ይሄ ከማላቆመው መልክቶቼ ውስጥ አንዱ ነው ! ( ሄኖክ የሺጥላ )

ይሄ ከማላቆመው መልክቶቼ ውስጥ አንዱ ነው ! ( ሄኖክ የሺጥላ )

የሃገራችን ፖለቲካ ፥ ትችት እና ዘለፋ እንደ ርችት እያብረቀረቀ የሚዘንብበት የነገር ሸራተን ነው ። ትናንት ወዳጅህ የነበረ ፥ ዛሬ እንደ አማዞን እባብ ቆዳውን ሸልቅቆ ሙልጭ አድርጎ ሊሰድብህ ይችላል ፥ ሃሳብህን ሳይሆን ሱሪህን ሊያወልቅ ይፈልጋል ፥ እሱ ራሱ የወጣለት ጠንጋራ ብሄርተኛ ሆኖ ፥ ኣይኑን በጨው አጥቦ « ለምን ስለ አንድነት አትሰብክም ይልሃል » ፥የሌሎችን ቁመና ሲያፍረጠርጥ ከርሞ ፥ የሱ ቁመና ሲነካ ፥ ኣደለም ቁመናዬን እዳሪዬን እንኳ መተቸት ( መንካት ) መብትህ አይደለም ሲል አያፍርም ፥ ዲሞክራሲ አቅም የሚኖረው እና ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው እሱ ለሚፈልገው አላማ ሲውል ብቻ ነው ፥ ኢ ፍትሃዊነት ትርጉም የሚኖረው እሱ ሲናገረው ብቻ ነው ፥ የነፃነት ጥያቄ በሱ ልሳን ካልሆነ በሌሎች ሰዎች ልሳን መነገር የማይችል የመለኮት ቃል አስመስሎ ይቀርፅልሃል ። ሃሳቡን ፥ አካሄዱን ፥ መንገዱን እና መድረሻውን እንደ አንድ ተቆርቋሪ ዜጋ « ይህ እንዳይሆን እንዲህ ይሁን » ብለህ ስታመለክት ፥ ከግንዛቤህ ከመማር ፥ የተሳሳትከውን በጨዋ መንገድ ከማረም እና ከማስተማር ይልቅ ከ የ ፓል ቶኩና እና መሰል ቦታዎች በጋራዥ ሴል ( በብላሽ ይለዋል ጉራጌ ) የተገዙ የሳይበር ወታደሮቹን ጥቃት እንዲፈጥሙ መረጃ ይሰጣል ።

እርግጥ ይህ አካሄድ እነ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማትን ከሜዳ ኣስወጥቶ ሊሆን ይችላል ፥ እነ ሳይንቲስት ጥላሁን ይልማን አስደንግጦ ( ወይም ተስፋ አስቆርጦ) ይሆናል ፥ ግን ለሁሉም ይሰራል ማለት አይደለም ። ፖለቲካው ምህዋሩን በማይረቡ ሰዎች ዙሪያ ሊቀልስ ና ሲሽከረከር ስናይ ዛሬ አዲስ ኣይደለም ፥ ትናንት አዲስ ኣልነበረም ፥ ነገም አዲስ አይሆንም ። እነ አባ መላ በአንድ ጊዜ የግሎባል አሊያንስ እና መሰል ድርጅቶች ወግ ከዋኒ ሆነው ወደፊት የመጡት በእውቀታቸው ሳይሆን ባላቸው ገደብ አልባ የመባለግ ብቃታቸው ነበር ። ከነሱ የብልግና እውቀት መጠቀም የሚሻ ፥ በደካሞች መሃል ትልቅ ሆኖ መታየት የሚሻ ትንኞችን ኢየመረጠ የደረቀ ባሊ ላይ ማሰማርቱ የምንነቱ መገለጫ ነው ። እርግጥ እንደዚህ አይነት ሰዎችን ከላይ እንደገለጥኩት «በርካሽ ከጋራጅ ሴል ላይ» ልታገኛቸው ትችላለህ ፥ ግን እንደዚህ አይነት ደካማ ፥ ነውረኛ እና አሳፋሪ ሰዎችን ወደፊት በማምጣት ለውጥ ማምጣት እንችላለን የሚል ተቋም ይሁን ኣቋቋም ለምን ተተቸሁ ብሎ አካኪ ዘራፍ ሲል ብትሰማው « ማነው ልክ » ብለህ ራስህን ትጠይቅ ይሆናል እንጂ አካኪ ዘራፉ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እውነት ኖሮት ያንተን የእምነት ተራራ በፍርሃት ጨረሩ ሊገፋ እያስችለውም ።

