በትግራይ ወርቅ ለማውጣት የሚውሉ አደገኛ ኬሚካሎች የደቀኑት ከባድ አደጋ
በትግራይ እየተካሄደ ነው የሚባለው ሕገወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጣት አነጋጋሪ ጉዳይ ከሆነ ወራት ተቆጥረዋል። የአካባቢ ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎች እንዲሁም የውጭ ዜጎች ሳይቀሩ ይሳተፉበታል የሚባለው የወርቅ ቁፋሮ አሳሳቢ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጥቅም ላይ በሚውሉ አደገኛ ኬሚካሎች ምክንያት በሰዎች፣ በእንስሳት እና በአካባቢ ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ነዋሪዎች እና አጥኚዎች እየተናገሩ ነው።