርሻችን ተባብሎ፣ ተመራርቆ ባልተለያይንበት ሁኔታና እንዲያውም ይባስ ብሎ ኢትዮጵያዊ እንደባይተዋር በአገሩ ጉዳይ ተቆጥሮ በጓሮ በር በተካሄደው “ውል” ኤርትራ ሄደች የሚባለውን ተረት ተረት ምንጊዜም የማይቀበለው መሆኑን፣ ችግሩ ከትውልድ ትውልድ ይተላለፋል እንጅ አሁን ፕሮፌሰር ገብሩ ሆኑ ሌሎች ሊሰብኩን ወይ “ሊመክሩን እንደሚፈልጉት አይሆንም።
    እንደተመኛችሁት አገሩን የሚያውቅ ትውልድ አሁንም አለ፣ አልጠፋም፣ የናንተ የቅኝ ገዥዎች ውል ምናምንቴን ማንም አይቀበለውም። ቅኝ ገዥ ምን ጊዜም በሰው አገር ላይ የራሱ አጀንዳ አለው፣ ያንን አንቀበለውም ብለው አይደለም እንዴ አያት ቅድመ አያቶቻችን ተዋግተው ያሸነፏቸው? አገራችንን አናስነካም ብለው የምትተካ ህይወታቸውን የገበሩላት፣ አጥንታቸውን የከሰከሱላት፣ ደማቸውን ያፈሰሱላት። እንግድያው አሁንም ይህንን አደራ ያልዘንጋ ትውልድ ጨርሶ ያላለቀ መሆኑን ለናንተና ለቀጣሪዎቻችሁ ንገሯቸው።
    ወደ መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ይዛ አንዲት ትልቅ ሃገር፣ በራሷ ወደቦች ተከራይታ እንድትኖር የሚደረገው ሰበካ ገዥ የለዉም። አንደኛው ቀጣፊና ነቀርሳ አሁን ስልጣን ላይ ያለው የወወያኔ መራሹ ኢሃዴግ አገዛዝ ነው። እርሱ ባደረጋቸው ዉሎች ገና ቋሚ መንግሥት ሳይመሠረት በሽግግር መንግሥት ላይ እያለ ነው ሪፈረንደም ተብዬውን ያካሄደው ያለ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ፤ ከዚያም የተደረገውን ሸርና ተንኮል ሁላችንም ስለምናውቀው መዘርዘሩ ፋይዳ የለዉም።
    ስለዚህ ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ወያኔ ኢህአዴግን በህዝባዊ አመጽ ማስወገድ ተግቢ ነው። ኢትዮጵያን በሚመለከት ለሚደርሰው ዉድቀትና ውርደት ይህ ሥርዓት ዋና ተዋናይ ስለሆነ ይህ ተግባራዊ መሆን አለበት። እርሱ በሚያካሂደው ጦርነትም ኢትዮጵያን የሚጠቅም ጉዳይ ሳይሆን ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት፣ የሰራዉን ሴራ ተገልጦ እንዳይታወቅ የሚሠራ፣ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ሁሉ እየተቃረነ የሚኖር፣ ለኤርትራ ጥብቅና የቆመ አገዛዝ ነውና እርሱ ጦርነት አድርጎ የሚያመጣው ጥቅም ስለሌለ፣ ህይወታችሁን ከንቱ እንዳታጠፉ አደራ ምክንያቱም ውጤትን በባድመ ዉጊያ አይተነዋልና።
    ጥቅሞቻችንን ለማስከበር ኢትዮጵያዊ ሽታ ያለውና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ መንግስት ማቋቋም ይጠበቅብናል።
    እነ ፕሮፌሰር ገብሩ አሁን የሚነግሩን ያሉት ብዙ ዓመታት ተዋግተን ያመጣነው ነገር የለም፣ የኤርትራን አገርነት ተቀብላችሁ ኑሩ፣ ወደቦችም ሁሉ የኤርትራ ናቸው ስለዚህ ወደቦቹን ከኢትዮጵያ ወዲያ የሚጠቀምባቸው የለም በመሆኑም ኤርትራዉያኖቹ ከኛ የሚያገኙትን ጥቅም እየሰጠናቸው፣”የነርሱን” ወደቦች እንጠቀም ይሉናል። እስኪ መጀመሪያ የራሳችንን መንግሥት እንመስርትና ከዚያ በኋላ እንዴት እንደምንዋዋል ይታያል። በተባበሩት መንግሥታት ድረስ ተሂዶ የኢትዮጵያን የወደብ ይገባኛል ጥያቄን ያላነሳ መንግሥት ኢትዮጵያዊነት እንዴት ነው ልንቀበለው የምንችለው?
    የተመጠነ ዋጋውን ሰጥተነዋል፣ አሁንም ሆነ ወደፊት ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንወስዳለን እየተባለ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፌዝበት ምን ማለት ነው? ለኢትዮጵያ ጥቅምማ ቢቆም፣ ብዙ ነገሮች አሉ። ከህዝብ መብት ማስከበር ጀምሮ ማለት ነው፤ ጦርነቱ የህዝብ ብሶት አቅጣጫ ማስቀየሪያ እንጂ የሚያመጣው ፋይዳ የለም። አምባገነኖች የስልጣን ኮርቻቸው በተነቃነቀ ቁጥር የሚፈጥሩት የማስቀየሻ ስልት ነው።
    ለዕውነተኛ ሰላምና ፍቅር ፈላጊ ኤርትራውያን፤
    ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችሁ ሁሌ ለናንተ ጥሩ ነገር እንደምነመኝላችሁነ ሁሉ እናንተም እንደዚሁ ማሰብና ከልብ መሥራት የሚጠበቅባችሁ ይመስልኛል። አገዛዞች ለራሳቸው የሥልጣን ዕድሜ መራዘም ሲሉ በህዝቦች መሃል እሳት እየጫሩ ለማያባራ ጦርነት፣ ዕልቂትና ቁርሾ ይዳርጉናል። መቼም እንደኔ ዕምነት በነጻ ፈቃዳችሁ ተጠይቃችሁ ቢሆን፣ ከኢትዮጵያ ወንድምና እህቶቻችሁ ጋር አብሮ መኖር እምነቴ ነው። ነገር ግን ነጻ በሆነ መንገድ ምርጫችሁ መለየት ከሆነ ግን ሁሉም ፍላጎታችሁን ያከብራል። ታዲያ ስንለያይ ደግሞ በብልጣብልትነት ሆን ስለሌለበት፣ ይህ ላንተ ይህ ላንቺ ተባብሎ ባልና ሚስት ስለያዩ እንደሚካፈሉት፣ ከዚያም በላይ እኛ እንደ ባልና ሚስት አገር ቀይረህ የማይኬድበት አንተን አያሳየኝ ልንባባል የማንችልበት የመልክዐ ምድር አቀማመጥ ላይ ስለምንገኝ፣ የምንሰራው ሥራ በቅንነት፣ በመግባባትና በመተሳሰብ እንዲሆን፣ ሁለቱን ወድቦች እኩል መካፈል ሲገባን፤ እናንተም ደግሞ ከኢትዮጵያ ልታገኙ የሚገባችሁን ልክ እንደወንድማማች ንገብታሁ ወጥታችሁ የምተሰሩበትን፣ የምትኖሩበትን መንገድ ማመቻቸት ተገቢ ይመስለኛል። በሂደትም ስጋታችሁ እየተወገደ፣ ፍቅራችሁ የበለጠ መተማመንን እያፈራ በሂደ ጊዜ በፌዴሬሽንስ ይሁን ኮንፈደሬሽን አብሮ መስራቱና መኖሩ አይቀርም ባይ ነኝ።
    ከዚህ ሌላ ግን ያ ቂምና ቁርሾ አብሮ ስለሚቀጥል፣ የተሰራው ተንኮልና ድባ ሁሌም ስለማያስተኛ ጥሩ ጎረቤታሞች ሆኖ ለመኖርም ችግር ነው። የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሆነ የወሰን ድንጋይ፣ አጥር አያግደዉም ችግሩ በቅንነት ያልተፈታ እንደሆነ። ትውልድ አልፎ ትውልድ ቢተካ፣ ችግሩን ከሥሩ፣ መፍትሄውንም ከጥሩ ተደርጎ ይፈታ። ለዚህም ከየመንግስት ተብዬዎቻችን ወጣ ብለን እኛው ብናየው መልካም ይመስለኛል።
    አመሰግናለሁ

