ባለቅኔ እና ፀሐፌ-ተዉኔት አያልነህ ሙላቱ – ዶይቸ ቬለ

Ayalneh Mulatu

ገጣሚ ናቸዉ። ፀሐፌ ተዉነትም። ከብዙ የግጥምና የተዉኔት ድርሰቶቻቸዉ መሐል ጣልቃ የገባች አንዲት የታሪክ መፅሐፍ አለቻቸዉ። መፅሐፏ በ19ኛዉ መቶ ክፍለ-ዘመን በሥነ-ፅሑፉ መድረክ ዓለም አቀፍ ክብርና ሞገሥ ያተረፈዉ የሩሲያዊዉ ባለቅኔ የአሌክሳንደር ሰርግዬቪች ፑሽኪን ታሪክን ነዉ የምትወሳዉ።

በእሳቸዉ አገላለፅ «ሕዝባዊ» የሚሉት ለገበሬዉና ለዝቅተኛዉ መደብ የመወገን ፍልስፍናን ያዳበሩት ግን ከፑሽኪን ታሪክና ስራዎች ብቻ አልነበረም። ገና በልጅነታቸዉ ከገበሬ ሳይወለዱ ግን ገበሬ ሆነዉ፤ ከገበሬ ጋር ኖረዉ እንጂ። የፊታዉራሪ ልጅ ናቸዉ። ጎጃም ጠቅላይ ግዛት አገዉ ምድር አዉራጃ ተወለዱ። እዚያዉ አደጉ። ትምህርትም ጀመሩ። መቀጠሉ ግን አሳር ነበር። ዘገባውን ያዳምጡ → listen