አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል አመልክቷል።
ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት – አይኤምኤፍ በየዓመቱ በሚያወጣው የአጠቃላይ ምጣኔ ኃብት ዕድገት ሪፖርቱ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርት ኤልኒኞን ተከትሎ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት እንደማይቀንስ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታውቋል።
“ድርቅ ባልተከሰተባቸው አካባቢዎች የተከናወነው የማካካስ ሥራ የምርት መጠን እንዳይቀንስና እንደተለመደው 270 ሚሊዮን ኩንታል እንዲሆን አስችሏል” ብለዋል የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ።
በሌላ በኩል ደግሞ ዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት – አይኤምኤፍ በየዓመቱ በሚያወጣው የአጠቃላይ ምጣኔ ኃብት ዕድገት ሪፖርቱ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል አመልክቷል።
በያዝነው የአውሮፓ 2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኃብት ምጣኔ በ4.5 ከመቶ እንደሚያድግ የገንዘብ ድርጅቱ ተንብይዋል።
ከአሥር ዓመታት በላይ ወደ ድርብ አኀዝ የሚጠጋ ዕድገት ሲያሳይ የቆየው የኢትዮጵያ ምጣኔኃብት በፍጥነት እንዲያሽቆለቁል ያደረገው የተከሰተው ድርቅና የዓለምአቀፍ የሸቀጥ ገበያ ዋጋ መቀነስ እንደሆነም ጥናቱ አስረድቷል።
የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት ቡድንን የመሩት ኦያ ሴላሰን በወቅቱ ምክንያቱን ሲያስረዱ “አንዱ ምክንያት ምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ብርቱ ድርቅ ተከስቶባቸዋል፤ የዝናቡ መጠን ለበርካታ ዓመታት ከተመዘገበው አማካይ በ40 ከመቶ ቀንሷል። ይሄ ሁኔታ በምጣኔኃብት ዕድገት ትንበያው ላይ ተንፀባርቋል፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ምጣኔኃብቶችን ጎድቷል፤ ማላዊ፣ ዚምባብዌ፣ ዛምቢያና ደቡብ አፍሪካንም ጎድቷል።” ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Imf mnm sayaTena gmt lay temsrto ye politica dgaf lemesTet new miyaworaw.
አለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ድህነት ድግስ እየደገሰ ያለእና ወደፊትም ከወያኔ ጋር በመተባበር የሃገሪቱን አንጥሮራ ሃብት በማሸሽ በምዕራባዊያን ባንክ የሚሰበስብ ብድር አብድራለሁ ርዳታ እሰጣለሁ እዳ ከፋይ ትውልድ ለመፍጠር በሃገሪቱ ውጤት የሌለው ፕሮጀክት ገንዘብ ለባለስልጣንና ለመሰሎቻቸው በአውሮፓ፣በአፍሪካ ሽርሽር፣ሰብሰባ፣ውርክሾፕ፣ጉብኝት፣አውደጥናት በሚል ኪሳቸውን ያደልባል.ይዘርፋሉ፣ያዘረፋል፣ይነጥቃል፣ያስነጣቃል! አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ጠላት እንጅ ተባበሪ አይደለም ሕዝብ ማወቅ አለበት
የሃገሪቱ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል አመልክቷልይህ የሚሉት ለማን ነው?
ተዋበው
ውድ ወንድሜ ተዋበው ትክክል አስተያየት ነው በጥንቃቄ አይተሃዋል የኢትዮጵያ ጠላቶች ምንጊዜም ተኝተው አያውቁም ያውም አሁን በጡት ነካሾች መሪነትና ትብብር ወደብ አልባ አድረገዋት በአለምዘቀፍ የገንዘብ ድርጅት በመታገዝ ይህውና ዛሬ አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያ ሽቆለቁል አመልክቷል ቀጣፉ ውሸታም ካሃድዎች ጋር በማበር ይሰረቃሉ!
እና ምን ፈልጎ ነው ትናንትና 11.4 በመቶ አደገ ሲል የነበረው አይ.ኤም.ኤፍ ዛሬ ይቀንሳል ይጨምራል የሚሉት ለማን ነው?
ውድ ወንድሜ ተዋበው ትክክል አስተያየት ነው በጥንቃቄ አይተሃዋል የኢትዮጵያ ጠላቶች ምንጊዜም ተኝተው አያውቁም ያውም አሁን በጡት ነካሾች መሪነትና ትብብር ወደብ አልባ አድረገዋት በአለምዘቀፍ የገንዘብ ድርጅት በመታገዝ ይህውና ዛሬ አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ የምርት ዕድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያ ሽቆለቁል አመልክቷል ቀጣፉ ውሸታም ካሃድዎች ጋር በማበር ይሰረቃሉ!
እና ምን ፈልጎ ነው ትናንትና 11.4 በመቶ አደገ ሲል የነበረው አይ.ኤም.ኤፍ ዛሬ ይቀንሳል ይጨምራል የሚሉት ለማን ነው?
ለማ
ለማ ትክክለኛ ሃሳብ ነው በደንብ ገብቶሃል እውነትም የተጠቀሱትና በድብቅ በሃገራችን እጃቸውን አስገብተው ወያኔን በማገዝ ሕዝብን ስደት የሚልኩ ድርጅቶች ብዙ ብዙ ነቻው፡፡
አይ.ኤም ኤፍ ፣ርዳታ ሰጭዎች የአለም ባንክ የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያን ድሃ ማድረግ ነው አላማቸው! ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ነበሩ!ናቸው!
መኮንን
ሰሞኑን የወያኔ ዪኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ሲያስመረኩ ኢትዮጵያ ሃገሬ ብሎው የጠሩት ሁለቱ ዪኒቨርሲቲዎች 1- ደብረታቦር፣2- ደብረብረሃን ብቻ ናቸው ሌሎቹ ግን ምንም ስለሃገር ያሉት ነገር የለም አይደንቅም ትላላችሁ!
መቼም ዘመን በማን እንደሚታይ አይታወቅም የክብር ዶክተሬት መውስድ፣መስጠት፣ማስረከብ ሃገርን ላጠፋና ላስጠፋ ነፍስ ገዳይ ተሰጣቸው አልተሰጣቸው ጅግና ሃገርን ወደብ አልባ ያደረጉ ከእነሱ ዩኒቨርሲት ከሚሉት ለምን እንዳቆቆሙት የሚያውቁት ወያኔ፣ብአድን፣ነጮች ብቻ ናቸው ምክንየቱም ኢትዮጵያ ለማፍረስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህሉን፣ሃይማኖቱን አስጠፍቶ ኢትዮጵያ ማዳከም ስለሆነ አላማቸው የሚያስደንቅ ሊሆን አይችልም እንግሊዝም እኮ ላልተማሩት ወያኔዎች የዶክተር እውቀት እንዳላቸው በማስመስል ስንቱ ነው ሰው በመግደላቸው ብቻ ኢትዮጵያ ስላዳከሙላቸው ዶክተር ዶክተር የእድገት እንቅፋቶችን አዘጋጅተውልናል! ስለዚህ አዲሱ ለገሰም ሆነ ስብሃት ነጋ ዶክተር የሚለው ስም የተሰጣቸው የኢትዮጵያ ልጆች ስለበሉ ብቻ ነው!