የቀድሞ አንድነት ም/ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ፕሬዚዳንት የነበሩትአቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ ብሩ ዲሞክራሲና ፍትህ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ሲታገሉ የነበሩ፣ በ1997ዓ.ም ከሌሎች የትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ቅንጅትን ወክለው የተወካዮች ም/ቤት አባል በመሆን የበኩላቸውን የተወጡ፣ እንዲሁም አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሲመሰረትም ከመሥራቾቹ አንዱ በመሆን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አቶ ብሩ ቢርመጂ ለነፃነት ለፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን የበኩላቸውን ሲወጡ የነበሩ ጠንካራ ታጋይ ነበሩ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለፍትህና ዲሞክራሲ ታጋይ ጉዋደኞቻቸው መጽናናትን ይስጣችሁ፡፡

የአቶ ብሩ ቢርመጅ የቀብር ስነስርዓት የሚፈፀመው ዛሬ ሰኔ 15/2008 ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መሆኑ መረጃው ለሌላቸው በማካፈል ተባበሩ፡፡ መኖሪያ ቤታቸው ገርጂ አካባቢ ወደ ፓርላማ ቤቶች መውረጃ በስተግራ በኩል በሚያስገበው መንገድ ሲሆን የቀበር ስዓቱም ዘጠኝ ሰዓት መሆኑ ከቤተሰቦች ተነግሯል፡፡ አስከሬኑ ከትግራይ ዛሬ ጠዋት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

3 Comments on “የቀድሞ አንድነት ም/ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ብሩ ቢርመጂ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡”

  1. ቤተሰቦቹንና መላዉን የፍትህ ታጋይ መፅናናቱን ይስጥልን

  2. እግዚአብሔር ነፍስዎትን ይማር፤ ለቤተ-ሰቦችዎና ለወዳጆችዎም መፅናናትን ይስጣቸው!!

  3. ለአቶ ብሩ በርመጅ ነፍሳቸውን ይማር እያልኩ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ። አቶ ብሩ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል በመሆን አገልግሎት የሰጡና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጠንካራ አቋም የነበራቸው ሰው ነበሩ። አቶ ብሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ1980 ዓ.ም. በባችለር ዲግሪ ተመርቀዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበሩበት ጊዜ አቶ ብሩ በገንጣይ፣ አስገንጣይና ለሌችም ጎጠኛ ቡድኖች ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ መሆናቸውንና በተለይም የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ጠባብ ቡድኖች ያራግቡት የነበረውን የተሳሳተና ከእውነታው የራቀ ፕሮፓጋንዳ አበክረው ሲቃወሙ የነበሩና ለአንድነትና ለእኩልነት መገነጣጠል መፍትሄ አለመሆኑን አበክረው ሲከራከሩ የነበሩ መሆናቸን አብረዋቸው በዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ይናገራሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*