ጠንካራ የፍትህ አካላትን ለመገንባት እና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ የወያኔን አገዛዝ መደምሰስ ግዴታ ነው:: ‪

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ፍትህ ካለ ሰላም አለ::ፍትህ ካለ እድገት አለ:;ፍትህ ካለ እስር ቤቶች በንጹሃን አይሞሉም:: ፍትህ ካለ ነጻነት እና መብት አለ:; ፍትህ ካለ የሚሸማቀቅ አይኖርም:: ፍትህ ከተረጋገጠ ሕጎች ሁሉ በበላይነት የሕዝብ ይሆናሉ::ይህ ሁሉ የሚረጋገጠው በኛ ለኛ ከኛ ነው:: እኛ አዎ እኛ በአሁን ወቅት እና ጊዜ ላይ ቆም ብለን ካሰብን የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር በራሳችን ትግል ነጻነታችንን እና መብቶቻችንን ታግለን ማረጋግጥ እንዲሁም አምባገነኖችን ላንዴና ላያዳግም መደምሰስ ነው::

በኢትዮጵያችን የሰብ አዊ መብት ጥሰት የመብቶችና የነጻነቶች ገፈፋ የፍትህ ድንቁርና መንሰራፋቱን እናውቃለን ደጋግመን ብናወራው ለቀባሪው ጆሮ ፍሰት መፍጠር ካልሆነ በስተቀር ምንም አይፈይድም የሚፈይድልን ነገር ቢኖር እነዚህን እኩይ ተግባራት ታግለን በማስወገድ የሕግ የበላይነትን እና የራሳችንን ነጻነት እና መብት ማስከበር ነው:: አሁን ማወቅ ያለብን ይህንን ብቻ ነው::
ፍትህ ፈላጊ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እስከፈለግን ድረስ ማንም ሰው ወይም አካል ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም:: ህገ ወጥነትን መታገስም በራሱ ወንጀልን ማበረታታት ነው:: ስለዚህ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የማድረገ ትግላችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት:;ለሕግ የበላይነት የምናደርገው ትግል በተግባራዊ ስራዎች እና ግንዛቤን ከበፊቱ በበለጠ በመፍጠር ሕዝባዊ ሰቆቃዎችን ለማስቀረት ታላቁን ስኬት ከግብ ለማድረስ ከጀመርነው ጉዞ ማፈግፈግ አያስፈልግም ::ሕዝቡ በሃገሪቱ ላይ የሚካሄደውን እና እየተካሄደ ያለውን የወያኔዎች አምባገነን አገዛዝ የፈጠረውን ጸረ ፍትህ አካሄድ አብጠርጥሮ ያውቃል ::ይህ ማለት ደሞ የለውጥ ሃይሎች የሚጠበቅባቸውን የለውጥ ስራዎች በመስራት ትግሉን ከግብ ለማድረስ አስፈላጊዉን የትግል መንገዶችን በመጠቀም ሕዝብን ከጎን በማሰለፍ ድሉን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል::

በሃገራችን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የምእራባውያንን አሳሳቢ በሚል የታጀበ መግለጫ አሊያም ድጋፍ መጠበቅ ለኛ ምንም አይፈይድም::እና ጠንክረን ከታገልን በአምባገነኖች ጫና ስር የወደቀውን ሕዝባችንን ነጻ ለማውጣት በምንገፋው ትግል ላይ የምናሳየው የትግል ታማኝነት እና ስኬት ምእራባውያንን ራሳቸውን ልንማርክ እና ሳንጠይቃቸው እርዳታውንን ለብሄራዊ ጥቅማቸው ሲሉ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሳይታለም የተፈታ ነው:: ስለዚህ እኛ ራሳችን በጋራ ሆነን ይህንን አምባገነን ስርአት ለመጣል ወደፊት መገስገስ ያለብን እኛው በኛ ሲሆን የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ካወቅን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ወገባችንን አጥብቀን እንታገል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

2 Comments on “ጠንካራ የፍትህ አካላትን ለመገንባት እና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ የወያኔን አገዛዝ መደምሰስ ግዴታ ነው:: ‪”

  1. ቆንጅት ስጦታው “ጠንካራ የፍጥ አካላትን ለመገንባት እና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ የወያኔን አገዛዝ መደምሰስ ግዴታ ነው” እውነት ነው። ይህን የሚተካ ግን በመለስተኛ ስምምነትም ቢሆን ተግባብቶ የሚሰራ የለም ለማለት ያስደፍራል። ችሎታው ኣለ። ተባብሮ በኢትዪጵያዊነት ጥላ ስር የመስራቱ ግን ኣልተገነባም። ያብዛኛው ተቃዋሚ ድክመት እዚህ ላይ ነው። መለስ ዘይናዊ በከፈተላቸው የዘር በሽታ ተለክፈው ነው ያሉት። የመዳን ኣይናቸው ሉቦናቸው ተዳፍነዋል። የእሳትና ቪሽን መልካም ወይይት ነው; ግን ድብቅ መልእክት ኣለው። ድሮም ኢሳያስ ኣፈወርቂ እያሞገስክ የሚመጣ ለውጥ የለም ለዚህም እነ ኣቶ ስብሃት ይቀድማሉ። ስለዚህ እውቀት ብቻ ሳይሆን ተሰባስቦ በኢትዮጵያዊነት ጥላ መስራት መጀመር፣ ማጎልበት፣ መስፋፋት ይጀመር።

  2. Woyanes masweged yehizb tibibirin yiteyikal. Hizbum yitebaberal enam woyaneese yiwegedal. Ageritan gin manew yemikebelat? Alamachewis mindinew? Esti lehizb yabrarut. Yefelegachihutin media tetekemu: ESAT, VOA. OMN: min lemadreg new ageritan sitimeru? Alamachihun yabrarut.

    A very short proposal has got details of introduction, objective, methodology, work plan or time plan.
    Leading the country is a big task, and it needs short term and long term objectives. Those who prepare these proposals are required to bring it forward. But we haven’t seen anything yet. Can we also lead the country by trial and error like Mengistu, Meles,and like the TPLF. Do we think that these peoples will live like the twenties century? In short, opposition’s should come together and put their proposals forward on how they are going to lead the country.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*