በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሻንጣ ሌቦች ስልታቸውን በመቀያየር ተጓዦችን የሚዘርፉበት መንገድ ተባብሷል ተባለ

በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከውጭ ወደ አገር ቤት የሚመጡ መንገደኞችን በመጠባበቅ የትራንስፖርት አገልግሎት ወይም ትብብር ለመስጠት በማስመሰል የተጓዦችን ሻንጣና ሌሎች ንብረቶችን የሚዘርፉ ሌቦች ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም፣ ዘራፊዎች በየጊዜው ስልታቸውን እየቀያየሩ መምጣታቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ የኤርፖርቶች ድርጅት ገለጸ፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ኃላፊዎች እንዳሉት ከሆነ፣ በኤርፖርት አካባቢ የትራንስፖርት አገልግሎት በሕጋዊ መንገድ ተደራጅተው የሚሠሩት የታክሲ ማኅበራት በተባራሪ ሌቦች የተነሳ ስማቸው መጥፋቱ እንደሚያሳስባቸው ለድርጅቱ እየገለጹ ነው፡፡

የሻንጣ ሌቦች በተለይ ከዓረብ አገሮች ተመላሽ ሴት ተጓዦች ላይ በዋነኛነት በማነጣጠር የስርቆት ወንጀሉን እየፈጸሙ ሲሆን፣ ለዚህ የስርቆት መባባስ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል ወንጀለኞቹ ከተያዙ በኋላ የሚተላለፍባቸው የሕግ ቅጣት አነስተኛ መሆን ተጠቃሽ እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጀት የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ድርጅታቸው ከታክሲ ማኅበራት፣ ከፀጥታ ተቋማትና ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በየጊዜው እየተመካከሩ የሌቦችን መንገድ ለመዝጋት ቢሞክሩም፣ በየጊዜው ስልታቸውን እየቀያየሩ ዘረፋውን ቀጥለዋል፡፡

በተለይ በከተማ ውስጥ ብቻ አገልግሎት መስጠት የሚጠበቅባቸው ባለታክሲዎች ኤርፖርት ድረስ በመምጣት ተጓዦችን በአነስተኛ ዋጋ እንደሚያደርሱዋቸው በማግባባት እንዲሁም ስልክ በማስደወል የሚተባበሩ በመምሰል እየዘረፉ መሆኑን አቶ ወንድም አስረድተዋል፡፡

በመደበኛነት የታክሲ ትራንስፖርቱን አገልግሎት መስጠቱ ሥራም የሚከናወነው በባለ ቢጫ ታክሲዎች ቢሆንም፣ ዋጋቸው ከመደበኛ ታክሲዎች ታሪፍ ከፍ ያለ በመሆኑ ተጓዦች ለዋጋ ቅናሽ ሲሉ የከተማ ታክሲዎችን በሚመርጡባቸው ጊዜ ለዝርፊያው እንደሚጋለጡ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ለዚሁም በቅርቡ በተደረገ የጋራ ምክክር ጉባዔ ላይ የታክሲ ማኅበራትም ሆኑ ባለንብረቶቹ የዋጋ ማስተካከያ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸው፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚረዱ መፍትሔዎች አንዱ ሊሆን እንደሚችል አቶ ወንድም ገልጸዋል፡፡

ተደራጅተው ከኤርፖርቶች ድርጅት ዕውቅና አግኝተው በጋራ እንደሚሠሩ የሚናገሩ ባለታክሲዎች በበኩላቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከከተማ በሚመጡ ተባራሪ ታክሲዎችና በግብረ አበሮቻቸው የሚፈጸሙ ዝርፊያ የእነሱንም ስም እያጠፋው መሆኑ አሳስቧቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ወንጀሉን ከምንጩ አድርቀናል ብሏል፡፡  የፖሊስ ኮሚሽንና የከባድ ወንጀል መርማሪ የሆኑት ኮማንደር ዓለማየሁ አያልቄ በአካባቢው ሲዘርፉ የኖሩት ሕገወጦች በአብዛኛው ማረሚያ ቤት እንደሆኑና ዋና ምንጫቸውን ማድረቃቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አብዛኛው ዘራፊዎች ከመያዛቸው ባሻገር የዘረፏቸው ዕቃዎችና ንብረቶቻቸው በሕግ ተወርሰው በኤግዚቢትነት መያዛቸውን አመልክተዋል፡፡

