“አቶ መለስ በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው” ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው

በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ የአገሪቱን ፖሊሲ አውጭዎችና ህግ አስፈጻሚዎችን በድፍረት ከመተቸትም ሆነ መልካም ጎኖችን ከማበረታታት ታቅበው ይታያሉ። ቁጥራቸው በዛ ያሉ አይሁን እንጂ በገዥው ፓርቲ ጉያም ሆነ በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ምሁራንም ምሁራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲንቀሳቀሱ እናያለን። ከተቃውሞውም ሆነ ከገዥው ጉያ ውጭ ሆነው ወቅታዊ ጉዳዮችን በአንክሮ እየተከታተሉ ሀሳባቸውን ለመገናኛ ብዙሃን የሚሰጡ ምሁራን ደግሞ ቁጥራቸው እጅግ በጣም አነስተኛ ይሁን እንጂ አልጠፉም። ሀሳባቸውን በነጻነት ከሚሰጡ ምሁራን መካከል የፍልስፍና ምሁሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ እና የስነ ምድር ምሁሩ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ይገኙበታል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ደግሞ በቀድሞው መንግስት ተቋቁሞ በነበረው የብሔረሰቦች ጥናት ኢንስቲትዩት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩትና በቅርቡ የኢንስቲትዩቱን የጥናት ውጤት በመጽሃፍ መልክ አዘጋጅተው ለንባብ ያበቁት የስነሰብ ምሁሩ ዶክተር ፍሰሃ አስፋው ሀሳባቸውን በነጻነት ከሚሰጡ ምሁራን ጎራ ተቀላቅለዋል።

ለአምስት ዓመታት በአሜሪካን አገር አንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አስተማሪ ሆነው ያገለገሉትና ተባባሪ ፕሮፌሰር ሆነው ወደ አገራቸው የተመለሱት ዶክተር ፍሰሃ አስፋው በወቅታዊ ጉዳዮች እና በተለያዩ መሰረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል። ከተወያየንባቸው ፍሬነገሮች መካከል የኢትዮጵያን ወደብ አልባነት ፖለቲካዊ አንድምታዎች፣ የብሔረሰቦችን የማካለል ጽንሰሃሳቦች፣ ወቅታዊ የማንነት ጥያቄዎች ላይ ያላቸውን አረዳድ፣ ሶማሌ ጅቡቲና አፋር ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ስትራቴጂክ ግቦች እንዴት እንደሚቃኟቸው ተናግረዋል፡፡ ቃለምልልሱን ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አቅርበነዋል፡፡

ሰንደቅ:- የወቅቱን የአገሪቱን የፖለቲካ እንቅስቃሴ እና የአገሪቱን ሁኔታ እንዴት ያዩታል? 

ዶክተር:- ፍሰሃ ይህንን ጥያቄ የምመልስልህ ከፖለቲከኞች ወገን ሆኜ ሳይሆን ከፖለቲካ ምሁራን ወገን ሆኜ ነው። የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ትንሽ አስደንጋጭ ሆኖ ነው የሚታየኝ። አስደንጋጭ ነው የምልህ በየአካባቢው ግርግር ስለተፈጠረ ሳይሆን ግርግሩ የተፈጠረው በወጣቶች በመሆኑ ነው። እነዚህ ወጣቶች ደግሞ ዝም ብለው ከመንገድ ላይ የተሰባሰቡ ሳይሆን በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ናቸው። ከልምዴ ተነስቼ የምነግርህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው በወጣቶች እንቅስቃሴ ነው። ዘውዱን አስወግዶ ደርጉን ያመጣውም ሆነ ደርጉን አስወግዶ ኢህአዴግን ያመጣው የወጣቶች እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ የወጣቱ እንቅስቃሴ መንግስት በሚሰጠው መልስ ሳይሆን በሰከነ መልክ በረጋ አመለካከት ሃቀኛ በሆነና ከልብ በመነጨ ውይይት ችግሩ ምን እንደሆነ አውቆ እና ተረድቶ መፍትሔ ካልተፈለገለት በስተቀር እያደር አንድ ደረጃ ላይ ይደርስና ውጤቱ የከፋ ይሆናል።

