በተለያዩ አካባቢዎች ጎርፍ በሰው በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው::400 ሺሕ ሰዎች ለጉዳት ይጋለጣሉ ተብሏል
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጣል ላይ በሚገኘው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተፈጠረው ጎርፍ የሰው ሕይወት ከመቅጠፍ በተጨማሪ፣ በማሳ ላይ የሚገኙ ሰብሎችና የመንገድ አውታሮች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ እየገለጸ ነው፡፡
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በቀናት ልዩነት ለሰዓታት ሳያቋርጥ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ከሰው ሕይወት በተጨማሪ በርካታ የቤት እንስሳት፣ ከ560 ሔክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ የሚገኝ ሰብል መውደሙ ተገልጿል፡፡ ይህ ጎርፍ ከሮቤ ወደ ጎሮ የሚወስደውን መንገድ በመስበሩ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተገቷል፡፡
በምሥራቅ ሐረርጌ የጣለው ዝናብ ደግሞ የሁለት ሕፃናትን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ ከድሬዳዋ ወደ ሐረር የሚወስደውን መንገድ መስበሩ ተገልጿል፡፡
በምዕራብ አርሲ የጣለው ከባድ ዝናብ ወደ ወላይታ በሚወስደው መንገድ ላይ ከፍተኛ መሰንጠቅ አስከትሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ 18 ሜትር ርዝመትና ሦስት ሜትር ስፋት ያለው የመሬት መሰንጠቅ አስከትሏል፡፡
አቶ ሳምሶን እንዳሉት ክስተቱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲገታ በማድረጉ፣ ባለሥልጣኑ ተለዋጭ መንገድ ቢያዘጋጁም ተለዋጭ መንገዱም በጎርፍ እየተመታ በመሆኑ ጉዳዩን ውስብስብ እንዳደረገው አመልክተዋል፡፡
ከሞጆ ወደ ሐዋሳ በሚወስደው መንገድ መቂ አካባቢ የጣለው ከፍተኛ ዝናብም መንገዱን ከባድ ደለል በማልበሱ የትራንስፖርት ፍሰቱ ላይ እንከን መፈጠሩ ተመልክቷል፡፡
ከዚህ ባሻገርም አሰላ ከተማን የመታው ጎርፍ የከተማውን መንገዶች መሰባበሩ ተገልጿል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተው ከፍተኛ ዝናብ በአፋር፣ በሰሜን ሸዋ (ሸዋ ሮቢት) ስልጤ ዞን፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ አርባ ምንጭ፣ ደቡብ ወሎና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ የብሔራዊ ሥጋት አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እየጣለ ባለው ከፍተኛ ጎርፍ ምክንያት እየተከሰተ ያለው ጎርፍ ጉዳት እያስከተለ ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በብሔራዊ ደረጃ ዕቅድ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ሦስት የተፋሰስ ባለሥልጣንና ሁለት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ያሉበት የተፋሰስ ከፍተኛ ምክር ቤት ሚያዚያ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በሰጠው ትንበያ፣ በአገሪቱ 400 ሺሕ ዜጎች በጎርፍ ጉዳት እንደሚደርስባቸው፣ 180 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ከመኖሪያቸው እንደሚፈናቀሉ ገምቷል፡፡
አቶ ምትኩ እንደሚሉት
የችግሩ ሰለባ ለሆኑ ዜጎች 200 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እየተሠራጩ ነው፡፡
Reporter Amharic

Take time?
taxii self lay egnam adega lay nen. gorf terargo yiwesidenal
መከራዋ የበዛ ሃገር ስንት አመት ትድማ (በጦርነት፣በድርቅ፣በርሃብ፣ በድህነት፣ በስደት፣በአፈና በጭቆና )ሂሳብ እያወራረደ ያለችና ሃገርና ሕዝብ ምን ይሆን ጥፋታችን ? ለመሆኑ የጎርፍ ምክንያት የሆነውስ ማን ነው ? ሰው በሃብት፣በሃገሩ፣በወገኑ ላይ በመዝመቱ ደኑን ፣ጫካውን ማሳውን በማጥፋቱ እነሆ ዛሬ በሃገሪቱ የተከሰተው ድርቅ በጎርፍ ተተክቶ ኢትዮጵያን ወደውርደት ስቃይ እያበዛባት ነው!ለዚህ ተጠያቂው ማን ነው ትላላችሁ? የሃገሪቱ ምሁራንስ እጅ የለበትም ትላላችሁ?
