በሲኖዶስ የጳጳሳት ሹመት ላይ የተነሡ ተቃውሞዎች ሲፈተሹ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሲኖዶስ ብየ ስል “የትኛውን?” የሚል አይጠፋም፡፡ በአንድ ሀገር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊኖር የሚችለው አንድ ሲኖዶስ ነው ሁለት ሲኖዶስ የለም፡፡ ሲኖዶስ ይሰደዳል ወይ?፣ እዚህ ሀገር ቤት ያሉትም ሲኖዶስ ነን ይላሉና የትኛው ነው ትክክለኛና እግዚአብሔር የሚቀበለው? ፣ ፓትርያርኩና ጳጳሳቱ መሰደድ ነበረባቸው ወይ? ስደታቸው ከወንጌልና ከሕገ ቤተክርስቲያን አኳያ ትክክልና የሚገባ ነው ወይ? ለሚሉ ጥያቄዎች ከተፈጠሩ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ ወንጌልንና ሕገ ቤተክርስቲያን እየጠቀስኩ ትክክል መሆኑን ከዚህ ቀደም በሚገባ መልስ ሰጥቸበታለሁና አሁን ወደዚያው አልመለስም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በስደት አሜሪካን ሀገር ያለው ነው፡፡ እዚህ ያሉት በእሱ ስር ሆነው በቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ (እያገለገሉ ከሆነ) አሜሪካ ያለው ሲኖዶስ አካል ናቸው እንጅ በራሳቸው ሲኖዶስ አይደሉም፡፡ ሰሞኑን ይህ በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ 6 ጳጳሳትን ከመሾሙ ጋር ተያይዞ ከያቅጣጫው ተቃውሞዎች ሲነሡ ነበር፡፡ እጅግ የገረመኝ ነገር ብዙዎቹ የዚህ የሲኖዶሱ ሹመት ተቺ ተቃዋሚዎች እዚህ ሀገር ቤት ያለአግባብና ያለ ቀኖና ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ነን ያሉት በወያኔ ታንቆ የተያዘው የጳጳሳት ቡድን የተጣለበትን ኃላፊነትና አደራ ባለመወጣት ቤተክርስቲያንን ለወያኔ ሸጦ የወያኔ መጫዎቻ መቀለጃ ሲያደርጋት፣ ዳግም ልታገኛው የማትችላቸውን በርካታ ጥቅሞቿን እንድታጣ ስትደረግ፣ መንጋዋ በገፍ ተበልቶባት ባዶዋን ስትቀር፣ ሥርዓቷ ቀኖናዋ ሕግጋቷ አልፎም ዶግማዋ ሲጣስ ሲሻር ሲፈርስባት በዝምታ ከመመልከት ውጭ ምንም ማድረግ ያልቻለ መሆኑን እያየ ትንፍሽ ብሎ የማያውቀው ሁሉ እየተነሣ በንዴት ጦፎ የማይገባ የነገር ዱላውን እየመዘዘ ምንም ባልገባው ጉዳይ ላይ የጳጳሳቱን ሹመት ሲቃወምና ሲያወግዝ ሳይ እጅግ ነው የገረመኝ፡፡ ብዙዎቹን ከሁኔታቸው እንደታዘብኳቸው ከወያኔ ቅጥረኝነታቸው የተነሣ ነው ያሉትን ሁሉ ሲሉ የነበረው፡፡ ስለሚናገሩት ነገር ሳያውቁ አግባብነት የሌለው ልፍለፋ ለመለፍለፍ አደባባይ ሲወጡ ሰው ይታዘበናል አለማለታቸው ግን በእጅጉ ገርሞኛል፡፡ እነኝህ ግለሰቦች ከጠቃቀሷቸው የተቃውሞ ምክንያቶቻቸው ዋናዎቹም፡-
  1. ሹመቱ ተገቢ አይደለም
  2. መናፍቅ ተሹሟል
  3. ካንድ መንደርና ቤተሰብ ብቻ የተውጣጡ ናቸው፡፡ የሚሉ ናቸው፡፡ እነኝህ ተቃውሞ ትችቶች ስላላቸው ተጨባጭነት እያንዳንዳቸውን እንመልከት፡-
ሹመቱ ተገቢ አይደለም፡- ይሄንን የሚሉ ሰዎች ለዚህ ተቃውሞ ምክንያት ሲጠየቁ የሚመልሱት “በቤተክርስቲያን ላይ ያለውን መከፈል ዘላቂ እንዲሆን ያደርገዋልና እርቅ ነው እንጅ መፈጠር ያለበት ክፍፍሉን ቋሚ ሊያደርግ የሚችል ተግባር አይደለም” የሚል ነው፡፡ ይሁንና እነኝህ ወገኖች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግን አጢነው መረዳት ያለባቸውን ነገር መረዳት አልቻሉም፡፡ ዝምብሎ በምኞት የሚሆን ነገር የለም፡፡ ይሄንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ? ተብሎ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም እዚህ ሀገር ቤት ያሉቱ ሊቃነ ጳጳሳት ይሄንን የእርቅ ሒደት ለመፈጸም በሚደክሙበት ጊዜ በወያኔ ከጥተኛ ጣልቃ ገብነት እርቁ እንዲቋረጥ በመደረጉና አሁን ደግሞ ወደፊት እንዳያስኬዱት በወያኔ ስለተከለከሉ ስለታገዱና “ይሄንን እርቅ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ቄሶችን እንሰቅላለን!” የሚል ከባድ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ከወያኔ ባለሥልጣናት ዘንድ ስለተሰነዘረባቸው እነኝህ ጳጳሳት ድፍረት አግኝተው እውነትንና ቀኖና ቤተክርስቲያንን መሠረት ባደረገና በጠበቀ መልኩ እርቁ እንዲፈጸም ማድረግ የሚችሉበትን ዕድል ባላገኙበት ቁርጠኝነቱም በታጣበት ሁኔታና ወያኔ እስካለ ጊዜ ድረስም ይህ ጉዳይ ሊፈጸም የማይችል በሆነበት ሁኔታ የሚፈለገው እርቅ እንዲፈጸም መጠየቅ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያላስገባ ባዶ የየዋሀን ምኞት ከመሆን የሚዘል አይሆንም፡፡ “ሲኖዶስ ወያኔ እስኪወድቅ ድረስ ዝም ብሎ ይጠብቅ” እንዳይባልም የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚጎዳ ሆነ፡፡ ቤተክርስቲያን አገልግሎቷን ለማስፋት፣ ለማጠናከር፣ ለማሟላትና ለማሳለጥ የኤጲስ ቆጶሳቱና የጳጳሳቱ ሹመት የግድ አስፈላጊ ሆነ፡፡ በመሆኑም ሹመቱ መፈጸም ነበረበትና ሊፈጸም ቻለ፡፡ ስለዚህም ይሄንን ነጥብ በማንሣት በዚህ ጉዳይ ላይ የተነሣው ተቃውሞ ብስለት ቅንነትና ሙሉ ግንዛቤ የጎደለው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሁለተኛው የተቃውሞ ነጥብ “በዚህ ሹመት ላይ መናፍቅ ተሸመዋል” የሚለው ነው፡፡ በእርግጥ ግን መናፍቅ ተካቷል ወይ? ብለን ስንጠይቅ መናፍቅ በተባሉ መነኩሴ ላይ የቀረቡ መረጃዎች በእጅጉ የዕውቀትና የግንዛቤ ማነስ ጎልቶ የሚታይባቸው በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረቱ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ መናፍቅ በተባሉት በአባ ወልደትንሣኤ ላይ ቀረቡ የተባሉትን ክሶች እንይ፡- አባ ወልደ ትንሣኤ አሳማ ይበላል ብለው ይሰብካሉ፣ በኦርጋን ያስጨፍራሉ፣ ሰንበቴን በቢራና በውስኪ እንዲወጣ ፈቅደዋል የሚሉ ናቸው፡፡ እስኪ እያንዳንዳቸውን ክሶች ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር እንያቸው፡- በእርግጥ ግን አሳማ ይበላል? ይሄንንስ አባ ወልደትንሣኤ ብለዋል ወይ? ከተባለ አባ ወልደትንሣኤ አሳማን ብቻ ሳይሆን አይጡንም ጉርጡንም እባቡንም ፈረሱንም ውሻውንም ሁሉንም ነገር ይበላል እንደሚሉ እገምታለሁ፡፡ ይሄንን በማለታቸው ግን መናፍቅ የሚሏቸው ሰዎች ካሉ በአብነት ትምህርትቤቶች በመጽሐፍ ቤትና በቅኔ ቤት የሚሰጠውን የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ጨርሶ የማያውቁ እንደሆኑ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሄ ማለት ግን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እነኝህን እርኩስ ነገሮች እንዲበሉ ትሰብካለች ታበረታታለች ማለት አይደለም፡፡ የመልእክታተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት ስታስተምር ይሄንን ትምህርት የግድ ማስተማር ስላለባት እንጅ፡፡ ከገማልያል ስር የተማረው ሳውል (ጳውሎስ) እነኝህ እንስሳት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እርኩስና የማይበሉ መሆናቸውን እያወቀ ዘሌ. 11፤1-47 ዘዳ. 14፤4-21 እንዴት “በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና” 1ኛ. ቆሮ. 10፤25 በማለት ያስተምራል? ከተባለ “…እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥ ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ” 1ኛ. ቆሮ. 10፤31-33 በማለት ይሄንን የሚያደርገው ክርስትና የሚሰበክላቸው አሕዛብ፣ አረማውያንና ኢአማንያን የለመዱትንና የሚወዱትን ነገር ሲከለከሉ ወንጌልን ከመቀበል ወደ ኋላ እንዳይሉ፣ ሁሉም እንዲድን ካለው ጉጉትና ስስት የተነሣ እንደሆነ ይነግረናል፡፡  ልብ በሉ ይህ የተደረገው ትምህርቱና ባሕሉ ስለሌላቸው፤ እንግዶች ስለሆኑት ስለ አሕዛብ አረማዊያንና ኢአማንያን ሲባል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሁሉም በክርስቶስ አምኖ ይድን ዘንድ ከመሻቱ የተነሣ “በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና” ሲል ግን “አትብሏቸው ያረክሳሉ” ብሎ የከለከለው እሱ እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ዘሌ. 11፤1-47 ዘዳ. 14፤4-21 አውቆ ዘንግቷል፡፡ ምን ያድርግ? ቢቸግረው ነው፡፡ ነገር ግን “የጌታ ነውና” በሚለውማ ከሔድን ሰይጣንስ ቢሆን የሱ አይደል? ሌላ ፈጣሪ የለ! እንግዲህ ጳውሎስን ከሐዋርያቱ ሁሉ ለየት የሚያደርገውም ይሄ ድፍረት የተሞላበት አኪያሔዱ ነው፡፡ በዚህ አኪያሔዱ የተነሣ ከሐዋርያት ጋር እስከመጣላት የደረሰበት ወቅትም ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ቅዱስ ጳውሎስ ይጠቅማሉ ይበጃሉ ከሚል ቀና አስተሳሰብ አንዳንድ ወጣ ያሉና የተለዩ ትምህርቶችን ሰጥቶ ሲያበቃ ግን “…እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም!” 1ኛ ቆሮ. 7፤12 “…የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥ ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ ከጌታ ምሕረትን የተቀበልሁ እንደ መሆኔ ምክር እመክራለሁ፡፡ እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር መልካም ነው” 1ኛ ቆሮ. 7፤25 በማለት መደናገር እንዳይፈጠር ያስጠነቅቃል፡፡ ይሄንን ሲያደርግ በጎ አስቦ ነውና በእግዚአብሔር ዘንድ በደል እንደማይሆንበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይሄ ድርጊቱ የሚያሳየን ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር ምንድን ነው? ለካህናት የተሰጣቸው ሥልጣን ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡“እውነት እላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል” ማቴ. 18፤18 ይላልና፡፡ ኃጢአት ስለሠራ ኃጢአተኛ የሆነንና እንደ የእግዚአብሔር ቃልም ለኩነኔ ሊዳረግ የነበረ ሰው ካህኑ ስለፈታው ብቻ በሰማይም የተፈታ ወይም የጸደቀ ይሆናል፡፡ ይሄንን ያህል ነው ሥልጣናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የተጠቀመው ይሄንን ሥልጣን ነው፡፡ አባ ወልደትንሣኤ የአሁኑ አቡነ በርናባስ የሐዋርያው ጳውሎስን መንገድ የተከተሉ እየመሰላቸው የሚያደርጉትን ነገር እንደሚያደርጉ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መረዳት ይቻላል፡፡ ያልተረዱት ነገር ቢኖር ቅዱስ ጳውሎስ ያንን ያደረገው ጥቅም ቀርቶባቸው፣ ቁስልን ተሰቅቀው ወንጌልን ከመቀበል በክርስቶስ ከማመን ወደ ኋላ እንዳይሉ ባሕሉ ላልነበራቸው፣ አስተምህሮው ለሌላቸው ለአሕዛብ ለአረማዊያንና ለኢአማንያን እንጅ ይሄንን በማስተማሩ ለተቃወሙት አስተምህሮው ባሕሉ ለነበራቸው አይሁዶች ወይም ኦሪትን ለተቀበሉ አለመሆኑን ነው፡፡ ሁሉቱ ሰፊ መሠረታዊ ልዩነቶች አሏቸው፡፡ በየትኛውም መንገድ፣ ባሕል፣ አስተሳሰብና አስተምህሮ ቢሆን በኩርና ተከታይ፣ ብዙ የደከመ ባለመቶና በመጠኑ የደከመ ባለ ሠላሳ ወይም ምንም የሌለው እኩል ሊታዩ ሊመዘኑ ሊገመቱ የሚችሉበት አግባብና አሠራር የለም፡፡ አባ ወልደትንሣኤ ወይም አቡነ በርናባስ የሳቱት ይሄንን ነው፡፡ አባ ወልደትንሣኤ የቅዱስ ጳውሎስን አስተምህሮ ለነማን መስበክ እንዳለባቸው አላወቁም፡፡ ለነማን? መቸ? ለምንና እንዴት? ሳይሉ ዝም ብለው እንደወረደ ነው እያስተማሩት ያለው፡፡ ይሄ ደግሞ ስሕተት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳንስ አማኙ አረማዊውና አሕዛቡ እንኳ አሳማውን ፈረሱን፣ አይጡን ጉርጡን፣ እባቡን ውሻውን የመብላት ባሕል የለውም፡፡ ይሄ ባሕል ለሌለውና ለሚጸየፈው ብሉ ብሎ ማስተማር ቅዱስ ጳውሎስ ጌታ የሞተለትን ከማሰናክል በማለት“…ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም” 1ኛ ቆሮ. 8፤13 በማለት እጅግ የተጠነቀቀለትን ምስጢር አለማወቅ ነው፡፡ አባ ወልደትንሣኤ በዚህ አስተምህሯቸው ምክንያት ለተሰናከሉባቸው ነፍሳት የሚጠየቁ መሆናቸውን የማያውቁ ከሆነ ምንም የገባቸው ነገር የለም፡፡ ወደ ተከታዩ ክሳቸው ስንሔድ “በኦርጋን ያስጨፍራሉ” የሚለው ነው፡፡ አዎ በእርግጥ እሳቸው ይሄንን ያደርጋሉ፡፡ ይሄንን የሚያደርጉት ደግሞ “እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን!” የሚለውን ቃል አሳስተው ተርጉመው በመረዳታቸው ነው፡፡ “እስትንፋስ ያለው ሁሉ” ማለት ድምፅ የሚሰጥ ነገር ሁሉ ማለት መስሏቸዋል፡፡ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ማለት ሕይዎት ያለው ነገር ሁሉ ማለት እንጅ ሲመታ ድምፅ የሚሰጥ ግኡዝ ነገር ሁሉ ማለት አይደለም፡፡ እሳቸው ያልተባለውን በተሳሳተ አረዳድ እንደተባለ ቆጥረው ሥጋዊ የዘፈን ፈቃድንና ስሜትን ለማርካት የዘፈን መሣሪያዎችን ሁሉ እያንጫጩ ለመጠቀም መሞከር በእውነት እግዚአብሔርን አለመፍራትና አለማፈር ነው፡፡ ይሁንና አባ ወልደትንሳኤ ይሄንን በማድረጋቸው የምእራቡ ዓለም የዜማ ባሕል ምርኮኛ ወይም ዳንኪረኛ ናቸው ሊያሰኛቸው ቢችል እንጅ መናፍቅ ሊያሰኛቸው አይገባም፡፡ ምክንያቱም የአኃት (እኅቶች) አብያተክርስቲያናት የመዝሙር መሣሪያም ይሄው ነውና፡፡ ኦርጋን የአኃት አብያተክርስቲያናት የመዝሙር መሣሪያ ነው ስል ግን እኛም ኦርጋንን በመዝሙር መሣሪያነት እንቀበለው እንጠቀምበት እያልኩ አይደለም፡፡ መሆንም የለበትም፡፡ ከአኃት (ከግብጽ፣ ከአርመን፣ ከሶሪያ፣ ከህንድ) አብያተክርስቲያናት ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ በሥርዓትና ቀኖና ጉዳዮች ላይም እንኳ ሰፊ ልዩነቶች እንዳሉን መገንዘብ ይገባል፡፡ እነሱ የሐዲስ ኪዳን ልጆች እንደመሆናቸውና በኦሪቱ ዘመን እግዚአብሔርን አለማወቃቸው በኦሪት ሥርዓት እግዚአብሔርን አለማምለካቸው ለልዩነቱ መፈጠር ዐቢይ ምክንያት ነው፡፡ በመሆኑም አኃት አብያተክርስቲያናት እኛ በብሉይ ኪዳንም እግዚአብሔርን አምላኪዎች በመሆናችን ያሉን ጠቃሚና አስፈላጊ አገልግሎቶች፣ ሥርዓትና ሃይማኖታዊ ባሕሎች እነሱ የሏቸውም፡፡ ጉዳዩ እንዲያውም ከዚህም አልፎ እኛ ነባር እግዚአብሔርን አማኝ አምላኪ እነሱ አዲስ እንግዶች ከመሆናቸው የተነሣ ዶግማዊ ሊባል የሚችል ልዩነት የሚታይበት ሁኔታም አለ፡፡ ለምሳሌ እኛ ጽላትና ታቦት አለን፡፡ የጽላትና የታቦት አገልግሎት ለእኛ ቤተክርስቲያን ሊቀር ሊለወጥ ሊሻሻል የማይችል ዶግማ (አምደ እምነት) ነው፡፡ እነሱ ግን በስውራን ቅዱሳኖቻቸው ዘንድ ካልሆነ በስተቀር ጽላትና ታቦት የላቸውም፡፡ ከዚህም የተነሣ “ከስሩ ከመሠረቱ እንዴት ነው?” የሚያሰኝ ሥርዓት ወይም ጥያቄ በሚያስነሡ ጉዳዮች ላይ ያላቸውና የሚከተሉት ሥርዓት አስተምህሮና ሃይማኖታዊ ባሕል እንደመሰላቸው በዘፈቀደ የሚደረግ ከመሆኑ የተነሣ ብዙ ጊዜ የተሳሳተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህም ምክንያት “እነሱ ዘንድ እንዲህ ይደረጋልና እኛም ዘንድ እንዲህ ብናደርግ ችግር የለውም! ወይም ማድረግ ይኖርብናል!” ልንል የምንችልበት አግባብ አይኖርም፡፡ እነ አባ ወልደትንሣኤ ይሄንን ቁምነገር ነው የሳቱት፡፡ እናም የዚህ ኦርጋን የተባለው የዜማ መሣሪያ ጉዳይ እንዲያ ነው፡፡ በኦርጋን ዙሪያ ስላለው ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ባሕልና አስተምህሮ አንጻር ያለውን አጠቃላይ ጉዳይ “እውን ኦርጋን የመዝሙር መሣሪያ ነውን?” በሚል ርእስ ከጻፍኩት ጽሑፍ መረዳት ይቻላልና ይሄንን ይዝ (ሊንክ) ተጭነው ይረዱ፡፡ http://www.satenaw.com/amharic/archives/13054 ሌላኛው ክስ ደግሞ “አባ ወልደትንሣኤ ሰንበቴን በቢራና በውስኪ እንዲወጣ ፈቅደዋል” የሚለው ነው፡፡ እንደ ይሄንን ክስ ያቀረቡ ምእመናን ግንዛቤ ሰንበቴም ሆነ ማኅበር የሚወጣው በጠላና በእንጀራ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ባለ መጠጥና ምግብ እንዳይደረግ በሕግ የተደነገገ ይመስላቸዋል፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ሕግና ድንጋጌ የሌለውና በተገኘው ነገር ሊፈጸም የሚችለው ብዙው ነገር ሁሉ እነሱ ከሚያውቁት በተለየ መንገድ ሲደረግ ሲያዩ ያ ለእነሱ ኑፋቄ ወይም ክህደት ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህን ወገኖች ለዚህ የተሳሳተ ድምዳሜና ፍረጃ የሚዳርጋቸው አለማወቃቸው ነውና ተቆርቋሪነታቸውን ልናደንቅ የሚገባ ቢሆንም ይሄንን ተቆርቋሪነት ከቤተክርስቲያናችን ቀኖና ሥርዓት ሕግና ድንጋጌ አኳያ እያዩ እንዲያደርጉት እየመከርኩ ስሕተታቸውን በክፋት ሳንመለከት ማለፍ ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በቀላል በተሳሳተ ግንዛቤ የሰው ስም መጥፋቱና መሰበሩ ለእነሱም ቢሆን ዕዳ በደል ነውና የሚሆንባቸው በዚህ ስሕተታቸው ሊሰማቸውና ሊጠነቀቁም ይገባል፡፡ ንስሐም መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ እና እንግዲህ አባ ወ/ትንሣኤን በመናፍቅነት ያስከሰሷቸውና የማውቃቸው እነኝህና ክሶቹም ተገቢ ያልሆኑ ናቸው፡፡ አባ ወ/ትንሣኤ ሌላ ዶግማን በተመለከተ ኑፋቄ እንዳለባቸው ወይም እንዲህ ብለው የተሳሳተና ኑፋቄ ሲያስተምሩ ሰምቻለሁ የሚል ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ እናም አባ ወልደትንሳኤ ከላይ የጠቀስኳቸው ሊያስተካክሏቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ሥልጣኑ ይገባቸዋል ስም ማጥፋቱ ተገቢ አይደለም እላለሁ፡፡ የኑፋቄ ጉዳይ ከተነሣ ግን አሁን ላይ በጵጵስና እንዳሉና እራሴን ምስክር አድርጌ በልጅነቴ ያየሁትንና የሰማሁትን በመጥቀስ በመናፍቅነት የከሰስኳቸው አቡነ ዮሐንስ ጉዳይ ቢጣራ መልካም ነው፡፡ ከኑፋቄያቸው ተመልሰው ከሆነ ለጵጵስና የበቁት እሰየው ነው፡፡ በእርግጥ አንድ ያጠፋ የተሳሳተ ሰው ንስሐ ገብቶ ሊመለስ የሚችልበት ሁኔታ ስላለ ያን ስሕተቱን አሁንም እየፈጸመ መሆኑ ካልታወቀና ካልታየ በስተቀር ቀድሞ በፈጸመው ስሕተት አሁንም መውቀስ መክሰስ ስሕተት ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ነው እንዲጣራ መጠየቄ፡፡ እንዲያው ልዑል እግዚአብሔር የማይመከሩ የማይገሰጹ የማይመለሱ እንደሆን እኒያን ሽማግሌ የዓለም ስማቸውን ባውቀው በዚያው ብጠራቸው ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር አቡነ መልከጸዴቅ የሚባሉትን ማለቴ ነው በቶሎ ንቅል አድርጎ ይውሰድልን እንጅ እሳቸው የሚሠሩት ሥራ ቤተክርስቲያንን እጅግ እያወከ ነው፡፡ ወደ ሦስተኛው ነጥብ ማለትም “ካንድ መንደርና ቤተሰብ ብቻ የተውጣጡ ናቸው” ወደሚለው ስናልፍ፡- መቸም ነገሮችን ማጋነንና ፈጥሮ ማውራት የሐሰተኛ ሰው ልማድ ነውና ልማድ ሆኖባቸው ካንድ ቤተሰብና መንደር የወጡ አደረጓቸው እንጅ እነሱስ አይደሉም፡፡ ከአንድ ክፍለ ሀገር ናቸው ቢሉ ግን ትክክል ናቸው፡፡ እሱም ቢሆን እንዲህ ሊሆን የቻለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ጎንደሬ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ወገንተኝነት እየተሰማቸው ከእሳቸው ጋር ማበር መሰለፍ በወያኔ ዘንድ በጠላትነት ማስፈረጁን ሳይፈሩና ሳያፍሩ እየተቀላቀሏቸው ያሉት ካህናት ጎንደሬዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ሌሎቹ ወያኔን እየፈሩ የማይቀላቀሏቸው ሆነ እንዴት ይደረግ ታዲያ? ምናልባት ግን ሲኖዶሱ የወያኔ ቅጥረኛ ያልሆነ፣ አሳልፎ የማይሰጣቸውንና የሚታመንን ሰው ሲፈልጉ የግድ የሚያውቁትንና የሚቀርቡትን ሰው ለመሾም ተገደው ከሆነና በዚህም ምክንያት የአንድ አካባቢ ሰዎችን የሚሰበስቡ ዘረኞች መስለው ታይተው ከሆነ ለዚህ ችግር ተጠያቂው የዘረኝነትን ከል ቤተክርስቲያን ላይ የጫነባት የመረዛት ወያኔ እንጅ ሲኖዶስ ሊሆን አይችልምና በዚህ ጉዳይ ላይ ሲኖዶስን እየከሰሳቹህ ያላቹህት ወገኖች ልብ ግዙ እላለሁ፡፡ ልዑል እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን ጋኔን ወያኔን አጥፍቶ፣ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና ደኅንነት መልሶ፣ ቤተክርስቲያን ወያኔ ካመጣባት ደዌ ተፈውሳ ለማየት ያብቃን አሜን!!! ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው [email protected]      