ስለዚህ መንግስት ከራሱ ጋር ሳይሆን ከሁሉም ጋር ውይይት አድርጎ ወደ መፍትሔው መሄድ አለበት ብዬ ነው የማምነው። ይህ ካልሆነ ግን የወደፊቱ ፖለቲካ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል ግልጽ ነው። ምክንያቱም ዛሬ የተቀየሰውም ሆነ እንቅስቃሴ የተጀመረው በብሔረሰብ ነው። ይህ የብሔረሰብ ግጭት ውሎ አድሮ ከመንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ብሔረሰብን ከብሔረሰብ ጋር ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋል። ያን ጊዜ ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ወደቀች ማለት ነው።

ኢትዮጵያ ስንል ብዙ ብሔረሰቦች ተሰባስበው ዳር ድንበሯን አስጠብቀው ያኖሯርት አንዲት አገር ነች። እነዚያ ብሔረሰቦች እርስ በእርሳቸው ግጭት ከፈጠሩ ኢትዮጵያ የምትላት አገር ላትኖር ትችላለች። በበጎ መንፈስ ውይይት ከተደረገበት እና እርስ በእርስ ምክክር ከተካሄደበት በወጣቱ የተነሳውን ንቅናቄ ወደ ፊት ለኢትዮጵያ እድገት እና ልማት እንዲውል በማድረግ አገራችንን ወደ ቀድሞ ገናናነት ይመልሳታል ብዬ በእርግጠኝነት እነግርሃለሁ።

ሰንደቅ:- የወጣቶች ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውጤቱ ገዥዎችን በሌላ ገዥ ሲተካ እንጂ መሰረታዊ የስርዓት ለውጥ በማምጣት አገሪቱን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲያሸጋግራት አልታየም። አሁን የተነሳው የወጣቶች እንቅስቃሴስ እንዳለፉት ዘመናት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ አገሪቱን ዋጋ እንደማያስከፍላት በምን እርግጠኛ መሆን ይቻላል?

ዶክተር:- ፍሰሃ ያነሳኸው ትክክል ነው። ነገር ግን የ1960ዎቹ የነበረው የወጣቶች እንቅስቃሴ በንድፈ ሀሳብ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነበር። ማኦ እንዲህ ብሏል፣ ሌኒን እንዲህ ብሏል እና ማርክስ እንዲህ ብሏል በማለት ነበር የሚንቀሳቀሰው። ሌላው ቀርቶ ብሔረሰብ የሚለውን ቋንቋ እንኳ ከስታሊን ወርሰን ያመጣነው ነው። ያን ጊዜ የነበረው የወጣቶች እንቅስቃሴ “ይህ መንግስት ወድቆ ለውጥ ይምጣ” የሚል እንጂ ቁጭ ብሎ ከመንግስት ለውጥ በኋላስ በሚለው ነጥብ ላይ ውይይት አልነበረም።

እኔ ከምከታተለው ተነስቼ ያሁኑን እንቅስቃሴ ካለፈው ዘመን ለየት የሚያደርገው ነጥብ ሆኖ ያገኘሁት “ለውጥ ይምጣ ብቻ ሳይሆን ለውጡ ከመጣ በኋላም በዚህ መስመር መሄድ አለበት” የሚል ነጥብ የተጨመረበት ነው። ስለዚህ “ወጣት ነው” ብለን ያለፈውን ስርዓት በማየት ብቻ ወጣቱ የሚያመጣው ለውጥ አገሪቱን ወደ አደጋ ይጥላታል የሚለውን ሃሳብ እኔ አልጋራውም። ለምን መሰለህ የማልጋራው? እነዚህ ወጣቶች የሚንቀሳቀሱት ብቻቸውን አይደለም። ምሁሩም ተቀላቅሎበታል። ስለዚህ የምሁሩንም ሀሳብ ይሰማሉ።

