ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል – ኖአሚን በጋሻው

ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል – ኖአሚን በጋሻው

(ሎንግ ቢች – ካሊፎርኒያ)
[email protected]

ሁለት ራዲዮ ጣቢያዎች አሉ። ከዲሲ የሚተላለፉ። የግንቦት ሰባት አመራር የሆኑትን አቶ ንአመን ዘለቀን አቅርበው አወያይተው ነበር። የነጻነት ራዲዮና የአቶ አበበ በለው አዲስ ድምጽ ራዲዮ። በሁለቱ ራዲዮዎች መካከል ትልቅ ልዩነቶች ይታያሉ። አንደኛው፣ የነፃነት ራዲዮ፣ የወያኔው ፋና ራዲዮ ነው የሚመስለው። የፕሮፖጋንዳ ራዲዮ። ገና አዳምጬ ሳልጨርስ ነው የዘጋሁት። ሁለተኛው የአዲስ ድምጽ ራዲዮ ግን፣ ለሁለት ሰዓት የተላለፈ ቢሆንም ሙሉዉን አደመጥኩት። የተለያዩ አመለካከቶች የተስተናገዱበት ዘመናዊ ራዲዮ ጣቢያ ነው።

በፕሮፖጋንዲስቱ የነጻነት ራዲዮ በተላለፈው ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም። የአዲስ ድምጽ ራዲዮ ላይ ግን በተላለፈው ላይ አንዳንድ ሐሳብ መጨመር እፈልጋለሁ።

አቶ ንአመን፣ አቶ አበበ ጥያቄዎችን እንኳን እስኪጨርሱ ለመታገስ ትግስት ጎድሏቸው በመሃል ጣልቃ እየገቡ ፣ እየደጋገሙ ያቋርጡ ነበር። ዶናልድ ትራምፕን ነው የመሰሉኝ።

“በምን ምክንያት ነው ግንቦት ሰባት ሻእቢያን በመደገፍ ፔቲሽን ለማስፈረም የሚንቀሳቀሰው ?” የሚል ጥያቄ ነው መጀመሪያ አቶ ንአመን የቀርበላቸው። ሲመልሱም ሶስት ምክንያቶች አስቀምጡ። አንደኛው ምክንያታቸው “በኤርትራ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ካለው አይበለጥም። Double standard ፣ hypocrisy አለ ” የሚል ነበር። “ኮሚሽኑ ፣ ኢትዮጵያ የሰዎች መብት የሚከበርባት አገር ናት ብሎ ቢናገርና እናንተ ያንን ብትቃወሙ እሺ። ግን ስለኢትዮጵያ የተናገረው ነገር የለም። ከኢትዮጵያ ጋር ምን ግንኙነት አለው ?” ብለው ሲጠየቁ አቶ ንአመን መልስ አልነበራቸው። በሻእቢያ ላይ የደረሰው ማበረታቻ ሆኖን፣ “ወያኔዎችም ለፍርድ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የበለጠ መስራት አለብን፤ ከኤርትራዉያኖች መማር አለብን” ማለት ሲገባ “ወያኔዎች የሚሰሩት ግፍ ስላልተካተተ የሻእቢያ ግፍ ለምን ይነሳል” ብሎ መንጨርጨር አስፈላጊ አልነበረም።

ሁለተኛው አቶ ንአመን ያቀረቡት ምክንያት በጣም የሚያስቅና የሚያስተዛዝብ ነበር፡፡ “እንዴ …ምን ነካቸው አቶ ንአምን ? “ ብዬ እጆቼን ራሴ ላይ እስካደረግ ድረስ ነበር የደነገጥኩት። “ኮሚሽኑ በኤርትራ ያሉ ጥሩ ነገሮችን ያላገናዘበ ነው። በኤርትራ ማህበረሰባዊ ፍትህ (social justice) አለ። እንደዉም እዚያ ሄጄ ያነጋገርኳቸው ኤርትራዉያን፣ ነጻ ምርጫ ቢደረግ ኢሳያስን ነው የምንመርጠው ነው ያሉኝ” ሲሉ ነበር፣ ሰው በላውን ኢሳያስ አፈወርቂን፣ ሳያፍሩና አይናቸውን በጨው አጥበው እንደ መልአክ ሊያቀርቡልን የሞከሩት።