የኛ ፖለቲካ ከሞላ ጎደል እውነትን በመፍራት እና የተናገረንን በማስፈራራት ላይ የተመሰረተ ነው ። ለራሱ ክብር የሌለው ሰው ሁለቱንም ሲያደርግ ልታየው ትችላለሁ ፥ ከዚህ ለራሱ ክብር ከሌለው ሰው ያነሰው ሰው ደሞ በዚህ ክብረ ነክ የሚደርስበትን ዘለፋ ፥ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመፍራት እንደ ቀንድ አውጣ ብርድልብሱ ውስጥ ተደብቆ « ፖለቲካ ለምኔ » ሲል ልታገኘው ( ልታየው) ትችላለህ ። በዚህ የመፍራት እና የማስፈራራት ትብታብ የተጠመዱት ፥ የወደቁት እና መነሳት ያቃታቸው ፥ በግሩፕ ዘለፋ ፥ በህዝባዊ ዛቻ እና በግብረ ሃይል ጥላቻ ከሜዳ እንዲወጡ የተደረጉት እና እጅ ሰጥተው የወጡት ( የወደቁት ) ፥ በኔ እይታ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ምን እንደሆነ የማያውቁ ናቸው ፥ በኔ ግንዛቤ « ተሳዳቢው » ከኔ በኢትዮጵያዊነት ይበልጣል ብለው ያመኑ ናቸው ፥ ተቀጣሪው ወይም አቃጣሪው የተሻለ የሰውነት አቅም አለው ብለው ሽንፈትን የተቀበሉ ደካሞች ናቸው ። ይህ ግን ልክ አይደለም ።

በሃገራችንም ሆነ ከሃገራችን ውጭ ፥ ሀገራችንን በተመለከተ የሚደረግ ማንኛቸውም ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳባችንን የመሰንዘርም ሆነ ቢሆን ጥሩ ነው ብለን የምናስበውን ነገር የመናገር መብት አለን ። ይህንን መብት መለስ ዜናዊ አልሰጠኝ ፥ አያስጠብቅልኝም ፥ ይህንን መብት ብርሃኑ ነጋ አልሰጠኝም ፥ ታግሎም ኣያጎናፅፈኝም!! ይህንን መብት ከማንም ሳይሆን እንደ ሰው ከእግዚያብሄር ያገኘሁት ምንነት ነው ፥ ማንነት ነው ። ብርሃኑ ቢሳካለት ምናልባት ለተፈጥሮ መብቴ እውቅና ይሰጥ ይሆናል ፥ ባይሰጥ ግን እሱ እነ መለስን እንደተቃወመው እኔ ደሞ በተራዬ እሱን እቃወመዋለሁ ። ያንን ያህልም ተራ የምጠብቅ አይመስለኝም እንደውም !

ለሃገራቸው በየ በርሃው መስዕዋት እየከፈሉ የሚገኙ ታጋዮች በመጀመሪያ ነፃ የሚያወጡት ራሳቸውን ነው ብዬ ነው የማስበው ። የወያኔም ትልቁ ክሽፈት ራሱ ነፃ ሳይወጣ ሌሎችን ነፃ ለማውጣት መታገሉ ላይ ይመስለኛል ። የሃሳብ ነፃነትም ሆነ የመሰብሰብ መብት በድህረ ወያኔ ስርዓት የተነፈግነው ፥ እኛ ሳንሆን ወያኔ ራሱ ነፃ ስላልሆነ ነው ። እኛማ ነፃ ነን ፥ ነፃም ስለሆንን ነው የነፃ ሰው ባህሪ ያሳየነው ። የመናገርም ሆነ የመፃፍ ነፃነት የነፃ ሰው ባህሪ ነው ። ያንን ማድረግ አትችልም የሚልህ አካል ግን ያንን ነፃነት የማያውቅ እስረኛ ስለሆነ ነው ። ለዚህም ይመስለኛል ካርል ማርክስ የዘመናዊ ሰው መነጠል ( The Alienation of Modern Man ) በተባለው መጥሃፉ

