አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ለናሽቪል ደ/ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ/ክ ላሰራጩት መልዕክት የተሰጠ መልስ
አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ኤፕሪል 14 ቀን 2016 በዩቱብ ያሰራጩት ቪዲዮhttps://www.youtube.com/watch?v=AV-Twe0a9jM የሚያሳየው በጥቅሉ መልዕክቱ አንድ ነው። ይሄውም:- የናሽቪሉን ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን መነሻ አድረገው ያው የተለመደዉን የካድሬነት መልክታቸዉን ለማስተለልፍ ነው። ‘እስካሁን ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ ያልተጠቃለላችሁ አብያተ ክርስቲያናት እድሉ ሳያመልጣችሁ ቶሎ ኑ’ ለማለት ነው። የአዲስ አበባው ሲኖዶስና ከወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ይህን አይነቱን ጥሪ ማስተላለፍ እዉነት ለሰማያዊው መንግስት ከሚሰራ አባት የሚጠበቅ ነውን? አባ መላኩ ፍርድ ቤት ቀርበው ጠበቃው ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። ጠበቃዉም ከመልሳቸው ያገኘውን ተጨባጭ መረጃ ይዞ የቤተክርስቲያኑን ምዕመናን ለመከፋፈልና ለማበጣበጥ በጣልቃ ገብነት የተጫወቱት ሚና የህግ ጭብጥ እያሲያዘው ስለሆነ አይቸኩሉ፣ ይደረስበታል እንላለን።
አባ መላኩን ህዝበ ክርስቲያኑ ለረጅም ጊዜ ጥሩ አድርጎ ያውቃቸዋል። በተለይም አቋም በመለዋወጥ አንዴ ከዚሂ አንዴ ደግሞ ከዚያ ሲሉ ከሰማያዊው መንግስት ይልቅ ከምድራዊዉ መንግስት ጥቅም ለማግኘት ቀላሉ መንገድ ጵጵስና ነው ብለው ስላመኑ የቤተክርስቲያኗን ስርዓት ባልጠበቀ መንገድ ከገቡት የዘመኑ ጳጳሳት አንዱ ናቸው። ያሁኑ ደፋ ቀና ደግሞ “ይህን ያህል አብያተ ክርስቲያናት ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ ስላመጡ አጋጣሚው ከተገኘ የፓትሪያርክነት ስልጣን በታሳቢነት” እንዲያዝላቸው ፈልገው እንደሆነ እናውቃለን። አዎ፣ የእርስዎ ቢጤ አባቶች በቤተክርስቲያናችን፣ በገዳማቱ በምዕመናኑና ለእውነት በቆሙ አባቶች ላይ በየጊዜው በመንግስት የሚሰነዘረዉን ጥቃት ሰምቶ እንዳልሰማ፣ አይቶም እንዳላየ ቸል በማለት በአቋራጭ ለሹመትና ለሃብት በቅታችኋል። በዚህም ከሰማያዊው መንግስት ይልቅ ለምድራዊው መንግስት መቆማችሁን አረጋግጣችኋል።
አባ መላኩ ፍርድ ቤት ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ መደረጉ እንዲህ አስደንግጧቸው ባስቸኳይ ማስተባበያ ሲያሰራጩ መንፈሳዊ አባትነታቸዉን ረስተው ከምድራዊው መንግስት ጋር በመሰለፋቸው ነገ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ያን ያህል የተጨነቁ አይመስሉም። ስለ ናሽቪል ደብረ ቀራኒዮ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ብዙም የሚያውቁት ስለሌለ መሰረት የሌላቸውን መረጃዎች ሲያቀርቡ ተደምጠዋል። የቤተ ክርስቲያኑ ህገ ደንብ ከሚያዘው ውጭ ከተመረጠበት ዘመን በላይ በካድሬዎች ጩኸትና ሁካታ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆየው የአስተዳደር ቦርድ ባቀነባበርው ድርጅታዊ አሰራር ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ የመቀላቀሉን ጥያቄ የ250 ምዕመናን ዉሳኔ አድረግው አቅርበውታል።
ቤተ ከርስቲያናችን 1995 ዓ.ም ሲመሰረት አባላቱ ጥቂት ከመሆናቸውም በላይ አብዛኞቹ የፖለቲካ ስደተኞች ነበሩ። በመሆኑም ህገደንቡን ሲያዘጋጁ ባንድ በኩል መንፈሳዊ አባት መሳይ ካድሬዎች እንዳይፈነጩብን ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ የሰጣቸው የመንግስትና የደህንነት ሰራተኞች ጽህፈት ቤት እንዳይሆን በመስጋት ጥንቃቄ አድርገን ነበር። ለዚህ ነው ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ አገር ቤት ዉስጥና ውጭ አገር የሚገኙት ሁለት ሲኖዶሶች በቃለ አዋዲው መሰረት ባንድ ተዋህደው አንድ ወጥ አመራር እሲኪኖር ድረስ የሁለቱንም ሲኖዶስ አባቶች ተቀብለን እናስተናግዳለን፣ ቡራኬአችውንም እንቀበላለን ስንል በህገደንባችን መግቢያ ላይ ያሰፈርነው።
በዚህ አቋማችን ሁለቱንም አንቀበልም ከሚሉት አብያተ ክርስቲያናት የተለየን ነበርን። አዎ፣ በአንዱ ሲኖዶስ ስር ሆነን በሌላው ላይ ድንጋይ መወርወር አልፈለግንም። ምክንያቱም በሁለቱም ሲኖዶስ ስር የሚገኙት አባቶች ይህችው የተዋህዶ እምነታችን በዘመናት ውስጥ ያፈራቻቸው ቅርሶች ናቸው በሚል ነው። እነ አባ መላኩ ጣልቃ እየገቡ እና ካድሬዎቻቸዉን አቡነ ፋኑዔል (አባ መላኩ) April 14 2016 ለናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት የተሰጠ መልስ ገጽ 2 ከ 2 ከናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስትያን ምዕመናን ለአስተያየትዎ፡ [email protected] ይላኩልን።
እያሰለፉ ሰላም እስከ ነሱን ጊዜ ድረስ በዚህ አቋማችን ያለምንም ችግር ላለፉት ሃያ ዓመታት ባአንድነትና በፍቅር አብረን ኖረናል፣ ክፉን እና ደጉን ተጋርተናል። በናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ጠፍቶ ሁከት የጀመረው ባንድ በኩል በዲቪና በነፃ ትምህርት እድል ሰበብ የሚመጡ፣ እንዲሁም በመንግስት ድጋፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ንብረት ያፈሩ የመንግስት ካድሬዎችና ደጋፊዎች በቁጥር እየጨመሩ በመሄዳቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ አባ መላኩን የመሳሰሉ ለምድራዊው መንግስት የቆሙ አባት ተብዮች የቤተከርስቲያናችንን መተዳደሪያ ደንብ ተቀብለውና ፈርመው ከተቀጠሩ በኋላ በስውር ለቆሙለት አላማ በመስራታቸው ነው።
እኛ አሁንም ቢሆን እንደክርስቲያንነታችን ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፣ ለዚህም ተግተን እንጸልያለን፣ እንሰራለን። እንደ አባ መላኩ ለምድራዊው ጥቅም ስንል በአቋም አንገለባበጥም። አባ መላኩ በዚህ በቪዲዮ መልክታቸው “ወደ አዲስ አበባው ሲኖዶስ እንግባ ሲሉ 250 አባላት በድምጽ ብልጫ ወሰነው ጥያቄ አቀረቡልኝ” ሲሉ የደብዳቤ መረጃ አሳይተዋል። በመሆኑም ሁሉ ነገር በህጋዊ መንገድ እንደተከናወነ ለማሳመን ይጥራሉ። ከዚህ ሁሉ ክንዋኔ በፊት ግን የካድሬዎችን ስድብና ወከባ መቋቋም አቅቷቸው በይሉኝታ ቤተክርስቲያናቸውን ጥለው የሄዱና ሌላ አብያተ ክርስቲያን የመሰረቱ አያሌ አባላት መኖራቸው ሊታወቅ ይገባል። ይሄም ብቻ አይደለም፣ አብላጫ ድምጽ ለማግኘት ሲባል በካድሬዎች ከፍተኛ ድረጅታዊ ስራ ተሰርቷል።
አንድ ወር ባልሟላ ጊዜ ዉስጥ ቤተ ክርስቲያን ደርሰው የማያውቁ ከ አርባ የሚበልጡ አዳዲስ አባላት ተመዝገባዋል፣ ለሁለት አመት እንዲያገለግል የተመረጠው የአስተዳደር ቦርድ ከአባ መላኩ የተሰጠውን አጀንዳ ለማስፈጸም ሲል ብቻ ያለ ምዕመናን ፍላጎት ከአራት አመት በላይ ቆይቷል። ስለዚህ በግንባር ሲታይ የአባ መላኩና የአበሮቻቸው የቦርድ አባላት ከሳሽ አንድ ሰው ይምሰል እንጂ አያሌ ምዕመናን ከበስተ ጀርባችን አሉ። የሰውን ልጅ ሰብዓዊ መብት ጥያቄ በቁጥር አሳንሰው ለማቅረብ ይሞክሩ እንጂ የህግ የበላይነት ባለበት ሃገር አንድም ሰው ቢሆን የመክሰስ መብት የተጠበቀ ነው። አባ መላኩ ከሳሻችን አንድ ሰው ነው ሲሉ ሊያንኳስሱት ቢሞክሩም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አባ መላኩ (አባ ፋኑዔል) በመሳሰሉ ለምድራዊው ጥቅም በአደሩ አባት ተብዮዎች ጣልቃ ገብነት ሰላም ያጡ የአያሌ አብየተ ክርስቲያናት ምዕመናን በመንፈስ በአካልም ከእኛ ጋር ሆነው ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተሉ ናቸው። (የህጉ ሂደት ያሰገኝውን ተጨባጭ ውጤት ይበልጥ ለማወቅ ከፈለጉ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በሚፈቅደው መሰረት ወደ ፊት እናሳዉቃለን።)
ከምድራዊው መንግስት ይልቅ ለሰማያዊው መንግስት ተግተው ይስሩ! ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ከናሽቪል ደብረ ቀራንዮ መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን ምእመናን
ለአስተያየትዎ፡ [email protected] ይላኩልን።
By any means the so called aba melaku must expellled and exposed to the world of truth
To all Ethiopians in USA! You do understand very well who AbaMelaku is and you know his dirty poletical game behind the black curtain,so why he is given a chance so far to divide the blievers? One way or the other this cadre must be avoided!!!!
እንደ ወትሮው ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ያቀናሁት በጥዋቱ ነበር፤አለባበሴም የሆሳእናን በአል ለማክበር አካሌ ባህላዊውን ለብሼአለሁ፡፡ውጪው አካሌ ቢደምቅም ውስጤ አንድ ነገር የጏደለኝ ያህል ይሰማኛል፡፡በአእምሮዬ ሁሉ በተለይም ያለፈውን የጥንቱን የትላንትናውን የናሽቬል ቀራንዮ መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ምዕመናን ፍቅር ህብረት አንድነት ጥንካሬና የረዥሙን የሃያ ዐመት ጉዞ ዕድገት ዛሬ ያ ሁሉ ፍቅር አንድነት ህብረት ተሽቀንጥሮ ተጥሎና ተዘንግቶ በእውቀታቸው በጉልበታቻው በገንዘባቸው የደከሙት ጠንካራ ምዕመናን በዕኩይ ከፋፋይ ስር የሰደደ ጥላቻና ወያኔያዊ ተልኮ ነባሩ ተባሮ በምትኩ ምንም ያልደከመ ዘርን ቡድተኝነትን መሰረት ያደረገ አስመሳይ ኢ-አማንያን ጏጠኛ ቡድን ቤተኮርሲቲያኑን ሲረከብ እምነት ተስፋ ፍቅር በጭራሽ ተዘንግተው ያለምንም ይሉኝታ ነበር፡፡መድረስ አይደለም አእምሮዬ ሁሉን እያሰብኩ ደረስኩ፡፡በጣም የሚገርመው ዛሬ ከወትሮው በአዳዲስ ሁሉም ይመስላል ፀአዳ የባህሉን ለብሶ ነበር፡፡ገዣ ቦታ ሁሉንም ማየት እንድችል ከኆላ ቆምኩ፡፡ሁሉንም ቃኘሁ ሁሉም ዉጪዉ አካሉ ነጥቶል ፡፡፡እነዛ ምዕመኑን ሰላም ሲነሱት ነገረኛ ተሳዳቢዎች አድመኞች ከአልተደባደብንን የሚሉት ካህንና መንኩሴ ሲያባሩ የከረሙት ተሳዳቢዉና አኩራፊዉ የቤተክርስቲያኑ ሊቀመንበር አቶ ሤሙኤልም ጭምር ደረስኩ ደረስኩ የሚሉ አንዳንድ ወጠጤ ዘማርያንም ጭምር ተመለከተኩ አምነንዳፍታ እምሮዬ ማሰብ ጀመረ፡፡አምነት ወይስ ባህላዊ እንዲያው በዘልማድ ሳይገባን ዝም ብለን በተንኮል በኃጢያት ዲያብሎሳዊ ስራ ሳንታክት አየተነዳን የአለን መካሪ አስተማሪ የሌለን የታይታ ሰዉ ሆነናል ወይስ ስህተቱ ያለው ከእምነቱ ወይስ ከመሪዉ ከካህናቱ?አወ ካህናቱስ ቢሆኑ ክህነቱን ገንዘብ ማስገኛ እንጂ መቼ የእምነት ሆነ?አንገታቸው ላይ ለማንጠለጠለው የወርቅ መስቀል ጌጥ መሆን ኸማን አንሼ ሆኖ የለ፡፡ለማሸጋገኛው ግዜ ወስጄ መልሱን የአገኘሁት መሪጌታው የበቀልና የጥላቻ የፌዝ ትምህርቱን በለቀቀበት ግዜ ቆይቼ ነበር፡፡ወደ ህሊናዬ ተመልሼ ስርአቱን መከታተል አቃተኝ ዙሪያዬ በመርዘኞች ተሳዳቢዎች ተመጻዳቂዋች መከበቤ ነበር፡፡ቤተክርስቲያኒቱ አስመሳይ ዉሸታሞች የጥላቻ ሰዎች ተመልታለምና፡፡ምናለ ውስጣችን እንዲሁ ባማረ፡፡አቤት እንዴት ተደርገው ተስርተዋል፡፡ሰው ለምን ይጠላላል?ናሽቤል በመጠላት ከአንድ ዛሬ 4 ቤተክርስታያን ደርሷል፡፡የኛን ያየ ቤተክርስቲያን ቢጠላ አይፈረድበትም፡፡አዎ ትላንትና ጌጥ ሆነው ለእውነት ለእምነታቺው የቆሙ የደከሙ ተገፍተው ወጥተዋል፡፡ሴት እህቶቻችን ኩሽና ገብተው ሻይና ቡና ዳቦ እንዳያቀርቡ ገብተውም አንዳያገለግሉ በመሰሪ ተንኮል ተደርገዋል፡፡ዛሬ እነዚሁ ሰዋች አምነታቸውን እንሿን ቢረሱ ነገ ምን ይመጣ ይሆንን ረሰተው ውጭ አካላቸው እንዴት አሳምረዋል?ወገኖች እምነት ወይስ ልማድ?ይህን በእምሮዬ ለደቂቃ ቢነጉድም የመጣሁበትን ጉዳይ አዉቃለሁና ፈጥኜ ወደ ልቦናዬ ተመለስኩ፡፡ወገኖች እኔንተስ ይህን ታዝባችሁ ይሆን?