እነዚህ ሁለት ምክንያቶች ፈር የለቀቁና ዉሃ የማይቋጥሩ፣ ደካማ ምክንያቶች ናቸው። ግንቦት ሰባቶች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ብቻ ሳይሆን ለስብእና ትልቅ ንቀት እንዳላቸው ነው ያሳዩት።

አቶ ንአመን ያቀረቡት ሶስተኛ ምክንያት፣ በኔ አስተሳሰብ ትልቁና ዋና ምክንያታቸው ነው። “ኤርትራ ብቸኛ ደጋፊያችን ናት። ሻእቢያ ተዳከመ ማለት እኛ ተዳከምን ማለት ነው” ሲሉ በትክክል ጭንቀታቸውን ነው ለሕዝብ ይፋ ያደረጉት። በርግጥም ሻእቢያ ከተመታ ፣ ሻእቢያ ከሞተ፣ የግንቦት ሰባት መጨረሻ ነው የሚሆነው። ግንቦት ሰባት እድል ፈንታዉ ሙሉ ለሙሉ ከሻእቢያ ጋር ስላደረገ ባለው አቅሙና ጉልበቱ ሻእቢያ ከመጠበቅ ዉጭ ሌላ አማራጭ አይኖረዉም። ለነርሱ ሻእቢያን መደገፍ የሕልዉና ጉዳይ ነው። ለዚህም ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ በዲሲ ባደረጉት ስብስባ፣ ለሻእቢያ ድጋፍ እንዲሰጥ፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን የሚቃወም ፊርማ እንዲፈረም፣ ተማጽኖ ያቀረቡት። ለዚህም ነው ግንቦት ሰባት እንደ ድርጅት፣ የወልቃይት ጠገዴ ፣ ለሱዳን የሚሰጠው መሬት የመሳሰሉትን በርካታ ኢትዮጵያዊና አገራዊ ጉዳዮችን ያካተቱ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሥራ በተሰራበት ወቅት፣ አንዳቸውም ጊዜ “ይሄን ፔቲሽን ፈርሙ “ ብሎ ፣ መግለጫ አውጥቶ የቀሰቀሰበት ሁኔታ ሳይኖር፣ ሻእቢያን ለመደገፍ በአዝማችነት ፔቲሽኖችን እያስፈረመ ያለው። ለዚህም ነው፣ እንደ አቶ ንአምን ያሉ አመራሮች በተለያዩ ሜዲያዎች በመቅረብ (media blitz) ከፍተኛ “ሻእቢያዊ” ቅስቀሳ ማድረግ የተያያዙት።

በነገራችን ላይ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን የኤርትራ መሪዎችን በሰው ዘር ማጥፋት ቢከስም ዉሳኔው የመጨረሻ ዉሳኔ አይደለም። ዉሳኔው 47 አገራት ( ኢትዮጵያን ጨመሮ 12 ከአፍሪካ፣ 8 ከአሜሪካ፣ 13 ከእሲያና 14 ከአዉሮፓ) ባሉበት በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ ይታያል። ጉባዬዉም የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርት ተመልክቶ ዉሳኔ የሚሰጠው ከአንድ ሁለት ሳምንት በኋላ ሲሆን፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ ኤርትራዉያን ጉብዬው፣ የኮሚሽኑን ዉሳኔ እንዲያፀድቅ ግፊት ለማድረግ፣ በጄኔቫ በሂን 23 ቀን 2016 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል።

ጉባዬው ዉሳኔውን ካጸደቀ፣ ወደ ተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያመራል። የጸጥታው ምክር ቤትም የጉባዬዉን ዉሳኔ በማጽደቅ የአለም ፍርድ ቤት አቶ ኢሳያስን እና ጓዶቻቸዉን ለፍርድ እንዲቀርቡ መመሪያ ይሰጣል። ክሱ በጸጥታው ምክር ቤት የሚወሰን በመሆኑም እነ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ከነሚሎሶቬች ምድብ ይቀመጣሉ።