<< The Germans toured us, used a poison gas to massacre us and even put us in a furnace, it is only because we are free>> ። የምንታሰረው ፥ ስንጥፍ የምንነቀፈው ፥ ስንናገር የምንፎተተው ፥ ስንደፍር « ኩም » አድራጊው የበዛብን እኛ ነፃ ስለሆንን ነው ። ለምን ፥ እንዴት ፥ እንዲህ ባይሆንስ ፥ ይሄ ቢሆንስ የሚል ሁል ጊዜም በእንቅልፍ ልቡ የሚኖር ስላለመሆኑ ማሳያ ነው ። ስለዚህ ሰድባችሁ የምታቆሙት ፥ አብራችሁ የምታስበረግጉት ፥ አሲራችሁ የምትጥሉት ፥ ወጥናችሁ የምታሰናክሉት ማንነት ትከሻችን አይሸከምም ። የተወሰነ ደረጃ መሄድ ትችሉ ይሆናል ፥ አራት ወይም አስር ሰዎችን አሳፍሮ ከጫወታ ውጭ ማድረግ ይቻል ይሆናል ፥ ሁሉንም ግን በአንድ አይነት መንገድ ማሸነፍ አይቻልም ። እንዲህ ያለውን ሰው ለማሸነፍ ብቸኛ መንገዱ ግን መብቱን ማክበር ብቻ ነው ።

መልክቴ ከወንዚያ ወዲህ ማዶም ወዲያ ማዶም ላላችሁት ነው ። መፃፍ ፥ ማጋለጥ ፥ ማስተማር ፥ ክርክር መፍጠር ፥ ጠያቂ እና መሪማሪ ትውልድ እንዲፈጠር የአቅማችንን ማድረግ እንቀጥላለን ። ከዚያ እኩል ተንኮሉ ፥ ሴራው ፥ ደባው እንደሚኖርም እናውቃለን ። ያፈቀሩን ለምን ጠሉን ብለን አይደለም የምንታገለው ፥ ወይም እንደ አንዳንድ ግብዞች በግሩፕ ፍቅር ሰክሮ ፥ በጋርድ እና በ ከበባ ለመሄድም አይደለም ። አላደግንበትም ። ከሊስትሮ ጋ ኳስ ተጫውተን ፥ ከቆሎ አዟሪ ጋ ተጋፍተን ነው ያደግነው ። የህዝብ ልጆች ነን ! አስተዳደጋችን አድር ባይነትን አይፈቅድም ! ማስመሰልን ደባል አድርጎ መኖር አይችልም ። ለድሃ መቆምህን ለማሳየት ስለ ድሃ ኣታውራ ፤ ከድሃ ጋ ኑር! ከድሃ ጋ ተዋለድ ፥ ከድሃ ጋ ብላ ፥ ከድሃ ጋ ጠጣ። ስለ ነፃነት መቆምህን ለማሳየት ጥቅስ አትጥቀስ ፥ አንተን ጠቅሰው ፥ ስህተትህን ነቅሰው የሚናገሩትን የማድመጥ ልምድ ይኑርህ ። ሃቀኝነትህን በምታገኘው ላይክ እና በያዝከው ማይክ ልክ አትለካው ፥ ሃቀኝነትህን ሌሎችን ለማዳመጥ ባለህ ቅንነት ልክ ለካው ! ይሄ ከማላቆመው መልክቶቼ ውስጥ አንዱ ነው !

ቸር እንሰንብት ( ሄኖክ የሺጥላ )

Henoke Yeshetlla's photo.

17 Comments on “ይሄ ከማላቆመው መልክቶቼ ውስጥ አንዱ ነው ! ( ሄኖክ የሺጥላ )”

  1. Keep it up as a life time principle what you write must be inner you Heni b/c this is a right value which came out from the better understanding of freedom and moral excellence. Expect unexpected chalenges from TPLF I work with them they fear such personality and nationalism as of Haydrogen bomb.

  2. Very balanced article. ይህንን መብት መለስ ዜናዊ አልሰጠኝ ፥ አያስጠብቅልኝም ፥ ይህንን መብት ብርሃኑ ነጋ አልሰጠኝም ፥ ታግሎም ኣያጎናፅፈኝም!! That is your god given right.