ለምሳሌ እኔ ያየሁትን አንድ ሃሳብ ልንገርህ። “ይህ መንግስት በህገ መንግስት የአስተዳደር መብትን ሰጥቷል። በተጨባጭ ሲታይ ግን መብታችን አልተከበረም” የሚል ነው አንዱ እንቅስቃሴ። ያ ማለት እንግዲህ ዝም ብሎ የተነሳ ወጣት ሳይሆን ስርዓትን የሚያውቅ መሆኑን ነው የሚያሳየው። ያለፈውን ዘመን ወጣት እንቅስቃሴ ካየህ ግን “ኢትዮጵያ ዘውዳዊ መንግስት አያስፈልጋትም ማርክሲዝም ሌኒንዝም መመሪያችን ነው” የሚል ነበር።

ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ወጣቶቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች አሉ። ለምሳሌ የቋንቋ ጥያቄ አለ የአስተዳደር ክልል ጥያቄ አለ የፍትህ ጥያቄም አለ። መሪዎቼን እኔ እንጂ ፓርቲ ሊመርጥልኝ አይገባም ብሎ የሚጠይቅ ወጣት አለ። ኢትዮጵያን የሚመራት ፕሬዚደንት ከሁሉም ብሔረሰብ ተወዳድሮ በማሸነፍ ሁሉንም ብሔረሰብ የሚወክልና የሚያምኑበት አንድ ፕሬዚዳንት መሆን አለበት የሚል ነው። ለዚህ እኮ ነው የሁለቱ ዘመን ወጣቶች እንቅስቃሴና ጥያቄ የተለያዬ ነው ያልኩህ።

ሰንደቅ:- እርሰዎ አባል በነበሩበት የብሔረሰቦች ጥናት ኢንስቲትዩት ውስጥ የብሔረሰቦች የአስተዳደር ግዛት አከላለልን ሰርታችኋል። በአሁኑ መንግስት በተሰራው የክልሎች አወቃቀር በርካቶች አገሪቱን እንዳትጠናከር የሚያደርግ “ከፋፋይ” የሆነ አወቃቀር ነው የሚሉ ቅሬታዎች አሉ። በዚያ ወቅት የነበረው የብሔረሰቦች የግዛት ወሰን ሲሰራ ምንን ታሳቢ አድርጎ ነበር?

ዶክተር ፍሰሃ:- የአስተዳደር ክልል ሲከለል ዓላማው የብሔረሰቦችን ችግር ለመፍታት ነው። የብሔረሰቦችን ችግር ለመፍታት ግን የተደረገው በብሔረሰብ ማካለል አይደለም ያደረግነው። እያንዳንዱ ህብረተሰብ ለልማት ያለው አመቺነት፣ ከአጎራባች ብሔረሰብ ጋር ያለው ግንኙነት፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡንና ቋንቋውን በማየት ነው የከለልነው። ለምሳሌ ኦሮሚያን ብቻ ብንወስድ በእኛ አከላለል ኦሮሚያን በሙሉ በአንድ የአስተዳደር ክልል ስር አልነበረም ያካለልነው። በአንድ አስተዳደር ስር ያልከለልነው ኦሮሚያን በአንድ የአስተዳደር ክልል ስር ብታካልለው በውስጡ ያለውን ሌላ ብሔረሰብ በሙሉ መደፍጠጥ ይሆናል። ስለዚህ ከላይ በጠቀስኳቸው የአከላለል መስፈርቶች መሰረት የሚከለልበትን መንገድ ነው የቀየስነው።

በዚህ መንግስት አከላለል ስትሄድ ግን አዲስ አበባን ብትወስድ ከተማዋ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ስትሆን በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል መንግስት ዋና ከተማም ነች። ኦሮሞው “ፊንፊኔ” ይለዋል የፌዴራል መንግስቱ ደግሞ “አዲስ አበባ” ይላል። በአንድ አገር ውስጥ በአንድ ከተማ ላይ እንዴት የተለያዬ ስም ሊኖር ይችላል? ለምሳሌ አንደ ሰው ስሙ “አበበ” ከሆነ በሌላ ሰፈር ሂዶ “አሰፋ” ነኝ ሊል አይችልም።

ሰንደቅ:- በእናንተ ጊዜ የተሰራው የብሔረሰቦች የግዛት ወሰን አከላለል ላይ ብንመለከት አንድን ቋንቋ የሚናገረውን ብሔረሰብ በተለያዬ የግዛት ስያሜ እንዲካለል አድርጋችኋል። ለምሳሌ ኦሮሚያን ብንወስድ በሰባት የግዛት አስተዳደር ክልል ነበር የከለላችሁት። ይህ ብሔረሰቦች እንዳይጠናከሩ አያደርጋቸውም ይላሉ?