ቪዲዮውን ተመለከትሁ። ከላይ ያለው ጽሑፍ ግን መልስ የሚሆነው እንዴት ነው? በመረጃ መልሱን ማስደገፍ አያስፈልግም? እንደእሳቸው። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ግን ንትርኩ ወይም ሀሜታው የሙዳየ ምፅዋት መነፈግ ያስከተለው የፍቅረ ንዋይ እሮሮ ነው ። የሰማያዊውንም ጥያቄ አስቀድሞ መተንበይ ከምድራዊው ትዕቢት ከመነጨ ግፊት እንጂ ቀናዊ ቤተክርስቲያን አይደለም ። እንዲያውም በክርስትና መንፈስ አይመስልም ። የፖለቲካም ይዘቱ ሚዛን አያደፋም። ምሬቱ ከሀገርና ከቤተክርስቲያ ፍቅር ይበልጥ ያለደከሙበትን ገቢ የማጣት ቁጭት ይመስላል ። ነውም ። ቲፎዞ ለማግኘት የመዳከር ሁኔታ ይታይበታል ። ልብ ልንለው የሚገባው ነገር በእውነት ነገር ላይ ቲፎዞ አያስፈልገውም ። እስቲ እባካችሁ በሰው ሀገር ያለምንም እረፍት ለራሱና ለቤተሰቡ ነጋ ጠባ እየሮጠ ለጭንቀቱ መፅናኛ በወረወረላቹ አስራት ጥግብ ብላችሁ የማወናበጃ ስልት እየቀየሳችሁ ምስኪኑን ምዕመን አታደናግሩት ። እዛው ትርፍራፊያችሁን በልታችሁ ተራገጡ ። ወደ ምዕመኑ አትድረሱ ። የበላችሁበትን ወጪት ሰባሪ ያደርጋችዃል ። የእንጀራ ገመዳችሁ ከማጠሩም በላይ ስለነፍሳችሁ ግድ ባይሰጣችሁም የሰው ፍርድ ይከፋባችዃል ። አዕምሮአችሁንም አሳርፉት ከክፋትና ከክርፋት አውጡት ። መልካም ሀሳብ ንፁህ እንቅልፍ አለው። በጭንቀት ውላችሁ በቅዠት አትደሩ ። አቦ ዘና ፈታ በሉ። እምነታችሁ የምትፈቱበት እንጂ የእስራት አይሁንባችሁ ።
አንተ ድንጋይ ራስ ደደብ እጅ እና ግን ዘንባባ ተቀብለህ ወተሀል ደረታቸው ላይ ያለው መስቀል አቃጠለህ እይደል ገና ያቃጥልሀል
አንተ ድንጋይ ራስ ደደብ የካህናት እጅ መስቀል በካህናት ተፈተህ ወተሀል ይቼ የቀረህን አንድ ሳምንት እምካን ንስሀ ገብተህ ወደ አምላክህ ብትመለስበት ተሳልመህ ዘንባባ ተቀብለህ ወተሀል ደረታቸው ላይ ያለው መስቀል አቃጠለህ እይደል ገና ያቃጥልሀል
እረገኝ እናንተ ሰዎች ምንኛ ጉዶች ፍጥረቶች ናችሁ?አሁንም መጥፎ ክፉ ፍጥረቶች ናችሁ፡፡እንግዲህ ወገን እነዚህ ነው የምለው እኮ፡፡መጽሐፍ ቅዱስን አውቁትም እኮ እናንተዬ፡፡እነዚህ ነው የናሽቤል መድኃኒአለም ቤተክርስቈቲያን የተሸከመው፡፡ኦነዚህ እኮ ናቸው የሰበካ ጉባኤ አመራር የሆኑት፡፡እንግዲህ አንባቢ ይወቅ ይረዳ፡፡
ይድረስልኝ ለቴድሮስ እና ጒደኞቹ ደግሞ በዚዚህ መጣህ አሁን ይቫላል ከቤተክርስቲያ ውጪ ተገቢውን መልስ እንሰጥሀለን
በጣም የሚገርመው አባቶችን ትሳደባላችሁ አቡነፋኑኤል ምን አደረጐችሁ ቤተክርስቲያናችንን ምዕመናኑ ተስማምቶ ነው ወደ እናት ቤተክርስቲያን የገባነው እናንተ ግን የምታወሩት ሌላ ነው ሕዝቡ ይታዘባል አትሉም የስጋአባቱን መሳደብ የለመደ በነካ አፉ የነፍስ አባቶችን ይሳደባል
ምንትዝአለኝ መሰላችሁ በአንድ ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚችምድር ሲመላለስ በዝሙት የተያዘች ሴት አቀረቡለትና ይቺሴት ዝሙት ስታደርግ ተይዛለች ብለው በድንጋይ ሊወግሮት ተዘጋጁ ጌታም ከእናንተ ሀጢአት የሌለበት ይውገራት ሲላቸው ህሊናቸው ወቀሳቸውና ትተዋት ሄዱ አየህ ቴዲ እነዚህ ሰዎች ከአኅተና ከጒደኞችህ ይቫላሉ ምክንያቱም ህሊና አላቸው እናንተ ግን ህሊና ስለሌላችሁ ምንም ያላደረጉ አባቶችን በስድብ ድንጋይ ወገራችኾቸው እግዚአብሔር ይፈርድባችዃል በመሳደብ የምትፀድቅ መሰለህ እናንተ ክርስቲያን ናችሁ ለመሆኑየትኛው እምነት ነው በሚድያ አባቶቹን የሚሳደብ እስልምና ወይስ ፕሮቴስታን ወይም ካቶሊክ ከእነሱ እንዲህ አይነት ባለጌ የለም
ሌላው ደግም ለስብከት የመጡ ሰባኪ አባቶችንም ወያኔ አላችሁ በእናንተ አቆጣጠር ወያኒ ያልሆነ የለም ጥላችሁንም ወያኔ ሳትሉ አትቀሩም
ቤተክርስቲያን የከሰሰው አንድ ብቻ አይደለም ከዃላ ሌሌችም አሉ ያልከው ለምን እልፍ አትሆኑም ምንም አታመጡም መድሐኔአለም በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ተከሶ ነበረ በዛን ጊዜ አይሁዶች ብዙ ነበሩ ዛሬም በዚህ ዘመን ተከሰሰ አለማፈርህ ለመሆኑ ከሙዳይ ምፅዋት ከአስራትበኩሪት የተሰበሰበው ገንዘብ የእግዚአብሔር ነው ትንቢተ ሚልክያስ ፫ ፥፯
እናንተ ግን ለጠበቃ አስበላችሁ አንደዚህ አድርጋችሁ የሰራችሁት ይባረክ ይመስላችዃል አልሰማ ብላችሁ በአመፅ ሄዳችዃልና እግዚአብሔር ይበቀላችዃል ይሁዳም ለድሆች ከሚሰበሰበው ይሰርቅ ነበረ ሉቃስ 22 እናንተ ደግም ቤተክርስቲ የተሰበሰበውን ለጠበቃ አስበላችሁ
ቴድርስ እባክህ አፍህ ይረፍ ሊቀመምህራን አባይ ደግም ምን አድርጉ ነው የምትላቸው እባካችሁ የተጣላችሁ ታረቁ ብለው መስቀል ይዘው ሲማፀኑ ጥለህ አልወጣህም እሳቸው ከመጡ ምንያህል የግልጋሎት ለውጥ እንዳለ የሚያውቀዉ ሰይጣን በአንተ ውስጥ አድሮ ይቃወማቸዋል ኢሄደግም በፀሎት ድል ያደርጉታል
አይ አንተ አቶ ሳሙኤልስ ምን አደረገህ በተክርስቲያን የሚያገለግሉ ሰዎችን ሰይጣን አይወዳቸውም ባለፈው ሳምንት ከዶክተር ቄስ መስፍን ጋራ ለማጣላት ሞከርክ የእግዚአብሔርቃል እንዲህ ይላል መ ምሳሌ 6:7 እግዚአብሔር ስድስት ነገሮችን ይጠላል ስባተኛውን ነፍሱ አጥብቃ ትፀየፈዋለች ይኸውም በወንድማማች መካከል ፀብን የሚዘራ አሁን አኝተ ያደረከው ማለት ነው ችግርእንኳን ቢኖር በወቅቱ ለራሱ ለአቶ ሳሙኤል መናገር ነበረብህ እስከዛሬ ለዶክተር ቄስ መስፍን ባለመናገርህ የቆጨህ አስመሰለብህ ዶክተር ቄስ መስፍን እንኳን በፆም በፍስክም አይጣሉም ቴድሮስ ከእንግዲህ ወዲህ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እና መድሐኔአለም አንድ ነን በመለያየት የሰይጣንን ስራ አትስራ እባክህ ተው ቴን ኘርሰንት ቤተክርስቲያን የምትመጣው ለነገር ለመታነፅ አትመጣ የሆሳእና ስብከት ለአንተ አይስማማ ጌታኢየሱስ እንዳንተ አይነቱን ቤተክርስቲያንን ሰላም የሚነሳ ያስወጣበት ዕለት ነው ብዙ የምለው ነበረ ለጊዜው በዚህ ላብቃ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይርጌ በቅድሚያ ሰላም ለአንቺ ይሁን
ጉዳዩ አንቺ እንደምትይው አይደለም አንቺ የምታዉቂው ቴድሮስ ማናዬ ቤተክርስቲያን ለምን በቅዱስ ሲኖዶስ ስር ሆነች ብሎ ፖለቲካ ይዞ ገብቶ ቤተክርስቲያንን ይበጠብጣል።
አንተ እኮ ቤተክርስቲያን ለፅድቅ አልመጣም ሰው ለማግኘት እንጂ ያልክ ሰውዬ ቦርድ ሆነህ ያውም ትምህርት ክፍል ነበርክ ሲያሳፍር
ከክፉ እንድንለይ እግዚአብሔር አዞናል።
ይህች ሳምንት ጌታ ለሰው ልጅ ሲል ማለትም ሰው ከክፋትና ከክፉ አድራጊዎች ተለይቶ ከተገፉት ጋር እንዲቆም ለእውነት እንዲታዘዝ ለሰው ልጅ ሲል መከራ የተቀበለባት ሳምንት ነች።
እኛ ግን የት ይሆን ያለነው? መከራን ከሚቀበሉት ጋር ወይንስ በሰዎች ላይ ይልቁንም በተዋሕዶ አማንያን እና በቤተክርስቲያናችን ህልውና ላይ ሳይቀር መከራን ከሚያደርሱት ጋር ነን?
የቤተክርስቲያንን ቀኖና፣ የክርስቲያኖችን አንድነት እንዲሁም የቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ሉአላዊነት እና የህዝቧንም አብሮነት ካፈረሱና ከለያዩ ክፍሎች የዚህም የጥፋት እቅድ አስፈጻሚ ከሆኑ ‘አባቶች’ ‘ እና ‘በክህነት ሥልጣን’ ውስጥ ከተደበቁ ካድሬዎች ጋር በመሰለፍ የቤተክርስቲያንም ሆነ የሃገር አንድነት አይመጣም።
ስለሆነም ከእነኝህ የጥፋት ሃይሎች ጋር በማንኛውም ደረጃ መተባበር የክፉ ሥራቸው አጋዥ መሆን ብቻ ሳይሆን ባንዳነትም ጭምር ነው።
፨ ቀኖና ቤተክርስቲያንን ሽረው በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ ከሾሙ
፨ ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ዋሻ ናት ብለው በአደባባይ ከሚሳደቡ
፨ መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብለው ከፎከሩ
፨ የታላቁን የዋልድባ ገዳም ከደፈሩና ካረሱ
፨ በመቶዎች የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲቃጠሉና እንዲፈርሱ ካደረጉ
፨ ምንፍቅናን በከፍተኛ ደረጃና ፍጥነት ኢትዮጵያ ውስጥ እያስፋፉ ካሉ
፨ ቤተክርስቲያንን እየሰደቡና እያዋረዱ መናፍቃንን ግን በፓርላማቸው ላይ ከሚያጸልዩ
፨ ምድሯ በሙሉ በቤተክርስቲያን በተሸፈነች ሃገር ላይ 50,000 የመናፍቃን አዳራሽ ለማሰራት በይፋ ከተስማሙና ቃል ከገቡ ከሃድያን
፨ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን በጠራራ ከጨፈጨፉና በባእድ ሃገራትም በስደት ካስጨፈጨፉና ለስደት ከዳረጉ
፨ እንደናቡቴ የአያቶቼን ርስት አለቅም ያሉትን ወገኖች ሁሉ እየጨፈጨፉና ደም እያፈሰሱ ደማቸውን ውሻ እንዲልሰው ከሚያደርጉ
፨ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር አልነበረችም እያሉ ታሪክን ከሚክዱና ከሚበርዙ ብዙዎችንም ከኢትዮጵያዊነት ስሜት አርቀው ሃገራቸውን ካስካዱና ለጥፋት ካዘጋጁ
፨ በየአገራቱ የጥፋት ሃይሉን የቤተክርስቲያን ሹማምንትና መመሪያ ካልተቀበላችሁ በማለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ጠብ በማስነሳት የቤተክርስቲያንን ክብር ከሚያዋርዱና ከሚያሰድቡ
፨ ይህ ሁሉ ግፍና በደል ሲፈጸም አይተው እንዳላዩ ሆነው በዘርና በጥቅም ምክንያት ግፍን ከሚፈጽሙ ጋር ህብረታቸውን ካደረጉ ‘ጳጳሳት’ እና በክህነት ስም ከሚጠሩ ካድሬዎች ጋር በመሰለፍ የቤተክርስቲያን እና የሃገር አንድነት አይመጣም!
እምነታችን የምታዘን ሐዋርያትም ያስተማሩን እንዲህ ያሉትን ክፉ ሥራዎችና ግፎችን ከሚፈጽሙ ከተባባሪዎቻቸውም ሁሉ እንድንለይ ነው።
በዚህች በሰሞነ ህማማትም የጌታን ህማሙን መከራና ሞቱን የምናስበው ከእንዲህ አይነት ክፉ ሥራ እንድርቅና በመከራው ተካፋይ እንድንሆን እንጂ መከራ ካደረሱበት ጋር እንድንሰለፍ አይደለም።
ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ እንዳለ፦
” ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ስለዚህም ጌታ። ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።
” 2ቆሮ. 6፥ 14–18
መልካም የህማማት ሳምንት።
I wounder why people left this so called Orthodox Church to Protestant or others? Is this church or Korean parliament? The only church in world that people fight inside instead of pray. It is disgusted. At least take the fight outside, and don’t let any tigere in Ethiopia church. Every tigeres are loyal to TPLF than GOD. Get rid of them than peace will come to your worship place.
አንተ መርዛም ዛሬም አታርፍም ያላመንክበት። ቤተ እግዚአብሔር,ያለደክበት ቤት ላንተ ምንም አይደለም ለምን አርፋህ አትቀመጥም ወይም ሌላ። የሚስሙህ ቦታ ፈልግ እኛማ አወቅናችሁ ሌሎች የሚስሙህ ፍልግ። አንተንና መስሎችህን በቅርቡ እናስወግዳችሃለን
Metema lay sudanoch ye aTie yohans 4gnan cinqlat qorTew bagerachew begmel eyazoru asaytew kartum enduruman biete mengst asqemTewt yigegnal.
Mengstawi yalhone ye atie yohans aTm asmelash comitie ke woyanie slTan meyaz behuala tequaqumo, aTmu endimeleslet le sudan Tyaqie aqrbual.
Yihn lemasakat, sudan eshi bla endtmels lemararat ye gonder, ye gumz-bienshangul meriet, ye hdasiew abay gdbun cemro ( ke miseTew meriet gdbu meseratun astawsu) le sudan besTota tgrie woyanie setual.
Ahun aTmu yetemelese yimeslal mkniyatum ye sudan baleslTanoch yale wotroachw merietun asrekbun yemil wutwota abztewal.
Wey nedo
be cirash yih endihon anfeqdm.
Yilqs sudan merietna gdbun agegnalehu bla agul tesfa atyaz. Bezih zemen yih twld ethiopiawi merietun tewagto yemasmeles mebtu be alem karta yeteregageTe new.
ማነህ ከዚህ በላይ የፃፍከው ደባልቄ ምን ትደባልቃለህ እኛ የምናወራው ስለ ቤተመቅደስ አንተ የምታወራው ስለ ቤተ መንግስት ምነው እንደ ባቢሎን ሰዎች ቓንቓችን ተደባለቀ አንዴ እሱንማ መች አጣነው እግዚአብሔር ይፈርዳል እሱንማ እራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል ትንቢተ አብድዩም ፩፤፫ አንብበው እግዚአብሔር ይፈርዳል እኛ ግን ቤተክርስቲያንን ሳንከፋፍል በአንድነት ወደ እግዚአብሔር እጃችን ይዘርጋ ነው የምንለው ስለ ፖለቲካ አትቀላቅል አንተ ከምትለ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ለወደፊቱም እንደዚህ አትደባልቅ እያልኩኝ ወንድማዊ ምክሬን እለግስሀለሁኝ ቸር ይግጠመን ደባልቄ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
10 ፐርሰንት አንተ የፓለቲካ ጥመኛ መስለችህ ሴጣኑች ይሄ ሳምንት ስለበደል ነው በደል ወደ አምላካችን የምንጩህበት ሳምንት ነው አንተ ግን የያዘህ ሴጣናዊ ተልኩ እያሩጠ አመጣህ ሆሳእናን ለማክበር መጣው ስትል አታፍርም አንተ እኩ የምትመጣው ለ10 ፐርሰንት እንደ ሴት ብረት ደርድረህ ጣትህ የማታምንበት ኤትዮጽያዊነት የባህል ልብስ ልታሳየን ነው የምትመጣው አታፍርም ግን እኔ ምን አልልህም
እግዚአብሔር አምላክ የናንተ መጨረሻ ያሳየን
Amhara hodu kemola
Yemin haymanot tawralh Amara iwunetim akerkariw
bicha sayon hlinawunm neaw yesebrut.