መርማሪው ይህን ይበሉ እንጂ ሪፖርተር በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ በመዘዋወር ያናገራቸው የታክሲ አሽከርካሪዎችና በዚያው አካባቢ በሥራ ላይ የሚገኙ ታዛቢዎች እንደገለጹት፣ ከዓረብ አካባቢ በሚመጡ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያ እየተለመደ መምጣቱንና ሌሎችም የራሳቸውን ኔትወርክ ዘርግተው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ዋና መርማሪው ግን አለ የተባለውን ኔትወርክ መኖሩን የሚያሳይ ነገር እስካሁን አለማየታቸውን ገልጸው፣ ሊኖር የሚችል ከሆነም ዕለት ከዕለት የፀጥታ ኃይሎች እንደሚከታተሉት ጠቁመዋል፡፡

ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ረፋድ ላይ መገናኛ አካባቢ ዝርፊያ ተፈጽሞባት ስታለቅስ አግኝቶ ሪፖርተር ያነጋገራት ወጣት ሴት ስሟን መጥቀስ ባትፈልግም፣ ቅዳሜ ጠዋት ለአራት ዓመታት በሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኝነት ስታገለግል ቆይታ መምጣቷን ገልጻለች፡፡ ከአውሮፕላን ወጥታ ሻንጣዋን በመያዝ የምትጠብቀውን ዘመዶቿን በመፈለግ ላይ እንዳለች አንድ ወጣት ጠጋ ብሎ ምን ልርዳሽ ብሎ እንዳነጋገራትና ዝርፊያውን የመፈጸም ሒደቱ እንደተጀመረ አመልክታለች፡፡

የሚቀበላትን ሰው እየፈለገች መሆኑን ስትነግረው ስልክ ልደውልልሽ በማለት ሊተባበራት እንደሚፈልግ ከገለጸላት በኋላ የስልክ ቁጥሩን መዝግቦ በተንቀሳቃሽ ስልኩ ደውሎ ያገናኛታል፡፡ ነገር ግን ደውሎ ያገናኛት ሰው መኪና እንደላከላትና አሽከርካሪውም ወደ ቤት እንደሚያመጣት ይነግራታል፡፡ የተነገራት አሽከርካሪም ወዲያው ከደረሰ በኋላ ሁለት ትላልቅ ሻንጣዎቿን በመጫን የመኪናውን ሞተር አስነስቶ ወሰደኝ በማለት ትገልጻለች፡፡

ነገር ግን ይኼው አሽከርካሪ ከዓረብ ተመላሽ መንገደኞች ካርድ መቁረጥ እንዳለባቸው እንደነገራትና ከዚያም መገናኛ አካባቢ ወደሚገኘው የውልና ማስረጃ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ወስዷት ሰልፍ እንድትሰለፍ፣ ከዚያም እንደሚጠብቃትና ቆርጣ እንድትመጣ ይነግራታል፡፡ ነገር ግን ከደቂቃዎች በኋላ እንደተሰወረባት በእንባ እየታጠበች ስልክ በመደወል እንደተባበራት በገለጸችው ሰውና በአሽከርካሪው ሙሉ ዕቃዋን መሰረቁን ገልጻለች፡፡

ተጎጂዋ ለሪፖርተር እንደገለጸችው በሁለቱ ሻንጣዎች ውስጥ በርከት ያሉ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ አራት ስማርት ፎን የሞባይል ቀፎዎችና ከ2,700 ሪያል (15,650 ብር) በላይ ገንዘብ ጨምሮ መዘረፉንና ባዶ መቅረቷን አስረድታለች፡፡

ስልክ በማስደወል ሊተባበሩ የሚችሉ በማስመሰል ተጓዦችን የሚዘርፉ ሌቦች በተደጋጋሚ ማስተዋላቸውን ያረጋገጡት የኤርፖርቶች ድርጅት ኃላፊው ነገሩን ለመቅረፍ ተጓዦች ከአውሮፕላን እንደወጡ ነፃ የስልክ አገልግሎትና ሲም ካርድ በቀጥታ በግዢ የሚያገኙበትን መንገድ ለማቅረብ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

10 Comments on “በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሻንጣ ሌቦች ስልታቸውን በመቀያየር ተጓዦችን የሚዘርፉበት መንገድ ተባብሷል ተባለ”

  1. Ayyy mengedgna mekerawn be leboch aye..ke west shanta tesbro yezerefal kewech yenetekal…ye wenbede zemen.

  2. On My last visit,people working in the airport open my suit case take some staff. The baggage handler are thief too. Please wrap you suitcase with shrink wrap when you travel to Ethiopia. Theft is normal in Ethiopia from top official to bottom floor worker. They have key to open your suitcase so wrap it and save yourself. They going to kill tourism industry because of this low life hodam Tigray worobella. Most people work in the airport come from Tigray,I try to report it but they laugh at me.it is a shame to stole from visitors and they don’t care about the country repetation. I guess the all structure of public office are corrupt and this kind theft are norm to them.