ዶክተር ፍሰሃ፡- ዓላማው እኮ አንዱ ብሔረሰብ እንዲጠናከር ሌላው እንዲዳከም አይደለም። ዓላማው ኢትዮጵያ እንድትጠነክር ነው። ኢትዮጵያ የምትጠነክረው እንዴት ነው? ያልክ እንደሆን ብሔረሰቦቿ ሲጠነክሩ ነው። ብሔረሰቦቹ እንዲጠነክሩ ለማድረግ ደግሞ ብሔረሰቦቹን በአስተዳደር ክልል ስታካልል ቋንቋን መሰረት አድርገህ ከተነሳህ ለልማትም ሆነ ለአስተዳደር አመቺነት ተስማሚ አይሆንም። ቋንቋን ብቻ መሰረት የምታደርግ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ችግር ትፈጥራለህ። ለምሳሌ እኛ ስናካልል ኤርትራ እና ትግራይ ለየብቻ ራስ ገዝ የተባሉት ቋንቋን መሰረት አድርገን ባለማካለላችን ነው። የጎንደር አማራ እና የሸዋ አማራ አንድ ቋንቋ ይናገር እንጂ በስነ ልቦናም ሆነ ለልማት ባለው አመቺነት ሁለቱን አንድ አድርጎ ማካለል አይቻልም። የወለጋ ኦሮሞ እና የሀረር ኦሮሞም በተመሳሳይ ነው። ቀደም ብዬ እንደነገርኩህ የአስተዳደር ክልል የሚካለለው የብሔረሰቦችን ችግር ለመፍታት እና ለልማት ማፋጠን እስከሆነ ድረስ ቋንቋን ብቻ መሰረት አድርገን ብናካልል ኖሮ መልካም አይሆንም ነበር።

በሌላ በኩል አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሀይማኖት እና አንድ ባህል ያለው አለ አፋር። የአፋር ህዝብ የአሰቡን አፋርም ሆነ የጺዮኑን አፋር በተለያዬ ጊዜ ብትጠይቃቸው አንድነታቸውን የሚገልጽ እንጂ በመካከላቸው ልዩነት የሌለ መሆኑን ይነግሩሃል።

ሰንደቅ፡- የኢትዮጵያ መንግስት የበርበራ ወደብን ለመጠቀም ከሶላሜ ላንድ ገዥ ጋር በቅርቡ ስምምነት ላይ ደርሷል። ከዓመታት በፊት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር “ወደብ ባይኖረንም ማደጋችንን አላቆምንም። የአሰብ ወደብ ለኤርትራ መንግስት ሊጠቅመው የሚችለው ለግመል ማጠጫ ብቻ ነው” ብለው የተናገሩ ቢሆንም አሁንም በወደብ አልባ መሆናችን አገሪቱ ዋጋ እየከፈለች ነው ተብሎ በስፋት ይነገራል። ለመሆኑ የአስተዳደር ክልል የሰሩ እንደመሆነዎ “አሰብ ወደብ” የኢትዮጵያ ነው የኤርትራ?

ዶክተር ፍሰሃ፡- ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት ልጠይቅህ እስቲ “አሰብ ውስጥ የሚኖረው ብሔረሰብ ማነው?” ያልክ እንደሆነ የአፋር ብሔረሰብ ነው የሚኖረው። የአፋር ህዝብ እኮ ራሱን የሚጠራው የድንበር ጠባቂ (Gate Keeper) እያለ ነው። የአፋር ህዝብ አመለካከቱ ወደ ውስጥ እንጂ ወደ ውጭ ሆኖ አያውቅም። አሰብ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ኢትዮጵያዊ (አፋር) ከሆነ ወደቡ የኢትዮጵያ ነው ማለት ነው። በታሪክም ያየን እንደሆነ የኢትዮጵያ ነው። እንኳን አሰብ ጂቡቲም የእኛ ናት። ጂቡቲ ለ99 ዓመት በሊዝ የተያዘች አገር ነች በፈረንሳይ። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የነበረው ጄኔራል ደጎል ጂቡቲ ለእናት አገሯ እንድትመለስ ደብዳቤ ጽፎ ነበር። ነገር ግን አብዮት በመነሳቱና የደርግ መንግስትም ከሶማሌ ወረራ በተጨማሪ በአገር ውስጥም በጦርነት ስላለፈ የጂቡቲ ነገር መልስ ሳያገኝ ቀረ።