ይድረስ ይህን መልዕክት ለፃፍክልን ዉዱ ወድማችን፡ የፃፍከዉን አነበብነዉ፡ እሺ ከዚህ ከተራ ጭንቅላት የተማርነው ስድብ ብቻ እና እናድንቅህ ወይስ እንደግፍህ? ግን እኔ የምልህ በዚያ ለሊት ህሊናህን ለማቆሸሽ ለምን መጣህ ሌላ አጥቢያ ቤተክርስቲያን አለ አይደል ወይስ እነርሱ ጋር ቀልድ የለም ለነገሩ ምን ታደርግ የማታዉቀዉን ትህትና የምታገኝበት እዚህ አይደለም ታዉቀዋለህ የህዝቡን ልብ ፍርድ ቤት ገትረህዉ እንዃን አልተቀየመህ ለዚህ ነዉ ግን አንድ ነገር ልጠይቅህ መቼ ነው ስለቤተክርስቲያኑና የምትጠይቀው ሁልጊዜ ስለሰው እረባክህ ስትቆምና የመቅደሱን ዉስጡን እየዉ፡ ዉስጥ እኮ ያለዉ ምንም ዘር፡ ፖለቲካ አድመኝነት፡የሌለበት፡ መዳን ብቻ ያለበት ምነዉ ከፊት ለፊት ቆመህ እርሱን ማየት አቃተህ ደሞ ዛሬም ስለስዉ፡ አንተ የምትላቸው ሰዋች በደንብ እናዉቃቸዋለን ከማንኛው፡እንጀምር እስቲ ታገደ ከሚባለው እርሱ ማለት በአንድ ወቅት ቖሞስን ያለምንም ፈቃድ ቤታቸዉ ካልበረበኩ ብሎ ያስቸገረ ሰዉ ነዉ ጭራሽ አስፈራራቸዉ ታዲያ ይህ ነዉ ቤተክርስቲያንን አላስነካም የሚለዉን ሌላዉ ለቤተክርስቲያኑ መለያየት አንዱ መነሻ ታላቁን አባት አላስፈላጊ ማህተም ሠጥቶ ለዚህ የዳረገን ማን መሰለህ ያንተ ሰዋች እኮ ናቸዉ ለምን ትረሳለህ ይህን እኮ ያደረጉት ሊቀማይምራን አይደሉም የቱ ጋር ነዉ ህዝብ የከፋፈሉት ደግሞ ምንም ስላልተማርክ ነዉ እንጂ ቀጭ እያለ ካህናትን መስደብ ከየት ነዉ የተማርከው አሁን ደግሞ ስለ አቶ ሣሚ እናዉራ አንድም ቀን ሲመረጡ እንዃን እሺ ብለዉ አያዉቁም ሁሌም ተለምነው ነዉ የሚያገለግሉት አንተ እኮ አስር ብር ሰጥተህ የገባዉን ገንዘብ ካልቆጠርኩ የምትል፡ ነህ።ስማ በአሁን ሰአት ይህ ቤተክርስቲያናት እናንተ ያፈረሳችሁትን በመገንባት ላይ ይገኛል። ሠንበት ተማሪዋች በምን እንደወጡ እረሳህ ዉይ ቤተክርስቲያኑ ወደ ኢትዪጵያዊያን ሲኖዶስ ይሁን ብለዉ ጥያቄ አቅርበዋል ነዉ ሌላ ምንም አልነበረም አየህ አሁን እግዚአብሄር ፈቅዶ እኛ ስንገባ አንድ ሆንን ምነው እነርሱ የኢትዮጵያ ናቸዉ ለምን ወያኔ አይመራቸዉም ለኛ ሲሆን ነዉ እየዉልህ በመለያየት አንድነት የለም እርሱ ያለዉ እናንተ ጋር ነው ስትጀምሩ ብዙ ነበራችሁ የከሰሳችሁን አሁን አልቃችሁ ትንሽ ነዉ የቀራችሁት ይህ የሚያሳየው ስትጀምሩ አንድ አለመሆናችሁን ነዉ አንድ ወቅት አንተም ክሴን አንስቻለሁ ብለህ ነበር ለነገሩ ያንተን ዉሸት ለምደነዋል። ግን አንድ ነገር እወቅ በመስደብ ትዋረድ ይሆናል እንጂ አትከበርም። ስማህ ደብረ ቀራንዮ በእንዳንተ፡ ባለው ተልካሻ ሀሞተ ቢስ እንዃን ልንረበሽ ቀርቶ ንቅንቅ አትልም ክርስቲያን እንደሚስማር፡ ሲመታ ይጠብቃል ስለዚህ አፋችሁን በከፈታችሁ ቁጥር ህብረታችን ይጠነክራል ስለዚህ አትድከም ከማትችለው ግንብ ጋር ነዉ የምትታገለው ደግሞ ብዙ ወንጌል መጥቀስ ይቻል ነበር ነገር ግን ለእንደእናንተ አይነቱ በለመዳችሁት መልኩ እንፃፍ ብለን ነዉ።ወንድሜ የረሳሁትን አንድ ነገር ምነው የሊቀማይምራን መስቀል አነሳሳሃት ምነው ችግር አለ እንዴ አይዞህ አትፍራ እንዃን መስቀል ታቦት ይሰረቅ የለም ብቻ ወደራስ ተመልሰህ ከአምላክ ጋር ታረቅሁ ጌታቸው ይርዳህ።
ወንድሜ አቤል አንድ ትልቅ የሁነ ነገር አስታወስከኝ የአባታችን ቤትን ማን ዘረፈው ይህ መስቀል ነገር አለው ማለት ነው ቴድሮስ ትላንት በደሰኩረው ላይ መስቀላን ለምን አነሳትሃት ችግር አለ ማለት???????
ምነው ነብስ ያልዘራበት ወጠጤ በረከተሳ?የሚጽፈውንም አውቀለሁ ጥሩ ልጆች ስለአሉት ለግዜው ልተወው ካይሮ ግሩብ መሪ አድሮ ጥጃ እረ ተለወጥ፡፡ህማማቱን በነፀሎት የምናነስበው እኮ የሰውን ጭካኔ በአምላካችንና ፈጣሬያችን ላይ ያደረሱትን አይሆዶችን የአይሁድ ካህናትን ፀሀነፍት ፈሪሳውያን ለማስታወስ ጭምሮ ነው፡፡አንተና መሰልህ ፈርዖኑ ሣሙኤል ከእነሲ በምን ታንሳለህ?ጨካኝ አረመኔ መጽፈፍ ቅዱስንማ የት ታውቀዋለህ፡፡ዮዲት ጉዲት፤ ግሪኝ አህመድ፡፤መለስ ከነ ነብስ አባቱ ታሪክ ሀነው አልፈዋል፡፡ክፋታቸው ግን አሁንም በእነ አናንተ መሳይ አለ፡፡ግዝ አልፎ ደግ ዘመን ሳመጣ ዐይ እኛ አልያም ስም እየጠቀነሱ የሚያነሱበት ዘመን ይመጣል፡፡ክፋታችሁ እኮ ተመላው ሰሜን አሜሪካ ያውቀዋል፡፡ጆሮ በአድ ከአልሆነብህ፡፡የቅምህንና የችሎታህን ያህል ብትሳደብም ሁሉ ለበጎ ብሎ ያልፋል እንጅ ሜን ከአንተ ጋር ቂልቁል ይወርዳል፡፡አልፈርድብህም ግን ልጆችህን እያስተማርክ ሰለሆነ ከእነሱ ትማራለህ፡፡እባክህ ክፉ ቃል ለሚያልፎ ግዜ አትቦርቅ፡፡
ግዜህን መልካም ነገር በመስራት አሳልፍ፣፣ለልጆችህ ማፈሪያ እንደ ሰካራሙና ፈቈርኦን ሣሙኤል አትሁን፡፡ረሳኽ እንዴ ፈርኦኑ ሣሙኤል ከ7 ዓመት በላይ ተቅሌታ ተለይቶ ቤተክርስቲያን ስንገዛ መመለሱ,፡፡
አንተ ሴታሴት ውነትም ስምህን ምንትዋብ አልከው ትንሽ ቆይተህ ቀሚስ ለብሰህ እናይሀለን ምክንያቱም ከሴት ምድጃ ስለማትወጣ ሴት ስር ስለሁንክ ሁል ጊዚ ካይሮ ትላለህ ካይሮችንማ እንኳን ስማቸውን ቀና ብለህ ማየት አትችልም ምን ያህል በሀይማኑታቸውን የበረቱ እና የቤተክርስትያን ቅን አገልጋዬች እንደሁኑ
ላንተ አልነግርህም አንተ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሽ ተኖረ እና ተሞተ አሉ የአንተ አይናቱ ነው ድንጋይ እራስ ነው ማማትን እማ ብታስብ አፀያፊ ቃል ባልፃፍክ ስለ እቶ ሳምኤል የምትፅፈው እሳቸው እንደሁኑ አጠገባቸው ብትሰድባቸው አይደለም ብትመታቸው ይቅር ይሉሀል ይሄንን መቼም ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ ጨዋ ጨዋ ያሳደጋቸው የቤተክርስትያን
አባት ናቸው። በአንተ የክፎ መንፈስ አፍ የሚጠሩ አይደሎም አሁንም የሌቀ ማእምራን ቤት ማን ዘረፈው????? ይቁየን
አይ ፋዘር ቴድሮስ ስምህን ሴያወጡልህ እናትህ ጀግና እና ወንዳ ወንድ እንትሁናለችው ነበር ምን ዋጋ አለው። ውይ ፈረደባት ያቼ ሜስትህ እንዴት ሁለት ሴት እቤት ውስጥ ይኑራል ይብላኝ ለወለችህ ሜስትህስ በቅርቡ ትፈታሀለች አልጨረስኩም እቀጥላለው……
መጅመሪያ አማርኛ ተማር 2ተኛ አንተ ቦርድ በነበርክብት ዘመን እንኮን የተከበረው ሳሙኤል ግብረ አበሮችህም ክደውህ ነበር
ወንድሜ እቤት ቁጭ ብለህ አሁን ደግሞ ፀቡን በየትኛውም በኩል ልሞክረው የምትል ትመስላለህ ሰዉ እኮ እያነሰ ሲመጣ የሚያወራው ሁሉ የልጅ ይሆናል እስቲ እንወቅህ፡ ስምህን በትክክል አስገባና ፃፍ ካልሆነ ግን አንተም እንደጒደኞችህ ትንሽ ነህ ማለት ነዉ ምክንያቱም አንዳችሁም በራሳችሁ ስለማትተማመኑ ስማችሁን ትቀይራላችሁ እዉነት ካለህ ስለእዉነቱ ፃፍ ከሌለህ ደግሞ እስከዛሬ የምትሰራዉን ቁጭ ብለህ አስተስዉል እዉነትን መዋጥ ይከብዳል ግን እዉነት ስለሆነ ቻለዉ
በኢትዮጵያ ያሉ ሃኪሞች ሰው በላ ወይስ የወያኔ አጋዚ ዛሬ ሆስፒታሎች ነፍሰ መብላት እንጅ የሰው አይነት ባህሪ የላቸውም ምን ይሻላል
በዘውዲቱ ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን በጥቁር አንበሳ፣የሚታይ ሲሆን ምን እየሰሩ እንደሆነ ወገናቸውን እጨረሱት/ን/ ወራሪ ናቸው እንጅ የህክምና ስነ-ምግባር አልፈጠረባቸው ከእነሱስ የዲር እንሰሳት ይሻለና ህመማችን ብንችል ሳይቻል አይቀርም
1- በየካቲት 12 ሆ/ል ለግርዛት ሂዶ የነበረ የ16 አመት ወጣት የተገረዘውን ቁስል በሬሳ ማድረቂያ አከሙት
2- በዘውዲቱ ሆስፒታል የእንቅርት ታካሚዋ ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ ይህ ስህተት ነው የምትሉት ዘር ማጥፋት ነው ወንድም/እህቶች
3- በደሴ ሆ/ል ስንት ሰው በሃኪም ስህተት እየተሳበበ ወገኖቻችንን ገድለዋ /አስገድለዋ/አስጨረሰዋል ምን እየተሰራ ነው
4- በባህርዳር ሆ/ል ስንት ወላጆች እናቶች ናቸው የሞቱት
5- በእኔ የደረሰውን ልንገራችሁ በ2000 ዓ.ም ታምሜ ሃኪም ቤት ስሄድ ሃኪም ያነጋገርኝ በመስኮት ነው ከዚያ ሃኪም ያዘዘልኝ መድሃነት በድምሩ ተጨማሪ የተከለከል መድሃኒቲ በመውሰድ ሌላ በሽታ ገዛሁ
ከመከራ የማትወጣ ሃገር ሆነች
ሳ.አ.
ቤተክርስትያኑ ውስጥ ብዙ የመንግስት ካድሬወች ተሰብስበውበታል ከመዘምራኑ ሰላይ አቶ ስዮም እንዳሻው ሲሆን ከቦርዶቹም ብዙወች ተሰግስገዋል፥ ሊቀመንበሩም ለዘላለም የተቀመጠ ይመስላል።
የመንግስት ካድሬ መሁን ምን ችግር አለ መቼም ተወልደን ያደግንበትን አገር አይካድ መንግስትም ቢሁን እግዚአብሔር የሚሹመው ባዱ ጭንቅላት መሁን የሚያስታውቀው ስዬም ምን አይነት ሰው መሁኑን ስለማትውቅ ነው እንደ አንተ በየቤቱ እየሄደ ስለ ቤተክርስታያን ውድቀት አያወራም ጥሩ አቃም ያለው ቢተሰቡን ልጁቹን በቤተክርስትያን ስርአት አንፁ የሜያሳድግ
የሚያከብር ከምን ነገር በላይ የቤተክርስትያን
ፍቅር አንድነት የሚፈልግ እንጂ እንዳንተ በየቤቱ እየተልከሰከስ ለስድብ አፎን የሚከፍት አይደለም ከፈለክ እጨምርልሀለው ጠብቀኝ።
“ለስድቡ ግድ የለም..!!”
ለስድቡ ግድ የለም!
ይህች ቤተክርስትያን ክርስቶስን አታውቀውም በሉ
ግድ የለም ለቃሉ!
ግን ድምፅ ቀንሱ!
የጌታን መከራ ሕማሙን አስባ
ስግደት ላይ ናትና ልጆቿን ሰብስባ
ግድ የለም አንቋሻት
ግን አትረብሿት!!!
ከ ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ
ሼር በማድረግ መልህክቱን ያድርሱል
እንግዲህ ማንን እንስማ።
እግዚአብሔር በሰው አድሮ ቤት ይገነባል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ ቤት ያፈርሳል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ ደካማውን ያበረታል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ ጎበዙን ያደክማል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ የወደቁትን ይመክራል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ ምክርን ገለባ ያደርጋል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ ምንም ያልጎደለብህ ሙሉ ነህ ይላል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ አንዳች የሌለህ ጎስቋላ ነህ ይላል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ ዙሪያህን በሙሉ በወዳጅ አጥሬዋለሁ ይላል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ ዙሪያህን በጠላቶችህ ተከበኻል ይላል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ አልጥልህም አልተውህም ይላል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ በሁሉ የተገፋህና የተዘነጋህ ነህ ይላል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ በፊትህ የተከፈተ በር ሰጥቼኻለሁ ይላል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ በሩ የተዘጋ መንገዱ የታጠረ ነው ይላል። እግዚአብሔር በሰው አድሮ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይላል፤ ሰይጣን በሰው አድሮ ነገር ሁሉ በአንተ ላይ በክፉ ተነስቶብኻል ይላል።…….
ዲያቆን ጥሩ ብልሃል፡፡የጌታን ህማማቱን ስናስብ እነዛ የአይሁድ ካህናት አለቃ፤ፀፈፍት ፈርሳውያን ብሉይን እናዌቃለን የሚሉ ቀናተጮች፣ክፉዎች አስመሳዮች እጅግ ጨካኞች፣በአምላክችን ላይ የአደረሱት ህመም፣የጌታን ቤተመቅደስ የአረከሱትን ላንዳፍታ አሰብካቸው፡፡እኛስ ቤተክርስቲያን ከጌታ ቤተመቅደሰ አየለመነው አቶ ሣሚኤል ተጎትቶ እያለቀሰ ሲወጣ ምን ተሰማህ ዲያቆን?አዘንክ ወይስ አንተም እንደ አለቃህ መሪጌታ ፈረድህ?ለዚህም ነው በቤተኬርስያናቾን ውስጥ አስመሳይ ኢ-አማንያኖች፣ካህን አሳዳጆች፣ጨካኞቾ፤መሠሪ ካድሪዋች ካባ ያጠለቁ ቆብ የደፈ ለጥቅማቸው ለአባ መላኩ ሹመት ያጎበደዱ አሳመሳይ የመሪጌታ አባይ አይነቱ ከነ አጃቢያቸው የተሰገሰጉበት፡፡ዲያቆን ህማማቱን የምናስበው ሰዉ ምን ያህል ወደ ክፋ አውሬነት በጥቅም ለስጋዊ ፍላጊቱ ተገዛ መሆን አትዘንጏ፡፡አስተውል፡፡
አይ አለማወቅ ከንቱ ደመላሽ ምን ሁን ግድ የለኝም ይሄ ነው ክርስትና ይሄ ነው ለቤተክርስትያን መቆርቆር ይሄ ነው አባትን እየሰደቡ ዬትብ ላይ መለጠፍ ይሄ ነው በየሜፍያው መደስኩር አየህ ክርስትና አልጋ በአልጋ አይደለም መሳደብ አይደላም መሞትም አለ ስለክርስቶስ ፍቅር ችግር የለም ከአፋችሁ ቆሻሻ እንጂ መቼ መልካም ወቱ ያቃል የእፎኝት ልጁች….
ወንድሜ ማቴዎስ ምዕራፍ ፳፫/23/ ሙሉዉን አንብበው የናት አለም፡፡ሙሴን አትርሳ፤ዶር ፡ ፓስተር ፡ማርቲን ሉተር ጊንግ እንዲሁ፡፡አስተውል፡ ያ ቀን ይዘገያል እንጂ ይመጣል፡፡ተረዳኸኝ?
All religions are created by people.
The universe including humane has no creator.
It just exists evolving/evolution.
The proofs are :-
1. There are more than 4000 religions because people create them as they guess and search for super power.
Therefore our mind/human being creates religion but religion doesnot create human being.
2. Thge Universe exists but no evident existence of creator.
Thus the no existence is
self-evident by abscence.
አባቶቻችን እንዳስተማሩን በሐይማኖት ድርድር የለም እስከሞት ድረስ
ነው፡፡ ውድ ኢትዮጵያውያን ይህን ፅሁፍ ታግሳችሁ እንድታነቡት ላልሰሙት
እንድታሰሙ አደራ፡፡
*1ኛ ፣ሰሞኑን የክሮስ ቸርች አባላት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሃምሳ ሺ
ቸርች በኢትዮጵያ ሊገነቡ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
*2ኛ የ666 የማይክሮ ችፕ ገጠማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገሮች
ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡
*3ኛ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አይነትነት አሰራር የኢትዮጵያ ዜጎች
እንዳያውቁና ስለዚህ ጉዳይ እንዳይወሩ የሚያግድ ህግ አርቅቆ ሊያፀድቅ
ነው፡፡በእነዚህ ሶስት ነጥቦች ዙሪያ መነጋገር አለብን፡፡
በቅርቡ የሰማችሁት ዜና እንዳለ እርግጠኛ ነኝ፡፡ክሮስ ቸርች ግሎባል
ሚሽን የተባለ እምነት ድርጅት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ 50 ሺ ሃምሳ
ሺ ቤተክርስቲያን ሊያቋቁም ነው፡፡ስራውን በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎች
ክልሎች በይፋ ሊጀምር ነው፡፡እነዚህ ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው
ከአገራችን ባለስልጣናት ጋር ተወያተዋል፡፡ፕሬዘዳንታችን ጨምሮ
ሁሉንም አግኝተው ተነጋግረው አስፈቅደውና ተፈቅዶላቸው ነው ስራቸውን
የጀመሩት፡፡ሁኔታው እንግዳ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም ነው፡፡ዓላማቸው
ወንጌልን መስበክ እንደሆነና በኢትዮጵያ ከፍተኛ በጀት መድበው 50 ሺ
ቤተክርስቲያን መትከል ነው፡፡እንግዲህ ይህን ጉዳይ በሚመለከት እንደ
አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ለየራሳችን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ይኖራል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ሰዎች የሚያስፈቅዱት መንግስትን ወይስ
የሚመስላቸውን ምዕመን?ማለት ስለወንጌል ሰበካ ነው አይደለም
የሚለውን መንግስት ነው የሚያጣራው?ወይስ የመፅሐፍ ቅዱስ
አማኞች?እንደ ሐይማኖተኛ ሳይሆን እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ቃል ለነሱ
ጥያቄ ማቅረብ ያለበት ማነው?ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ ‹‹በመጨረሻው
ዘመን ብዙ ሐሰተኛ /ሃሳዊ/ሰዎች ይነሳሉ ብዙ ታዓምራትንም ያደርጋሉ
ህዝቡንም ያስታሉ ስለዚህ መርምሩ›› ይላል፡፡ይህን የመመርመርና
መንፈስን የመለየት ተግባር የማን ነው?ኢትዮጵያ ውስጥ ማንን ነው
የሚመለከተው?የኔ ጥያቄ ነው፡፡
ምንም ይሁን በብዛቱ አስደንጋጭ መሆን ብቻ በርካታ ጥያቄዎችን
እንድናነሳ እንገደዳለን፡፡
ልብ በሉ 50 ሺ ቤተክርስቲያን እንዲሁ በአይምሮዋችሁ፤ጎንደር 44
ታቦት፣ጎጃም 44 ታቦት፣ወሎ 44 ታቦት አዲስ አበባ ይህን ያህል፣ ጂማ
ይህን ያህል፣እያላችሁ ቁጥሩን ለመገመት ሞክሩ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ቦሌ
አንድ መካነ ኢየሱስ፣ጦር ሃይሎች አንድ፣ ኮተቤ፣ ሸጎሌ፣ እያላችሁ
ለመቁጠር ሞክሩ፡፡በተመሳሳይም የሌላውን ኢትዮጵያዊ ሐይማኖት
የማምለኪያ ስፍራ ቁጠሩ፡፡ወይም ለመገመት ሞክሩ፡፡
ከዚህ በፊት በአገራችን የነበሩት እነዚያ ሁሉ የማምለኪያ ስፍራ በረጅም
ዘመናት ሂደት እየተገነቡና እየተስፋፉ የመጡ ናቸው፡፡በአንድ ጊዜ 50 ሺ
የማምለኪያ ስፍራ በኢትዮጵያ የገነባ የእምነት ድርጅት ወይም ተቋም
የለም!!
