የ86 መንትዮች እናት በምጥ ትሰቃያለች– Girma Bekele

የ86 መንትዮች እናት በምጥ ትሰቃያለች– የአዋላጅ ሃኪሞች ‹‹ ቡድን ›› እየተጣራች ነው፤ በእናት የምትመሰለው አገራችን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በተለይም ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ከአንድ ምንጭ በሚቀዱ ህመሞች እየተሰቃየች በመፍትሄ ምጥ/መድሃኒት ፍለጋ/ ውስጥ ነች፡፡ እኛ ልጇቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ የለቅሶ ድንኳን እየቀያየርን ከሃዘን ቤት ወደ ሃዘን ቤት እየተመላለስን እያነባን ነን፡፡

ሁላችንም እንባችንን ለማድረቅ በየፊናችን ችግሩን ለመተንተንና ከደረስንበት ድምዳሜ በመነሳት ትክክልና ያዋጣል ባልነው መንገድ መፍትሄ ከመፈለግ አልቦዘንንም፤ ግን የተናጠል ጥረታችን ህመማችንን አልፈወሰም፣ ከዘላቂ መፍትሄ አላደረሰንም፡፡ ከመፍትሄው ያልደረስነው ችግራችን ቀላል፣ ጉዳታችን የሚረሳ በመሆኑ ሳይሆን በህመማችን ስረ-መሰረት መንስኤና ዘላቂና ቀጣይ መፍትሄ ላይ ባለመግባባታችንና በተናጠል የህመማችን ምልክት እያከምን ህመሙን በቅጡ ማስታገስ እንኳ ባለመቻላችን ነው ሥቃያችን ከለት ወደለት እየበረታ ያለው፡፡

በሽታው በየጊዜው ስሙንና መልኩን ፣ የመግቢያ ቀዳዳውንና ስልቱን እየቀያየረ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ፣ ካቀረብነው የተናጠል ጊዜያዊ የማስታገሻ መድሃኒት እየተላመደና እያላመደን ከዚህ ደርሰናል፡፡ ይህ የአናሳዎች ዘረኛ አምባገነናዊ ቡድን ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የጥፋት ሴራውን ያላሰራጨበት የኢትዮጵያ ምድርና የልማትና አስተዳደር ሴክተር ፣ በጥፋት በትሩ ያልተገረፈ የኢትዮጵያ ህዝብ/ የማኅበረሰብ ክፍል/ ፣ ያልደረሰብን ተፈጥሮኣዊና መንግስት ሰራሽ የችግር ዓይነት የለም፡፡ ከህጻናት እስከ አረጋዊያን፣ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከገበሬ እስከ ከብት አርቢው፣ ከመናጢ ድሃው እስከ ባለሃብቱ፣ ከማይም እስከ ምሁሩ ፣ ከባህላዊ እምነት እስከ ኃይማኖት ተቋማት፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ጫፍ … በየጊዜው እየረሳነው ካልሆነ ችግሩ ያልደረሰበት አይገኝም፣እንዲያውም ችግሩና ህመሙ ድንበራችን አቋርጦ እየተከተለን በውጪም ሥቃያችን አክፍቶታል፡፡

ትምህርት ዓላማውን ስቷል፣ ግብርናው የፖለቲካ መስክ ሆኗል፣…. የኢኮኖሚ እድገትና የአገር ልማት በቴለቪዥን መስኮት እንጂ ለኑሮኣችን ከጓዳችን አልደረሰም፤ በቴለቪዥንና ሬዲዮ ፕሮፖጋንዳ ቁንጣን በምንሰቃይበት፣ባለሁለት ዲጅት ዕድገት ባስመዘገብንበት ከአስር ሚሊዮን ዜጎች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ነው፡፡ ዛሬም በሞት ውስጥ ለማለፍ ስደቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ በኦጋዴን ፣በጋምቤላ ፣ በትግራይ ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ፣ በቤንሻንጉል፣ በአፋር፣ …. የዜጎች ደም ያልፈሰሰበትን የእናቶች እምባ ያልተረጨበትን ፈልጎ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ዛሬም በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወልቃይት -ጠገዴና ቅማንት፣ በኮንሶ…የጣር ድምጾች እየተደመጡ ነው፣ በጋምቤላ የደረሰው ለጆሮና ለማመን ይከብዳል፡፡ ግን መሆኑን ‹ደፋሮቹ› አረጋግጠውልናል ፡፡