በመጨረሻ አንድ ነጥብ ላስቀምጥ። ሻእቢያ ከተባበሩት መንግስታት ጋር በሰብአዊ መብት፣ በፍትህና በሕግ የበላይነት …ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፍቃደኛ ከሆነ፣ ግንቦት ሰባቶችና ሻእቢያ እንደተመኙት፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉብኤ፣ የአጣሪ ኮሚሽኑን ዉሳኔ ሊቀለብሰው ይችላል።
ሻእቢያዎች የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽኑን ለማነጋገርም ሆነ ወደ ኤርትራ ገብቶ ማጣራት እንዲያደርግ ፍቃድ ለመስጠት ከጅምሩ ፍቃደኛ አልነበሩም። ሪፖርቱ ከወጣ በኋላም፣ ኮሚሽኑን መሳደብና ማውገዝ ነበር የመጀመሪያው ስራቸው። ሆኖም ጥቂት ቀናት እንዳለፉ፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ንግግራቸውን እያስተካከሉ የመጡ ይመስላል። በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ኦስማን ሣሌ በኩል ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባዬ በላኩት ደብዳቤ፣ አገራቸው በሰብዓዊ መብት መከበር ዙሪያ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆነች ነው የገለጹት። “ I wish to assure the Council that Eritrea shall remain open and committed to constructive engagement to promote and protect human rights and fundamental freedoms and Eritrea will lend its hands to make this body more credible and relevant to all stakeholders.” ነበር ባለስልጣኑ ያሉት። ይሄ በሻእቢያ ታሪክ ተሰምቶ የማያወቅ፣ ሻእቢያ አፍንጫው ተይዞ ፣ ተገዶ የደረሰበት አቋም ነው።

ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ሻእቢያ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉብዬ ጋር አብሮ ለመስራት ከወሰነ፣ እንደፈለገ ሊሆን አይችልም ማለት ነው። በተለይም በተባበሩት መንግስታት፣ በአፍሪካ ሕብረት በመሳሰሉት የማይወደዱና የሚያስነቅፉ ተግባራቱን ማቆም ይኖርበታል።

የጸጥታው ምክር ቤት እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 ያወጣው ፣ ” ሕግ 1907″ የተባለው፣ በኤርትራና በሶማሊያ ዙሪያ ያስቀመጣቸው ነጥቦች አሉ። አንዱ ኤርትራ በአካባቢዋ ያሉ አገራት መንግስታትን የሚቃወሙ የትጠቅ ትግል የሚያደርጉ ድርጅቶችን መደገፍና መርዳት እንድታቆም የሚጠይቅ ነው። ከዚህም የተነሳ ሻእቢያ፣ ፈልጎ ሳይሆን ተገዶ በኤርትራ ያሉ የትጥቅ ትግል የሚያደረጉ ተቃዋሚዎችን ሊያግድ ይችላል።

በመሆኑም በነ አቶ ኢሳያስ ላይ የተወሰነው ዉሳኔ፣ ተቀለበሰም፣ አልተቀለበሰም፣ ግንቦት ሰባትና ሌሎች አስመራ ያሉ ደርጅቶች፣ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው የወደቁት። በኤርትራ በኩል እናደርገዋለን የሚሉት ትግል መጨረሻም ሊሆን ይችላል። ወይም አቶ ኢሳያስ ለፍርድ ቀርቦ ፣ ግንቦት ሰባቶች ወዳጃችን ያሉትን በማጣት ዜሮ ይገባሉ፤ አሊያም ኢሳያስ ለራሱ ሲል፣ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር መስማማት ስላለበት ይሽጣቸዋል። በዚህም በዚያ ኤርትራ ያሉ ተቃዋሚዎች ቀለጡ ማለት ነው።

ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ለዉጥ ለማምጣት የሚደረገው ትግል፣ በምን አይነት ሁኔታ ከሻእቢያ ጋር መያያዝ የለበትም አይሉ ብዙ ሲከራከሩ የነበሩት። ሻእቢያ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደንታ የለውም። በማናቸዉም ጊዜ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከገደል ላይ ለጥቁሙ ሲል የሚፈጠፍጥ ነው። ታማኝነት ብሎ ነገር በታሪኩ አያውቅም።የኢሕዓፓ ወዳጅ ነበር፤ ወዲያው ተገልብጦ ወደ ወያኔ ሄደ። ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ከወያኔ ጋር ደመኛ ሆነ። ነገርም ግንቦት ሰባቶች እንደ ቁሻሻ ይወረወራቸዋል።

በተለይም በዳያስፖራ ብዙ ወገኖች ለግንቦት ሰባት ድጋፍ እንዳላቸው ይታወቃል። አብዛኛው የግንቦት ሰባት ደጋፊ ድጋፍ የሚሰጠው በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ተደረጎ ስለተነገረው ነው። አገሩን ከመዉደዱ፣ ለወያኔ ካለው ጥላቻ የተነሳ ነው።