50 ሺን በብር ደረጃ ብትስሉት ወይም ብትገምቱት አምስት እስር ብቻ
ናት፡፡በምንም ብትስሉት ቁጥሩ ብዙ ላይመስል ይችላል፡፡በቸርች ወይም
በማምለኪያ ስፍራ ደረጃ ሲሆን ግን ምን እንደሚፈጠር አስቡት፡፡
ቦታን በካሬ እየሸነሸናችሁ በደንብ አብሰልስሉት፡፡ለማመን እንቸገራለን፡፡
ይህን ያህል ቸርች በመገንባቱ ደስ የሚለው ሊኖር እንደሚችል ሁሉ
የሚከፋም ይኖራል፡፡ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ነገር ግን ደስ የተሰኘው አካል
እሱ ልክ ነው ብሎ ከያዘው እምነት ጋር እነዚህ ይዘውት የመጡት
አይቃረንም ወይ?የሚለውን ማሰብ ለምዕመኑ የሚተው ይሁን በሚል
ብንተተወው እንኳን፤ የአካሄዱ አስደንጋጭነት ብቻውን ወደ ሌላ ጥርጣሬ
ያመራናል፡፡ጥርጣሬ ብቻ አይደለም ወደ ሌላ ዕውነት ያመራናል፡፡
በእርግጥ ለኢትዮጵያ 50 ሺ ቸርች ያስፈልጋታል?አያስፈልጋትም! ብሎ
የሚወስነው አካል ማነው?እስከዛሬስ የት ነበሩ?50 ሺ ቸርች
የሚያስፈልገው ምዕመን ስለመኖሩስ እርግጠኞች ናቸው?ወይስ ምዕመኑ
በዝቶ ስለተጥለቀለቀና ቸርቾች ስለጠበቡ?የነዚህ ሰዎች ትክክለኛ ኣላማ
ምንድነው?ዓላማቸውንስ ለኛ ነግረውናል?ኦኬ መንግስት ማለት ህዝብ
ስለሆነ መንግስት ካመነበት በቂ ነው ልትሉ ትችላላችሁ ነገር ግን
መንግስት የሰዎችን የነብስ አዳኝ መርጦ ሊሰጥ አይችልም፡፡በዚህ ዙሪያ
ያለውን ነገር ለሌላ ጊዜ እናቆየውና ስለተፈቀደላቸው ወይም
ስለተሸጠላቸው ቦታ ብቻ እናስብ፡፡ ሃምሳ ሺ ቤተክርስቲን!መቸም ፈረንጅ
ሳያቅድና ሳይዘጋጅ እንዲህ አይነት ነገር ይፋ አያደርግም፤ወደ ተግባርም
አይገባም፡፡ሲመጡ ደግሞ እኛ ሰይጣን ነን አይሉም፡፡ በቂ ዝግጅት
አድርገው ቅዱሳን እንደሆኑ አድርገን እንድቆጥራቸው የሚያደርግ
ተግባር እየፈፀሙ ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ብቻ ተዘጋጅተው የመጡ መሆናቸው
ለማንም ግልፅ ነው፡፡ተመልከቱ፤ለአንድ መኖሪያ ቤት እንኳን 500 ካሬ
ሜትር ነው በተለምዶ የምናውቀው፡፡ለቸርች ሲሆን ስንት ይሆናል?አንድ
ቸርች በስንት ካሬ መሬት ላይ ያርፋል?ይህ ብቻውን ቀና ነገር ይዘው
እንዳልመጡ ያረጋግጥልናል!
50 ሺ ቸርች ሊሰሩ ነው፡፡እያንዳንዱ ቸርች በጣም በጣባቡ 1ሺ ካሬ
ቢይዝ ብለን እናስብ፡፡ከዚያ በላይ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ግን
ነገሩን እናቅልለው ብለን በ 1ሺ ካሬ አረፈ እንበል፡፡እንዲሁ ጠባባብ
ቸርች፡፡50000 ሲባዛ በ 1000 50000000/ሃምሳ ሚሊዮን ካሬ ሜትር
ቦታ ይሆናል፡፡በ2ሺ ካሬ ካረፈ 100 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ይሆናል፡፡
ወደ ሄክታር ቀይሩት!የሚዘገንን ነው!ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላ ነገር
እንድታስቡ ልጋብዛችሁ፡፡አንድ ቸርች በአማካይ በጣም በትንሹ ስንት
ሰው ይይዛል?ወይም ስንት አባል ይኖረዋል?ቸርች ሲባል አገልጋይ
አስተዳዳሪ ሰባኪ ወዘተ…ብዙ ሰው ይኖራል፡፡ምዕመንም ይኖራል፡፡
ስለዚህ እያንዳንዱ ቸርች በጣም በትንሹ 1ሺ ሰው ቢይዝ/እስከ 5ሺ
እስከ 10 ሺም ሊደርስ ይችላል/በትንሹ አንድ ቸርች 1ሺ ሰው ቢኖረው
ብለን ካሰብን 1ሺን በ 50 ሺ ብናበዛው 50000000/ሃምሳ ሚሊዮን
ሰው ይኖረዋል፡፡አንድ ቸርች በትንሹ 2ሺ አባል ቢይዝ የ 50 ሺ ቸርች
አባላት ብዛት 100000000 /መቶ ሚሊዮን/ ሆነ ማለት ነው፡፡የኢትዮጵያ
ህዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ በ2015 99 ሚሊዮን ነው፡፡ጠቀለሉት ማለት
አይደል?ይህንን ነው አቡነ ፍራንሲስ አንድ ዓለም አንድ ሐይማኖት እያሉ
በየአገሩ እዞሩ የሚያሳምኑት!መቸም አንድ ቸርች ከ አምስት መቶ ያነሰ
ሰው ይዞ ቸርች አይሆንም፡፡ስለዚህ ጉዳዩ የአንድ ሐይማኖት ጉዳይ ብቻ
ሳይሆን ጉዳዩ የኢትዮጵያ እንደሆነ ማሰብ አለብን!ይህን እየሰማንና
እያየን ምን እየተከናወነ እንዳለ ማሰብ ካልቻልን ሙሉ በሙሉ ክፉ
መንፈስ አይምሮዋችን ተቆጣጥሮታል ማለት ነው! 50ሺ ቸርች!!!
መፅሐፍ ቅዱስ ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ›› ይላል፡፡ነገር
ግን እነዚህ ሰዎች ወይም ይህ ድርጅት መጀመሪያ ቸርቹን ከዚያ
ስብከቱን እያሉ ነው፡፡ሙሉውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀስ በቀስ በቁጥጥር
ስር እንደሚያውሉትና ሌላ የሐይማኖት ተቋማት እንደሚጠፉ እርግጠኞች
ናቸው ማለት ነው፡፡ወንጌል ተሰብኮ ምዕመን እየበዛ ሲሄድ ነው ቸርች
የሚስፋፋው፡፡ያውም በራሱ በምዕመኑና በሐይማኖቱ ተከታይ በሚዋጣ
ገንዘብ! እንደዚህ ዘሎ እንደ መንገድ ስራ ፕላን 50 ሺ ቸርች
የሚባልበት የሐይማኖት ስርዓት የለም፡፡መንግስትስ መሬት መሸጥ ነው
የያዘው ወይስ የሀይማኖት ነፃነትን ለማንሰራፋት? እኔ ኦርቶዶክስ ብሆንና
አንድ የውጭ የሐይማኖት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ 50 ሺ ቸርች
ልሰራ ነው!ቢለኝ ‹‹ኧረ አባ 50 ሺ ቤተክርስትያን በዚች ጠባብ
አገር?››ብየ እሞግታለሁ፡፡እኔ ፕሮቴስታንት ብሆን ‹‹50 ሺ የፕሮቴስታንት
ቸርች ልናቋቁም መጣን!›› ቢሉኝ፤‹‹ኧረ ፓስተር 50 ሺ ቸርች?››ብየ
መቃወሜ አይቀርም፡፡እኔ ካቶሊክ ብሆንና የሌላ አገር ቅርንጫፍ
ተቁዋም መጥቶ ‹‹50 ሺ ቸርች በኢትዮጵያ!››ሲለኝ
ብሰማ፤‹‹እንዴት?››ብየ መቃወሜ አይቀርም፡፡እኔ ሐይማኖት አልባ
ብሆንና ይህን ነገር ብሰማና ባይ፤ ‹‹እንዴ እንዴት?ያገሬ ገበሬ ምን
መሬት አርሶ ሊበላ ነው?››ማለቴ አይቀርም፡፡እኔ ከየትኛውም ወገን
ብሆን ይህን ዜና መቃወሜ አይቀርም፡፡መንግስትም ብሆን ‹‹ከፍተኛ የሆነ
የመሬት ወረራ›› እለዋለሁ፡፡ስለሚፈናቀለው ሰው አስባለሁ፡፡ይህን
ያስቀደምኩት ጉዳዩ የሐይማኖትና የሐይማኖተኞች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን
የአገር ህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጭምር ለማስገንዘብ ነው፡፡ይህ ጉዳይ
በቀጥታ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሌላው ዓለም ህዝብ በፊት የአውሬው
ምልክት የሚባለውን የ666ን ወይም የማይክሮ ችፕ ገጠማን
ለማከናወን የተጀመረ ጅምር ወይም የመሰረት ድንጋይ እንደሆነ
ከመጠርጠርና ከማሰብ ውጭ ሌላ ስያሜ ልንሰጠው አንችልም!ሌላ
ማሰብና መገመት የምንችለው ነገር የለም፡፡ይህን አርማ ደግሞ
በቀላሉና በቶሎ አይቀበሉም ተብለው የተፈሩት የኢትዮጵያዊ ዜጎች
ናቸው፡፡ በዚህ ሀሳብ የሚስቅ ሰው ካለ ቀስ እያለ እንደሚያለቅስ የታወቀ
ነው፡፡‹‹ኢትዮጵያን ይፈልጉዋታል፡፡ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ዘመን ጋር
በተያያዘ ትልቅና ወሳኝ የሆነ መንፈሳዊ ነገር በውስጡዋ አለ፤ኢትዮጵያ
በዚህ ጉዳይ ልዩ አገር ናት››ሲባል የሚያፌዙ ምሁራን እንዳሉን
እናውቃለን፡፡ግድ የለም ሁሉም በዘመኑ ይፋ ይሆናል!ለታወሩት ሳይሆን
ላልታወሩት ነው ነገሩ ግልፅ የሚሆነው፡፡
ይህን ጉዳይ በስተኋላ የምንመለስበት ይሁንና ስለተያያዡ ነገር እንይ፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 13 ቁጥር17-18 እንዲሁም
ምዕራፍ 14 ቁ 9 ላይ ‹‹የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለው
ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል፡፡
ጥበብ በዚህ አለ፡፡አእምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው፤ቁጥሩ
የሰው ቁጥር ነውና፤ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው፡፡
…..ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግድ፤በግንባሩ ወይም በእጁ ምልክቱን
የሚቀበል ማንም ቢኖር፤….የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና
ሌሊት እረፍት የላቸውም፡፡››ይላል፡፡ሙሉውን እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡
ባሁኑ ሰዓት በአሜሪካና በሌሎች የ666 ማይከክሮ ችፕ /የአውሬው
ምልክት ተዘጋጅቶ አልቆዋል፡፡ምስሉን ዝቅ ብላችሁ እንደምታዩት ሂደቱ
እየተጠናቀቀ ነው፡፡ይህ ለዓለም ህዝብ ሁሉ የተዘጋጀና በእጅና በግንባር
የሚሰጥ ምልክት ተመርቶ ወይም ተዘጋጅቶ ወደ ቀጣዩ ስራ እየተገባ
ነው፡፡
የቀረው የስርጭት ጉዳይና ከማን ይጀመር የሚለው ነው፡፡ልብ
በሉ፤የግብረሰዶማውያን ህግ ቀድሞ እንዲፀድቅ ተፈልጎ የነበረው
በኢትዮጵያ ነው፡፡ሳይሳካ ሲቀር በአሜሪካ ፀደቀ፡፡ከዚያ በዘዴ ተመልሰው
መጡ፡፡
በቅርቡ ደግሞ ባራክ ኦባማ ‹‹በሲ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ቀርቦ እስከ
2017 ሁሉም አሜሪካዊ ማይክሮችፕን በቀኝ እጁ መግጠም
አለበት››የሚል ይፋዊ መግለጫ ሰጠ፡፡የቫቲካኑ ጳጳስም በየአገሩ እየዞረ
አሳመነ፡፡
እስካሁን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ብቻ ተቀብለው ሌላው
በማጉረምረም ላይ ይገኛል፡፡ሆኖም የሚቀርለት የለም፡፡ይህ በሆነ
ማግስት ልክ እንደ ግብረሰዶሙ ህግ ሌላው ዓለም ቀስ ብሎ መቀበሉ
እንደማይቀር ስለሚታመን በዋናነት ትኩረቱ ኢትዮጵያና ህዝቡ ላይ ሆነ፡፡
ማይክሮ ችፕን በቀኝ እጁ ያላስገጠመ ሰው መሸጥ መለወጥ
አይችልም፡፡በዚህ ማይክሮችፕ አማካኝነት የገንዘብ አካውታችን፣የደም
ዝውውራችን፣ያለንበት ቦታ፣በአይምሮዋችን ያለው አስተሳሰብ ሁሉንም
ውስጡ ባለው ip numbere አንዱ አካል ይቆጣጠራል፡፡ልጆችን
ማስተማር፣ታሞ መታከም፣ገንዘብ መላክ፣ገንዘብ መቀበልም ሆነ ምንም
ማድረግ ስለማይቻል ነገሩ የውዴታ ግዴታ የሆነበት ይቀበላል ነው
ቀመሩ፡፡ ያልተቀበለ እምነቱን ጠብቆ መሞት ይችላል፡፡ለኢትዮጵያውያን
ግን እንደሌላው ዓለም ህዝብ በፍላጎት ሳይሆን በሀይል ለመጫን ነው
ፍላጎታቸው፡፡ለዚህም ይረዳ ዘንድ የበግ ለምድ ለብሶ የመጣ ተኩላ
እንደሚባለው በወታደራዊና በደህንታችን ላይ ምናምን..በሚል ሽፋን
የተሰጠው መርዝ የሆነ ህግ ከ ሶስት ቀን በፊት በኢትዮጵያ ላይ ተረቆ
በፓርላማ ሊፀድቅ ነው፡፡ይህ ህግ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ህጉ ከምንም ነገር
ጋር እንደማይያያዝ ተደርጎ በይፋ የተገለፀውንና ሪፖርተር ጋዜጣ
ያወጣውን ብዙዎቻችሁ አይታችኋል፡፡
እንነጋገርበት!