  3. ዘራፊዎቹ በአውሮፕላን ማረፊያው ያሉ ባለስልጣናት እኮ ናቸው ሌሎቹማ አቀባዮች ናቸው ወያኔ ሌባ ነው ሲባል ከላይ እስከ ታች ባዋቀረው መዋቅር ሁሉ እኮ ነው ይህ ሌብነት ከተጀመረ እኮ ቆየ አንድ ታብሌት ተወሰዶበት የበላይ ባለስልጣን ዘንድ ስላመለከተ በፌዴራል ከብት ፖሊሶች ሶስት ቀን ታሰሮ በአጃቢ ቦሌ ተወስዶ ወደ አሜሪካ እንዲመለስ የተደረገው የቅርብ ዘመዴ ምስክር ነው

  4. ጉድ ነው!! ኤርትራውያንና ብዙ
    ኢትዮዽያውያን ደጋግመው የሚናገሩት እውነት ሆነ ወያነ ድሀ ስለሆነ የሰው ቤትና ንብረት የሰው አገርና መሬት ይዘርፋል ባለስልጣናቱ የሰው ሚስት መድፈር ጀምረዋል አንዳንዶቹም ሰለሳና አርባ አመት ልዩነት ያላቸውን በገነዘብና በሀይል እያስገደዱ ይደፍራሉ ሰግብግቦች ስለሆኑ ሽሮ በርበሬና እንጀራ ሳይቀር ወደ ውጭ ይልካሉ ታሪካዊ ቅርሶችን ሪፕሊካውን በማስቀመጥ ኦሪጅናሉን ለቱሪስቶች እየሸጡ ነው መሬት ለውጭ ባለሀብቶች ሸጠው እጅግ ብዙ ገንዘብ አካብተዋል ለትግሬዎች በሚመች ሁኔታ የከተማ ቦታና ቤት የባንክ አገልግሎት ሰጥተዋል አመቻችተዋል ወዘተ የተባለው ሁሉ አውነትና ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ሆነ shame on us the Tigreans. ሰፊው የትግራይ ሀዝብ የልጆቻችንን ገበና ተመልከት ከአማራው ከኦሮሞው ከሱማሌው ከደቡቡ ከአፋሩ ከኦርቶዶክሱ ከሙስሊሙ አቃቅረውን እነሱ ሲኮበልሉ እኛን እንደ ገና ዳቦ ከላይ እሳት ከታች እሳት ነዶብን እንድንቃጠል ሊያደርጉን ነው ልጆቻችንን በቃ ልንላቸው ይገባል ታሪክ ውሉን አይስትም ከመራራውና ከአስከፊው ተጠያቂነት አንዳን ንቀትና የት የደርሳሉ ማለት እንኯን ለእኛ ለኮሳሳዎቹ ለሀያላኖቹም አልጠቀመም ውርድ ከራሴ!!!!

  5. Yes that is the woyane job…………all the thieves are woyane tigres, cus every one in the airport is woyane tigre…..this problem been there for a while, so please shrink rap your suit cases to protect your valuables and please don’t put any money in the luggage……..the woyanes are like a hound dog…..they will smell it from a mile

  6. ” … they don’t care about the country repetation.  ”

    It is far worse than that.

    They encourage ferenjis to help destroy the country’s reputation, say by facilitating human traffic, such as selling of kids to ferenjis and sending of women to slavery in the middle east, by inviting ferenji so-called NGOs to produce harmful films about the country, by manufacturing famines and then appealing to ferenjis while at the same time exporting millions of tons of organic food to Europe, Middle East, Africa and elsewhere, etc.

    TPLF’s Ethiopia is allegedly Africa’s No.1 organic milk exporter and major organic food exporter to Europe

    ” Aside from river water, rainfall allows Ethiopia to raise 100 million cattle on natural grassland, making it the largest exporter of organic milk in Africa. Because it has the advantage of farming with clean rainwater, not the polluted river water Egypt uses, Ethiopia is high on the list of organic food exporters to Europe. ”

    http://weekly.ahram.org.eg/News/4736/17/Tough-talk.aspx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*