ይህ ጎርፍ፣ድርቅ፣ርሃብ፣ስደት እያለ ሕዝብ ስራ እንዳሰራ፣ወጣቱን፣ ሴቱን አዛውንቱን ሁሉንም በስብሰባ ስራ ማስፈታት ድህነትን ርሃብን ማንገስ አይደለምን? አዎን ስንት አመት እንራብ፣እነጠማ፣ስደት እንሂድ/እንንጎድ/ ? ለምን ወሰን አናበጅለትም እንዴት? በማን? መቼ?
ስብሰባ የደንቆሮዎች መጠራቀሚያ ነው እንጅ አሁን በኢትዮጵያ ስብስባ አስፈላጊ ሳይሆን አጥፊ ነው!
ዘሩ
እባካችሁ አንብቡት/አስነብቡት/ የበኩላችሁን ተወጡ! አደራ!
ድሃዎች ለምን የድሃ ድሃ ሆኑ? ለምንስ ርዳታ ይቀበላሉ? ርደታውስ ለማን? እውነት ድሃ ናቸውን? ወይ ልማድ አደረጉት?
በዜጎቾ ድህነትን የተረከበች ሃገር ማንናት? ስንት አመት እንራብ ፣እንጠማ፣እንሰደድ፣እንገደልመ፣እንታፈን፣እንሰቃይ፣አይበቃንም!
ስብሰባ ዳቦ
መከራዋ የበዛ ሃገር ስንት አመት ትድማ (በጦርነት፣በድርቅ፣በርሃብ፣ በድህነት፣ በስደት፣በአፈና በጭቆና )ሂሳብ እያወራረደ ያለችና ሃገርና ሕዝብ ምን ይሆን ጥፋታችን ?ለመሆኑ የጎርፍ ምክንያት የሆነውስ ማን ነው?ሰው በሃብት፣በሃገሩ፣በወገኑ ላይ በመዝመቱ ደኑን፣ጫካውን ማሳውን በማጥፋቱ እነሆ ዛሬ በሃገሪቱ የተከሰተው ድርቅ በጎርፍ ተተክቶ ኢትዮጵያን ወደውርደት ስቃይ እያበዛባት ነው!ለዚህ ተጠያቂው ማን ነው ትላላችሁ? የሃገሪቱ ምሁራንስ እጅ የለበትም ትላላችሁ?
ይህ ጎርፍ፣ድርቅ፣ርሃብ፣ስደት እያለ ሕዝብ ስራ እንዳሰራ፣ወጣቱን፣ ሴቱን አዛውንቱን ሁሉንም በስብሰባ ስራ ማስፈታት ድህነትን ርሃብን ማንገስ አይደለምን? አዎን ስንት አመት እንራብ፣እነጠማ፣ስደት እንሂድ/እንንጎድ/ ? ለምን ወሰን አናበጅለትም እንዴት? በማን? መቼ?
ስብሰባ የደንቆሮዎች መጠራቀሚያ ነው እንጅ አሁን በኢትዮጵያ ስብስባ አስፈላጊ ሳይሆን አጥፊ ነው! ስብሰባ የሚጠቅማችው ሰዎች ቸሉ እነሱም ካድሬዎችን፣ሰላቶችን፣የሰው ምስጦችን የሃገር ጠላቶችን በአፋቸው ለሚኖሩ እንጂ ገበሬውን ለዘላቂ ድህነት/ርዳታ/ተቀባይ/በሃገሩ ተንበረካኪ እንድሆን እያዘጋጀው ነው! ስለዚህ ከጎሳ በጎጥ አስተሳሰብ
ብትቀጣ ምን ይመስላችኋል?ድርቅ በጎርፍ ተተካ እየበላን ነው! በጋራ መፍትሔውን እንፈልግ?
ቸር ይግጠመን!
ዘሩ
The solution is turn yourself to almighty GOD. Are you !!!.