ይህን ህግ ምን አገናኘው ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ነገር ግን መቶ በመቶ
ይገናኛል፡፡ሌሎችን አንቀፆች ስናይም በደንብ ይገባናል፡፡
ይህ ህግ በኢትዮጵያ ፀደቀ ማለት ኢትዮጵያውያን አይናቸውን ጨፍነው
ስለምንም ነገር ሳያውቁ ወደማያውቁት ጥልቅ የጭለማ ህይወት ውስጥ
እንዲገቡ ማድረግ ማለት ነው፡፡ይህ ህግ በኢትዮጵያ ፀደቀ ማለት
የተማረው ጥቂቱ ህዝብ በወሬ ደረጃ እንኩዋን ላልተማረ ወገኑ አንዲት
ፍሬ ያላት ሃሳብ ማስተላለፍ አይችልም ማለት ነው፡፡ህጉ ፀደቀ ማለት
የኢትዮጵያ ህዝብ በጅምላ ለመስዋዕትነት የሚነዳ በግ ተደረገ ማለት
ነው፡፡በግ ሲነዳ ለግጦሽ ይሁን ለእርድ አያውቅም፡፡ይህ ህግ ቀጥተኛ
ትርጉዋሜው ዓይናችሁን ጨፍኑና እኛ እናሞኛችሁ፤ጆሮዋችሁን ድፈኑና
እኛ እንስማላችሁ ማለት ነው፡፡ህጉ ፀደቀ ማለት ወላጆች ስለ ልጆቻቸው
ምንም መብት የላቸውም ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ ስለ ህፃናት ስርቆት አንድ ዓለም አቀፍ መረጃ ቢኖር ያን መረጃ
ኢትዮጵያውያን ወላጆች ሰምተው መጠንቀቅ አይችሉም፡፡ዓለም
በሂውማን ትራፊክ እየተሰቃየችና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ተሰርቀው
ለክፉው መንፈስ ለመስዋዕትነት እየዋሉ ነው፡፡ይህን መረጃ ከዓለም
የመረጃ መረቦች ወስደን በብቸኛዋ መተማመኛችን ተርጉመን በፌስ ቡክ
ብንለቅና ወላጆች ተጠንቀቁ የሚል ነገር ፅፈን ፖስት ብናደርግ፤በህዝቡ
ዘንድ ሽብር በመፍጠር በሚል 25 ዓመት ያሳስራል፡፡በዚህ ምክንያት
የሚታሰረው አንድ ሰው ሳይሆን፤ላይክ ያደረገ፣ያነበበ፣ሼር
ያደረገ፣ኮሜንት የሰጠ፣ሁሉም ይታሰራል ነው፡፡ስንቱን አስሮ ይችላል?
ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ጥቂት ሰዎችን ካሰሩ ሌላው ፈርቶ ይተዋል፡፡ደግሞም
ለእንዲህ አይነቱ ቀና ተግባር ጊዜ መድበው የሚፅፉት ውስን ሰዎች
ናቸውና ዋና ዋናውን ማሰር ብቻ በቂ ሆኖ አግኝተውታል፡፡
ይህ ህግ ፀደቀ ማለት ለምሳሌ ስለ ግብረሶዶማውያን አፀያፊነት
ተግባር እየፃፈ ተጠንቀቁ ወገኖቸ፣ልጆቻችሁንም በትምህርት ቤት ስለ
ግብረሰዶም ጥሩነት የሚያስተምር ኩዋርኩለም ቀርፀው እያስተማሩ
ነውና….እባካችሁ ጥብቅ ክትትል አድርጉ ወዘተ…ተብሎ ቢፃፍ፤
መረጃውም በፎቶና በቪዲዮ ቢደገፍ ያን ያደረገ ሰው ይታሰራል ማለት
ነው፡፡ሌላውም ፈርቶ መረጃውን ይፋ ከማድረግ ይቆጠባል ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ታዋቂ የሐይማኖት አባት በይፋ ግብረሰዶማዊ ቢሆንና
መሆኑን የሚያረጋግጥ ይፋዊ መረጃዎች ቢኖሩ እንኩዋን ስለዚያ ታዋቂ
የሐይማኖት አባት ግብረሰዶማዊ መሆን መናገርና መረጃውን
ማሰራጨት፤መረጃውንም ይፋ አድርጎ ቅኑን ምዕመናን ለማስጠንቀቅ
ቢታሰብ አይቻልም፡፡ስም ማጥፋት፣ህዝቡን ማወናበድ በሐይማኖት ላይ
ሽብር መፍጠር፣አመፅ ማነሳሳት፣ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በመረበሽ
በሚል እስር ይጠብቀናል፡፡ስለዚህ የሚያውቁትም ዝም እንዲሉ ህግ
ያስገድዳል!የሚያውቁትም ለማያውቁት መንገር ክልክል ነው! ማለት
ይሆናል፡፡እጅግ የሚያሳዝንና ሁላችንንም ሊያስቆጣ የሚችል ህግ ነው፡፡
በጣም የሚያሳዝነው ይህ ህግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረው
በኢትዮጵያ ላይ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ለምን ኬንያ ላይ ይህ ህግ
አልወጣም?ለምን ኡጋንዳ ላይ ለምን ናይጀሪያ ላይ አይወጣም?ለምን
ኢትዮጵያ ላይ?
ይህ የኮምፒውተር ህግ በሚል ሽፋን የወጣው ህግ በቀጥታ
ከማይክሮችፕ ገጠማ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ምንም ሳይልና ሳመነታ
እንዲቀበል ለማስገደድ እንጂ ለሌላ ለምንም አይወጣም፡፡ነገርየው
በኮምፒውተር አይፒ ነምበር ሁሉንም ዜጋ ከመሰለል ጋር የተያያዘ
ይምሰል እንጂ ከዚያ ያለፈ ነው፡፡ማይክሮችፕ ሲባልም ልክ ኮምፒውተር
ላይ እንዳለው አይ ፒ ነምበር ሰዎች ላይ አይፒ ነምበር መግጠም ማለት
ስለሆነ ተመሳሳይ ነው፡፡ኮምፒውተር የሚሰለለው በ ኤ ፒ ነምበ ነው፡፡
እናም የ666ን ምልክት ስንቀበልና ደማችን ውስጥ ለዘላለም
እንዳይወጣ ሆኖ ሲቀበር የሚቀበረብን ነገር ቁጥር ወይም አይ ፒ
ነምበር ነውና በዚያ አማካኝነት በአንድ በጥልቁ ወይም በአውሬው
አገዛዝ ስር እንሆናለን ነው፡፡ቴክኖሎጂው ረቂቅ ስለሆነም ለብዙዎች
በቀላሉ ላይገባ ይችላል፡፡መረጃ በደንብ ከተለዋወጥን ግን ግልፅ ነው፡፡
ያንን ነው እንዳናውቅና እንዳናወራበት የተፈለገው፡፡ይህ ደግሞ
በሐይማኖት ስም ነው የሚሰጠው፡፡ስለዚህ አሰራሩን የተቃወመ
ኢትዮጵያዊ በኮምፒውተር ህግ ወንጀለኛ ይባላል ይታሰራል ለፍርድ
ይቀርባል ነው፡፡
ዜጎች የክፉውን መንፈስ አሰራር እንዳያውቁና እንዳያሳውቁ አውቀውም
እንዳያጉረመርሙ በሚል ነጥብ ብቻ ነው ይህ ህግ ያስፈለገው፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የተረረቀውና ለመፅደቅ የተዘጋጀው ደግሞ በኢትዮጵያ
ነው፡፡
ልብ በሉ ዓለማችን ላይ ብዙ ሽብር ያለባቸው አገሮች አሉ፡፡ብዙ ጦርነት
ያለባቸው አገሮች አሉ፡፡ብዙ የኢንተርኔት መረጃ ጠለፋ የሚከናወንባቸው
አሉ፡፡ብዙ የደህንነት ስጋት ያለባቸው አገሮች አሉ፡፡በኮፒውተር ሳይንስ
ጣራ የደረሱ አገሮች አሉ፡፡ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉባቸው አገሮችም አሉ፡፡
የእነዚህ አገራት መንግስታት ግን ይህን አይነት ህግ አላስፈለጋቸውም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር ስንት እንደሆነ
ይታወቃል፡፡እ.ኤ.አ በ 2015 የወጣው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር
ልንገራችሁ፡፡ኢትዮጵያ 3.7 ሚሊዮን ህዝብ ኢንተርኔት ይጠቀማል፡፡3.7
ሚሊዮን ህዝብ ፌስቡክ ይጠቀማል፡፡እንግዲህ የሌላውን አገር ስናይ
ለምሳሌ ኢንተርኔት ተጠቃሚው 10 ሚሊዮን ይሆንና ፌስ ቡክ
ተጠቃሚው 2 ሚሊዮን ይሆናል፡፡ይህ ማለት በሌላው አገር ኢንተርኔት
ተጠቃሚ የሚባለው ፌስ ቡክ ተጠቃሚው ብቻ አይደለም፡፡ሌሎች ብዙ
ማህበራዊ ድረ ገፆች ስላሉ፡፡ኢትዮጵያ ላይ ግን 3.7 ሚሊዮን ህዝብ
ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡3.7 ሚሊዮኑም ፌስ ቡክ ላይ ብቻ ነው
እንደማለት ነው፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ተጠቃሚ የሚለው ፌስቡክ
ተጠቃሚውን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
ታዲያ ይህ ህግ ለምን አስፈለገ?ከብት ባልዋለበት ለምን ኩበት
ይለቀማል?መልሱ ቀላል ነው፡፡ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው የመረጃ
መረብ ባሁኑ ሰዓት ፌስ ቡክ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡እነ ዩቲዩብ እነ ምናምን
አሉ፡፡እነሱን ለማየት አቅም ያለው ውስን ነው፡፡ከቁጥርም አይገባም፡፡
ቤታችሁ ውስጥ 10 ሰዎች ካሉ በእርግጠኝነት 9ኙ ፌስ ቡክ እንጂ
ቲዊተር ወይም ሌላ አይጠቀሙም፡፡
ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ክፍያ የመጨረሻዋ ውድ ሂሳብ ያለባት አገር ናት፡፡
በዚህ ዙሪያ ፕሮፌሽኔ ነውና በቀጣይ በሰፊው መረጃ እሰጣችሁዋለሁ፡
ላሁን እዚህ ላይ ይቆየን፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ቤተክርስቲያናችንን
ይጠብቅልን፡፡Habtewold Abebe
ሲራክ ከቤ/ክ የወጣው ለምን ቢባል በቦታው
የነበርን ሰዎች አይተናል ሰምተናል በቦታው ያልነበሩ
ደግሞ ይችን ምክንያት አድርገው የራሳቸው website ከፍተው ፖለቲካቸውንና ስድባቸውን
ያሰሙናል ያውም ከእውነት የራቀ ለማንኛውም
መነሻው ለምን ሲኖዶስ ገባን ነው ለዚህም
ደግሞ ክስ መስርተዋል የክሱን ፍፃሜ እንጠብቅ
ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ አንመለስም ቤ/ክ መጥተው
መደንፋት ቢያቅታቸው ያው በከፈቱት ሚዲያ
እየተሳደቡ ነው ሌላው ፓለቲካንና ሀይማኖትን
እንለየው ምን ያድርጉ መልስ ካገኙ ሰሚ አግኝተዋል
ማለት ነው እባካችሁ የመድሀኒአለም ቤተስቦች
ለእነዚህ ሰይጣኖች መልስ አትስጡ ብትችሉ
Website ከፍታችሁ አታንቡ ፍሬ የለውም
ቤ/ክ የፀሎት ቤት ነው
እውነት ነው ከላይ የተገለፀው ነገር ቤተክርስትያን የፀሎት ቤት ናት እውነት ነው መግባት ስላልቻሉ ፓለቲካ ማስተላለፍ ይሄንን ወብስዬት የከፈቱት ምእመን ትህትና ፍርሀት አይደለም የነሱ ስድብ እኛን እያጠነከረ እንጁ እየላላን እንሄድም በዚ ደስ ይበላችሁ ቀራንዬል መድሀኔያለም ቤተክርትያን የኤትዬጽያ ተዋህዱ ቤተክርስትያን ናት ከዚ ቦሀላ ወድ ሃላ አትመለስ ለምን ትለፋላችሁ እባካችሁ የተወደዳች ብርቅዬ የመድሀኔያለም ወዳጅች ለነዚ ከመመለስ እንፀልይላቸው የተደፈነ ልባቸው ተከፎቶ ቢመለስ
ወደቅድስት ቤተክርስትያን።
betam yemigerm newu ewunet ten eger bilo sewun mesadeb betam dedebnet newu abzagzwu ezeh yesafut tekmachewu yetekabachewu ewunetin mesemat yemayefelegu areyosoch nachewu betekirestiyan ye wenbede washa satehon yeselot bet nat beteleye minitewab bemil sem yemitesefi weyem yemtesef aryos egziyabeher libona yesetachu wededachehum telachihum ye feredebet wusane mekerebu ayekerem yenantem betebach papase tebye leba kadere wagawun yagegale endeleba libsun keyerona amed meselo leteyake sikereb limin atagebuten neber tadiya ewunetega kiristiyan Sirake hayemanoten alasedeferm bilo le ewunet komoal ye enante ayenetu maferiya gin bebado meda yechohal asemesay kiresetiyanoch nachu ewunetegoch bitihonu noro ewunetegawun eyasadedachehu leacheberberiwu kese agezachu atesadebum neber kiresetina yebeletal ye kes chira teketlo ke menchachat. libona yesetachu Melaku endehone badebabaye eyetegalete newu ye enante achebchabinet waga yelewum.