ሆኖም ሕዝቡ የተነገረው ነገር ዉሸት ነው። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ እንኳን አገር ዉስጥ እንቅስቃሴ ሊያደርግ ቀርቶ፣ ከላይ ለመገልጽ እንደሞከርኩት፣ በኤርትራ መኖሩና አለመኖሩ ራሱ በትልቁ አጠያያቂ ነው የሆነው። ምናልባትም ጅማናስቲክ ሰርተው፣ አንድ ምክንያት ፈጥረው፣ “ሰራዊታችን ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። በኤርትራ ያለንን ስራ ጨርሰናል” በሚል በዚያ ያሉ በርካታ ወጣቶችን ትተው ወደ አሜሪካ ኑሯቸው ሊመለሱና በዳያስፖራ ባሉ ከተሞች “የሌለ ነገር አለ፣ ያልተደረገ ነገር ተደረገ” እያሉ ማጭበርበራቸዉን ቢቀጥሉ ብዙ መደነቅ የለብንም።

ብዙዎች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዉጥ የሚመጣው በኢትዮጵያዉያን ነው። መመካት እና ማደራጀት የሚያስፈለገው የኢትዮጵያን ህዝብ ነው። እኛዉ ኢትዮጵያዉያን በቂ ነን።

( አቶ አበበ ከአቶ ንአምን ጋር ያደረጉትን ለመስማት 36 ደቂቃ ወደ ፊት ይሂዱ – http://www.addisdimts.com/podpress_trac/web/16295/0/06-12-16.mp3

 

31 Comments on “ግንቦት ሰባት ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል – ኖአሚን በጋሻው”

  1. ግንቦት 7 ከኤርትራ አይደለም ከዲሲ ሣይባረሩ ይቀራሉ! ብላችሁ ነው?

  2. Wishoch nachu ginbot7 and niamn zeleke are fighting for Ethiopia miskin agamewoch anyways keep dreaming

  3. It is possible to criticize but you don’t have any solution.
    If ginbot7 is not in erteria where do you suggest the struggle to be?
    Addis dimitis radio become destructive no solution but criticism.
    If you want TPLF to end you should support any form of struggle, but Abebe Belew and others criticize ginbot7 without any alternative solution.
    Of course I don’t expect Elias KIFLE and Abebe Belew to have any solution they simply criticize to look like they are knowledgeable.
    Every body knows eriteria is not the best place but the only option close to Ethiopia.
    This is the only organization shakes TPLF if you love Ethiopia support G7.

  4. ቅማላም የቅማላም ልጅ!!!! እናንተ ጻፉ እኛ የምንሰራውን እየሰራን ነው። ያ ስራችን ነው እንቅልፍ የነሳችሁ፣ ግንቦት 7 ነን እዛው እስራችሁ ነው ያለነው!!

  5. Which one obligated to you to write this article a) payment of 50cents b) filling rotten belly c) to get home 40/60 d) jealous

  6. NAOMINE BEGASH- – you are a living death you are lost,you are disappointted and you have blieved in your mind woyane would not stay any more on Ethiopian soil and you have known GINBOT7 is surely coming to free Ethiopia from your masters Tplf

  7. I am sorry for your business. You are doing stupid work.you are standing against freedom stragglers. Abebe

  8. PATRIOTIC GINBOT-7 has become a nightmare to TPLF/Woyane and all Tigre accomplices. This includes Elias Kiflr, Abraha Belay and Abebe Belew. So continue with your lies, misinformation and better yet hallucination. So the best you can do at this time is to crawl back to your Dedebit where you belong. The day of reckoning is fast approaching.

    TPLF / Woyane regime is the “enemy” of the Ethiopian people – it is to bring it to the ICC by pointing to a mountain of evidence of TPLF/Woyane and Tigre accomplices for crimes against humanity, war crimes and genocide committed against the people of Ethiopia. Notwithstanding the massive violations of human rights and political repression, rigged and stolen elections, systemic corruption, economic mismanagement and the rapacious plunder of the country’s resources by a syndicate of criminals who try to palm themselves off as a legitimate “government”.

    TPLF/Woyane leadership consists of cunning, ruthless, vicious and stone-cold criminals who maintain themselves in power by force of arms only. TPLF/Woyane regime is far more brutal and cruel than the Italian Fascist army that invaded Ethiopia, and no different in its aims to completely destroy the social, economic and political fabric of the country.

