የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ የአመራርና የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ ነዉ።

ሙስና በኦሮምያ DW Amharic

በዚህ ባሳለፍነዉ ሁለት ወራት ዉስጥ የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የአመራርና የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።

የቀድሞ የኦሮምያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘላም ጀማህን ጨምሮ፣ የሱሉልታ ምክትል ካንትባ የነበሩት አቶ ዲሮ ዳሜ፣ የላገ ዳዲ ለጋ ጣፎ ከንቲባ የነበሩት አቶ ፋሲል ኃይሉ፤ የቀድሞ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዓለሙ ለሜሳ፣ የቀድሞ የጋላን ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሙሉጌታ ከበደ እንዲሁም ሌሎች 10 ግለሰቦች አንድ ወር ባለሞላ ጊዜ ዉስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ አገር ዉስጥ ያሉ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
የኦሮሚያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክሱን ስመሰርት እኝ ግለሰቦች ስልጣናቸዉን በመጠቀም ኃብት አከብተዋል፤ አብዛኞቹም ተከሰሾችም መሬት እና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ሙስና ፈጽመዋል ሲል ወንጅሏቸዋል። የፀረ ሙስና ትግሉ በኦሮሚያ ብቻ ባይገደብም ክልሉ ለሙስና ለምን እንዲህ ተጋላጭ ሆነ ብለን የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽኔር አቶ ሃምዲ ክንሶ ጠይቀናቸዉ ነበር።

Symbolbild Geldwechsel በኦሮሚያ ክልል በሙስና ተጠርጥሮ ቁጥጥር ስር የሚዉሉት ግለሰቦች በሙስና ቢሳተፉም ከአስተዳደሩ ጋር የፖለቲካ ግጭት ሲፈጠር ነዉ ብለዉ አስተያየታቸዉን የሚሰነዝሩም አልጠፉም።

የኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የሚፈፀመዉን ሙስና ለመከላከል የኦሮሚያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የግንዛቤ ማስቸበጫ እየሰራ መሆኑንና በዚህም ላይ ለሙስና በር የሚከፍቱ ነገሮች ላይ ጥናትና ምርምር እያደረጉ መሆኑን ምክትል ኮምሸነሩ ተናግረዋል። ከዚህ ሌላ የባለስልጣናትና የሰራተኞች ንብረት ምዝገባ ላይ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልፀዋል።

http://www.dw.com/popups/mediaplayer/contentId_19360562_mediaId_19360491
መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ

5 Comments on “የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ የአመራርና የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ ነዉ።”

  1. Enzih demo Leba yazn yemilut Chiger semetabachew new. Leboch enante tsere musna ymtebalut Leboch nachihu….Weshoch.

  2. .

    የሰብል ግብርና የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ተስፋችን ነው::
    የተፈጥሮ ሃብት ማለት የሰው ልጅ የሚጠቀምባቸው የተፈጥሮ ሃብቶች ሲሆኑ ዉሃን፣ ልዩ ልዩ እፅዋትንና እንስሳትን፣ አፈርን፣ ድንጋይን፣ ብረታብረትን፣ ወርቅን፣ ቤንዚንን፣ ጋዝን እና ሌሎችንም ይጨምራል።
    የተፈጥሮ ሃብታችንን በደንብ ባለመያዛችን አፈር ባክኗል፣ የዝናብ እጥረት ደርሷል፣ ምንጮች እና ወንዞች ደርቀዋል፣ የሰብል ምርት ቀንሷል፣ የማገዶ እና የቤት መስሪያ እንጨት ጠፍቷል፣ በርካታ የዱር እንስሳት ተሰደዋል፣ ረሃብ፣ እርዛት እና ከፍተኛ የሰው እልቂት ተከስቷል። ስለሆነም የተፈጥሮ ሃብትን በአግባቡ መጠቀም ካልተቻለ ጉዳቱ የከፋ ነው። ስለዚህም የተፈጥሮ ሃብትን መንከባበብ አስፈላጊ ነው።
    የመሬት እና የአፈር መከላት
    .
    ዴስሞዲየምን በማብቀል የአፈር ለምነትን ማሳደግ
    ዴስሞዲየም በግብርና ዉስጥ ከፍተኛ ጥቅም ያለዉ ሲሆን ገበሬዎች ይህንን ተክል እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ፡፡
    ዴስሞዲየም ለምን ያስፈልጋል?
    • ጥሩ የከብቶች መኖ ሊሆን የሚችልና የአፈርን ለምነት የሚጨምር ነዉ፡፡
    • ስትሪጋ የተባለዉ አረም በሚያስቸግርበት ወቅት ዴስሞዲየምን በመትከል መከላከል ይቻላል
    • የዴስሞዲየም ዘር ብዙ የማይገኝና ዉድ ቢሆንም የአካባቢዉ ገበሬዎች በማምረት ማከፋፈል ይችላሉ
    እንዴት ማሳደግ ይቻላል?
    • ከግማሽ ላነሰ ሔክታር 2 ኪግ ዘር በቂ ነዉ፡፡
    • ጥሩ የችግኝ ማብቀያ መሬት ያዘጋጁ፡፡
    • በቀጥታ መስመር ይዝሩት
    • ዘሩን ከትሪፕል ሱፐርፎስፌት ማዳበሪያ ይቀላቅሉት (2 ኪግ ዘር ከ 1 ከረጢት ትሪፕል ሱፐርፎስፌት ጋ