መሰንበት ደግ ይባል ነበር ድሮ…ግን የሰነበቱበትን መልካም ነገር አይንም ለማያት ስትታደል፤ጆሮም ለመስማት ሲበቃ ነው። መሰንበታችን የሚሟላው። አሁን አሁን ግን በተቀደሰችሁና ስንቶች ዳጋጓች አባቶቻችንና ቅዱሳን አባቶቻችን መስዋህት በከፈሉባት በደሙም በተዋጀች የእግዚአብሔር ማደሪያ የሚሰማውና የሚታየው ለሰሚውም የሚከብድ፤ ለተመልካቹም ግራ የሚያጋባ ከሆነ ውሎ አድሯል። ፍርዱ ተዛብቷል። ለእውነት ያደረ ካህንም በባቲሪም ተፈልጎ አልገኝ አለ። (የሉም ማለቴ አይደለም ነገር ግን ቁጥራቸው አነሰብን ማለቴ ነው) የቀደሙትም ሽማግሌዎች በቤተ መቅደሱ ስለዓለም ምን አለችና ምን ተወራ እንጂ ቅዱስ ወንጌሉ ምን ይላል ከማለት ተቆጥበዋል። በእርግጥ ይህ የቤተክርስቲያን ችግር የተባባሰው በሰሜን አሜሪካና በአውራፓ ሲሆን ችግሩም የቤተክርስቲያን መስራቾች በተለያየ ምክንያት ከሀገራቸው በስደት የሚገኙ ምዕመናን በመሆናቸው ነው። አጀማመሩ ለመልካም ቢሆንም ቅሉ የመሰረቷትን ቤተክርስቲያን እንደ ግል ንብረታቸው የሚመለከቷት ግለሰቦች ቀጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከት ይገኛል። ታዲያ እነዚሁ በለ ሀብቶች ( ጥሬ ቃሉ ተገቢ ባይሆንም) ቤተክርስቲያኗ በስርዓትና በትውፊት ከመሄድ ይልቅ እነሱ በተለያዩ ጊዜ በሚሞነጫጭሩት መተዳደሪያ ደንባቸው እንድትሄድ ስለሚፈልጉ ካህኑም የነዚህ ሰዎች ቅጥረኛ ነው ማለት ነው። በጣም የሚገርመው ስለቤተክርስቲያን ስርዓትና ትውፊት መናገር በእነዚህ ሰዎች ፊት በጣም ያስጠይቃል። ሌላም ተቀጥያ ስም ያሰጣል። በተለይ ለወጣቶች የሚሰጥ ስም “ወያኔ ልኳቸው ነው! “ማህበረ ቅዱሳን ናቸው!፣ ቤተክርስቲያናችንን ለወያኔ ሊያስረክቡ ነው!፣ ብቻ በጣም ብዙ… በየቦታው የደረሰበት ያውቀዋል። በጣም የሚገርመው ግን እነዚህ ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፍተው ቢወጡም ከወጡበትና ከተተከለችላቸው ቤተክርስቲያን ምንም የተሰማ ኲሽታም አለመኖሩ ነው። በእርግጥ ስርዓቱና ቅኖናውን ተከትለው ስለሚተከል በቀላሉ ሊናወጡ አይችሉም። እያየን ያለውም ይህን ነው። በየቦታው በዚህ ምክንያት የተተከሉ አብያተ ክርስቲያናት ዕድገታቸውና አገልግሎታቸው የሚያስደስት ነው። የቤተክርስቲያናችን ችግር የፈለገውን ያህል ቢበዛና ያለውም ሁኔታ ብዙም ባያስደስተንም የቤተክርስቲያን ችግር እኛው እራሳችን የፈጠርነው መሆኑን ተገንዝበን ቢቻል እንዳይባባስ ችግሩን ከምንጩ ማድረቅ ካልተቻለም መፍትሔውን በጋራ ማፈላለግ ይጠበቅብናል እንጂ የኃሊት እየሄድን ተቆርቊሪ ይመስል የቤተክርስቲያንን ፈተና ማብዛት ከእኛ አይጠበቅብንም። ለዚህ ጥሩ ትምህርት ዲን ዳንኤል ክብረት በአንድ ወቅት በጣም ጥሩ ትምህርት “ችግሩን አብረን እንፍታ ወይስ ችግሩ ሲፈታ አንድ እንሁን” በሚል ርዕስ ያስተማረውን ትምህርት መስማት በቂ ነው። እግዚአብሔር አምላክ የቤተክርስቲያናችንን ፈተና ያስታግስልን።
ወደ ተነሳሁበት ልመለስና ይህን ሀሳብ እንድሰጥ ያስገደደኝ ይህን ጽሑፍ አንብቤ ዝም ብዬ ማለፍ ስላልቻኩ ነው። እንደመወያያ ሆኖ የቀረበውን ጽሑፍ ይዘት እንዲሁም ለጽሑፉ መነሻ የሆነውን የአባ ፋኑኤል ምላሽ እና በዚህ መወያያ ጽሑፍ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉትን ግለሰቦች ማየት ተገቢ ነው።
በመጀመሪያ ለናሽቪል ደብረ ቀራኒዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በአቡነ ፋኑኤል የተመለሰው ምስላዊ ምላሽ በጣም የሚደነቅ መረጃ ሆኖ ሳለ ለምን አድበሰብሰውት አላለፉ በማለት ተገቢ ያልሆነ ትችት በጸሓፊው ሲቀርብ በጣም ያሳዝናል። ጸሓፊው አግባብ ያልሆነ ትችት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት የተባለውንና አቡነ ፋኑኤል ምላሽ የሰጡበትን ምክንያት ማጤን ነበረባቸው። ስለዚህ ትክክለኛ እርምጃ በመውሰድ ምዕመኑ እንዳይወናበዱ ተገቢ ምላሽ ሰጥተዋል ማለት ነው። ይልቁኑ በተራገበው አሉባልታ ሀገረ ስብከቱ ምላሽ ባይሰጥ ኖሮ እውነትም ችግር መኖሩን ያመላክት ነበር። ስለዚህ እነ ጳጳስ(ካህናት) ተሳዳቢና ቤተክርስቲያን ከሳሽ በአደባባይ እናዋርዳለን ብለው እራሳቸው ቀለው መገኘታቸውን አየን ማለት ነው። እንግዲህ ይህን ነው ያገኘነው ከምስሉ። ለምን እውነቱን ተናገሩ ሕዝቡም ያለውን እውነታ ለምን ያውቃል ማለት አግባብ አይመስለኝም። ሲጀመርም ቤተክርስቲያንንም ሆነ ካህናቱን ለምድራዊ ፍርድ ማቅረብ ባልተገባ ነበር። ማንም ከክርስቶስ ቤት ጋር እልህ ተያይዞ አሸንፎ አያውቅም። የፖለቲካ ጥማትን በቤተ ክርስቲያን ካልተወጠው ብሎ ለገላጋይ አልመች ማለት አግባብ አይደለም። ይሁንና መሸነፍን አምኖ መቀበል ያባት ነው በድጋሚ ይህንን ግራ የገባው ትችትና ቅራቅቦ ለሕዝብ እይታ ማቅረብ ተገቢ አልነበረም። በዚሁ ጽሑፍ ውስጥ ምንም ትርጉም የማይሰጡ ብዙ አረጎች ቢኖሩም ለሁሉም መልስ በመስጠት ጊዜ ከማባከን ተቆጥቤለሁ።
2ኛው.አሁንም የዚህ ቅሬታ አቅራቢ ቡድን ይሁን ግለሰብ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ችግር በግልጽ መወያያት የፈሩ ነው የሚመስለኝ በግሌ። ምክንያቱም ብዙ ሊነገሩ የሚገቡ እውነታዎችን ሸፋፍነው ለሳቸው የፈለጓትን ትንሿን ችግር ላይ ማተኮር መፈለጋቸውን በተደጋጋሚ ሲያሳዩ ተስተውለዋል።ሌላው ይቆየንና ጸሐፊው በሚያነሱት ዙሪያ እንኳን ብንነጋገር ብዙም የሚያስኬዳቸው አልመሰለኝም። በተደጋጋሚ በርካታ ምዕመናንና ካህናት ጭምር ከቤተክርስቲያኑ ሲለዩና ካህናቱ በቦርድ (በግለሰቦች) ሲባረሩ ዝምታን የመረጡ አሁን አንድ ግለሰብ በደል ደርሶበታል ማለት ምን የሚሉት ጩአት ነው? የሚገርመው ይህ ግለሰብ በተደጋጋሚ የሚያሳየው ኢ-ክርስቲያናዊ ምግባሩ አግባብ አለመሆኑን መቼም ሳይረዱት ቀርተው ነው እንዳልል ያስቸግረኛል። በተለይ በካህናቱ ላይ የሚያሳየው አቋሙ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ አልነበረም። የተወሰደበት እርምጃ እንደ ቤተክርስቲያን አግባብ ነው ብዬ ባላምንም(የፈለገውን ቢበድል በፖሊስ ከቤተክርስቲያን ማስወጣቱን እንደ አንድ ምዕመን ይከብደኛል። ሌሎች አመራጮችን መጠቀም ይቻል ነበር። አስፈላጊ ከሆነ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይደርስ ቤቱ መጥሪያ ማስላክ ይቻል ነበር። ይህ ግን በካህኑ ተመክሮ እሻፈረኝ ካለ ማለት ነው) ቤተክርስቲያኗ ግን ምናልባት ከዚህ የተሻለ ምርጫ ስላልነበራት አድርገዋለች። ይህ ሰው በየሳምንቱ ለሚያሳየው ምግባሩ ስንት ቀን ተው ይህ ቦታው አይደለም ብለውት እንደሆነ አላውቅም። ካህናቱም ላይ እጁን ሲቀስር ተው ብላችት እንደሆነ ለራችሁ መልሱ። ምዕመኑንም ሲሳደብና ቤተክርስቲያኑን ሲያምስ አሁንም ተው ማለታቹን አላውቅም። ስለዚህ አሁን የተወሰደበትን እርምጃ ተገቢ አይደለም የምትሉ ሁሉ አስቀድማችሁ ይህን ሰው ተው ከተግባርህ ተመለስ ከማለት ይልቅ በርታ ከጎንህ ነን ያላችሁት ይመስል የውንብድናውን ተግባሩ ሲያደርስ ቆይቷል። ስለዚህ አሁን ላይ ደርሳችሁ የተወሰደበት እርምጃ አግባብ አይደለም ከማለት ይልቅ አስቀድማችሁ ከዚህ እኩይ ተግባሩ ማስቆም ትችሉ ነበር። በአጠቃላይ ይህ ሰው ጥሩ ስራ አልሰራም። ቀድማችሁ በለቀቃችሁትም ኢ-ክርስታናዊ ምግባርም የምንሰማው ድምጽ የዚህ ሰው ድምጽ ከሆነ(ብዙዎቹ የሚስማሙበት) ደጋግሞ ስህተት ከመስራት አንዴ እንኳን ወደ ራሱ መመልከት ነበረበት። በአለም መድረክ የሰለቸንን መሰዳደብና መወራረድ ወደ ቤተክርስቲያን ማምጣት አልነበረበትም።ለዚህ እኩይ ተግባሩ እዚያ ድረስ መሄድ ባልተገባው ነበር። አየህ ይህንን ሁሉ ስህተት ሲሰራ አንዳችሁም ተው ልክ አይደለህም አላላችሁትም። ስለዚህ ለሚሰራው ስህተት የልብ ልብ ከመስጠት ውጭ። ማንም ሰው ፖለቲካዊ አቋሙን እደግፍለታለሁ ( በግሌ) ነገር ግን የግል ፖለቲካዊ አቋማችን ከቤተክርስቲያን ውጭ መሆን ግን ይጠበቅብናል። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ቤትና ስለመንፈሳዊ ሕይወታችን የምንማማርበት ቦታ እንጂ ስለ ቄሳር የምንፖተልክበት ስፍራ አይደለችም። መቼም ይህን ጠንቅቃችሁ እንደምታውቁት ባውቅም በብዙዎች ግን ሲተገበር አይስተዋልም። ስለዚህ ሰዎችን ወደ ነጻ የሆነ ውይይት መድረክ ከመጋበዛችን በፊት ርዕሳችን ያወያያል ወይ ብለን ማሰብ አለብን። የቤተክርስቲያን ስርዓት ፈረሰ ከማለት በፊት አስቀድማችሁ ማየት የነበረባችሁ፦
1ኛ. በመጀመሪያ ፖለቲካና ሐይማኖትን ለያይቶ ማየት። ይህም ብቻ ሳይሆን የቱን የት ቦታ አንስተን መወያየት እንዳለብን ማወቅ። ያኔ ቤተክርስቲያኑ ለምን በእናት ቤተክርስቲያን ስር ተጠቃለለ ለሚለው ግልጽ መልስ ማግኘት ይቻላል። አለበለዚያ ግን እንዲሁ እንደተዘበራረቀብን የተሰጠችን ጊዜ በአግባቡ ሳንጠቀምባት ትሄድና በታሪክ ተጠያቂ ታደርገናለች።
2ኛው.በዚህ ሰው ተወሰደ ካላችሁት በደል ይልቅ በካህናቱ ላይ የተወሰዱት በደሎችና እርምጃዎች የከፉ ናቸውና ይህን ያህል አያነጋግርም ነበር። በእርግጥ ሁላችንም ሲደርስብን አይደል የምንናገረው? ይህ ነው እንግዲህ የታየው። ያን ሁሉ በደል ሲደርስ ዝምታን እንዳልመረጣችሁ አሁን ምን አነሳሳችሁ?
3ኛው. እየሄዳችሁበት ያለው መንገድ እንኳን ብዙ እንደማያስኬዳችሁ እያወቃችሁ ገንዘባቹን ለጠበቃ ማጥፋታችሁ ምን የሚሉት እብደት ነው? እስቲህ አሁን ማን ይሙት ቤተክርስቲያን በምዕመናን ስትከሰስ ማንን እንኲን እየከሰሳችሁ እንደሆነ ለአንድም ሰከንድ ቆም ብላችሁ አለማስታዋለችሁ ያሳዝናል። ሁላችንም በአንድ ወቅት ለቤተክርስቲያን አቅማችን የፈቀደልንን አድርገን ይሆናል ነገር ግን የምናደርገው በሰማይ የበለጠ እንደሚጠብቀን በማመን እንጂ ባንክ ቤት እንደምናደርገው ባሰኘን ጊዜ ተነስተን እንዳሸን እንሆናለን ማለት አግባብ አይደለም። ከቀደሙት ወንድሞችና እህቶች ብዙ መማር ይቻል ነበር። ስለደረጉት ሁሉ በሰማይ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይጠብቀናል ብለው ምን ድምጽ ሳያሰሙ ወጡ እንጂ እንደ እናንተ ለገላጋይ አላስቸግር አላሉም። የግዴታ መስማማት ባይጠበቅባችሁም በልዩነት መስማማትን መቀበል መቻል ግን ነበረባችሁ። ስም ማጥፋትና እኛ ካልነው በቀር ማለት ግን በየትኛውም ስሌት አግባብ አይደለም። ሽንፈትንም ተቀብሎ ተስማምቶ መኖርም አንድ ነገር ነው አሊያም ሌላ አማራጭ መውሰድ ሲቻል አታካራ መፍጠር አግባብ አይደለም ነው።
3ኛው. በዚህ የውይይት መድረክ ላይ አስተያየት የምትሰጡትን ግለሰቦች ይመለከታል። በእርግጥ ማንኛውም ሰው የተሰማውን ስሜት የመናገር መብቱ የተጠበቅ ቢሆንም መሰዳብ ግን አግባብ አይደለም። ሲቻል ተናግሮ በምሳሌ ማስረዳት አለዚያም ስህተቱን በእርጋታ ማስረዳት እየተቻለው በስሜት ብቻ መነዳት ተገቢ አይመስለኝም። ይህ የሚያሳየው የብስለት ማነስ ይታይባችዋል። ስሜታዊና ግልፍተኝነትም አግባብ አይደለምና በተለይ ለነገሩ ገና እሸት የሆናችሁ ለስድብ ባትገባበዙ መልካም ነው። ከስድብና ከዛቻ የምታተርፉት አንዳችም ነገር አይኖርምና። አንዲት ጫፍ ይዛችሁ ነገሩን ከስሩ ሳታጤኑት ለቁጣና ለጥል አትሩጡ። አሁን በቦታው ላይ ስላላችሁ ብቻ እንደቆረቆራችሁት ያህል ደረታችሁን ነፍታችሁ ባለጊዜ አትሁኑ። ትላንት በቦታው ሌሎች ነበሩ ዛሬ ደግሞ ጊዜና ሁኔታዎች እናንተን በቦታው አደረገች ነገ ደግሞ ማን በቦታው እንደሚሆን አይታወቅምና ትዝብትንና ጥልን አንወራረስ ነው መልዕክቴ። በተለይ በጣም ለቤተክርስቲያኑ አዲስ የሆናችሁ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት እንደ ፈላጭ ቆራጭ የሚሰማችሁን በለጊዜዎችን ለማለት ነው። በተደጋጋሚ ይህ ስህተት በዚህ ቤተክርስቲያን ስለሚታይ ነው።
በመጨረሻም አሁን ቤተክርስቲያኑ እየሄደበት ያለው መንገድ ጥሩ ጅማሬ ቢሆንም ብዙ የሚቀሩትና መስተካከል ያለባቸው ስራዎች አሉ። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቀስ በቀስ እንደሚስተካከሉ ተስፋ አድርጋለሁ። ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እንቅፋት የምንሆን ሰዎች ቦታችንን ብናውቅ በተሰጠንም መክሊት እንድንጠቀም እርሱ ይርዳን። ቤተክርስቲያኗ ብዙ ይጠበቅባታልና ነጻነቷን ታውጅ ዘንድ ለቀቅ አድርጓት። ፖለቲከኞችም እባካችሁ የፖለቲካ አጃንዳ ይዛችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን አትሂዱ።ቤተክርስቲያን የክርስቶስ መንግስት የሚሰበክባት ቦታ ናትና ለምን ወደ ቤተክርስቲያን እንደምንሄድ በአግባቡ እንወቅ። የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ በቤተክርስቲያን ውስጥ ምዕመኑን ማወክ ከሌሎቻችን ይበላጥ ለሀገራችን የተለየ ፍቅር እንዳለን አያመላክትም። የሀገር ፍቅርም በቦታው ሲገለጥ ውበት ይኖረዋል። ሀገር ወዳድ መሆናችንም ይታያል። ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት!!! ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ ይላልና የክርስቶስ ክብሩ ስጋውና ቅዱስ ደሙ በሚፈተትባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ልናከብር ይገባል። የቆምንባት የተቀደሰች ስፍራ መሆኑን አውቀን የሚታየውን የእግራችንን ጫማ ብቻ ሳይሆን በልባችን ውስጥ የሚመላለሰውንም የትብዕት ጫማ አውልቀን እንድንቆም እግዚአብሔር ይርዳን። ልቦናችንን አስገዝተን በቤቱ እንድንመላለስ እግዚአብሔር ይርዳን!!!