ሥራ አጥነትና ስደት፣ ረሃብና ድርቅ፣ እስራትና አፈና የፍትህ እጦትና የክብር መደፈር፣ … አገራችን ቤታቸው ናት፡፡ በመሆኑም ተፈናቅለናል፣ አካላችን ጎድሏል፣ ሥነ- ልቡናችን ታውኳል፣ ተሰደን (ለአረመኔዎች ሠይፍና ጥይት፣ ለባህር አውሬና ለዱር አራዊት እራት ሆነናል፣አካላችን ተሸጧል፣በእሳት ተቃጥለናል፣… ) ፣ተገድለናል፣ ሙስሊም ክርስቲያኑ ቤተ እምነቱና ትምህርተ-ሃይማኖቱ ተደፍሯል ፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ክብራችን ተዋርዷል፣ ድንበራችንና ሉዓላዊነታችን ተደፍሯል፡፡ የዛሬው የጋምቤላው ግን ከመቼውም የከፋ ነው፡፡ የእስከዛሬው ጥይት በእኛው ከእኛው ፣ ወይም ለስደት በምንጓዝበት መንገድ ወይም በተሰደድንበት ከአገራችን ውጪ ነበር ፡፡

ዛሬ ግን ‹‹ባለቤት የናቀውን …፣ ወይም ባለቤቱን ካልናቁ ….›› እንዲሉ ድንበራችን ዘልቀው እስከቤታችን ገብተው ጨፈጨፉን፡፡ ከመድረሱ በፊት የሚከላከለን ፣ ከደረሰ በኋላ የሚበቀልልን ያለመኖሩን የተመለከቱ ከመንደር መንደር እየተዘዋወሩ ከ200 በላይ ወገኖቻችንን ጨፈጨፉ፣ በመቶ የሚቆጠሩትን ጠልፈው ለባርነት ወሰዱ፡፡ ልብ እናድርግ — ይህ በቤታችን በቀዬኣችን ባለንበት መጥተው ያደረጉት ነው፡፡ ከዚህ በላይ እንደ አገርና ዜጋ መዋረድ ከቶ ከወዴት አለ፣ በታሪካችን መቼ ተሞክሮብን ተሳክቶ ይሆን ? አዎን እስከዛሬ ችግሩ የእርስ-በርስ የውስጣችን ይመስል ነበር፣ እስከዛሬ ‹‹ ይጨርሱናል፣ ያጫርሱናል ›› ስንል ነበር፡፡ ዛሬ ግን ደረጃው አድጎ ከመጨረስና ማጨራረስ አልፎ ወደ ‹‹ ማስጨረስ ›› ተሸጋግሯል፡፡ ታዛቢና ጠባቂ እንደሌለን ብቻ ሳይሆን በሞታችንም የሚቆጭ እንደሌለን በተጨባጭ አረጋግጠናል፤ አሁን ጥያቄው ከዚህ በኋላ ምን እስከምንሆንና እስኪያደርጉን ሳይሆን እስኪያስደርጉብን እንጠብቅ ? እስከመቼ በተናጠል በየራሳችን መንገድና ዘዴ (ባህላዊ ሥራ- ሥር ይሁን፣ ዘመናዊ መድሃኒት በሉት የቀዶ ጥገና ህክምና ) የበሽታውን ምልክት እያከምን ፣ በሽታው የበለጠ ስር እንዲሰድና ከማይታከምበትና እናታችንን ከሚገድልበት (የሠይጣን ጆሮ አይስማው) ደረጃ እንዲደርስ እንፍቀድለት? ነው፡፡ የመፍትሄው ጥያቄ እንግዲያውስ ከእስከዛሬው ተምረን ምን ማድርግ እንችላለን ፣ ለዚህስ ምን እርሾ አለን፣ ምንስ ተስፋ ቋጥረን/ሰንቀን እንነሳ ? ነው፡፡

አዎን // ከላይ እናታችን የአዋላጅ ሃኪሞች ‹‹ቡድን›› እየተጣራች ነው ብለናል፡፡ አዎን// እነዚህ አዋላጅ ሃኪሞች የየራሳቸው ዕውቀት፣ ክህሎት፣ ችሎታና አቅም ይዘው በየግላቸው የየራሳችን ላሉት ‹በሽታ› መድሃኒት ያሉትን ሲያቀርቡ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ግን የየራሳችን ያሉት በሽታ — በሽታ ሳይሆን ምልክት መሆኑን የተረዱበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል፤ በሽታው የሁሉምና የጋራ አንድ ዓይነት መሆኑን፣ ለብቻቸው በሽታውን ከስር-መሰረቱ በዘላቂነት ነቅሎ የሚያወጣ መድሃኒት እንደሌለ ተምረዋል፡፡ በመሆኑም በእያንዳንዳቸው ያለውን የየግል ዕውቀት፣ ክህሎት፣ ችሎታና አቅም በአንድ ዓላማ ሥር ለጋራ ግብ አሰባስበው /አቀናጅተው የሁሉንም የጋራ በሽታ ከሥሩ የሚነቅሉበትንና በውጤቱም ሁሉም የሚጠቀሙበት የጋራ ተግባር የሚፈጽም ስብስብ መፍጠር ላይ መግባባት እየተደረሰ እንደሆነ ጠቋሚዎች አሉ፡፡

