በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::

በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Unity‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አንድ ነን እያልን ራሳችንን አየሸነገልን አናታለው፤እጅለእጅ ተያይዘን ወያኔን የመጣል ታሪካዊ የትውልድ ግዴታ ኣለብን። ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና የውርስ አደራ የታላቅነት ተምሳሌት ነው – ኢትዮጵያዊነት!!! በዚህ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው።በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም::የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ ሕዝቦችን ያማከለ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::

እውነትን እና ስልጡን ፖለቲካን ቢተናነቀንም እንደምንም ልንውጠው ግድ ይላል::ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::በፈረንጅ አገር ወያኔ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የላካቸው ባለስኮላርሺፖች አዛኝ ቂቤ አንጓች የአንድነት ሃይል መስለው ሰርገው በመግባት እየሰሩ ያለው ስራ እጅግ ያሳዝናል::ከመወራጨት ውጪ ከነአጨብጫቢዎቻቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡና የለውጥ እንቅፋት እንደሆኑ ልንነግራቸው ይገባል::የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል።

ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

5 Comments on “በተናጠል እየሄድንበት ያለው መንገድ አስጊም አደገኛም ሲልም ሊወጡት የማይችሉ አዘቅት ነው::”

  1. awo ye tenatel tiglu mekeran yarazmal Ethiopian yatefal

    gin gin ..

    ke shabya qetregnoch gar metebaber,,weyane shabya new

    beteamin kenezeh qetregnch gar metebaber yelebinim #

    Hger kidew le siltan tim ,,ke telat gar abirewal ena Hizb lekedachew yegebal !!!

  2. Be etiopiana hzbua lay tgrie
    woyanie slemifeTmbn gf,
    bedelna maswegeja zediew
    bzu tenagrenal/qesqsenal.
    Ye Tere-tgrie woyanie
    qsqesa/yeqalat Tornet gbu
    hzbawi ameT asnesto
    woyanien medemses new.
    Gn gbun sayasaka wedqual
    mkniyatm:
    Qesqashochu, “afreTrTen
    sletenagern tgrie woyanie
    aleqelat!” blen slasebnna.
    Semiw hzb, “gobez
    tenagariwech woyanien
    gamawn yizew liyaTefuln
    ziena absrewalna eyeToletn
    betgst enTebq.” slemil new.
    Semi ameT betenagariw
    yideregal blo yiTebqal,
    tenagarim ameT miyaderg
    semi new blo yiTebqal.
    Eyandandu ye ameT sraw be
    lieloch endisera yigefawal.
    Manm behayl ye ekonomi,
    yakal, weym liela gudat
    adreso ye tgrie woyanien
    yadema/yeneka yelemna
    altewegedum.
    Menager ena madmeT
    tgrie woyanien lemasweged
    beqi hunew alTalutm.
    Flagotn menager kewsTachn
    yetameqe ndietn astenfso,
    be efoyta yaqezqezal enji
    Telatn bemt slemayadema
    wTie albo new.
    Masawequ qsqesa beTratna
    bebzat, tenesu-mtu, enmta
    eyal tadso meqeTel alebet.
    Gn ledl hulachin aTqi hunen
    betegbar tenesten tgrie
    woyanien sndemess new.

  3. ችግሩ እኮ በተቀዋሚ ጎራ ያሉት የፖለቲካ መሪዎቸ የምናውቃቸው 25 ዓመት ሙሉ ምንም ለውጥ ያላመጡ የድሮ የደርግ ኢሠፓ፣ኢሕአፓ፣መኢሶን እና የተሐህት አባላት የነበሩ ናቸው።
    እነዚህ ሣይወገዱ ወያኔ አይወገድም።

  4. Be etiopiana hzbua lay tgrie
    woyanie slemifeTmbn gf,
    bedelna maswegeja zediew
    bzu tenagrenal/qesqsenal.
    Ye Tere-tgrie woyanie
    qsqesa/yeqalat Tornet gbu
    hzbawi ameT asnesto
    woyanien medemses new.
    Gn gbun sayasaka wedqual
    mkniyatum:
    Qesqashochu, “afreTrTen
    sletenagern tgrie woyanie
    aleqelat!” blen slasebnna.
    Semiw hzb, “gobez
    tenagariwech woyanien
    gamawn yizew liyaTefuln
    ziena absrewalna eyeToletn
    betgst enTebq”, slemil new.
    Semi ameT betenagariw
    yideregal blo yiTebqal,
    tenagarim ameT besemi
    yideregal blo yiTebqal.
    Eyandandu ye ameT sraw be
    lieloch endisera felgual.
    MadmeTna flagotn menager
    kewsTachn yetameqe qucitn
    /ndietn astenfso, be efoyta
    yaqezeqzal enji beqi hunew
    Telatachn ye tgrie woyanien
    bemt admtew megdel
    yemichlu honew altegeñum.
    Manm behayl ye ekonomi, ye
    akal, weym liela Tqat adrso
    ye tgrie woyanien slalgoda
    woyanie saywodm yigeñal.
    Masawequ/qsqesaw degafi
    huno beTratna bebzat enmta
    ,tenesu-mtu blo tadso yiqeTl.
    Gn ledl hulachin aTqi hunen
    betegbar tenesten tgrie
    woyanien sndemess new.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*