  3. Henoke! Your message is so constructive and good lesson for those who are playing and gambling on peoples struggle against the brutal tplf bandits. Please don’t give up:GOD BLESS YOU!!!

  4. Mesadeb hulie yeminor yimeslal.
    Biyans enkua mashmuaTeTna habet ayqerie new.
    Glfteña moltual dulana Tyit miTeqem.
    Be mesedebu, bemezelefu tesemtot afro weim ferto tglun mitew bzu ale.
    Be enie eyita manñawm tagay begara smmnetu meTnat alebet. Rasun ende tera tagay qoTro, guadochun mezlef yelebetm.
    tkkl new yalewn hasab bethtna menagere Tru new.
    Chgru mimeTaw enien man akloñ, enie neñ aragi feTari, enie yalkut yihun bemnlbet gizie new.
    BergT aTfi hasab miyaqerbu sewch yinoralu yan gn beslt new magaleTna mastekakel.
    Hasabun aqrabiwn sanashemaqq.
    Maweraw sle politika srjit new.
    Gn le degafiwechm cimr new.
    Rasun yalkabe beqelalu afrona tebesacito aynkotakotm.

  5. Mesadeb hulie yeminor yimeslal.
    Biyans enkua mashmuaTeTna hamiet ayqerie new.
    Glfteña moltual, dulana Tyit miTeqem.
    Be mesedebu, bemezelefu tesemtot afro weim ferto tglun mitew bzu ale.
    Be enie eyita manñawm tagay begara smmnetu meTnat alebet. Rasun ende tera tagay qoTro yinqesaqes.
    Guadochun mezlef yelebetm.
    tkkl new yalewn hasab bethtna menagere Tru new.
    Chgru mimeTaw enien man akloñ, enie neñ aragi feTari, enie yalkut yihun bemnlbet gizie new.
    BergT aTfi hasab miyaqerbu sewech yinoralu, hasabachew miwaxq, smmnet mayakebru yinoralu, yan gn beslt new magaleTna mastekakel.
    MeTfo hasab aqrabiwn sanashemaqq mastekakel yichalal.
    Maweraw sle politika drjit new.
    Gn le degafiwechm cimr new.
    Rasun yalkabe beqelalu afrona tebesacito aynkotakotm.

  6. ጥሩ አስተያየት ነው።ያነበብነዉን በልቡናችን ያሣድርብን።የሐገሬ ምሑራን ፖለቲከኞች እጂግ ወደኋላ የቀሩ እዉቀትን በክፍል ቆጠሩት እንጂ ሊኖሩበት እና ሊያስኖሩበት የማይፈቅዱ እንደ ጣኦት እነርሱ ብቻ እንዲመለኩ የሚፈልጉ ናቸው።አዲሡ ትዉልድም የእነዚህን ከዘረኝነት ያልፀዱ ምሑራን ሠለባ እየሆነ ሣየዉ እጅግ አዝናለሁ።እስቲ እራሳችሁ ፍረዱ እነዚህ ንጉሡን አስለቅሰዉ ከወታደሩ ስርዓት ጋር ገለዉ፣ አስገድለዉ፣ተገድለዉ በሕይወት የተረፈዉም በስደት ያለው ያትዉልድ ምሑር ከአንደበታቸው የሚወጣው አፀያፊ ቃላት ለሰሚው አሣፋሪ ነው የሚገርመው ይሕ ትዉልድ ለእንደዚህ አይነት ምሑር ማጨብጨቡነዉ።ይሕ ትዉልድ ከዚያኛው ትዉልድ በብዙ ይለያል የራሱ የሆነ ዘፈን፣ለቅሶ፣አለባበስ፣አነጋገር ዘይቤ፣አመጋገብ ወዘተ አለው።ስለዚሕ እናንተ የጥንት ሠዎች ይሕን ትዉልድ በዘረኝነት አትተብትቡት።ብዙ ወጣቶች በእናንተ ምሑርነት ተሠናክለዋል።አገርቤት ያለው ገዢ ፓርቲ ከወጣቶች ጋር መግባባት ያቃተው የወጣቱ ቋንቋ ስላልገባዉ ነው።እባካችሁን እኛም አባቶቻችን ያቆዩልን ሐገር እያልን እንድንዘክራችሁ እናንተም የሐገር ተረካቢ ብላችሁ እንድትመርቁ ያስፈልጋል።እስቲ ይህ ትዉልድ ምን ይፈልጋል?ቅረቡና ጠይቁት።በዉጪዉ ዓለም በሺዎች የምትቆጠሩ ምሑራን አላችሁ ተባብራችሁ በስማችሁ አንድ ቤተመፃሕፍት መክፈት የተሣናችሁ ለጦርነት እና ለስድብ ስትተባበሩ ማየቱ ለእኔ አይነቱ ዜጋ ድርጊታችሁ አሣፋሪ ነው።

