Bego Sew 2008 Award/ Ethiopia – ዶክተር መረራ ጉዲናን እናሸልም !
ዶክተር መረራ ጉዲናን እናሸልም!
#Ethiopia #MereraGudina #AAU #Medrek #Begosew2008 #MinilikSalsawi
ዶክተር መረራ ጉዲና በ1947 ቶኬ በሚባል ከአምቦ ከተማ 35 ኪሎ ሜትሮች የሚርቅ መንደር ውስጥ የተወለዱ ሲሆን፤ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዛው በተወለዱበት መንደር፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ አስከትለውም ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ቢጀምሩም በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከትምህርታቸው ተስተጓጉለው ለሰባት ዓመታት ታስረው ከቆዩ በኋላ ከእስር መልስ ያቋረጡትን ትምህርት በመቀጠል በ1978 የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፖለቲካል ሳይንስና ዓለማቀፍ ግንኙነት የትምህርት መስክ አግኝተዋል፡፡ በማስከተልም ግብፅ አገር በሚገኘው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካይሮ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን (ማስተርሳቸውን)፤ እንዲሁም የሶስተኛ ዲግሪያቸውን (ፒኤችዲያቸውን) በኔዘርላንድስ ከሚገኝው ‘Institute of Social Studies’ የትምህርት ተቋም አግኝተዋል፡፡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ሲሰሩ በመመመረቂያ ጽሑፍነት የጻፉት ‘Ethiopia: Competing Ethnic Nationalism and the Quest for Democracy: 1960-2000’ በተለያዩ ምሁራን በምርጥ ፅሁፍነት ምንግዜም ይጠቀሳል፡፡
ከሰባት ዓመታት እስር በኋላ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት በማግኝታቸው ተመርጠው 1979 ጀምሮ ዶክተር መረራ ጉዲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካል ሳይንስ የትምህርት ክፍል መምህርት ሆነው ሲያገለግሉ፣ ካሳተሟቸው አራት መፅሃፍት ማለትም፡-
1.Ethiopia: Competing Ethnic Nationalisms and the Quest for Democracy: 1960-2000
2.Ethiopia: from Autocracy to Revolutionary Democracy: 1960’s – 2011
3.የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች እና
4.የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎችና የሚጋጩ ሕልሞች፡ የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ
በተጨማሪ በተለያዩ ዓለምአቀፍ ‹ኮንፈረንሶች› ላይ በመገኘት የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችንና ልምዳቸውን ለዓለም ህዝብ አካፍለዋል፡፡ ከሰላሳ በላይ ጥናታዊ ፅሁፎችንም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ዦርናሎች ላይ አሳትመዋል፡፡ ካሳተሟቸው ጽሁፎች ከፊሉን => www.aau.edu.et/css/merera-gudina በመመልከት ማየት ይችላሉ፡፡
መምህሩ መረራ!
