በራያ ቆቦ ለሆላንድ ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር መሬት ሊሰጥ ነው፡፡

በራያ ቆቦ   ለሆላንድ  ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር መሬት ሊሰጥ ነው፡፡
******************************************************************************
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ልዩ ስሙ ጎለሻ የሚባል ቦታ ለሆላንድ ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር በሬት ሊሰጥ ነው ሲሉ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፁ ፡፡እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፃ ለባለሀብቱ ሊሰጥ የታቀደው መሬት በደን የተሸፈነ ቢሆንም ትእዛዙ ከፌደራል መንግስት በመተላለፉ ደኑን ለመመንጠር እና ለባለሀብቱ ለመስጠት የወረዳው ባለስልጣናት መወሰናቸውን አያይዘው ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በህወሀት የንግድ ተቋማት ስር ጥረት በሚል የሚጠራው የዘለቀ እርሻ ማህበር በቆቦ ከተማ ከሚገኘውን አቧሬ ደን 160 ሔክታር በብአዴን እና የህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲመነጠር በመደረጉ የድርጅቱም እንቅስቃሴ የደኑን እንጨት በመሸጥ ላይ ብቻ የተወሰነ ሆኖ መቆየቱን በወቅቱ የደኑን መመንጠር ከትሎ የነበረውን የህብረተሰቡን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ግዙፍ ፋብሪካ አሚናታ የሚባለው ቦታ ላይ ለመገንባት ስምምነት ላይ መደረሱን የከተማው ባለስልጣናት በተለያዩ ስብሰባዎች ሲገልፁ መቆየታቸውንና በመጨረሻ የአዘለቀ እርሻ ተገቢውን ምርት ሊያመርት አልቻለም በሚል ምክንያት መሬቱ ለወልድያ አትክልትና ፍራፍሬ ማህበር ለሚባል አካል መተላለፉን ተከትሎ ህብረተሰቡ በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሞውን እየገለፀ እንደሚገኝ እና አርሶ አደሩ ለረጅም አመታት ጠብቆና ተንከባክቦ ያቆያቸው ደኖች በአምባገነኖች ማናለብኝነት እየተመነጠሩ አካባቢው ለበለጠ በርሀማነት መስፋፋት ተጋላጭ እንዲሆን መደረጉ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ምነጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል፡፡

 Source  – በያሬድ አማረ
Yared Amare's photo.

7 Comments on “በራያ ቆቦ ለሆላንድ ድርጅት ነው በሚል ሽፋን ለትግራይ ባለሀብት 160 ሔክታር መሬት ሊሰጥ ነው፡፡”

  1. Hulu neger metaglna meswatnet mekfeln yeTeyeqebet gizie lay nen.
    Hzbu anasmeneTrm blo meqawemna begulbet yemimeTan memtat alebet.

  2. yewsedud !!! weyane sehed yetefuwatal !!!

    YE,,wollo zimita gin germognal

    wollo Hageru asrekibo kuch ale ?????

  3. akrari hula zembeleh seged. mn agebah? konjet sitotaw akrari mehonun tawokowal. kelay asteyayet yesafachihut enatem ye akrari nachihu.
    leba hula.
    ensu yeshalunal

  4. ለሆላንድ መንግስት ወይም ባለሃብት ተሰጥቶ ቢሆን እንቃወም ነበርን?
    ያሳዝናል የነጭ አምላኪነት ችግር አሁንም እየተስተዋለ ይመስለኛል።
    ለማንኛውም፣ ጥረት የብአዴን ኢፈርት እንደ ማለት ነው። ዘለቀ የእርሻ ድርጅት፣ የብአዴን ንብረት ሲሆን በበርካታ የአማራ ክልል አካባቢዎች የእርሻ ልማት እያካሄደ እንደሆነ የሚታወቅ ነው።
    ታዲያ ምን አዲስ ወራሪ መጥቶ ነው አሁን ይህ ሁሉ ከበሮ የሚደለቀው፨
    ብአዴን ለትግራይ ኢንቨስተር ቢሰጠውና ቢያለማስ፣ ከውጭ አገር ኢንቨስተር ሳይሻል አይቀርም? ቢያንስ የሃገር ውስጡ አልሚ ግን ትርፉንና የምርት ውጤቶቹን ወደ ዉጭ አያወጣም።
    ይኸ ትግራይን በጥላቻ ዓይን መመልከት ማቆም ያለብን ይመስለኛል። ስርዓቱንና ህዝቡን ለያይተን ማዬት ተገቢና አስተዋይነት ነው። ህዝብን እንደ ህዝብ የሚጠላ ወደፊትም ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ አይሆንም።

    ዘረኝነት በሽታ ነው፣ በሰዓቱ ህክምና ካላገኘ ወደ ወረርሽኝነት ተቀይሮ ግዙፍ ጥፋት ያደርሳል።

  5. ወያኔ ደን ማጥፋት ስራው ነው!
    መሬት መሽጥ አላማው ነው!
    ወያኔ ለማጥፋት እንጁ ለማልማት አልተፈጠረም!
    ከወያኔ ጋራ ማጥፋት እንጁ መግደል እንጁ፣ክህደት እንጁ ወያኔ ሰውም አይደለም ነው የሚል ካለ ሰህተት ነው!
    ወያኔ ጋራ መስረቅ እንጅ!ኢትዮጵያ ሲባል ወያኔ ያማዋል!
    ከወያኔ ምንም አይጠበቅም!
    ብአዴን የሚባል የለም! በጥቅሉ መነገጃ እንጅ ወያኔና ሻቢያ ናቸው!
    የብአዴን ንብረት አለ የሚል ካለ እሱ ወያኔ ነው!
    ካሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*