    የመሬት መከላት ማለት የአፈር፣ የውሃ፣ የዕጽዋት እና የአየር ሁኔታዎች መዛባት ነው። የመሬት መደርመስ አንዱ ምሳሌ ነው። የአካባቢውን ጤናማ ሕይወት ይቀይራል። ቤቶች ይፈርሳሉ። የዕለት ዕለት ኑሮ ይናጋል። በተጨማሪም ለመሬት መከላት የአፈሩ አይነት ተዳፋትነት፣ የዕጽዋት ሁኔታ እና የአየር ንብረት መዛባት አስተዋፅኦ አላቸው። ስለሆነም ጥሩ የነበረው የመሬት ቅርፅ ተለውጦ ለሰው ልጆች መኖሪያ መሆኑ ይቀራል።
    የመሬትና የአፈር መከላት መገለጫዎች አያሌ ናቸው። በእንስሳት መኖ እና ማገዶ ላይ ከፍተኛ እጥረት መፈጠር ዋናው ምልክት ነው። ከዚህ በተጨማሪ፦
    • የውሃ ስርገትን ይቀንሳል
    • ለምለም እና ጤናማ ዕጽዋት አይታዩም
    • እሾህና አሜከላ ማብቀል ይጀምራሉ
    • ለሙ አፈር ተሸርሽሮ ገደላ ገደል ይሆናል
    • ለም አፈር ታጥቦ በድንጋይ ይተካል

