በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ – VOA

ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ ጥገኝነት ካቀረቡበት ታሪካቸው ጋር ስለማይመሳሰል ነው። ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen
lemin Ethiopianoch inwashaln ? “abzagnaw ”
Ethiopiawi negne bilo ziegnet keteqeble
behoala be facebook page lay yebatun yeqotun
Be Amaregna siletf siqebater gamawn teyaze malt neaw .
Izih US betemesasay merja iyetsbesbe indale
be VOA tegltsoal . Tenqeq mallet yebjal .
Gena D C bizu political asylum wesdew
le terrorist Eritrea beqetrgnet yemisru bebzat
alu .
ህዳር 29 በሃረር ከተማ ለሚከበረው በአል የኢህአዴግ አባል የሆኑት አቶ በላይነህ ተስፋዬ ለእንግዶች ማረፊያ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ለመገንባት የነጋዴዎችን እና ነዋሪዎችን ቤቶች ማስፈረሳቸውን የተፈናቀሉት 30 ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ሲሆኑ፣ እነዚህ ቤተሰቦች ሲፈናቀሉ እስከ 300 የሚደርሱ የቤተሰቡ አባላት በመንግስት ላይ ህዝብን በማነሳሳት መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ አድረገዋል የሚልና የሽብርተኝነት ክስ ተከፍቶባቸዋል።የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ወጣት አባላት በአመራሩ ላይ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ታሰሩ:: የሃረሪን ክልል በመምራት ላይ ያለው የኢህአዴግ ተለጣፊ ድርጅት የሆነው ሀብሊ ወጣት አባላት በድርጅቱ መሪዎች ላይ ያነሱትን የሙስና ክስና የመልካም አስተዳደር ችግር በፌስቡክ እና በስብሰባዎች ላይ በማጋለጣቸው ተይዘው መታሰራቸውን የክልሉ ወኪላችን ተገልጿል።
ወጣቶቹ በሙስና የተጨማለቁ መሪዎች ወርደው ለፍርድ ይቅረቡ፤ የመልካም አስተዳደር ችግር ይብቃ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት የወሰዱትን ገንዘብ ይመልሱ፣ ከስልጣን ወርደውም ለፍርድ ይቀርቡ የሚሉት ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ሰንብተዋል። ለሁለት ቀናት በተደረገው ግምገማ፣ ወጣቶቹ ያነሱዋቸው ጥያቄዎች የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱላሃዲን ማእከል ያደረጉ ነበሩ። ፕሬዚዳንቱ በውጭ አገራት ከሚኖሩ የክልሉ ዜጎች የተላከውን 80 ሚሊዮን ብር የእርዳታ ገንዘብ ዘርፈዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣ እሳቸውም ገንዘቡን መቀበላቸውን አምነው፣ ነገር ግን ገንዘቡን ውጭ ሃገር ሄደው የጠፉት ባለቤታቸው መውሰዳቸውንና እሳቸው ከችግሩ ንጹህ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከውጭ የመጡትም ሆነ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ የሊጉ አባላት የፕሬዚዳንቱን ማስተባባያ ያልተቀበሉት ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱ በህግ ይጠየቁልን የሚል ጠንካራ አቋም አንጸባርቀዋል።
ግምገማውን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱን ተችተዋል የተባሉ እና ለወጣቶቹ መረጃ በመስጠት ተቃውሞውን ያስተባብራሉ እንዲሁም ለፕሬዚዳንቱ ህይወት አደጋ ፈጥረዋል የተባሉት የፕሬዚዳንቱ የግል ጠባቂና አዛዥ አቶ ባህሩ በፕሬዚዳንቱ ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተቃውሞውን ይመራሉ፣ በፌስቡክም የፕሬዚዳንቱን ስም ያጠፋሉ ተብለው በሌሊት እየታደኑ የታሰሩት የሊጉ አባላት ወጣት መረሃ የሱፍ፣ ወጣት ብሂር አብዲ፣ መምህር አብዲ አህመድ ፣ ወጣት አፈንዲ መሃመድ እንዲሁም ወጣት ነይብ ሲሆኑ፣ በመንግስት ላይ ህዝብን በማነሳሳት መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ አድረገዋል የሚልና የሽብርተኝነት ክስ ተከፍቶባቸዋል። ግንቦት7 እና 8 የዋለው ፍርድ ቤት በወጣቶቹ ላይ የቀረበውን ክስ ከተመለከተ በሁዋላ ፣ ፖሊስ የማጣራት ስራውን በ20 ቀናት ውስጥ አጠናቆ እንዲያቀርብ ለግንቦት 29 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የወጣቶቹን መታሰር ተከትሎ የሃረሪ ወጣቶች ግንቦት10 ፣ የታሰሩ ጓደኞቻችን ይፈቱ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር የሚል የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊስ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ተገኝተው ተቃውሞ አድርገዋል። በፓርቲው ውስጥ እንዲህ አይነት እንቅስቃሴ ሲደረግ የመጀመሪያው መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ከህዝቡ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድና ውጥረቱን ለማርገብ 4 የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባላት ከስልጣን እንዲነሱ ተደርጓል ብሎአል።
በሙስና ወንጀል ተገምግመው ከሃላፊነት ከተነሱት መካከል የሃብሊ አባል፣ ስራ አስፈጻሚና የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የሊጉ አባልና የሃረር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እንዲሁም የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ ያሲን ሁሴን፣ የሊጉ የስራ አስፈጻሚ አባል እና የትምህርት ቢሮ ም/ል ሃላፊ እና የወጣቶች ሊግ ሊ/መንበር አቶ ሙክታር ሳልህ፣ እንዲሁም የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪና የአደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ሃሊድ አልዋን ናቸው። አቶ ያሲን ቀደም ብሎ የቀበሌ 10 ጽ/ቤት በሁዋላም የህዝብ ጤና ጣቢያ የነበረውን ቤት ፣ ጤና ጣቢያው ወደ ሌላ አካባቢ እንዲዛወር በማድረግ እና ቤቱን በ1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲታደስ በማስደረግ የእርሳቸው የግል መኖሪያ እንዲሆን ማስደረጋቸው ህዝቡን ማስቆጣቱን የክልሉ ፕሬዚዳንት የቀድሞ ባለቤት ለእርዳታ የተላከውን ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸውን ተመለከተ ዘገባም ሽኩቻው በሃብሊ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአሃብሊና በኦህዴድ መካከል መሆኑንም ተገልጿል።
That is a good measure we should offer our support to the concerned gov by providing the necessary information.
Because a number of Tigres and TPLF slaves are splashed over Europe and USA as political refuges while they are still remain loyal to the aparthied regime in Ethiopia.
Though they can fool others for a while the truth would be revealed in time.