19 Comments on “በሲኖዶስ የጳጳሳት ሹመት ላይ የተነሡ ተቃውሞዎች ሲፈተሹ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)”

  1. ማንኛውም ክህን አለማዊ ትምህርት ቢማረ ቢመራመር ተምሯል ለማገናዘብ ለስጋው ተብሎ ነው የሚነገርለት እንጂ ከላይ እስከ ታች የሉት የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ እና እውቀት በሙሉ አባቶቻችን እግር ስር ቁጭ ብለን የተማርናት ትምህርት አይቀየርም። ዶግማ እና ቀኖናውን መቀየርም ሆነ ጥቅስ እየጠቀሱ አሁን የነቃውን የኦርቶዶክስ አማኝን በድጋሚ መሸወድ አይቻልም። ዱሮ ከህኑ ትክክለኛ ስለነበረ እንደዚህ ስተት የምትስሩ ከሆነ አውግዣለሁ ይሉ ነበር። አሁን አሰመሳዪች ሰርፀው በሐይማኖቱ ውስጥ ስለገቡ ቢያወግዝ እንኳን አሰመሳዬቹ ከእነሱ ጋር ዲያቢሎስ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ሰለሌላቸው፣ ለማውገዝ ቢሞክሩ እንኳን ማንም አይቀበለም።
    እራሳችሁን ምርምሩ እኛ የእናንተን ሐጥአት ማመላለስ አንፈልግም ቀና ብላችሁ ወደ ፈጣሪያችን ተመልከት። ለማን ማድላት ይበልጣል ለነፍስ ወይስ ለነዋየ ስጋ?
    Watch ከቻላቹ?
    https://youtu.be/SOKcPeAux-M

    [Reply]

  2. Holy Synod in exile capable and strong challenger of Woyana formation Synod in 4kio ! They have the legitimate patriarch they are doing great job, they are still defending firmly their own right ! I admired them. Long leave our fathers. They are not divided like MEHAD,KINJITES, such and such meaningless political party achieved nothing for the last 25years. Holy Synod in exile recognised in American congress sill they are claiming theirs legitimacy based on the church Constitution, At least very good lesson that the which ever government no more involved on the church matter, no more killing the holy father and appointed their own supporter, it is a good lesson for Ethiopian Orthodox Tewahedo church. how our father strong enough to challenge woyane made up synod in 4kio!!