    በኢትዮጵያ በአብዛኛዉ የሚመረቱ የሰብል አይነቶች እንደጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ሽምብራና እንዲሁም የተለያዩ አትክልቶች ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም እንደቡና፣ ሻይ እና ሰሊጥ የመሳሰሉ ገቢ አስገኚ ዕፅዋት ይመረታሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የአበባ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነዉ፡፡ የእነዚህን ሰብሎች ምርት ለመጨመር የተለያዩ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
    ቁጠባ ለአጭር ጊዜ ሲሆን ኢንቨስት ማድረግ ግን ለረጅም ጊዜ ነዉ፡፡
    ኢንቨስትመንት ማለት ገንዘብ ለማግኘት የሚደረግ የረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ ነዉ፡፡ ኢንቨስት በማድረግ ዋጋቸዉ ወደድ ያሉ ቁሶችን ወይም አገልግሎቶችን (እንደቤት እና ትምህርት የመሳሰሉ) ለማግኘት ያስችለናል፡፡
    በዚህ ክፍል ዉስጥ ስለሚከተሉት ነገሮች እንመለከታለን፦
    · በቁጠባና ኢንቨስት በማድረግ መሀል ያለዉን ልዩነት
    · ለእርስዎ ትክክለኛ ኢንቨስትመንት ምንድን ነዉ?
    · የኢንቨስትመንት ጥቅሞችና አደጋዎች
    · የራስዎን ፖርትፎልዮ ማዘጋጀት
    የእንስሳት እርባታ
    በኢትዮጵያ በአብዛኛዉ የሚያዙት የእንስሳት አይነቶች እንደከብት፣ በጎች፣ ፍየሎች እና ዶሮዎች ናቸዉ፡፡ ከነዚህ እንስሳቶች ለመጠቀም ከፈለጉ ጥሩ ዝርያ መፈለግ፣ ጥሩ መኖ መመገብ፣ ጥሩ መጠለያ፣ ከበሽታዎች መጠበቅና ጥሩ የመዝገብ አያያዝ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ጥሩ ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ እንስሳትንም ማርባት ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ እንደ ጥንቸልና ሰጎን የመሳሰሉትን፡፡ በዚህ ክፍል ዉስጥ ስለነዚህ ጉዳዮች በስፋት ይመልከቱ፡፡
    አሳ እርባታ
    የአሳ እርባታ ማለት አሳን በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ የውሃ አካል ውስጥ በማራባት፣ በመጠበቅ፣ በመመገብ፣ ለግል ፍጆታ ወይም ለንግድ አገልግሎት እንዲውል የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። አሳ ለምግብነት ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚውል የማህል ሀገር እምቅ ሀብት ነው። አሳ የሚገኘው ከ7400 ካሬ ኪሎሜትር ከፍታ ባላቸው ሀይቆችና ግድቦች፣ 250 ካሬ ኪሎሜትር በላይ የሚሸፍኑ ትናንሽ ኩሬዎችና 7000 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ ባላቸው ወንዞች ውስጥ ነው።
    በዓመት በግምት ከ44-49 ሺህ ቶን አሳ ይመረታል። ከሚመረተው የአሳ ሀብት ከዋና ዋና ሀይቆች 72%፣ ከወንዞች15% እና ከሰውሠራሽ ግድቦችና ከሌሎች የውሃ አካላት 13% ነው። አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች ከግድቦችና ከሀይቆች በሚገኝ አሳ በጣም የታወቁ ናቸው። ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ ክልል በወንዝ አሳ የታወቁ ናቸው።
    በሀገሪቱ የአሳ አጠቃቀም አነስተኛ ነው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀይቆች አሳ ምርት እየጨመረ መጥቷል። ይህም የሆነው ከሀይቆች አሳ በ1986 ዓ.ም 6200 ቶን የነበረው በ1994 ዓ.ም ወደ 10,900 ቶን ማደጉ ነው። ለዚህም ዋና ምክንያት የሆነው የግብአት ፍላጎትና የገበያ አውታሮች መዘርጋታቸው ነው። አገሪቷ የአሳ ግብርናን ለማስፋፋት አመቺ የስነምህዳር ቀጠናዎች አሏት።
    የአሳ ሀብት ክምችት
    • ከዋና ዋና ሀይቆች
    • ከዋና ዋና ወንዞች
    • ከዋና ዋና ግድቦች፣ ከትንንሽ ግድቦችና ኩሬዎች
    የወተት እንስሳት አረባብና የወተት ተዋፅኦ አመራረትና አጠቃቀም ለተለያዩ ግልጋሎቶች ማለትም ለእርሻ ጉልበት፣ ለወተትና ለሥጋ የሚውሉ የተለያዩ ዝርያዎችን በመጠቀም በባህላዊ እና በዘመናዊ አያያዝ ከሌሎች የግብርና ሥራዎች ጋር በተጓዳኝና በጣምራ የሚሰራ ነው። የወተት እንስሳት አረባብ በአብዛኛው ባህላዊ ነው። ይሁን እንጂ ከ 40 ዓመታት በፊት የተሻሻሉ የውጭ ዝርያዎች በደጋውና በወይናደጋው ክልሎች ጊደሮችን፣ ኮርማዎችንና አባላዘር በመጠቀም ዘመናዊ የአረባብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተሞክሯል። ዘመናዊ ዘዴዎችን ለማስፋፋት የጭላሎ እና የወላይታ እርሻ ልማት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

    ከዚህም በተጨማሪ የሰው ሠራሽ ማዳቀያ ማዕከል ተቋቁሞ የተለያዩ ሰፋፊ የማራቢያ ጣቢያዎች አገልግሎት በመስጠት ዲቃላ ጊደሮች የሚሰራጩበት መንገድ ተከፍቷል። በደጋውና በወይናደጋው የወተትና የወተት ተዋፅኦ ያነጣጠረው በዳልጋ ከብት ላይ ነው። ይህም 88% የሀገሪቱ ህዝብ የሚኖርበት 70% የዳልጋ ከብት የያዘ ነው። በአርብቶ አደሩ ዘንድም ከዳለጋ ከብት፣ ከግመልና ከፍየል የሚመረተው ወተት የምግብ ምንጭና ዋስትና ነው። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የእርባታ ዘዴው በአርብቶ አደሩ አካባቢ አልተስፋፋም። ይህም የሆነው ከፍተኛ ሀሩራማ የአየር ንብረት፣ የውሃ እጥረትና ተደጋጋሚ ድርቅ በመከሰቱ ነው።
    በዚህ ክፍል ዉስጥ የሚከተሉትን ነገሮች እንመለከታለን፦
    • ስለእንስሳቱ ዝርያዎች
    • ስለአረባብና አስተዳደር
    • ስለከብቶች መዝገብ አያያዝ
    • ስለጥጃዎች አወላለድና እንክብካቤ
    • ስለከብት መኖ
    • ስለበሽታዎች
    • ስለእንስሳቱ ተዋፅዖዎች.
    ቦጋለ ተሰማ , አርኪኦሎጂስት ከአዳማ

  3. @bogale tasama, ante rase yabet insasa nhe. The topic is corruption, what got to do with farming and natural resources? I wish you teach our farmers about this, you could change something. This site belong to politics farming, we only use hate,insults,and criticism unlike farming rain,land,seeds and fertiliser.so join us or get back to those who need your advice desperately. See ya

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*