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል።እባካቹን ሁላችንም አንድ እምነት ያለን የተዋህዶ ልጆች ነን።በመሀከላችን ጊዚዬዊ አለመግባባት ቢኖርም እንኳን እርስ በእራሳችን በአለማውያን ፊት መዘላለፋችን ተገቢ አይደለም።እያንዳዳችን ለኦርቶዶክስ እምነታችንም ሆነ ለኢትዮጵያዊነታችን አንባሳደሮች ነን።አንዳችን ባጠፋነው ሀይማኖትም ሆን አገር በኛ ሰም ይሰደባል።ቤተመቅደሱ የክርስቶስ እንጂ የግለሰብም ይሁን የመንግስት አይደለም ሊሆንም አይቻልም።ሌላው ባለንበት አገር ህግ አለምንም መሸራረፍ በስራላይ የሚውልበት እና ማንም የማንንም መብት ከህግ አግባብ ወጭ የማይደፈርበት ስርአት ባለበት እገር ውስጥ የምንኖር መሆናችንን አንዘንጋ።ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን። ባደባባይ ቢሰድቡንም እኛ ግን የክርስቶስን። መንገድ እንከተል።
የነበረዉን ማን ይናገር” አስተያየት ግዜ ዐስጄ በደንብ ባነበውም ሚዛናዊነትና መረጃ የጏደለው ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡ለነገሩ ፀሀፊዉ አነደጠቀሱት ለእውነት የቆሙ ካህናትና ሰባክያን ፈልጎ ማግኘት ዘመኑ ከባድ እንደአደረገው ሁሉ እውነተኛ የእምነቱ የቆመ ምዕመንም የዛን ያህል መሆኑ የምንስማማ ይመስለኛል፡፡ይህ ከሆነ መነሻ ችግሩ “ለምን ኦውነተኛ ካህን፤እውነተኛ ሰባኪ፣እውነተኛ ምዕመን በዚህ ባለንበት ዘመን ጠፋ?ቾግሩስ ምንድነው?በተለይም በአለደጉ ሀገሮች በተለይም በኢትዮጽያ መንግስትና ቤተክርስቲያን ተለያይተው ያውቂ ነበር?በተለይም አሁን በአለንበት ዘመን የመንግስትን በቤተክርስታያን አስተዳደሪያዊ ተጽእኖና ቀጥተኛ አፍራሽና አውዳሚ ድርጋት በኢትዮጽያ ሀገራችን ላይ የሚታየውን መቃወም ፖለቲከኛ ያስብላል?እስቲ ለይተው ያሳዪኝ?እርሶ እንዳሉት በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ያሉ ምዕመናን ለምን ከማናቸውም የኣትዮነጽያ መንግስት ፖለታካ ተፅእኖ ውጭ እራሱ በቀረፀው መተዳደራያ ደንብ ልተዳደረ ብሎ ህግ ቀረፀ?እንደርሶ የቀለልኩ አይደለሁምና;የሚመነጫጭሩትመተዳደሪያ ደንባቸው”አልልም፡፡ኢትዮጽያማ ምርጫም ነፃነትም የለም እርሶም ወደዚህ ያቀኒት ይህን ፍለጋ መሰለኝ፡፡አባመላኩ ቀደም ሲል ኢትዮጽያ ቢሆን ኖሮ ልክ እናስገባቸዋለን፡፡ሌላው መረጃ በሌለህ ላይ መፃፍ መዋሸትና በአንድ አይን ብቻ ከምትመለከተው ያየኸውን ቢሆን ይመረጣል፡፡የሚሆነውን በትግስት ማየት ይመረጣል፡፡ለመፍረድ ግዜ መሰጠት፡፡ብዙ የተምታቱ ነገር ልክ እኖደነበረ ማቅረብህ ከላይ በመግቢያህ ላይ እንደጠቀስቀው አሲቲ “ይህን ይህን አደረ፡ካሆኖ ተሳበ ቦለህ እሶቲ ጥቀስ?አረግጠኛ ነኝ ለመዋሸት ኬልሆነ በቀር የለሆም፡እግዝአብሕሮ ከያየኝም አያውቀኝም ከሆነ ጥሩ፡፡እኛ እሿ የተሰራውን ድራሜ በአይናቾን የአየነው ነው፡፡የአባ መላኩ ቅጥፈት 250 ፈረሠ የሚሊት ውነሸት ነወ፡፡እነዴት ድርጉት ታሪክ ነው በቪድዮ የተቀረፀ ነው፡፡ሰው ቁጮ ተብሎ ሀሳብ ተለዋውጦ ዮህ የተሻለ ነው ተብሎ የተሻለው በመግባባት ይደረጋል፡፡ይሆ አልሆነም የፖለቲካ ቁማር ነው እኮ ቀሲስ፤፤ስለአልነበርክ አላዝንብህም፡፡ደሞ እንደ ወጣቶቹ ያልፈለጠ ሹልክ ብሎ ይውጣ ትላለህ የደናቂርት መፍትህ፡
እፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ወሬውሬወሬ ምን አለ ዝም ብትሎ እንደፈለግ ይፈንጩ ምእመን ዝም በሉ
መስፍን አንተና መሠሎችህ ግን ለምን የሰው ልክ አይገባቹም?ለመተቸትም እኮ እሚያገናዝብ ህሊና ሊኖረን ይገባል።እናተ እኮ አለኛ የተማረ የሚያውቅ ላሳር አላቹ።ለመሆኑ ከስህታቹ መቼ ይሆን የምትማሩት?ወድቃቹም እንኳን ለመማር ፍላጎቱ የላቹም።ለሰው ልጅ በህይወት ዘመኑ መውደቅ መነሳት አዲስ ነገር አይደለም።የናንተን የሚለየው ግን ከስህተታቹ ለመማር መቼም ዝግጁዋች አይደላቹም።ከፖለቲካው ልጀምር እና ሀሳቤን ልዘርዝር። አንድ ፖለቲከኛ ሕዝብን አሳምኖ አገርን ለመምራት በመጀመሪያ ለራሱም ለሌላው ጥሩ ምሳሌ መሆን አለበት።የአንተንና የምስሎችህን አገር ያውቀው ፀሀይ የሞቀውን ከሰማኸኝ አውነታውን ከትህትና ጋር ላስረዳህ።አንተና እኔ ክምንጠላው ኢሀዴግ ይልቅ የኢትዮጵያ ጠላቶች እናንተ ናቹ፤ምክንያቱም ኢህዴግ በዘር ሲለያየን አላማውን በተግባር አንተ የእገሌ ዘር ነህ አንተ ደግሞ የዚህኛው ጎሳ በማለት የኢህዴግ አላማ አስፈፃሚ ከናንተ በላይ ማንም የለም።በመጀመሪያ ደረጃ ያብዛኛዎጭቹ የናንተ የሂይወት ታሪክ ብንመለከት እቁብ በልቶ የማይከፍል፣አራርቆ መውለድ ሲሉ ሰምቶ ከሁለትና ከሦስት ሴት ወልዶ ሴቶች እህቶቻችንን የደም እንባ የሚያስለቅስ፣እውነተኛ ጓደኛውን በገንዘብ ለውጦ የሚከዳ እና ብዙ ማለት የቻላል።ምን እይነት መንደርተኛ ነው አትበሉኝ?አውነታውን ቢመርም ይጋቱ ብዬ ነው።በጣም የሚገርመው ሰልፍ እንውጣ ተብለን ስንውጣም የሠልፉ ፈላጭ ቆራጭ አስተባባሪዋቹም እነዛው በጥሩ ምሳሌነት ሊታጩ የማይችሉት የኢህዴግ አላማ አውቀው ሳይሆን ባለማወቃቸው የሚያስፈፅሙት እነዛው ሰዋች ናቸው።ዝምታችን ኢህዴግን በማፍቀራችን ሳይሆን ዝምታችን ሥራው ለሰሪው እሾኽ ላጣሪው ባለመሆኑ ነው።ችግራችን ምን ድነው ብሎ እራስን ከመፈተሽ ይልቅ ቤተመቅደስ ገብቶ በሰላማዊ ምእመናን ላይ ዘራፍን ምን አመጣው?እኛ ኢትዬጵያውያን እንደ ልጆች የሰጣቹንን ሁሉ በማንኪያ አንጎርስም።የሚያስተውል የሚያገናዝብ ህሊና አለን።ክርስቶስ እንድ ያደረገውን ሰው ሊለያይ ቢሞክርም ትርፉ ኪሳራ ነው።ቤንዝን ብታርከፋክፉ ክርቢት ብትጭሩ በክርስቶስ ቤት ውስጥ የሚነድ እሳት አይኖርም!!!በዘርና በእምነት እንለያይም!!!በክርስቶስ ደም በታነፅው ቤተመቅደስ ውስጥ ምድራዊ ፖለቲከ ትርጉም የለውም!!!ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ከናሽሺቪል ቀራንዮ መድኅኒአለም
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=10205617098136421&id=1522572250
እውነት ብለሀል ግን እነዚህ መሠሪ ካድሬዎቾ ክርስቲያን መስለው ለያዬን ከፋፈሉን የካህናት ቆብ አድርገዎ ካባ ለብሰው መነኩሴመስለው አንድ የነበረውንከፈሉት፣ገዳማት ታረሱ ተቃጠሉ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ ንብረትዋ ተመዘበረ፣አባቶች ተሰደዱ፡አባቶቾ እቤቴቸው ቸሰብሮ ተደበደቡ፣ምዕመኑን ተሰደደ፣ይህም አልበቃ ብሎ 50000ኢእማንዬን ህንነፃ ሊሰሪ ነው፣የምዕመኑ ቁጥር ወደ ታች ወረደ፣፣እርስ በእርስ አፋጁን፣የናሽቤል መድኃኒአለም አንድ የነበሸው ዛሬ አራት ደርሷል፣ምዕመኑን አየተሰደበ በቤቱ እንዲቀር ሆነ፣፣እነሱ ቂጠጭ ብለው እኛን መሰሎቻቸውን በጥቅም ገዝተው ምዕመኑን እያባሉት ነው፡፡ይህን መቃወም እንጂ ቤተክርስቲያን ማን ያፈርሳል?የገነባው ለዚህ ያደረሰውስ ማን ሆኖ ነው?ቤተክርስቲያን ነፃ ትውጣ፡፡አባቶች አንድ ይሁኑ፤ያለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ቤተክርስቲያንን ያስተዳድሩ፡፡ማለት ፓለቲካ ነው?ፎቅር ይስፈን ቤተክርስቲያን ከጎሳ አስተሳሰብ ነፄ ትውጣ ሜለት ፓለቲካ ነው?አንድ ከመንግስት ነፃ የሆነ ሲኖዶስ እስኪመጣ ድረስ ሁለቱንም እንቀበል አባቶች እንድ እስኪሆኑ ድረስ ማለት ፖለቲካ ነው?ለ
በግፍ የታሰሩት ይፈቱ፣ስደት ይብቃ፤ማለት ፓለቲካ ነው?እስቲ አስረዱ?ሙሴ የተመረጠው እኮ የፈርዖን በባርነት መገዛት አስቀጥቶት ነው ግፈኛና የፈርኦን ወታደር ጠድሎ የተሰደደው፡፡ያስቆጣው በሰው ላይ የሚደርሰውን ግፍ ጠልቶ ነው፡፡ታዲያ ፖለቲከኛ ነበር እንዴ?በታላቅ ክብር የተጠራ መሪ ነው፡፡እንዴ እናች በግብጽ እስራኤል ህዝብ ላይ አሁን እየደረሰ ያለው ግፍ አይበልጥም?ይህን መናገር ፖለቲከኛነት ነው?እነዚህ ማቅ የማያስተምሩት ነገር የለም በሀይማኖት ሽፋን ትውልዱን አኮላሹት፡፡እነስቲ እንወያይበት ጎበዝ፡፡እናስተውል አንገት የተሰራው ዞር ብሎ ነው ይላሉ አቤቶቾ እነሱ በስንት ጦርነት ነው ያስረከቡን፡፡እንወያይ፡?
ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ልጆቿን ፡ የምታስተኛ ፡ ሞግዚት ፡ ሳትሆን ፡ የሚቆሙላትን ፡ ጀግኖች ፡ የምትወልድ ፡ እናት ፡ ነች ፡፡
ነፍስ : የሌለው : ስጋ : ለወገኑ : ምንም : እንደማይጠቅም : ሁሉ : ምግባርና : ሃይማኖት : የሌላቸው : አዋቂዎችም : ለሀገራቸው : እንደማይጠቅሙ ፡ የታወቀ ነው ፡፡ ምክኒያቱም ፡ አንድ ፡ አዋቂ ፡ እራሱን ፡ ችሎ ፡ ወገኑን ፡ ለመረዳትና ፡ ለመታደግ ፡ በመጀመሪያ ፡ ሃይማኖት ፡ ከዚያም ፡ ሥነ-ምግባር ፡ ያስፍገዋል ፡ አለዚያ ፡ ሕዝብ ፡ የሚጠፋበትን ፡ ደሀ ፡ የሚሞትበትን ፡ አገር ፡ የምትዋረድበትን ፡ መርዝ ፡ ይረጫልና ፡፡
ቤተ ፡ ክርቲያንን ፡ የሚጠብቅ ፡ ትናንት ፡ የነበር ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ዛሬም ፡ የሚወለደው ፡ ጭምር ፡ እንጂ ፡፡ ማናችንም ፡ ሰው ፡ እንደመሆናችን ፡ መጠን ፡ ለመፈጠራችን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዓላማ ፡ ውጪ ፡ ሌላ ፡ ምንም ፡ ዓይነት ፡ የግል ፡ አላማ ፡ አለን ፡ ብንል ፡ መለኮትን ፡ እየተጋፋን ፡ እንደሆነ ፡ ሁላችንም ፡ ልናውቅ ፡ ይገባናል ፡፡ ያለ ፡ እናት ፡ የተፈጠረ ፡ ልጅ ፡ የለም ፡ ያለ ፡ አባትም ፡ የመጣ ፡ ልጅ ፡ የለም ፡፡ በሰው ፡ ሰውኛል ፡ እኛን ፡ ያስገኙ ፡ ቤተሰቦቻችን ፡ አሉን ፡፡ ስልዚህ ፡ ከእነዚህ ፡ ቤተሰቦቻችን ፡ የቱንም ፡ ያህል ፡ ርቀትና ፡ ሁኔታዎች ፡ ቢለዩንም ፡ ቤተሰብነታቸውን ፡ ፍቅን ፡ ልንጥለው ፡ አንችልም ፡፡ የእናቱን ፡ እና ፡ የአባቱን ፡ ፍቅር ፡ ለመጣል ፡ የሚያስብ ፡ እና ፡ የሚርቅ ፡ ሰው ፡ አወዳደቁ ፡ እጅግ ፡ የከፋ ፡ ነው ፡፡
ይህም ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ማንም ፡ እራሱ ፡ እንደአዋቂ ፡ አይቱ ፡ መሰረቱን ፡ መናቅና ፡ መንቀፍ ፡ አዋቂ ፡ የሚያስብልበት ፡ ምንም ፡ ጭብጥ ፡ የለም ፡ ይልቅ ፡ ጽንፈኝነትን ፡ ያሳያል ፡ እንጂ ፡፡
ይህን ፡ እንደ ፡ ምሳሌ ፡ እንየውና ፡ ከቅድስት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ በአጋጣሚም ፡ ወይም ፡ በሰው ፡ ሰራሽ ፡ ችግር (ፖለቲካ ) ፡ ወጥቶ ፡ (ከአገር ፡ ውጪ ) ፡ የራስን ፡ የእምነት ፡ አቋም ፡ ማራመድ ፡ የሚችሉበትን ፡ መንገድ ፡ መመስረት ፡ የሚቻል ፡ የግል ፡ መብት ፡ ቢሆንም ፡ ስርዓቱን ፡ ቀኖናውን ፡ ዶግማውን ፡ ሁሉ ፡ ከእናት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ወስዶ ፡ በእርሷ ፡ ሲኖዶስ ፡ አልመራም ፡ ማለት ፡ ይሄ ፡ ከመረቁ ፡ እንጂ ፡ ከአጥንቱ ፡ የለውበትም ፡ ብሎ ፡ እራስን ፡ ማጃጃል ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ የግል ፡ ጥቅምንም ፡ ጭምር ፡ ማጋለጥ ፡ ነው ፡፡ ኦርቶዶክስ ፡ ነኝ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ የአገር ፡ ቤቱን ፡ ሲኖዶስ ፡ አልቀበልም ፡ ማለት ፡ ደመናን ፡ ወዶ ፡ ዝናብን ፡ የመጥላት ፡ ፈሊጥ ፡ ነው ፡፡
ማንም ፡ ክርስቲያን ፡ የሆነ ፡ ሰው ፡ የሚሞትበትን ፡ አያውቅም ፡ ከተወለደበት ፡ በስተቀር ፡፡ ስለዚህ ፡ በብዙ ፡ መልኩና ፡ በብዙ ፡ ችግሮች ፡ ስደትን ፡ አሜን ፡ ብሎ ፡ የተቀበለ ፡ ሕዝብ ፡ የእምነቱን ፡ መሰረት ፡ ነቅንቆ ፡ አዲስ ፡ መሰረት ፡ ልመስርት ፡ ብሎ ፡ መነሳት ፡ ይህ ፡ እራሱን ፡ የቻለ ፡ ሌላ ፡ አጀንዳ ፡ ነው ፡፡ እርግጥ ፡ የፖለቲካ ፡ ስደተኛ ፡ መሆን ፡ እና ፡ ሲኖዶሱ ፡ የፖለቲካ ፡ ጥንስስ ፡ አለበት ፡ የሚለው ፡ አሳብ ፡ ሲታይ ፡ ይህ ፡ እራሱ ፡ ሌላ ፡ እራሱን ፡ የቻለ ፡ የግል ፡ አጀንዳ ፡ እንጂ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አጀንዳ ፡ አይደለም ፡፡
ቤተ ፡ ክርስቲያንን ፡ በፖለቲካ ፡ የመፈረጅ ፡ አባዜ ፡ የመጣው ፡ ከጥቂት ፡ አመታት ፡ በፊት ፡ ነው ፡፡ ከእኛ ፡ አሳብ ፡ ጋራ ፡ መስማማት ፡ የማይችል ፡ ሲኖዶስ ፡ የካድሬዎች ፡ ጥንስስ ፡ ውጤት ፡ ነው ፡ እያሉ ፡ ማማት ፡ በራሱ ፡ ሲኖዶሱን ፡ ሳይሆን ፡ እራስንም ፡ የሚያስጠረጥርበት ፡ ጥቆማ ፡ መሆኑን ፡ መረዳት ፡ አለባችሁ ፡፡ አሁን ፡ የአገር ፡ ቤቱን ፡ ሲኖዶስ ፡ አንቀበልም ፡ አምቀላቀልም ፡ ለማለት ፡ ምክኒያታችሁ ፡ እርግጥ ፡ መንፈሳዊ ፡ ነው ? ፡ ወይስ ፡ ፖለቲካዊ ፡ አጀንዳን ፡ ለማስፈጸም ፡ የግል ፡ ጥቅመኛ ፡ ጥንስሳችሁን ፡ የሚጋትላችሁ ፡ የልባችሁ ፡ ሰው ፡ ስለሚያሳጣችሁ ፡ ነው ? ፡፡
በእርግጠኝነት ፡ አንድን ፡ አሁጉረ ፡ ስብከት ፡ መሪ ፡ ሊቀ ፡ ጳጳስንም ፡ እንደ ፡ አንድ ፡ ተራ ፡ ግለስብ ፡ እንኳን ፡ ማየትና ፡ በተራ ፡ ነገር ፡ የግል ፡ ፍላጎታችሁን ፡ ስላላሟሉ ፡ የአባትነት ፡ ድርሻቸውን ፡ በመናቅና ፡ በአልባሌ ፡ የወረደ ፡ ቋንቋ ፡ ለመገሰጽ ፡ መነሳቱ ፡ እራሱ ፡ ይህ ፡ የውስጥ ፡ ፍላጎታችሁን ፡ እና ፡ የግል ፡ ጥቅማችሁን ፡ ስላመከነባችሁ ፡ አይመስላችሁምን ? ፡፡
እርግጥ ፡ ነው ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ነገር ፡ እየሰሩ ፡ የሚያጦዟትና ፡ ወደፊት ፡ እንዳትራመድ ፡ ከዓለም ፡ ኋላ ፡ እንድትከትል ፡ የሚያደርግ ፡ አስተሳሰባችሁ ፡ ለቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ዓለማቀፋዊነት ፡ ትልቅ ፡ የሆነ ፡ በሽታ ፡ ነው ፡፡ እንዲህ ፡ ደግሞ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ለግል ፡ ጉዳዩ ፡ ሲጠቀም ፡ ለኖረና ፡ ለፖለቲካዊ ፡ እሳቤ ፡ የሚዳርጋት ፡ የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ተቆርቋሪ ፡ የሚመስል ፡ ሰው ፡ ለቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ትልቅ ፡ ጉንፋን ፡ ነው ፡፡ ቤተ ፡ ክርሰቲያን ፡ ደግሞ ፡ እንዲህ ፡ እያደረገ ፡ የሚጎትታትን ፡ እያባባለች ፡ የምታስተኛ ፡ ሞግዚት ፡ ሳትሆን ፡ ጀግኖችን ፡ በየጊዜው ፡ የምትወልድ ፡ ድግቅ ፡ የጸጋ ፡ እናታችን ፡ ናት ፡፡ እናንት ፡ ዛሬ ፡ ደረስን ፡ ደረስን ፡ የሚሉ ፡ ወጠጤ ፡ የምትሉዋችውን ፡ ድንቅ ፡ የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ የጀርባ ፡ አጥንት ፡ የምትውልድ ፡ እንጂ ፡፡ እንደ ፡ እናንት ፡ ዘመናትን ፡ ጆርባዋ ፡ ላይ ፡ ታዝሎ ፡ ደሟን ፡ ሲመጥ ፡ የኖረን ፡ የጀርባን ፡ ቅማል ፡ አልወለደችም ፡፡ ይልቅስ ፡ እነዚህን ፡ የጀርባ ፡ ቅማሎች ፡ ለቃቅሞ ፡ የሚያወርዱላትን ፡ መልካም ፡ ወንዶችና ፡ ሴቶችን ፡ ወልዳለች ፡ እንጂ ፡፡ በአባቶች ፡ ፋንት ፡ የሚመሰክሩትን ፡ ልጆች ፡ ወልዳለች ፡ እንጂ ፡፡
ለማንኛው ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ልጅነታችሁን ፡ እልካደችም ፡ እናንተ ፡ ግን ፡ እናትነቷን ፡ ካዳችሁ ፡ እንጂ ፡፡ ልጅ ፡ ወደ ፡ እናቱ ፡ እና ፡ አባቱ ፡ እቅፍ ፡ እንዲናፍቅ ፡ ናፍቀን ፡ ወደ ፡ ቤታችን ፡ ተሰበሰብን ፡ እንጂ ፡ አልተበተንም ፡፡ ምንም ፡ ሊሆን ፡ ይችላል ፡ እኛ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አስቀድሞ ፡ የመሰረተውን ፡ ሲኖዶስ ፡ እንጂ ፡ የምናውቀው ፡ እናንት ፡ የፖለቲካ ፡ ሜዳ ፡ ያደረጋችሁትን ፡ እሳቤ ፡ አይደለም ፡፡ ለዚህም ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የራሱ ፡ ጅራፍ ፡ ስላለው ፡ እኛ ፡ ቤቱን ፡ ሲያጠራ ፡ እንደ ፡ እንጀራ ፡ ልጅ ፡ ከምንቀላውን ፡ ቤተኛ ፡ መሆናችን ፡ ዘላዓለማዊ ፡ ምርጫችን ፡ ነውና ፡ ወደ ፡ ቤቱ ፡ ገብተን ፡ እንኖራለን ፡፡
biniyam lakew (lij bini)
እውነት ብለሀል ካልሽ ግንን ምን አመጣው።እኛ የምናወራው ስለራሳችን ነው።ስለሌላ ቤተመቅደስ ከማውራታችን በፊት የራሳችንን አስተካክለን ለሌላው አርኧያ እንሁን።እያንዳንዳችንን የምንጠየቀው ምን ሰራቹ እንጂ ሌሎቹ ምን ሰሩ ተባለና አንጠየቅምና እናስብ።
የጠላታችን ቢሆንም ጊዜው
ኃይሉ ቢፀናውም ቢያስፈራም ግራማው
ዛሬም እኛው ነን የምናሸንፈው
ነገም እኛው ነን ምናሸንፈው
የአንበሳው ግሳት ቢሰማ ሞገዱ
የተጣልንበት ቢጠልቅም ጉድጓዱ
መላዕኩን ሲልክ ይረግፋል ጠላት
እንቆማለን በአሸናፊነት
አዝ…..
