አሜሪካ ግቢ ፈረሰ:: የአከባቢው ሕዝብ ሜዳ ላይ ተጥሏል:: (Photos)

መርካቶ አከባቢ ከአንዋር መስኪድ ፊትለፊት የሚገኘው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደሃ ዜጎችን አቅፎና ደግፎ የኖረው የአሜሪካን ግቢ መፍረሱን ከስፍራው የደረሱ የፎቶግራፍ ማስረጃዎች አረጋግጠዋል:: ደሃውን ዜጋ ካለካሳ እና ምትክ ቤት አፈናቅሎ በምትኩ ሃብታሞችን በቦታው ለመተካት በሚደረገው ሩጫ ላይ ዜጎች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው::ባለፈው ሳምንት በቦልጥ አከባቢ ወረገኑ የተባለ ቦታ እንዲሁ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን አቅፎ የያዘ ወደ 5000 የሚጠጋ ቤት መፍረሱ ሲታወስ ዜጎች ለምን እንፈናቀላለ በማለታቸው ከፖሊስ በተወሰደ እርምጃ መገደላቸው መቁሰላቸው መታሰራቸው ይታወሳል:: #MinilikSalsawi