    PATRIOTIC GINBOT-7 know that TPLF/Woyane will never give up power through the ballot box, only at gun point. As illustrative proof, one can cite the arrogant invitation once extended by the dead former criminal Zenawi himself to the effect that anyone who wants get rid of him must do what he did to the previous regime: Fight all the way from the bush and eject us from power.

    PATRIOTIC GINBOT-7 knows that a military victory over the TPLF/woyane would not be particularly difficult, pointing to the fact that the woyane army has been bogged down in Somalia and unable to defeat a ragtag coalition of Somali insurgents.

    Neamin, Berhanu and all other patriots – the silent majority of Ethiopians are with you. KEEP UP THE GOOD WORK!

  9. ተይ አትልፊ ማነኝ አልሺኚ አቶ ነአምን ከሻቢያ በፊት ሞቴን ያድረገዉ ሲል የነበረ አይደል? አሁን በሁለቱ ትግሬዎች መሀል ልዩነት አለ? እንዲሀ ክንዳችንን ጠምዝዛችሁ መከራችንን የምታበሉት? ግድ የለም ይህ ትዉልድ ሁለቱ ትግሬዎችና መሳሪያዎቻቸዉ እናንተ የጣላችሁበትን መጋረጃ ቀድዶ በትክክለኛ አእምሮዉ ማሰብ ሲጀምር እናንተም እንደ ጉም ትበናላችሁ።፡ከዋለልኝ ዘመን ጀምሮ ማን ሲጋልባችሁ እንደ ነበረ ጠንቅቀን እናዉቃለን ችግሩ የኢትዮጵያ ጠላቶች የድር ጥንጥን ሰርታችሁ ትደንሱብናላችሁ ለጊዜዉ ነዉ።የእኛ የሆነ ራዲዮ የእኛ የሆነ የድር ጥንጥን የእኛ የሆነ የፓል መወያያ ሲጀመር ንብ ሳይሆን ዝምብ ያደራባችሗል።

  10. የጸሐፊው ‘ቅንነት’ በጥያቄ ውስጥ ሆኖ “በኢትዮዺያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በዋነኛነት ኢትዮዺያዊያንን በማደራጀት ነው” የሚትለው አስተያየት ጥያቄ የሚነሳባት አይደለችም።ባይሆን “ኢትዮዺያዊያን”ስንል ወጥና ልሙጥ ያለመሆናችንና በርካታ ተደጋጋፊም ተቃራኒም የፖለትካ ጥያቄዎች ያለን በርካታ ብሄሮች፣ማህበረሰቦች ከመኖራቸው አንጻር “ግንቦት 7” ለሶማሌው፣ለሲዳማው፣ለኦሮሞው፣ ለሀዲያው፣ለአማራው፣ወዘተ ጥያቄዎች ምን መልስ አለው?ይህን የሚለው የወያኔን አምባገነን አገዛዝ መታገል በራሱ ግብ አይደለምና ከዚያስ በኃላ?ለሚለው ግንቦት ሰባቶች ምላሽ ቢሰጡኝ ደስ ይለኛል።

  11. ገና ዝባዝንኬህን ማንበብ ስጀምር ልክ አር እንድነካው እንጨት መሽተት ጀመረ ማነህና ነው አንተ የተባበሩት መንግስታት ስራ ውስጥ ገብተህ የምትዘባርቀው? ወያኔ መሆንክን ከማሳወቅ ባለፈ ምንም የስራሀው ነገር የለም የፖለቲካ ክህሎቱም የለህም እንዱሁ ፊደሎችን ማገጣጠም ካልሆነ በስተቀር የሻብያን እግር እያጠብክ እዚህ እንደደረስክ የዘነጋህ ይመስላል።

  12. If something goes up it must come down!!! TPLF will come down and crush to earth.How? Because the EThiopian people said enough is enough.it doesn’t matter when it doesn’t matter how, TPLF already lost grip and public trust .power to EThiopian people.

  13. Metaweq yalebt
    Neamin Zeleke
    Yenfse gedayu ina
    Ye Rapist abatu
    Col. Zeleke Beyene
    Lej ina Kassa Kebede Agotu kehonu
    Nefsegadyoch yeweta
    betley abatu be 100
    Yemiqoteru ye EPRP
    Wetatochin yechefechefe Aremenaye lej min
    yetebqal. Bemulu yetachequt agerbet
    yemayimelsu personal case yalebachw nachew.