  3. … “እግዚአብሔር እንደ ሰው አይቸኩልም። ዝምታውም ነገሮችን ፈቅዶና ወድዶ የመቀበሉ ምልክት አይደለም። ወደ አሜሪካ ያሉት “አባቶች”፣ በቤተ ክርስቲያናችንና በሕዝባችን ላይ እየፈጸሙት ያሉትን ግፍ የቤተ ክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ያያል። አይቶም ዝም አይልም፤ ይፈርዳል። ርስቱና ጉልቱ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን የነኩ የተዳፈሩ ኹሉ የት ነው ያሉት? የቆዩትንስ ትውልዱ በምን ታሪካቸው ነው ዛሬ የሚያስታውሳቸው? እኛም ከቅዱስ ዳዊት ጋር በአንድነት፣ “አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትኽ ቤትኽ ገቡ፤ ርስትኽንም አረከስዋት“ እያልን እናለቅሳለን። እርሱም ልመናችንን ይሰማናል። ከሥጋዊ ከደማዊ አእምሮ በራቀ ሕሊናም እንባችንን ወደ እርሱ እናፈሳለን። እርሱም እንባችንን ያብስልናል። እግዚአብሔር ሆይ፣ በምሕረትኽ አስበን፤ ወደ ጽድቅኽም መልሰን፤ ፍርድንም ለሕዝብኽና ለቤትኽ ስጥ። አሜን።”

  4. ወይ ጉድ ኦርቶዶክስ መቀለጃ ሆነች።
    የውጭ አባቶች ሁሉም ጰጰስ መሆን አለባቸው ተባለ አፈቸወን የሚያሾሉ አንዳንድ ታሐድሶ የኦርጋን እና አርጋኖ አፍቃሪ እና የስድብ መንፈስ ዲያቢሎስ ያጠመቃቸው ከጎንደር ብቻ ተሾሙ።
    አገራችን በጣም ችግረ ላይ ነች ለአንድነታችን የወጭ ሰኔዶስ ብዙ አስተዎፀዎኦ መዳረግ ነበረበት። ህዝቡ አያለ ያለው የአባቶቻችን ተወፈት፣ቀኖና፣ዶግማ አትቀይሩ ፣ ኦርጋን ለዘፈን እንጂ አውጡ ከቤተክርስትያን እንዲሁም አንዳንዶቹ በራሳቸው ፍልስፍና ወደ ተሐድሶ ጎዳና ላይ ናቸው ለምን አስፈለገ የአባቶቻችን ደም እና የክርስቶስ ደም ይረሳል ወይ? ከህዝቡ ጋር መድረክ ከፈታቹ ተወያዮ። የጎንደር ክርስቲያኑ ስትሳሳቱ አይነግሯቹም። በክርስትና ሰው ወደ ገሃነም እየሄደ ካለ ተሳስተሀል ገነት ይሻላል ብሎ ግልፅ መነጋገር ትልቅ አስፈላጊ ነው።
    የአገር ውስጥ ደግሞ አባ ማትያስ ደግም ከአደዎ ብቻ ጉበኞችን እና ተሐድሶዎችን እየሰበሰቡ ሰሞኑን ሊሾሙ ነው። ለመሾም የህዝቡን ገንዘብ ስብስቦ ጉቦ መስጠት ያስፈልጋል። በክፍ ቀን ላይ ቆማ ውሸት በ እውነት ላይ እየሳቀች ነው። አዎ ግዜው ተገጣጠሚ ሌባው ሆድን ከበሮ አስመስሎ፣ ሌላውን እየተሸሎከሎከ ተከፈተለት።
    አቡነ መርቆርዮስ ሆኑ አቡነ ማትያስ ዲያቢሎስ በውሸት ሰንሰለት እያሳሳቀ አስሮአቸዎል። እባካችሁ ፀልዪላቸው።

  5. Holy Synod in exile capable and strong challenger of Woyana formation Synod in 4kilo ! They have the legitimate patriarch they are doing great job, they are still defending firmly their own right ! I admired them. Long leave to our fathers. They are not divided like MEHAD,KINJITES, such and such meaningless political party achieved nothing for the last 25years. Holy Synod in exile recognised in American congress still they are claiming theirs legitimacy based on the church Constitution, At least very good lesson which ever government changed no more involved in the Church matter, no more killing Patriarch /Holy father/ and appointed their own supporter, Is is a good lesson for Ethiopian Orthodox Tewahedo church stand firmly for ilegal involvement. It is practical how our father strong enough to challenge woyane made up synod in 4kilo, Stop been hipocratic, you shall say No for illegal invansion. Our fathers Hoy Synod in exile said No for Woyane, Hiypocratic did said nothing when woyane appointed his own spy as an archbishops, for the last 25 years 23 tigrian born Woyane spay appointed as archbishop by Abuna Paulose. Our fathers in exile still saying No! We shall learn how to say No from our fathers. Stop been Hiyporatic criticising our fathers in exil but we shall support them in all possible means ! Say no for your right!

  6. ጆሮ ካለቹ ማንኛውም በአገር ወስጥ እና ውጭ ያላችሁ መስቀል ለጌጥ ይዛቹ የምትዞሩ ገንዘብን የሴይጣን የውሽት የዘረኛ ፓለቲካ የያዛቹ፣ ትውፈት፣ዶግማ፣ቀኖና ሆዳቹ ሲሞላ ኦርጋን ይዛቹ በቤተ ክርስቲያን የጨበጨባቹ የስጨበጨባቹ መጨረሻቹ ዜሮ ነው። አሁንም በዚህ የጎደለ ፍልስፍና የምትከተሉ ገዝቻለሁ የባቶቻችን ደም ይፈረፈዳችሁ። መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ ይራቅ ።

  7. Bahetawi: who are you silly, you can not jock with holy sprite He is not in your mind of thinking, his judgement above our imagination, he doesn’t work as you wished his job is an absolute. Do you expect Meles and Poulose came to power the same month and passed away the same month, it is the dugement of Holy Sprite not as you wish. Your whish is rubbish!!.

  8. Bahitawi, you are absloutely right. We saw in Abune Matheas through out holiy sprit and he wearn EPRDFA GAWAN. The other side Abune Morkorios not speak anything. That is not good and he need to speak the truth as much as he breath. He need to correct all the mess up to change the doctorine by wisler. If u change any doctorine of our founder u are not Orthodox rather you follow your mind of philosophical thought as Tehadeso. If you are Tahedeso
    Your hoily sprit is gone and you never realize anything about your thought is correct always. If u belive to change the doctorine u cannot proceed in Orthodox church and don’t missled others.