ተማሪዎቻቸው እንደሚናገሩት መምህር በነበሩበት ወቅት ቢሯቸው ለሁሉም ተማሪ ክፍትና ማንኛውም ተማሪ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስቶ ምክር መጠየቅ የሚያስችለው ቤተሰባዊ መንፈስ ነበራቸው ይላሉ፡፡ አንዳንድ ተማሪዎቻቸው እንደሚሉት “ከሌሎች መምህራን በተለየ እሳቸው የቢሯቸውን በር ከፍተው በመቀመጥ ይታወቃሉ” ብለው ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ ችሎታቸውንም ሲናገሩ፣ “ሲያስተምሩ፣ የጥናት ፅሁፎችን ሲያማክሩ፣ ሙያዊ አስተያየቶችን ሲሰጡና በተለያዩ መድረኮች ንግግር ሲያደርጉ አፍ የሚያስከፍቱ ምሁር ናቸው” ይሏቸዋል፡፡ እሳቸውም “በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምን ያህል ጊዜ አስተምረዋል?” ተብሎ ለሚሰነዘርላቸው ጥያቄ በኩራት “እሱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፣ ለ28 ዓመት ፖለቲካል ሳይንስ አስተምሬያለው” ብለው ይመልሳሉ፡፡ በሶስት የተለያዩ ጊዜያትም የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ክፍል ተጠሪ ሆነው መስራታቸው ሳይዘነጋ፡፡ በአንድ ወቅት ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመምህርነት ህይወታቸው ለዩኒቨርሲቲውም ሆነ ለሀገር አበርክቻለው ስለሚሉት ትልቅ ነገር ሲናገሩ፣
«ሰው ስለራሱ ባይናገር ይመረጣል፡፡ የሆኖ ሆኖ ሁለት መፅሐፍት አሳትሜአለሁ፡፡ በተደጋጋሚ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ሌክቸሮችና አለማቀፍ ስብሰባዎች ላይ ተካፍዬ ሃሳቤን ገልጫለሁ፡፡ ፖለቲካንና ሃገሪቷን በሚመለከት ጉዳዮች በዓለም ታላላቅ በሆኑት እነ ቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ሲኤን ኤን፣ ቪኦኤ እና በመሳሰሉት ላይ አስተያየቶችና ቃለምልልሶችን በስፋት ስሰጥ ነበር፡፡ በአሜሪካና አውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎችም ሌክቸር የማድረጉ አጋጣሚ ነበረኝ፡፡ አካዳሚውንም ፖለቲካውንም በሚዛናዊነት ለማስኬድ ሞክሬአለው፡፡» ብለው ነበር፡፡
ስለምን ስለ ዶክተር መረራ ጉዲና ማንሳት አስፈለገን?
ለአገርና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው ‹የበጎ ሰው ሽልማት› አራተኛው መርሐ ግብር ግንቦት 24 ቀን 2008 በይፋ መጀመርን ተከትሎ የሽልማት መርሃ ግብሩ ከዘረዘራቸው ዘርፎች መካከል መምህርነት በአንደኝነት ደረጃ የተቀመጠ ሲሆን፣ መስፈርቶቹም:
-ለአገራችን ኢትዮጵያ መልካም የሚሰሩ፣
-ሀገራዊ ተልዕኳቸውን በብቃትና በልዕልና የሚወጡ፣
-የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለውጥ አምጭ ተግባር የፈጸሙና የሚፈጽሙ፣
-በብዙ ሰዎች የማይደፈርን ተግባር በተነሳሽነት የከወኑ፣
-ለድጋፍ ፈላጊ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት ሃገራዊ ኃላፊነት ወስደው የሠሩ[…]ኢትዮጵያውያን መሆን ይኖርባቸዋል ይላል፡፡
በመሆኑም ከላይ እንደጠቀስነው ዶ/ር መረራ ጉዲና የላቀ ሁለገብ የሆነ ችሎታና እውቀት ያላቸው ሰው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ እንደ መምህር ሰላሳ ለሚጠጉ ዓመታት ያስተማሩ፣ እንደ ምሁር እጅግ ብዙ ጽሁፎችን የጻፉ፣ እንደ ግለሰብ ኢትዮጵያዊያን ካሉበት አሳዛኝ ሁኔታ መውጣት ይኖርባቸዋል በማለት ሕይወታቸውን በሙሉ ለሕዝብ የለገሱ ሰው ናቸው መረራ፡፡ በመሆኑም ‹የበጎ ሰው ሽልማት› አራተኛው መርሐ ግብር ተገቢውን መስፈርት በማሟላት ዶ/ር መረራ እጩ መሆን የሚችሉ አገር ወዳድ፣ ቀናኢ፣ ብሎም ለፃነትና ለዲሞክራሲ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ብቁ ዜጋ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
ይህ የፌስቡክ ገፅም ስለሳቸው የሚወራበት፣ ድምፅ የሚሰበሰብበት፣ ተማሪዎቻቸው ስለ እርሳቸው የሚጽፉበትና ምስክርነት የሚሰጡበት እንዲሆን በማሳብ የተከፈተ ገፅ ሲሆን፣ ለዚህ መልካም ዓላማ የእርስዎ ድምፅ ዋጋ አለውና፤ የእጩ በጎ ሰዎች ጥቆማ ከግንቦት 24 ጠዋት 12፡00 ሰዓት እስከ ሰኔ 24 ማታ 12፡00 ድረስ የሚከናወን በመሆኑ ዶ/ር መረራ ጉዲናን፡
በስልክ፡ 0915445555
በቫይበር፡ 0915445555
በግንባር በመቅረብ፡ ለም ሆቴል ማትያስ ሕንጻ ቢሮ ቁ. 408
በፖስታ፡ 150035
በብሎግ፡ www.daneilkibret.com
በኢሜይል፡ [email protected]
ለሽልማቱ በመጠቆም እኒህን ታላቅ ሰው ተሸላሚ እናድርግ፡፡
Dr Merera is our legend!!