  7. The professor has deliberately distorted the history of Ethiopia including Eritrea. He omitted the role the TPLF junta played to separate Eritrea from its mother land Ethiopia. He never mentioned the support of TPLF to Shaabia during ‘ operation red star ‘. In addition, the pro-Weyanie professor intentionally skip the pivotal role played by Weyanie by signing and recognising Eritrea as an independent country, even though the vas majority of Ethiopian people was sad by the decision Weyanie made. Moreover, unbelievably he admired the apartheid ethnic federalism of Weyanie that divided the people of Ethiopia and helped Weyanie to annex massive lands from Gonder and Wello. In general, the analysis of the Weyanie profess can not convince any one who knows Ethiopan history.

    God bless Ethiopia

  8. The professor has deliberately distorted the history of Ethiopia including Eritrea. He omitted the role the TPLF junta played to separate Eritrea from its mother land Ethiopia. He never mentioned the support of TPLF to Shaabia during ‘ operation red star ‘. In addition, the pro-Weyanie professor intentionally skip the pivotal role played by Weyanie by signing and recognising Eritrea as an independent country, even though the vast
    majority of Ethiopian people was sad by the decision Weyanie made. Moreover, unbelievably he admired the apartheid ethnic federalism of Weyanie that divided the people of Ethiopia and helped Weyanie to annex massive land from Gonder and Wello. In general, the analysis of the Weyanie professor can not convince any one who knows Ethiopan history.

    God bless Ethiopia

  9. Profesor
    I appreciate for your time. I urge you also to get together with the other ethiopian elite to come up with creative ideas how to solve Ethiopian problems. You know the core solution. which is real democracy.

  10. ሁኔታዉ ስለ ጉዳዩ ትላንት የሰማ ይመስላል ከመለሰ ዘራዊ ጋር አብሮ ዶልቶ ያስፈጸመዉን ስራ። የስራችሁን ታገኛላችሁ አሁንም እያገኛችሁ ነዉ ትግራይ ትግርኛን እርሳዉ ኤርትራዊ ከትግሬ ጋር አብሮ ከሚኖር ሞቱን ይመርጣል።መቸም እፍረት እና ክብር እናንተ ዘንድ የለም

  11. This pro he from tigra. All the same no difference tigra elites. the ather ethiopia do you home work stand together

  12. ወያኔ ለ50 አመታት በአማራው ሕዝብ ላይ ያደረሰው ግፍና በደል
    1- ድህነትን በአማራው ውስጥ እድሰርጽ ማስፋፋት/ማስገደድ
    2- አማራ ዘሩን እንዳይተካ ዘሩ እንድጠፋ ማምከን በቀጥታና በተዘዋዋሪ የተንኮልን ጥበብ በመለዋወጥ በመተግበር
    3- መሬቱን ለባዕዳንና ለባንዳ ወያኔ መሸንሸን ለትግረዎች ማከፋፈል ማስፈር
    4- ኢትዮጵያ የሚሉትን/የሚለውን/ ትውልድ ማጥፋት ተከታትሎ መግደል/ማስገደል
    5- በአማራው ክልል ውስጥ መርዛማ ኬሚካሎችን እንድጠቀምና እንድሰራጭ በካድሮዎቹ ማስገደድ/ስራ ላይ ማዋል
    6- ከኢትዮጵያ ሃገር ማፈናቀል፣መድርሻውን ማሳጣት ዘወተ
    የወያኔ ደባ በአማራ ላይ የተሰራው ደባ ዳኛም አይፈርደው! ብቻ ፈጣሪ ይፈረደኝ!

    በላይ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*