አቶ መለስ ብዙ ሊመሰገኑበት የሚችሉበት ስራ ሊኖር ቢችልም በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው። ኤርትራን ማስገንጠላቸው ሌላ ጥያቄ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሰብን ሲሰጡ እንኳ “እምቢ” ማለታቸው በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። ያኔ የተሰራ ስህተት ውሎ አድሮ አገሪቷ ላይ ትልቅ ችግር አምጥቷል። ከዚህም በላይ ሌሎች ችግሮች ሊከተሉ ይችላሉ።

ሰንደቅ፡- አንድ አገር ወደብ አልባ በመሆኑ ከኢኮኖሚያዊ ትርፍ በዘለለ የሚያጣው ጥቅም ምንድን ነው?

ዶክተር ፍሰሃ የምታየው ነዋ። አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ። ቤት ሲሰራ ለምንድን ነው በር የሚሰራለት? አየህ ቤት ሰርተህ ዙሪያውን አሽገህ የምትተወው ከሆነ መውጫ መግቢያ የለህም ማለት ነው። አገርም እንደዚህ ነው። ወደብ ማለት በር ማለት ነው። የወደብን ጥቅም ለማወቅ እኮ የተማርክ መሆን ወይም የጂኦግራፊ ምሁር መሆን አይጠበቅብህም።

ሰንደቅ፡- የኤርትራ ወደቦች (አሰብን ጨምሮ) ሁሉም በአረብ አገራት እንዲተዳደሩ የኤርትራ መንግስት አድርጓል። የኢትዮጵያ አጎራባች አገሮች (ከኬኒያ እና ደቡብ ሱዳን በስተቀር) የአረብ ሊግ አባል እና ታዛቢ (ኤርትራ ታዛቢ ናት) ናቸው። የአረብ አገራት ደግሞ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ባላንጣ መሆናቸውን ስናስብ አካባቢያችን በአረቦች ቁጥጥር ስር መዋሉ የኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?

ዶክተር ፍሰሃ፡- በታሪክ የኢትዮጵያ ጠላቶቿ የቅርብ ጎረቤቶቿ ናቸው። የቅርቦቹን እንኳ በአጼ ዮሃንስ፣ በአጼ ምንሊክና በአጼ ኃይለሥሳሌ ጊዜ የነበሩትን ችግሮች ለማየት ብንሞክር እነዚህ ነገስታት ደማቸውን ያፈሰሱትና ህይወታቸውን መስዋዕት የከፈሉት መውጫ በራችን ስለሆነ ነው።

አረቦች ደግሞ የእኛን እድገት፣ሀያልነት እና አንድነት የማይሹ ሁልጊዜ የእኛን አካባቢ ስቃይ ለመጫን እና ለመዝጋት ነው የሚፈልጉት። ስለዚህ እነሱ አንድም ጥይት ሳይተኩሱ የእኛው የራሳችን መሪዎች ቃታውን ሳቡላቸው። አሰብ ተዘጋ ማለት ነው። አረቦች አሁን ተንደርድረው እነዛ ወደቦች ላይ የሰፈሩት ለምን ይመስልሃል? አቶ መለስ ወደቡ የግመል ማጠጫ ያሉት ወደብ ነው አሁን ወርቅየሆነው። ይህ አርቆ ባለማስተዋል የተፈጠረ ስህተት ነው። አቶ መለስ አርቀው ማሰብ ይሳናቸዋል ብዬ ሳይሆን “አቶ መለስ ኢትዮጵያ ላይ ጨክነውባታል” ነው የምለው።

ሰንደቅ፡- በአሁኑ ወቅት አገራችን ውስጥ የማንነት ጥያቄን ጨምሮ የፖለቲካ ጥያቄዎች በስፋት ሲነሱ ይታያል። ለአብነት ያህል ብናነሳ በኦሮሚያ፣ በአማራ ክልል ወልቃይት አካባቢ እና የኦጋዴን አካባቢዎች እነዚህ ጥያቄ ተደጋግመው ይነሳሉ። ለመሆኑ ለጥያቄዎቹ መነሳት ምክንያቱ ምንድን ነው ይላሉ?