  9. Asemamaw, who trained all the monk those in addis don’t you know both Abuna Poilose and Abuna Mathias triend by his grace Abuna MelkeSedik! Are you really ? Who are you try to Christie in religion our fathers in exile? They are an iron ! Zemedkun serviced from micrage and immatured !

  10. Tafete,
    አሁን የዝና መፈለግያ ግዜ ላይ አይደለም።
    አባቶቻችን ያስቀመጡልን ትውፈት፣ ቀኖና፣ ዶግማ በኦርቶዶክስ እንደ ስሙ ምንም ከዘመን ዘመን አንድም ነገር አይቀየርም።
    የውጭ ሴኔዶስ አርጋኖ አስገባ ብዙ ሕጎችን ቁየረ የራሳቸው ፍልስፈና ያስከራቸው ተሐድሶ ብለው የማይገናኝ ነገር በግድ የማይናገር የጎንደር ህዝብ አገኙ አልታረም አሉ እነ ማን
    አባ መላኩ፣ አባ ወልደ ትንሳኤ፣ ሉኡለቃል፣ አባ ወልደትንሳኤ፣ አባ መለከፃዲቅ። አቡነ መርቆረዩስ መናገር አለባቸው ምንድነው ችግራችን ከሕዝቡ ጋር የሚያጣላን ብለው መጠየቅ አለባቸው። አገራችን እንደዚህ አደጋ ላይ ሆና እውነትን ተናግሮ በውጭ ያለውን መንጋ መስበሰብ አለባቸው። እኔ ከጎንደር ነኝ ብየ ሲሳሳቱ እያየሁ ከጀርባ እያማሁ ወደ ሲኦል ሲሄዱ ማየቱ የክርስትያን ተግባር አይደለም። እንደዚህ ከሆነ ባህታዊው እንዳሉት በጥላቻ ጎሳ ላይ የተመሰረተ ቤተ ክርስቲያን ፀሎቱም ከዳመና በታች ይቀራል፣ መንፈስ ቅዱስም የወሰድባቸዎል፣ በቃ ግእዝ አነብንቦ መመለስ ይሆናል። ባህታዊው አቡነ ማትያስም ሆኑ የውጭው ወደ እውነት ካልተመለሱ መንጋውን ካልስበሰቡ መሪሪ እንባ ወደ ጌታ አልቅሰው ገዝተዋል። በነገራችን እኝ አባት በቀን ስንት የተጉ በወልድባ ጉዳይ ላይ መርር ብለው አልቅሰው ትንሽ ግዜ ስጣቸው ከተመለሱ
    አባ ጳውሎስ እና መለስ ግን በሰውነታቹ ተመኩ አሁን ሁሉንም ግፍ ይዘው ሄዱ።
    ተዋህዶ እምነት ላይ ገንዘብን አስቀድሞ በክርስቶስ ደም፣ በእነ አቡነ ጴጥሮስ ደም
    ቆሞ መቀለድ እያበቃ ነው ብትሬን አነሳለው ብሏል ነው የባህታዊው መልእክት። ታርሞ መቀበል ወይም ለፈራጁ መዘጋጀት እኔ ምንአገባኝ ብለዋል።

  11. Tafete,
    ስድብ እና ስህተት ላለመቀበል አውቆ እእምሮውን የሚዘጋ ስው” He travelling like always in one way” እንደዚህ አይነት ሰዎችን ከገኘህ ዲያቢሎስ ተቆጣጥሮአቸዎል ማለት ነው ሰለዚህ አንተም ከሆንክ ወይም ሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድም ካለህ ፀልይላቸው!!! ከርስትያኑ እኮ እያለ ያለው በኢትዩጵያዊነታቸው ሁሉም ይወዳቸዎል ግን የአባቶቻችን ስርአት አንድም ነገር ለመቀየር አትሞክሩ ምክንያቱም መገለል የመጣል እኔ ጎንደሬ ሆኜ ክርስትና እምነቴን ሊቀይር ቢመጣ ለድርድርም አለቀርበውም። ግዜው ተቀይሯል አሁን ህዝቡ ነቅቷል መሸወድ አይቻልም በፓለቲካም ሆነ በእምነቱ። በአሁን ሰአት ከህዝቡ ይልቅ በንዋይ ተታሎ ክህኑ ነው በእግዚአብሔር ሚስጥር አውቆ እንደላወቀ ሆኖ የዘመኑን ፋልስፈና ጨምሮበት እያሳዘነው ያለው። በቃ እንግዴ ወንድሜ የስድብ መንፈስ ያሰወግድልህ እያልኩ ይህንን መልእክት በማስተዋል አንብበህ አባቶችን መክረህ በፍቅር መንጋውን የሰበስባለሁ በዮ አምናለሁ። እስቲ ከአንተ ይጀመር አንዱ የሠላም ሐዎሪያ ሆነህ ተነስ ቀኑ እየረፈደ ነው ምክንያቱም ነገ ፈራጅ ድንገት ይመጣል፣ ፓለቲከኞችም በፈስሱት ደም እና የግፍ ገንዘብ ሳይበሉት፣ ካህናትም በፍቅር መንጋውን ለምን አለሰበሰባቹም የሚባልበት ደርሷል። ከዚህ የበለጠ እግዚአብሔር የማስተዎል ልቦና ይስጣቹ እላለሁ ስላም ሁኑልኝ ከዚህ በላይ እኔም አንዱ ሐጥያተኛ ነኝ።
    ወስብሐት ከእግዚአብሔር።

  12. Zemedkun, I do not blem you you exactly look like how you grow up you face and your word shows thar how you are badly clitivated. Your dream can not be Gondrian you wish, you wear born road side you do not know even your fathers do not even open your mouth hiding behind the computer. Are you trying to teach to Gondrian how to worship ? It is loughble,” LEB ENEKERT YEMEGNAL” you need a lot to learn.

