የትግራይ የኦሮምያና ሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ከአውስትሪሊያ ታስማኒያ ግዛት በአስቸኳይ ለቀው እንድወጡ ተደረገ።

ሰኔ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለገንዘብ ማሰባሰብና ለቅስቀሳ ስራ በአውስትራሊያ የተገኙት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ሙክታር ከድር እና ሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያን ያጋጣመቻውን ተቃውሞ ተከትሎ የአገሪቱ ፖሊስ ዋና ከተማዋን ሆባርትን ለቀው እንዲወጡ በማዘዝ፣ በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል። ሶስቱ ባለስልጣኖች ቀደም ብሎ በካምቤራና በሜልበርን የደረሰባቸውን ተቃውሞ ተከትሎ ደጋፊዎቻቸውን ኢትዮጵያውያን በብዛት አይገኙበትም ተብሎ በሚታሰበው የታስማኒያ ግዛት ለመሰብሰብ አስቀድመው ቢገኝም፣ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰባስበው ተቃውሞ በማሰማታቸው ፖሊስ ለጸጥታ አስቸገሪ ነው ከተማዋውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። በታስማኒያ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ሰብሳቢ አቶ ደሴ አሰፋ ሰዎቹ እንዲወጡ ለፖሊስ ማመልከታቸውንና ፖሊስም ሁኔታውን በመረዳት እንዲወጡ አድርጓል ብለዋል። የኦሮሞ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ አቶ ዘይድ ሙሃመድም በበኩላቸው በአውስትራሊያ በሶስት ግዛቶች ለማድረግ ያቀዱት ስብሰባ ከተጨናገፈ በሁዋላ ወደ አካባቢያቸው እንደሚመጡ መረጃ ሲደርሳቸው ሌሊቱን በሙሉ በአየር ማረፊያ ሲጠብቁዋቸው ማደራቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም ያረፉበትን ሁቴል እንዳገኙ የኦሮሞ ኮሚኒቴ አመራሮችና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት በጋራ በመጠራራት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ኢትዮጵያውያን ስራቸውን እየተው በመምጣት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ፖሊስ የህዝቡን ጥያቄ በመስማት ከከተማዋ እንዲወጡ አድርጓል። በከፍተኛ ድንጋጤና ፍርሃት በፖሊስ ታጅበው ወደ አየር ማርፊያ ከሄዱም በሁዋላ ተከታትለው ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ተናግረዋል በሌላ በኩል በቤልጂየም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ትናንት በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት ተቃውሞ አሰምተዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የልማት ትብብር ለመፈራረም በቤልጂየም መገኘታቸውን የተቃወሙት ኢትዮጵያውያኑ ፣ ወያኔ ከኦሮምያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ጋምቤላ ለቀህ ውጣ፣ ሰላማዊ ዜጎችን መግደል አቁም ፣ የአውሮፓ ህብረት የወያኔን ገዳዮችና ወንጀለኞችን መደገፍ አቁም የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል።

Ras Darge's photo.

9 Comments on “የትግራይ የኦሮምያና ሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ከአውስትሪሊያ ታስማኒያ ግዛት በአስቸኳይ ለቀው እንድወጡ ተደረገ።”

  1. አውስትራሊያዎች እነዚህን የባንዳ እዳሪዎች አሳፍራችሁ በማባረራችሁ ትልቅ ምስጋና ይገባችኇል።
    Thank You!!!

  2. please please do not be divided this the so called amhara, oromo afar…. get rid off it and be united as one ETHIOPIA.

  3. @ united ETHIOPIA –
    ይህንን ላመጡብን ለእነዛ ትላም ትግሬዎች ንገራቸው።

  4. Geleta
    What is the difference Gonder and tigray?all are the same ortodox killers.So you are the same liers,dirty habesha.

  5. Abay woldu face looks like hayna. All woyanes have the same face like Abay woledu. Be ware of the Ethiopia people from those hayenas.

  6. አማራን አሁንም በሕዝብ ቆጠራ ለማሳነስ ጠንክረው እንደሚሰሩ ወያኔና ተባባሪዎቹ በእቅድ ላይ ሁነው የመረጃ ሰብሳቢዎቹን በገንዘብ እየደለሉና ከፍተኛ ሚስጥራዊ ስራ ተሰራ!
    አማራን በማደን ለስደት ለማዳረግ የጥፋት ተልዕኮዋቸውን እየተወጡ ናቸው!
    በአማራው ውደቀት ወያኔ ይስቃል! ያስቃል! ያስደንሳል!
    የአማራን ሃብት በመዝረፍ ሕዝቡንም በመግደል፣በማፈናቀል ተግተው ይስራሉ!
    ሰይፍ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*