አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች – VOA

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ውስጥ በመካከለኛ ርቀት 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ19 አመትዋ አትሌት ኩለኒ ገልቻ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአትሌት ጓደኛዋ እጅ ህይወቷ በስለት ማለፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብን በምንጭነት ጠቅሶ ለአሜሪካ ድምጽ ገለፀ።

የአትሌት ኩለኒ ገልቻ ገዳይ እንደሆን የተጠረጠርው ጓደኛዋ እራሱ እጁን ለፖሊስ በመስጠቱ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እንደተጀመረ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የጥናት ባለሞያ አቶ ስለሺ ብስራት ገልጸዋል።

አትሌቷ ለወደፊቱ በጣም ተስፋ ያላት አትሌት እንደነበረች ወጤቷ ይናገር ነበር ብለዋል። ፌደሬሽኑ በአትሌት ኩለኒ ሞት እና የአሟሟት ሁኔታ በጣም ማዘኑን አቶ ስለሺ ጠቁምው ሴት አትሌቶችን ከእንዲህ አይነት አደጋ ለመታደግ የተለየ ሥልጠና እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የአትሌት ኩለኒ ገልቻ አስከሬን በምኒሊክ ሆስፒታል ምርመራ ሲደረግለት ቆይቶ ግንቦት 5 ቀን 2008 ዓ. ም. ላይ በትውልድ አካባቢዋ ኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ የቀብር ስነስርአቷ መፈጸሙ ታውቋል።

ጽዮን ግርማ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የጥናት ባለሞያ አቶ ስለሺ ብስራትን ስለዚሁ አነጋግራ አጠር ያለ ዘገባ አሰናድታለች። ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen

4 Comments on “አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች – VOA”

  1. I can’t say anything except rest in please I advice people ( specially ) young to avoid such horrible incedient first talk with ur special & honest someone otherwise leave that person not to go unnecessary action time will manage everything .Otherwise by doing such action there is rest in the rest of ur life. Again rest in pease .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*