የቪዥን/ራዕይ ኢትዮጵያ እና ኢሳት ያሳዩን መልካም ጅምር ፣ በጽንፈኛ ፖለቲካዊ አመለካከትና ተግባራት መካከል የተደነቀረው የልዩነት ግንብ እየተናደ መምጣቱን የሚያመለክቱ እርምጃዎችና በዲሞክራሲ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በጋራ ለመስራት ከተደረጉ ጥረቶች የተገኘው ተሞክሮና ዛሬም ስላለው ፍላጎት የምንሰማቸው ተስፋን የሚያጭሩ ፣ የቀጣይ ትግላችን ስንቅ ናቸው፡፡ አዎን ይህ የብዙዎች መንታ እናት አገራችን በአንድ ላይ ካላዳንናት ያለእናት( በእናት አልባ) የምንቀረው ሁላችን ነን፡፡ ግማሽ፣ ሲሶ ፣ ሩብ … እናት ለማናችንም አትተርፍም፣ ብሎ ነገር የለም፣አይኖርም፡፡ ስለዚህ ዘላቂ ስር-ነቀል መፍትሄው የአዋላጅ ሃኪሞቹ ‹ቡድን › ‹‹ ይህ በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲና በመሳሪያና ደህንነት አፈና የሚያሰቃየን ፣ ግን ከውጪ ጠላት እንኳ የማይጠብቀን የአናሳዎች ዘረኛ አምባገነን ስርዓት መቀየር አለበት፤ ለዚህም በብሄራዊ መግባባት ዕርቅ አውርደን በአካታችና አሳታፊ የሽግግር መንግስት አልፈን አዲስቱን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት በኅብረት መቆም ›› በሚል የጋራ እምነት የተጀመሩትን ጥረቶች አጠናክረን መቀጠል አለብን፡፡ ከዚህ ውጪ አካታች ሰላማዊ የሥርዓት ለውጥ (የሥልጣን ሽግግር አላልኩም) ፣ዘላቂ ሰላምና ልማት ፣ ፍትህና የህግ የበላይነት፣ ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ፣እኩልነትና አብሮነት…. መሪዎቻችን በክብር የምንጦርበትና የምንቀብርበት ሁኔታ የሚቻል አይደለም፡፡ ከዚህ ውጪ በተለመደው አግላይና ጠቅላይ ፖለቲካ የሥልጣን ሽግግር ይቻላል፤ በዚህ ሁሉንም የዛሬ መሪዎች አንድም ወህኒ ፣ ሌላም በስደት አገር እናገኛቸዋለን፣ ይቀበራሉ፣ ወይም ተሳደው ለፍርድ ይቀርባሉ ፡፡

በሽግግር መንግስት ግን ሁሉም ሳይሆኑ ቀንደኛ ወንጀለኞች ብቻ የሚጠየቁበት ስርዓት ሊዘረጋ ወይም ሌሎች የዕርቅ የመፍትሄ አማራጮች ሊቀርቡና በአካታችና አሳታፊ ውይይት መግባባት ሊደረስባቸው ይችላል፡፡ ለዚህ ምርጫው ኳሷ/ እንዳለፉ ጊዜያት በኢህአዴግ እጅ/ሜዳ ብቻ ነው ብዬ አላስብም፤ አዋላጅ ሃኪሞቹ ተግባብተውና ተባብረው ‹ቡድን › ከመሰረቱ በጉዞ ላይ ያለቺውን ኳስ ወደ ሜዳቸው በቅርብ ያመጣሉ ፡፡ ዋናው ነገር –ከዚህ የከፋ ሊደርስብን የሚችል ጥፋት፣ አደጋና ውርደት አለ /የለም ፣ እያንዳንዳችን ለየራሳችን የተናጠል መፍትሄ አለን/የለንም ብሎ ለመከራከር፣ በታሪክ ለመነታረክ …. የምናባክነው ጊዜ የለም ፡፡ ዛሬውኑ ለ ‹‹ቡድኑ›› ምስረታና ለተግባራዊ እንቅስቃሴው መጀመር ሁላችንም እንደዜጋ ተደራጅተን፣ እንደድርጅት በተናጠልና በጋራ አሁኑኑ ወደ ተግባር ፡፡ ባለፈው እንዳልኩት አገራችን ለዚህ የሚበቁ ብቻ ሳይሆን ለሌላ የሚተርፉ ልጆች እናት ናትና ‹‹ ይቻላል ›› ብዬ መሳሳትን እመርጣለሁ፡፡ ለአገራችንና ለልጇቿ ደግ ደጉን ያሳስበን. ፣ ያሰራን፣ ያሰማን ፡፡ በቸር ያገናኘን ፡፡ 10/08/08. UNITE. ( በጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን መታሰቢያ)