I LOVE HIM! DOCTOR. MARARA IS ONE OF OUR BEST MAN
yes it realy consern him
Yigebachuwal dr sew lerasu le betesbu sisera le hizbi nestanet yenoru nachew
Am happy happy happy to heaf that to acknoweledge our all time hero to a candidate for ( Good man ) award for teirr tremendous work for theirpeople, countryand even for foreign .So brothers and sisters lets confirm our love to our hero-ine.Thanks.
ahun yalenibet weqt yemeshelalemeya new ?
በዶክተር መረራ የበጎ ሰው ሽልማት ዕጩ
ሆነው በመቅረባቸው ድጋፍ ስሰጥ ከታላቅ አክብሮት ጋር ነው ፡፡
ወይ ጣጣ መራራ ጉዲና ሆነ ለ ኢትዮጵያ አሳቢ? በነገራችን ላይ መጽሀፉን አንብባችሗል? ለዚህ ነዉ ፎቶዉ ላይ እንዳያችሁት የሚስቅባችሁ። ለመሆኑ በናንተ ፈቃድ ነዉ እሱም ተስማምቶበት ፎቶዉን በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቃችሁለት? መራራ አክሮባት ፖለቲከኛ ነዉ ኢትዮጵያዊ የሚሆነዉም እንደ ባጣ ቆየኝ አይነት ነገር ነዉ ያሰቡት አልሆነም ኢትዮጵያዊነትም ከተረገጠበት ብቅ እያለ ሄደ ሰፈር የለወጡትም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ መሆንዋ አይቀሬ መሆኑን ሲረዱ ነዉ።፡ሰዉየዉ ያልሆነዉን እየጻፋችሁ ሰዉ አታሳስቱ ስለሱ ጊዜ ሲያልፍ ዜጋ ይመረምራል።
Ke shelmachus enien beshelemachu.
Yes Dr.Merera…
Filfilu,
Your brain may be smaller than that of a filfil, asshole!. Merera has exactly the same political programme in 1995, 2005 or today. He was despised by Oromo at the beginning because of his stand towards Ethiopia. He supports the idea of solving Oromo issue in the Ethiopian context. Now imbeciles like you blame him for being “unEthiopian”. That attitude is exactly why we are in a messy position in Ethiopia for the past 100 or more years.
I am supporter of him
It would be a great shame if a tribalist such as Dr. Merara is granted an award. Such an award would be no better than a laughing stock!
Long live to our Hero!!!
The first homeless professor.
Irasun mastedadr yemaychel
sele hager lemawrat beqat aynorwum.
Mengist bet kasetgne yelele indie ?
idemie lekun bemengist degaf nore .
indiyw simun techekmew lemiyayachw
seaw yemeslalu . pro. yabatu sem Asefa
indezihu ke mengist bet alwetam bilo
behig tegedo neaw yewtaw .
Ethiopia = one nation, one people, one flag, human rights for each Ethiopian, rule of law/justice, a balanced economy (no CORRUPTION!), accountability;
No tribalism, no ethnicism, no cessation!
By the way, why do not you mention Merera’s mother name and her ethnic background? Do you know that his mother is GAMMO? He is half Oromo. Ask him by calling on his phone number and viber number 0915445555. Merera hates many Oromo elites and OLF as because of identity crisis.