  13. Hey Tafete,

    Please think twice all is constructive comment to deliver for the truth unity. No matter who commemt all are right. Learn to take it for forgivness. We are not at war with this group, but teaching them we love u come back per the founders passing over to generation.

    This is the time to come together. No, one comment about hate all about love.
    I hope now it is straigjt shot to make over with tear to your God! You can’t get this kind of open heart advice to be wittnessed by public on judgment day soon!!!

  14. Asemamaw! I agree with you do not forget it is difficult to know who is who behind the computer however I will take risk a person like Zemedkun shall be illuminated in this world, he is mantaly sick !!

  15. We shall learn how to say NO from holy synod in exil, NO for your independant EOTC, say NO for illegal interfrianc in the EOTC affaires, say NO abusing the EOTC constitituion, say NO killing or removing the legitment Patrirch whenever the government change to appointed theirs own supporter. It is a meracle whilset His Holyness Abuna markorios and his grace Abuna Melkesedik 94 doing theirs duty actively, MELES AND Abuna Powelos came from the same village Adewa, came to power the same month, dead the same month. MELES appointed 50 army Generals from Tigray Abuna Poulos appointed 23 spy monks as arecbishops. We shall learn to say NO from our fathers in exile.

  16. Tafete,
    Now, we are on the same page.
    This is reality & facts about the two Syndos:-

    በመጀመሪያ ይቅርታ አርግልኝና ዘመድኩን ተሐድሶዎችን አጋለጠ ማለት ተሳስታችኋል ተመለሱ ከውስጥ ሆናችሁ አታድሟት ነው ያለው ምክንያቱም በአንድ ወቅት እነዚህ ስዎች የቤተክርስቲያኗ ጌጦች ነበሩ። ዛሬ ግን ዲያቢሎስ ምላሳቸውን፣ ልባቸውን ተቆጣጥሮ ገንዘብ እንደ አሞሌ ጨው እያሳየ ከመንገድ አወጣቸው ያሳዝናል አይ የስምንተኛ የካህናት ፈተና? እግዚአብሔር ይርዳቸው ወደ ትክክለኛ መንገድ ይመልሳቸው። ይገርማል ዲያቢሎስ ካህናትን ከመንገድ ሲያወጣ ሎተሪ እንደደረሰው ነው የሚቆጥረው ምክንያቱም አንደኛ ከእውነተኛው ነጠለው እንዲሁም በሱ ላይ ያለው በሜዳ ላይ ያሉትን ሁሉ ያሳሰታል።

    በአጭሩ እራሳችዎን መመርመር አለባቸው።
    1ኛ አቡነ ማትያስ በውሸት ተመረጡ ከዚያ የኢሐዲግ አባላትን ና የታሐድሶ አቀንቃኞች አስተዳዳሪ አርገው ብሩን ከየቤቱ ክርስትያኑ ዘረፈ አዳራጆች ሌባው ብጹዕ እድ አልያስ የስንት ፎቅ ባለቤት። ለቤተ ክርስቲያን የሚሰሩትን ማኅበራት እና ጥሩ አባቶችን በየቦታው አገለሉ። አሁን ማንኛውም ደብዳቤ ስፅፍ ግልባጭ ለኢሕአዴግ ሆነ ምሳም እንኳን ሲበሉ ነው። ይገርማል ያሁሉ ሕዝባችን በኢትዮጵያ ሲያልቅ ፍታት እንኳን አላደረጉም። እነዚህ አይነቶቹ የተሰጣቸውን የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስሱደዎል። ከእነሱ በረከት አገኛለሁ ብለህ ግዜህን አታጥፈ ነው የምለው ግን ሐይማኖትህን ጠብቅ ነው የምለው ለህዝባችን ጌታችን የለው እርስ በእርሳቹ ተዋደዱ እንደ እርግብ ሁኑ ግን ጠላትን ስታዩ እንደ እባብ ሁኑ ነው ያለው።
    2ኛ አቡነ መርቅሪዎስ ህጋዊ ጳጳስ ናቸው። እድሜ ለዛሬው አስመሳዪ ፓስተር ታምራት ላይኔ ዛሬ የሚናገረው ሁሉ ፍሬ ከርስኪ የሆነ እና ባክኖ ያለው በዚሁ ግፍ ነው። አገር ውስም ሆኑ ውጭ ህጋዊ ስለሆኑ እውነትን መናገር፣ ቡራኬ መስጠት መንጋውን ያለውን የተሐድሶ አመለካከት አስወግደው በፍቅር መንጋውን በውጭ ያለውን ሁሉ በአንድ ቤተክርስቲያን መሰባሰብ አለባቸው። እንደዚህ ሲሆን ነው እግዚአብሔር የሚለመነን እና ጥሩ ነገ ኢትዮጵያ የምትለው ምድር ላይ በፍቅር የምንሰባሰበው አለበለዚያ የመከራችን ግዜ እየረዘመ ይሄዳል ማለት ነው።
    ለማንኛውም የእነ አቡነ ጰጥሮስ፣ የእነ አቡነ ተክለኃይማኖት ዘኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን እላለሁ። አየህ ወንድሜ እግዚአብሔር የፈለገውን አስነስቶ ያስተምራል እንዳንጠፈ ግን የኛ ድርሻ ነጋ ጠባ ወደ ፈጣሪ መበርከክ ነው ከዚያ ለውጡን ከቤተስብ እስከ አገር ታዩታላቹ። እግዚአብሔር ይርዳን ቻው።
    ለማን ማድላት ይበልጣል ለነፍስ ወይስ ለነዋየ ስጋ?
    Watch ከቻላቹ?
    https://youtu.be/SOKcPeAux-M

  17. The time has change donot be inocent like before and you have to tell to every KES or PAPAS. Your founders relgion is first and if anything u see outside the rule and regulation tell them u are wrong. If u are not do your part to correct today and you are also responsible on our freedom day following the judgment day. Speak up the truth for what u see for it is not about u are from Tigeri or Gonder and your relgion is first than trash politics!!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*