7 Comments on “የ86 መንትዮች እናት በምጥ ትሰቃያለች– Girma Bekele”

  1. Le 41 amet, le afta
    sayaqom Telatachn yetgrai
    woyanie eñan eyegedele
    ena agerachn eyaTefat
    ygeñal.
    Lemedan bcheña mrcha
    alen.
    Esum: woyanien megdel
    new.
    Jegnoch, beyalenbet,
    beyegiziew wedaj meslen
    bemeqreb, lemanm
    sanasawq bedbq yetgrai
    woyanien engdel.
    woyaniewochn sngelachew
    yeterefut sisheshu weym
    siyalqu bcha neTanet ygeñal.
    Megdeya mesariyana
    sltoch:
    Tyit, bomb, slu mesariya
    (goradie, seyf, meTrebiya,
    bilawa, Tor, ankasie),
    bebox, qomeT, dngay, merz,
    maqaTel, maneq, mafen,
    wede gedel, gudguad
    megefter, kewha masmeT,
    bebeshta maslekef, etc new.
    Zm blen mawelawel lemaleq
    new.
    Saichersun qedmen megdel
    alebn.
    tgrie woyanien betegbar
    snwegaw bcha ydemesesal.

  2. 86 ? 100mil kemola koye eko !

    BALEBET ANIREGTIM GIN EYEBEZAN WEYANE EYEQENESEN NEW

    YEMEGERMEGN WEYANE BE HAYALU ERDATA EYAGEGNE FEJEN

    YAWIM YEMECHERESHA ANASA TIGRAY WEYANE !!!!

  3. ገና መቼ ቀጣይ የዕናት ምጥ በጎጥና በጠባቦች የተለከፈችው ሃገራችን መከራዋ እንድህ በዋዛ የሚለቃት አይመስልም ምክንያቱም ቀይ ሽር ተሸንፎ በተረኛው ነጭ ሽብር (ኢሕአፓ) ስልጣን ይዞ በተራው ኢትዮጵያን ለከፋ ችግር አጋልጠዋታል የኢትዮጵያን ልጆች ማጥፋትና የሃገሪቱን አንድነት፣ግዛት ማጥበብ ስራው ነው፡፡
    የአማራ ማንነት አደጋ ላይ መሆኑን እየታየ ነው
    እሱ ነው

  4. ወገን ሲገደል አይደለም በደል ሲደርስበት ያስቆጫል!ያናድዳል!
    እውነት ይህ የሰው ዘር ማጥፋት የፈጸሙት እነማንናቸው? ትክክለኛው መረጃ ለሕዝብ ይቀርባል የሚል እምነት የለኝም ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉ ነገር ሰለሚደበቅ ጥቃቱ ከውስጥ፣ከውጭ፣ከቤት ከሩቅ ወይስ ሌላ አለማ ያለው ነው?
    እ.ው

  5. ርሃብ ምንድር ነው? ማን አመጣው እንደትስ ተፈጠረ መቼስ ነው የሚጠፋው/የምናጠፋው? ኢትዮጵያ ከድረቅና በረሃብ ነጻ የምናወጣት ? ድርቅም ሆነ ርሃብ ከሰው የተሰጠ ስጦታ ነው ስጦታ የሚሰጠው መልካም ነገር፣በጎ ነገር ጠቃሚ ለወግን ለሃገር ነበር ግን አመታደል ሆኖ ዛሬ በጎጥና በጠባብ በሰዎች ትናንሽ አስተሳሰብ አሰማርታ ተሰማረተው የዩኤስኤይዲ/USAID / የአለማችን ሰጣኖች እንጅ ገብታ የምግብ እጥረት የቁማር ጨዋታዎች በኢትዮጵያዊያን ላይ መቀለድና መነገድ ማለት ነው፡፡ ለድርቁ ተጣያቂው፣ለርሀቡ ተጠያቂው ማን ነው?የዩኤስኤይዲ/USAID /፣የአውሮፓ ሕብረት ለጋሽ ድርጅቶች በሰው ሕይወት ኪሳቸውን ያደልባሉ፣በሃገሪቱ እንደፈለጉ ለትውልድ ሃሽሽ፣ በሽታ የተመረዘ ምግብ መድሃኒት በማከፋፈል ትውልድን እያጠፋ ናቸው
    ማን አለሁ ይበል ለኢትዮጵያ ከዳተኛው ብዛቱ በወገኑ ችግር የሚደሰት ሰንት ናቸው? ተው ነቃ በል ትውለድ ተው ሃገርን አትክዳ፣አታስቆርስ ለምለም ሃገር እያለን ለምንድር ነው የምንራበው ለጠላትእጅ የሚሰጥ ትውልድ አይፈጠር!
    እ.ው