ቀስት አንገትርም አንይዝም ወንጭፍ
ጦር አንጨብጥም አንመዝም ሰይፍ
ሰልፉ የሱ ነው የታላቁ ጌታ
ግንቡን ለማፍረስ ይበቃል እልልታ
አዝ…..
ፈርኦን ሊያጠፋን ቢፋጠን በቁጣ
ሞት አድብቶብን መድረሻ ብናጣ
ውሃው ተከፍሎ እንደግንብ ይቆማል
ማንም አይሞትም ሁሉም ይሻገራል
አዝ…..
ሽንፈት አናውቅም የንጉስ ልጆች ነን
በደም ተገዝተን ወራሾች የሆነን
በስሙ ብርታት በመስቀሉ ጉልበት
ይፈራርሳል የጠላት ሰገነት
አዝ…..
የወደቀ ነው ከጥንት የተጣለ
ክብሩን ተነጥቆ ባዶውን የቀረ
በእንስራ እንዳለች የውሃ ጠብታ
የአህዛብ ጉልበት ብናኝ ነው ለጌታ
አዝ…….
እንዘምራለን!!!እውነት ብለሻል።እግዛብሄርን አለማውያን ፖለቲከኞች ሊረቱት አይቻላቸውም!!!
ጀብን ፡ መውጋት ፡ አህያን ፡ ተጠግቶ ፡ ነው ፡፡
የብጹ ፡ አቡነ ፡ ፋኑኤልን ፡ መልዕክት ፡ በአንክሮ ፡ ሙሉ ፡ ለሙሉ ፡ ተከታተልኩትኛና ፡ የአንተንም ፡ የወቀሳ ፡ እና ፡ የጥላቻ ፡ ጦማር ፡ ሳነብ ፡ በትክክል ፡ አንድ ፡ የአገራዊ ፡ ቢሂል ፡ አስታወስከኝ ፡ ፡ ወጣት ፡ ወይም ፡ አቶ ፡ ቴዎድሮስ ፡ ምን ፡ መሰለህ ፡ ቢሂሉ ፡ ከላይ ፡ እንደ ፡ ርዕስነት ፡ ብጠቀመውም ፡ አሁንም ፡ እደግመዋለው ‹‹ ጀብን ፡ መውጋት ፡ አህያን ፡ ተጠግቶ ፡ ነው፡፡ ›› ይላል ፡፡
ምሳሌው ፡ በጊዜው ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ የሚፈልገውን ፡ ለማግኘት ፡ በማይፈልገው ፡ እና ፡ በማያምንበት ፡ ነገር ፡ ጥገኛ ፡ በመሆን ፡ የልቡናውን ፡ መሻት ፡ የሚያሳበት ፡ ሂደት ፡ ነው ፡፡ ምናልባት ፡ ይህ ፡ አባባል ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ምን ፡ ያገናኘዋል ፡ ያልከኝ ፡ እንደሆነ ፡ አሳምሮ ፡ የሚያገናኝበትን ፡ ነጥቦች ፡ ላስጨብጥህ ፡፡
መጀመሪያ ፡ በአንተ ፡ ጽሁፍ ፡ የአጉረ ፡ ስብከቱ ፡ ሊቀ ፡ ጳጳስን ፡ እንዳሻ ፡ እየጠራህ ፡ የምጸት ፡ በሚመስል ፡ ቅንፍ ፡ ውስጥ ፡ የክብር ፡ ስማቸውን ፡ ከትችት ፡ ለመጽዳት ፡ በሚመስል ፡ ጥሪ ፡ ትጠራለህ ፡፡ ሲቀጥል ፡ ጳጳሱ ፡ ሳይከሰሱ ፡ ተከሰሱ ፡ ማለትህ ፡ የፍርድም ፡ ውሳኔ ፡ የሚጠብቃቸው ፡ አስመስለህ ፡ የጻፍከው ፡ ጹሁፍ ፡ የውስጥህን ፡ ፍላጎት ፡ ያሳያል ፡፡ በእርግጠኝነት ፡ ለቤተ ፡ ክርስቲያኒቷ ፡ ሰላም ፡ በመጨነቅ ፡ ሳይሆን ፡ የግል ፡ ጉዳይ ፡ እስኪመስልብህ ፡ ድረስ ፡ የወረደ ፡ ውንጀላ ፡ ማቅረብህ ፡ ነው ፡፡
ሌላው ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያኒቷ ፡ በ1995 ዓ.ም ፡ በፖለቲካ ፡ ስደተኞች ፡ የተቋቋመች ፡ መሆኗን ፡ መስክረሀል ፡፡ ከዚያም ፡ መተዳደሪያ ፡ ደንብም ፡ እንዳወጣችሁ ፡ አስቀምጠሀል ፡፡ ይህም ፡ መተዳደሪያ ፡ ደንብ ፡ ምቹ ፡ ጊዜ ፡ እስኪመጣ ፡ እና ፡ አባላቱ ፡ አምነውበት ፡ ወደ ፡ አንዱ ፡ ሲኖዶስ ፡ እስኪጠቃለሉ ፡ እንዲያገለግል ፡ ተደርጎ ፡ እንደተቀረጸም ፡ መስክረሀል ፡፡ በዚህም ፡ ምክኒያት ፡ ከሁቱም ፡ ሲኖዶስ ፡ ገለልተኛ ፡ በመሆን ፡ ቤተ ክርስቲያን ፡ አቋቁማችኋል ፡፡ ግን ፡ ከሁለቱም ፡ አባቶች ፡ ቡራኬን ፡ እና ፡ ትምህርትን ፡ ስትቀበሉ ፡ ቆይታችኋል ፡፡ ይህም ፡ ይበል ፡ ነው ፡፡ ሕገ ፡ ደንቡ ፡ የተቀረጸበት ፡ ወና ፡ አላማ ፡ ግን ፡ መንፈሳዊ ፡ አገልግለትን ፡ ለማከናወን ፡ እስከማይመስል ፡ ድረስ ፡ የጻፍከው ፡ ጦማር ፡ ከኋላ ፡ ሌላ ፡ አጀንዳ ፡ ያለበት ፡ ያስመስላል ፡፡
ምክኒያቱም ፡ የካድሬ ፡ ቢሮ ፡ እንዳይሆን ፡ ጊዜውን ፡ በሚመራው ፡ የመንግስት ፡ ወይም ፡ ኤህዲግ ፡ የሚመራው ፡ የአዲስ ፡ አበባው ፡ ሲኖዶስ ፡ ብለህ ፡ መጻፍ ፡ በራሱ ፡ ሌላ ፡ ዓላማ ፡ ያለው ፡ አይመስልህም ፡፡ እስቲ ፡ አስተውል ፡ ከአንዲት ፡ አገር ፡ አንድን ፡ ከተማ ፡ ነጥለህ ፡ በመጥራት ፡ የአንዲት ፡ አገር ፡ ከተሞች ፡ ሁሉ ፡ የራሳቸው ፡ ሲኖዶስ ፡ ያላቸው ፡ እስኪመስል ፡ ድረስ ፡ መቅረቡ ፡ በራሱ ፡ የሆነ ፡ የተሳሳተ ፡ ዓላማ ፡ እንዳህ ፡ ያጋልጣል ፡፡
ቅዱስ ፡ ሲኖዶሱ ፡ ውስጥ ፡ የትኛውም ፡ የፖለቲካ ፡ ድርጅት ፡ እጁን ፡ ሊያስገባና ፡ ፈላጭ ፡ ቆራጭ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል ፡፡ ግን ፡ አንድ፡ ነገር ፡ አስታውስ ፡ ክርስቶስን ፡ ሲከተሉ ፡ ከነበሩት ፡ ሐዋሪያት ፡ ውስጥ ፡ አበይት ፡ ሁለት ፡ ነጥቦችን ፡ ላሳይህ ፡ ወይም ፡ እንይ ፡ አንዱ ፡ ይሁዳ ፡ ነው ፡፡ ይሁዳ ፡ ታማኝ ፡ ማለት ፡ መሆኑ ፡ አይጠፋህም ፡ ዛሬ ፡ በረባውም ፡ ባረባውም ፡ ነገር ፡ የምናነሳው ፡ በተለይም ፡ አብሮ ፡ እየኖረ ፡ አሳልፎ ፡ የሚሰጥን ፡ ወዳጅ ፡ ስናይ ፡ ይሁዳ ፡ ትልቅ ፡ ምሳሌያችን ፡ ነው ፡፡ ሌላኛው ፡ ደግሞ ፡ ጴጥሮስ ፡ ነው ፡ ጴጥሮስ ፡ ማለት ፡ አለት ፡ ማለት ፡ ነው ፡፡ ጴጥሮስንም ፡ የምናስታውሰው ፡ በክህደቱ ፡ ነው ፡፡
አስቀድሞ ፡ እስከሞት ፡ ለመታመን ፡ የተናገረ ፡ ኋላ ፡ ግን ፡ ያፈገፈገና ፡ ሶስት ፡ ጊዜ ፡ አላውቅም ፡ ብሎ ፡ የካደ ፡ ነው ፡፡ ልዩነቱ ፡ አንዱ ፡ እራሱን ፡ ሲሰቅል ፡ ሌላኛው ፡ በንስሐ ፡ ተመልሶ ፡ ለሁሉ ፡ ነገር ፡ መሰረት ፡ ሆነ ፡፡ እንግዲህ ፡ ሲኖዶስ ፡ ውስጥም ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ያለው ፡፡ አላማህ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ የሚሰራባትን ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ መጠበቅ ፡ ከሆን ፡ ይህን ፡ አምነህ ፡ ተቀበልህ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ጊዜ ፡ በጾምና ፡ በጾሎት ፡ ትጠብቃለህ ፡ እንጂ ፡ እንደተበደለ ፡ እንደተገፋ ፡ ሰው ፡ ለመሆን ፡ ባትሞክር ፡ መልካም ፡ ነው ፡፡
ሲኖዶስን ፡ ማንም ፡ ሊመራው ፡ ይችላል ፡ ግን ፡ ግን ፡ የእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ከሁሉ ፡ የላቀች ፡ ናትና ፡ መጨራሻውን ፡ ለማየት ፡ መናፈቅ ፡ ነበረብህ ፡ ወደ ፡ እናት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ በመጠጋት ፡፡
ስለዚህ ፡ ወዳጄ ፡ ይህቺ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ የስንቶቻችሁን ፡ የግል ፡ የስጋ ፡ ፍላጎት ፡ አጀንዳ ፡ ስታስፈጸም ፡ እንድትኖር ፡ ነው ፡ ፍላጎታችሁ? ጅብ ፡ የሆነ ፡ ኑሮዋችሁን ፡ ለማስታገስ ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያንን ፡ ተጠግታችሁ ፡ ስትደላደሉ ፡ ኖራችሁ ፡፡ እውነት ፡ በሌለበት ፡ ፈርሀ ፡ እግዚአብሔር ፡ ባለነገሰበት ፡ ስነ-ምግባራችሁ ፡፡ ጅብ ፡ የሆነውን ፡ የፖለቲካ ፡ አጀንዳችሁን ፡ ለማራመድ ፡ አሁንም ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያንን ፡ የሙጥኝ ፡ ማለቱ ፡ ትርጉም ፡ የለውም ፡ የተኛው ፡ ሲነቃ ፡ ገለባውን ፡ የሚለይበትን ፡ መበተኛ ፡ መንሹን ፡ ሲያነሳ ፡ ገለባው ፡ ለእሳት ፡ ስንዴው ፡ ለበረከት ፡ ነውና ፡ እወቅበት ፡፡ ከፖለቲካ ፡ ገለባው ፡ ወይስ ፡ ከመልካሙ ፡ ዘር ፡ ስንዴ ፡ ነህ ? ፡፡
የግል ፡ አጀንዳችሁንና ፡ ፖለቲካችሁን ፡ እዛው ፡ በጸበላችሁ ፡፡ እኛ ፡ የተመለስነው ፡ ወደ ፡ እናት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ወደ ፡ ተሰደድንላት ፡ መሰረታችን ፡ እንጂ ፡ የአስተዳደር ፡ ስርዓት ፡ ናፍቆን ፡ ጊዜ ፡ ሆዱ ፡ ሆነን ፡ አይደለም ፡፡ ይገርማል ፡ የሄድነው ፡ እኮ ፡ ወደ ፡ እናታችን ፡ ቤት ፡ እኮ ፡ ነው ፡፡ እረኛው ፡ ሲመጣ ፡ እንዳያጣን ፡ በስፍራው ፡ ሆነን ፡ ለመጠበቅ ፡ ትህዛዙን ፡ ላለማፍረስ ፡ ‹‹ ኃይልን ፡ እስክትለብሱ ፡ በኢየሩሳሌም ፡ ቆዩ ፡ ›› እንዳለ ፡ እስካሁን ፡ ከቤቱ ፡ እርቀን ፡ ነበር ፡ አሁን ፡ ግን ፡ ወደቤታችን ፡ ገብተናል ፡ እንጂ ፡ እናንተ ፡ እንደምትሉትስ ፡ አይደለም ፡ አይሆንም ፡ ቢሆን ፡ እንኳን ፡ እናት ፡ የሌለው ፡ ልጅ ፡ ከመባል ፡ አይብስምና ፡ ወደ ፡ እናት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያናችን ፡ ተመልሰናል ፡፡
አንተና ፡ መሰሎችህ ፡ ግን ፡ የግል ጉዳያችሁን ፡ ለማሳካት ፡ ፖቲካችሁንም ፡ ለመንዛት ፡ ወደየትኛውም ፡ ሲኖዶስ ፡ አትሂዱ ፡፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ካላችሁ ፡ ግን ፡ ለነፍሳችሁ ፡ እረፍትን ፡ ፈልጋችሁ ፡ ብቻ ፡ ሂዱ ፡ እንጂ ፡፡ እግዚአብሔር ፡ ለሁላችንም ፡ ማስተዋልን ፡ ይስጠን ፡፡ አሜን !!!
አሁንም ያው ልጅ ቢኒ ነኝ። ይቅርታ አበዛሁት አይደል?
በእውንተ: በጣ:ነው:ይዘንክብህ:ወንድም:ቴድሮስ:ለምን:ግን???ይህ:ሁል :ነግር። ቤተክርስቲያን :እኩ:እየሱሰ:ክርስቶሱ:በደሙ: የመስረታት:ነው። ምንሞ:እናደፈለገ:ተነሶቱ:በረሱ:እስተሳስብ:ሊነዳት:እይችልም።ቤተክርስትይን: የእሪሳ :የሁነ:ስርህት: እላት:ምናም: ሊቮረው:የምይችለው:ውደዶንም;ጠላንም:ብድሙ:የፅፍው።እውንት:ስለ: ቤተክርስትይን:የምንቆረቆር:ከሁነ:ይህንናም: እምኖ: መቀበል: ተገቤ:ነው; እኛ:ሀፅይተኝ:&በደለኛ:ሳለን:እሱግን;ስለኛ:ሁሉን:ሆነ። ታድይ: ለምን:ይሆን:ፕለትካና:የእግዝብሔር: ቤት:መለየት:የቃታችሁ????ስለምን:ለልጅቻች: መጥፍ:እርይ:ትሁናላች:ልክ:እንደ:ይሁዳ:ስለምናሶ:ቤተክርስትይን:ዝም;ብልችሁ: ትመላለሳላችህ? እግዚአብሔር:እምላክ: ትግስቱ:የበዝነው።ስለምንስ:እባቶችን: ትሳደባላችህ? መቼስ:እግዝብርሔር:ያስቅመጣችውን: እንናት: ብተስድባችው:ምንም:እታመጡም:ለእነሱ:በእግዝብርሔር:ዘንድ:ታላቅ:ነው: መቼስ:ቄስ:መሆን:እይቻልም: ግን: ፕስተር: መሆን :እንጅ። ሊልው:ነገር:ስለ:መዝምራኖች:እግዝብርሔር: እምላክ:እብዝቱ:ይባርክችሁ: የቤተክርስቲያን;ናችን: የቆርት:ቅን:ልጅች;በረቱ። እኔም; ስለ: ቅደስት:ቤተክርስትይን:ይገባንኝል።