ዶክተር ፍሰሃ፡- በወልቃይት ጉዳይ እንጀምር። እኔ በታሪክ እንዳነበብኩትም ሆነ ባለፈው መንግስት የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲትዩት አባል ሆኜ ስሰራ በነበረበት ወቅት እንዳየሁት የወልቃይት ህዝብ የሰሜን ጎንደር አካል ነው። ወልቃይትን ወደ ትግራይ ያካለሉበትን ምክንያት ምን እንደሆነ ባላውቅም አሁን ግን በአዲሱ አስተዳደር ወደ ትግራይ አድርገታል።

የወልቃይት ህዝብ አሁን እየጠየቀ ያለው አነጋገራችን፣ አለባበሳችን፣ ባህላችን፣ አጠቃላይ ሁኔታችን እና ስነ ልቦናዊ አመለካከታችን ከአማርኛ ተናጋሪው እንጂ ከትግርኛ ተናጋሪው ወገን አይደለም እያለ ነው የሚጠይቀው። ቋንቋን በተመለከተ ግን ትግርኛ፣ አማርኛ እና አረብኛ እንናገራል ይላሉ። አየህ ቅድም ቋንቋን መሰረት አድርገን ያላካለልነው ለዚህ ነው። እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን የሱዳን መንግስት መጥቶ “ሰዎቹ ሱዳንኛ ይናገራሉና ሱዳናዊያን ናቸው” ሊል ነው ማለት ነው? ሰዎቹ ትግርኛንም ሆነ አረብኛን የሚናገሩት ከትግርኛ ተናጋሪውም ሆነ ከሱዳን ጋር ተጎራባች በመሆናቸው ነው። ስለዚህ ይህ የወልቃይት ህዝብ የተያዘበት መንግድ ለትግራይም ሆነ ለአገር አይበጅም። ጠብመንጃ ማንንም አላተረፈም። ንጉሱ 40 ወይም 50 ሺህ ወታደር በስራቸው ቢኖርም አላዳናቸውም። በደርግ ጊዜም ያ ሁሉ መሳሪያ እና ጦር እያለ መንግስቱን አላዳነውም። ኢህአዴጎችም የአስተዳደር ክልሉን ዘወር ብለው መመርመር አለባቸው።

የኦጋዴን ችግር ያነሳኸውን እንመልከት። በታሪክ የተመለከትን እንደሆነ የእንግሊዝ ቅኝ ሶማሌ፣ የጣሊያን ሶማሌ እና የፈረንሳይ ቅኝ ወደብ የሚባል እንጂ ሶማሌ የሚባል መንግስት አልነበረም ጃንሆይ (ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ) ናቸው የመሰረቷት።  እንግሊዞች ከቅኝ ግዛት ሲወጡ እንግሊዝ የተናገረችው የእንግሊዝ ሶማሌ እና የጣሊያን ሶማሌ ተብለው ለሁለት እንዲከፈሉ ነበር ሀሳብ ያቀረቡት። በዚህ ጊዜ በደንብ ያልተመለከቱት ነገር ኦጋዴን ውስጥ የሚኖረው ሶማሌዎች አሉ። ኬኒያ ውስጥ ሶማሌዎች አሉ። ኢትዮጵያ ስትረዳው የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር ሸርማርክ የሚባለው ታላቋን ሶማሌ እንመሰርታለን ብሎ ኦጋዴን እና ኬኒያ ውስጥ ያሉትንም ማጠቃለል አለብን ብሎ ከተናገረ ጀምሮ ነው ይህ ነገር የተፈጠረው። ኬኒያ ውስጥ ባለው ሶማሌም ሆነ በኦጋዴን ሶማሌ ላይ ተመሳሳይ ጥያቄ የሚነሳ ቢሆንም በእኛ ላይ ጠንከር ብሎ የሚታየው የውጭ አካላት ጣልቃ ገብነት ስላለ ነው።