  6. ፕሬዚዳንት ኦባማ የ50 ዓመት የኩባንእና አሜሪካ ግንኙነት በሌላ ዘዴ ተጠቅመው ለአሜሪካ ጥቅም የሚበጅን ግነኙነት በአዲስ መልክ ቀየሡ እሠየዉ የሚያሱኝ ነው።ወደሐገራችን ስንመጣ ግን በተቀዋሚዉ ጎራ 25+27፡42 ዓመታት ሲነገሩ ሲፃፉ
    ሲደሰኮሩ የነበሩት አሁንም ያሉት ነገሮች በጥልቀት ሳያቸው ሐሜት፣እርግማን፣ፉከራ እና ዛቻ ናቸው ።ለ42 ዓመታት ከአገር መሪ እስከ ምሑራን፣ከጦር ጄኔራል አስከ ተራዉ ወታደር እንዲሁም ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በሚያሠኝ ኢሐአዴግን በጦርሜ ፈትነዉታል፣በስብሰባና በሠላማዊ ሰልፍ ኮንነውታል፣እረግመዉታል፣አምተዉታል አልፎ አልፎም ለተለያዩ መንግሥታት አቃጥረዉበታል ከፍ ሲልም ከተለያዩ መንግስታት ጋር በማበር አሢረዉበታል።ይሕ ሁሉ ሆኖ ኢሐአዴግ መንግሥት መስርቶ ከተቀመጠ 25 ዓመት ሆነው።በተዋረድ ያለው አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ከጠላዉ ለምን 25 ዓመት ተቀመጠ????ብዙ ምክንያቶች ሢዘረዘሩ እስካሁን ደርሰናል በተለይ የተወሰኑት ተደጋግሞ ይደመጣሉ ኢሐአዴግን መወነጃጀል ለሕብረታችን መፍረስ፣ሠላማዊ ትግሉ አለማደግ፣በተቀዋሚዉ መንደር ኢሐዴግ ሠላይ በማስገባት ድርጅቶችን ማፍረስ እርስ በእርስ መወነጃጀል ይገኙበታል።በእኔ እምነት ይሕ ሁሉ ዝባዝንኬ ነው።ኢሐዴግን ከስልጣን በጦርነት ለማስወገድ የሚታገሉ አሉ ሰላማዊ ተቀዋሚዎች ግን አንድም የለም።ሠላማዊ ተቃዋሚ ማለት ፩_ የሐገሪቱ ሕገመንግሥትን ያሠራኛል ብሎ በሙሉ ልብ የተቀበለ በዚህም መሠረት ገዢውን ፓርቲ ስንጠራዉ ኢሐአዴግ ብለን እንጂ ሕዉሐት/ኢሐአዴግ እያሉ መቀላቀል አያስፈልግም ፪_ለመራብ፣ለመጠማት፣ለመደብደብ፣በእስር ለመንገላታት፣ስራን ለማጣት፣ለመሞት እንዲሁም ይሕን ሁሉ ግፍ ለሚፈፅሙብን ወገኖች ምሕረት ለማድረግ የተዘጋጀ አካል መሆን አለበት።ለዚሕም ከ4 መአዘን የሚነሣብንን ማእበል ሕዝቡ በታላቅ ትእግስት እና ጨዋነት እንዲወጣዉ ያለመሠልቸት ማስተማር በዚህ ማዕበል ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል እንዲሣተፉ ማድረግ።ከመሐከላችን ዉስጥ ኢሐአዴግ ጨካኝ እርምጃ ቢወስድም አለመበርገግ ሠላዮቹ መሐላችን እንደሚኖሩ ማመን ስለዚህ ጥያቄው አንድ ብቻ መሆን አለበት እሡም ስልጣን ለሕዝብ ስጥ።ሚስጥር የሚባል መኖር የለበትም።ብሔረሠብ ለብሔረሰብ እንዲጋጩ ስራን አለመስራት።ለምጣዱ ሲባል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*