  7. የምን መናገር ነው የምታወራው ወንድም!
    በኢትዮጵያ ውስጥ እምነትን አታመን፣አሰግድም፣አትጽፍም፣ አታነብም፣አትወያይም መሰብሰብ አትችልመ ነው እያሉ ያሉት ወያኔዎች፣ባዕድኖች፣የሻቢያ ቅጥኞች

  8. እናንተ ዛሬ ብቻ ነው የሚደንቃችሁ ሰው መገደሉ.መቃጠሉ ስንቱ የኢትዮጵያ ልጆች የገቡበት አይታወቅም ምን ይሻላል ወየኔ ለምን መጡ ለመግደል አይደለም እንዴ!
    እውነቱ
    የምን መናገር ነው የምታወራው ወንድም!
    በኢትዮጵያ ውስጥ እምነትን አታመን፣አሰግድም፣አትጽፍም፣ አታነብም፣አትወያይም መሰብሰብ አትችልመ ነው እያሉ ያሉት ወያኔዎች፣ባዕድኖች፣የሻቢያ ቅጥኞች

  9. እናንተ ዛሬ ብቻ ነው የሚደንቃችሁ ሰው መገደሉ.መቃጠሉ ስንቱ የኢትዮጵያ ልጆች የገቡበት አይታወቅም ምን ይሻላል ወየኔ ለምን መጡ ለመግደል አይደለም እንዴ!
    እውነቱ
    የምን መናገር ነው የምታወራው ወንድም!
    በኢትዮጵያ ውስጥ እምነትን አታመን፣አሰግድም፣አትጽፍም፣ አታነብም፣አትወያይም መሰብሰብ አትችልመ ነው እያሉ ያሉት ወያኔዎች፣ባዕድኖች፣የሻቢያ ቅጥኞች
    ዛሬ ኢትዮጵያ “ነጻ” አገር ናት ትላለህ እንዴ ብሎ!ውሽት አይደለችም በጎሳ ዘረኞች ቁጥጥር ስራ ናት እንጅ አዎን ቀደም ብላ ነጻ ሃገር ነበረች አሁን ግን ተው አትዋሽ ነጻ አይደለችም እየተገደልን፣ እየታራብን፣እየተጠማን፣ እየታፈን ከቤታችን እየተፈናቀልን፣ቤታችንን ንብረታችን ሽጠን ለእነሱ እየሰጠን ነው ነጻነት ነጻነት ትረጉሙ ምንድር ነው?
    እውነቱ

  10. ጥያቄ
    1- እባካችሁ የሃበሻ ጀብዲ መጽሃፍት ወደፊልም ቢለወጥ ለትውልድ ማስተማሪያ ይሆናል!
    ለባለሙያዎቹ ሃሳብ ብታቀረቡና ወደተግባር ቢለወጥ ምን ይመስላችኋል?
    2 -በትናትናው እለት የተከበረውን የአርበማች የደል ቀን በተመለከተ አንዱ ምን እናዳለ ሰማችሁ ለእኔ የሚታዩኝ እና እያየሁ ያለሁት የግንቦት 20 በዓል ነው በቮኦኤ ጉድ ነው ዘመን
    እስቲ ቀስቅሷቸው እነሱ ይናገሩ! መቼ ነው የሚነጋው? ዛሬስ በዛ ግፍ!
    ሳተናው አሊ

  11. Henok weyane mesel tekawami G7 new ende ?
    KKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKK
    KKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKK

  12. Henokye besint ametish new be abatish entin mechawet yejemershiw?hahaha be abatu entin sichewet yadege lij asmeselesh eko hulun menkesish.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*