የኦሮሚያ ችግር የተፈጠረው መንግስት መጀመሪያ አስተውሎ ካለማሰብ የፈጠረው ችግር ነው ብዬ ነው የማመነው። በእኔ እድሜ ያየሁትና የምነግርህ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ብሔረሰብ በቋንቋው እንዳይናገር የተደረገበት ጊዜ አልነበረም። ፍርድ ቤት እንኳ “አማርኛ አልችልም” ካለ ህጋዊ አስተርጓሚ ይመደብለት ነበር። በደርግ ጊዜ ህገ መንግስት ተቀርጾ ለህዝብ ውይይት እንዲደረግበት ሲደረግ የህገ መንግስቱ ረቂቅ የተዘጋጀው በ14 ቋንቋዎች ነበር።

ወደ ጥያቄህ ስመጣ በቋንቋ እንዲናገርና እንዲማር ሲደረግ ወጣቱ ተምሮ ከክልሉ ሲወጣ መናገር የሚችለው ኦሮምኛ ብቻ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ ያለ ህዝብ መግባቢያ ቋንቋው አማርኛ ነው ትግራይ ብትሔድ፣ ሀረር ብትሔድ ህዝቡ የሚግባባው በአማርኛ ነው። ይህ የኦሮሞ ወጣት ከክልሉ በኦሮምኛ ብቻ ተምሮ በማደጉ ወደ ሌላ ክልል ሲወጣ ሊያሰራው የሚችል የቋንቋ መግቢያ የለውም። ስለዚህ ያለው አማራጭ ምንድን ነው ወደ አደገበት ቀዬ ሂዶ ከአባቱ ጋር መሬት ተጋርቶ ማረስ ነው። ይህን ለማድረግ ሲሄድ ደግሞ መሬቱ ተሽጦ (መንግስት በካሳ አስነስቷቸው) አባቱ በቀድሞ መሬቱ ላይ በተሰራው ሆቴል ጥበቃ ሆኖ ነው ያገኘው። እውነቱ ይህ ነው።

ሰንደቅ፡- የኢህአዴግን የ25 ዓመታት የስልጣን ዘመናት እንዴት ይመዝኑታል?

ዶክተር ፍሰሃ፡- እኔ አስበው የነበረው ኢህአዴግ ከ25 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲ ቀይሮ ነጻነትን አስከብሮ አገሪቱን ይመራል የሚል ነበር። ምክንያቱም ኢህአዴግን ከጫካ ጀምሮ ያስተላልፉ የነበረውን የሬዲዮ ፕሮግራማቸውን እከታተል ነበር። በወቅቱ አቶ መለስ ሲናገሩ የነበሩት ስሰማ በእውነት ለኢትዮጵያ አንድ ልጅ ተወለደላት ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር። ነገር ግን የአቶ መለስ ንግግር በየጊዜው እየቆረቆዘ እየቆረቆዘ በመሄድ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል።

በሌላ በኩል ደግሞ የተሰሩ በጎ ስራዎችን ስመለከት ህንጻዎችና መንገዶች ተገንብተዋል። ከሞላ ጎደል በርከት ያሉ የሬዲዮ ጣቢያዎች ተከፍተዋል ምንም እንኳ አብዛኞቹ የሚያስተላልፉት አሸሸ ገዳሜ እና ኳስ ቢሆንም።

እኔ በተደጋጋሚ ጊዜ የምናገረው የማይሞት ሀብት ቢኖር እውቀት ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቱ በምን አይነት እውቀት ነው የተገነባው ብለን የጠየቅን እንደሆነ በትምህርት የተገነባ ሆኖ አላየሁትም። ወጣቱ የተገነባው በገንዘብ ላይ ነው። ስለዚህ መንግስት ትኩረት ሊያደርግ የሚገባው ወጣቶችን በእውቀት ላይ መገንባት ነው።

Sendek amharic newspaper

31 Comments on ““አቶ መለስ በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው” ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው”

  1. ” “አቶ መለስ በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው” ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው ”

    I have yet to read the article. Based on the title, how did he come to such conclusion ?

