ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል; 100 ያህል ሰዎችን ለሞት ተዳርገዋል::
ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል ተባለ
አደጋዎቹ 100 ያህል ሰዎችን ለሞት ዳርገዋል
ጎርፉ ተጨማሪ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅል ይችላል
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው እንደተፈናቀሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁንና መንግስትም 100 ያህል ዜጎች በአደጋዎቹ ለሞት ተዳርገዋል ማለቱን አልጀዚራ ዘገበ፡፡
በአገሪቱ በመከሰት ላይ ያሉት የጎርፍ አደጋዎች ዜጎችን ከማፈናቀል ባለፈ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች እርዳታን በማከፋፈል እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን የጠቆመው ዘገባው፤ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብር የኢትዮጵያ ተወካይ ፖል ሀንድሊም የተፈጥሮ አደጋዎቹ በቀጣይ ሰብሎችንና እንስሳትን ከማውደም ባለፈ ዜጎችን ለከፋ ችግር ሊያጋልጡ ይችላሉ ማለታቸውን ገልጧል፡፡
የእርዳታ ድርጅቶችም የጎርፍ አደጋዎቹ ቀጣይ እንደሚሆኑና ሌሎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅል እንደሚችል ግምታቸውን መስጠታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የተፈጥሮ አደጋዎቹ የተከሰቱባቸው አንዳንዶቹ አካባቢዎች የድርቅ ተጎጂ መሆናቸውንና ዜጎችን ለተጨማሪ ችግር መዳረጋቸውን አስረድቷል፡፡
Source addis admass

denun chfchfew new lezeh ye Gorf adega yedarewgun !!!
WEYANE Egziyabher yebetnachu
Mot le weyane
እግዚአብሄር ይታደገን እንጅ ምን ይደረጋል።
Ethiopian egzaber ytadegat
ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል ተባለ
እውነት በተፈጥሮ አደጋ ነውወይ የተፈናቀሉት? ስህተት ነው ምክንያቱም አደጋዎቸ የተከሰቱት ሁሉ በሰው ልጆች ተንኮልና ሴራ እንጅ ተፈጥሮ ብቻ ምክንያት አይሆንም ተውኝ/ተውን እባካችሁ ደኑን አጥፍታችሁ/አሰመንጥራችሁ የሽፋታ መደበቂያ ሆነ ብላችሁአቃጠላችሁት፣አስጠፍታችሁ አውድማችሁ/ አስወድማችሁ መሬት ተናደ ጎርፍ ሰውን በላ ብትሉን የምድራችን ሰይጣን ሰው የሚባል አጥፋ /ቀጣፊ፣ዋሾ፣አስመሳይ በወገኑ ቁማር የሚጫዎት/የምትጫዎት/ እኔ ብቻ ልኑነር የሚሉ ስግብግቦች ሞልተው ተዳራጅተው በጎርፍ፣በድርቅ፣በጦርነት ዜጎችን እያሳደዱ/እየገደሉ/ ከመኖሪያ ቤታቸው/ ሃገራቸው/ በአደጋው ምክንያት ወደኪሳቸው ገንዘብ የሚያካብቱ ስንት ሰው በላዎች አሉ ብልጠት የጥላቻ ልጅ ነው!
አሰፋ
እግዚአብሄር ይታደገን እንጅ ምን ይደረጋል።
ሌብነት እና የሙያ ድርሻ የምሁራን በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያዊነት ማለት ታማኝነት ማለት ነበር ግን አሁን በሰፈር፣በጎጥ ተደራጅተው የስርቆት የዘረፋ ማህበር ሃገር ተለወጠች!
ሌብነት በሉ እንጅ ዛሬ እየሆነ ያለው ነጠቃ ድርቅና፣ርሃብ፣ጎርፍ በሕዝብ ላይ እያደረሰ ካለው መከራና ስቃይ በጎጥ የተሰበሰቡ ሙስና ዋና ተግባር መሆኑ የማይሰርቅ ሰው እሱ ምን ይባላል መሰላችሁ ቀሽም ደንቆሮ አስተሳሰብ ያለው/ያላት/ የሚል ስም ያወጡልናል! የዘመኑ፣የሥርዓቱ ባህል ነጣቂ በሉት!
በአለፈው ሳምንት ተማሪዎች ጥያቄ ሲጠየቁ ተምራችሁ ምን ትሰራላችሁ ሲባሉ 1- በአዲስ አበባ እና በክልል የመሬት አስተዳደር መስትራና በቂ የሆነ ገንዘብ ማካበት፣2- በገቢዎች መስሪያ ቤት ተቀጥረን ብዙ ገንዘብ ማገኘት እንፈልጋል ነበር ያሉት
ቸ.ድ