  14. Inie yemaznew Berhanu Bonger idmie lekun sltan
    indgomje. Ke Kineget jemero. Mayor lemebal indasefese fese weshimetu tebetso
    chirash beiser mako
    ye Woyanen iger leso beadebabay yiqerta teyqo weta.
    — Baldkemebt Asmera bemehied
    Field Marshall likon tasbo thanks to Molla Asgedom
    ahunm weshemetun beteslin. Ahunma beafu zenib yegbabetal.
    “KAFERKU AYMELESGNE”
    AY GIM -7 Irasu ye
    Shabia Barria huno
    arefew ?
    Thanks to the true
    Sons and daughters
    Of Ethiopia.
    Among those who exposed that Shabia is an enemy of Ethiopia were:
    The forefront fighter Elias Kefele, Abebe Bellew, Birhanu Damte ( Aba Mela )
    Demis Belete . etc
    from Main steam Media the famous Radio Diaspora the most trusted,
    Hager fiker , Tsnat
    Radio ,Selam Radio
    Leyou Radio and the
    Famous T. G Television that trashed Gim -7 for
    once and for all in
    exposing those Mercenaries by name
    in front of the Camera. We Ethiopians are very great full for letting us to know more about the Slave Master ISIS
    AFEWORKI and the vulnerable Gim -7
    Slaves.

  15. እናንተ ወያኔዎች ግንቦት 7 እንካን ኢትዮጵያ ይቅርና እየቤታችሁ ውስጥ ሳይቀር አለ።

  16. Ye weyane wishoch tenichachu be ze-habesha lai yared yemebali wisha
    yikebatiral.Ato Anidarigachew Tsige ke meyazu befit besu lai yisef
    nebere ahun degimo be Ato Neamin Zeleke lai tenesitual libe belu
    betikekil ke weyanne gare yemeseru yalew new yememesilew bicha
    ye weyanne wishoch betam tenesitewl ahun Noame Begashawe tikile new
    yesafeciw enem huletunem radio semichalehu lemin wishochu chohu?

  17. We will never believe woyane dogs.
    Ato Neamin is a person who knows what to talk not how this woyane buchila has tried to draw him.
    The last days are coming and woyane is jerking to die like a sheep, whose neck is cut off.

    Victory to the Ethiopian and Eritrean people

  18. ሰልፍ የወጡት ዜጎች እነማን ናቸው ማን ነበሩ ከየት መጡ ማን አመጣቸው የሃገሪቱን ዜጎች ማለት ኢትዮጵያዊያንን አትኖሩም፣አትሰሩም፣አትሰለፉም፣አትናገሩም፣አትጽፉም፣
    ወያኔ ምን አሰቦ ነው ትናንት ወደሃገራችሁ ሂዱ ብሎ ያባረራቸው ኤርትራዊያን ዛሬ ኑ ሰልፍ ውጡ ተቃወሙ
    ወያኔ አላማው ምንድን ነው እውነት ወያኔ ኢትዮጵያን ነው ለሃገር አስቦ ሳይሆን ድብቅ አጀምዳውን ኢትዮጵያን ለማዳከምና የበላይነቱንና ትግራይ ርፓብሊክ ለመመስረት እንዳመቸው ነው! ምን ጊዜም ወያኔ ለኢትዮጵያ ተኝቶ አያውቅም፡፡
    ሳሚ

  19. Gim Mot 7 is anti Ethiopia

    Birhnu ena Naomi ye shabya Qetregnoch

    Ethiopian kemeshet aymelesum

    tirf kametach kkkkkkkkk

  20. Hi dear countryman ቅማላምየቅማላምልጅ this is really from bad mouth thrown to your own likeness brother. It is shame to throw bad words against your own brother.Try to convince him through dialogue tell him why the tplf is BAD to the people of Ehiopia, why tplf does not represent ethiopians,tell tplf is an ethnic based back ward narrow nationalist and who suffer from inferiority complex.t\
    Tell people Tplf hijacked the revolution of the ethiopian students and the people of ethiopia. There are tons of reasons to convince people the curren rigime of Ethiopia is backed by westerners who hate ethiopia.
    Any way whatever differeces we have among us let us respect each other if we do this we are practicing democracy,

  21. Derom gimatam yetbalut lezieh neaw .
    inkuwoan Ethiopia Shabiam yabarerachwal
    kezih befit be Ethiopia tarik yaltaye
    be banda yetmola ye Ginbot 7 Sebesb becha
    neaw . ine EPRP indanebru.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*