    Based on this Herman Cohen and Meles story ?

    1. Such an important issue is not decided in the last hour.

    2. Traditionally the TPLF decides key issues together.

    3. If the USA really wanted Ethiopia to keep the Aseb region, as the puppet master, it could have easily made puppets Meles and TPLF accept that.

  2. ” ዘውዱን አስወግዶ ደርጉን ያመጣውም ሆነ ደርጉን አስወግዶ ኢህአዴግን ያመጣው የወጣቶች እንቅስቃሴ ነው። ” —– LIE !

    It is the CIA.

  3. ” ዶክተር ፍሰሃ፡- ዓላማው እኮ አንዱ ብሔረሰብ እንዲጠናከር ሌላው እንዲዳከም አይደለም። ዓላማው ኢትዮጵያ እንድትጠነክር ነው። ኢትዮጵያ የምትጠነክረው እንዴት ነው? ያልክ እንደሆን ብሔረሰቦቿ ሲጠነክሩ ነው። ብሔረሰቦቹ እንዲጠነክሩ ለማድረግ ደግሞ ብሔረሰቦቹን በአስተዳደር ክልል ስታካልል ቋንቋን መሰረት አድርገህ ከተነሳህ ለልማትም ሆነ ለአስተዳደር አመቺነት ተስማሚ አይሆንም። ቋንቋን ብቻ መሰረት የምታደርግ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ችግር ትፈጥራለህ። ለምሳሌ እኛ ስናካልል ኤርትራ እና ትግራይ ለየብቻ ራስ ገዝ የተባሉት ቋንቋን መሰረት አድርገን ባለማካለላችን ነው። የጎንደር አማራ እና የሸዋ አማራ አንድ ቋንቋ ይናገር እንጂ በስነ ልቦናም ሆነ ለልማት ባለው አመቺነት ሁለቱን አንድ አድርጎ ማካለል አይቻልም። የወለጋ ኦሮሞ እና የሀረር ኦሮሞም በተመሳሳይ ነው። ቀደም ብዬ እንደነገርኩህ የአስተዳደር ክልል የሚካለለው የብሔረሰቦችን ችግር ለመፍታት እና ለልማት ማፋጠን እስከሆነ ድረስ ቋንቋን ብቻ መሰረት አድርገን ብናካልል ኖሮ መልካም አይሆንም ነበር።

    በሌላ በኩል አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሀይማኖት እና አንድ ባህል ያለው አለ አፋር። የአፋር ህዝብ የአሰቡን አፋርም ሆነ የጺዮኑን አፋር በተለያዬ ጊዜ ብትጠይቃቸው አንድነታቸውን የሚገልጽ እንጂ በመካከላቸው ልዩነት የሌለ መሆኑን ይነግሩሃል። ”

    This shows the guy is a tribalist.

  4. An invitation to usa decline
    could you visit the website
    In defence of marxism
    and read the april 12, 2016 edition, titled
    perspectives for the u.s revolution 2016 (draft)
    by workers international league

  5. ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው: “አቶ መለስ ብዙ ሊመሰገኑበት የሚችሉበት ስራ ሊኖር ቢችልም በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው።” ዶ/ር ፍሰሃ ኣሰብን በተመለከተ ከርስዎ እስማማለሁ። እንድያውም በታሪክም፣ በይገባኛል፣ በኣለም ሕግ መሰረት ኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነበራት፤ ሆን ብለው ኣቶ መለስ ለስልጣንና ለስም ትልቅነት የኣፋርም ህዝባችን ዶቆሱት እንጂ።
    “ኤርትራን ማስገንጠላቸው ሌላ ጥያቄ ሊሆን ይችላል።” እዚህ “ሌላ” ሊሆን ኣይችልም። ኣጼ ምኒልክ መረብ ምላሽ ለጣልያን ሸጥዋት። ሻእቢያ ትግል ኣካሄደ። የኤርትራ ህዝብ ፍላጎት ግልጽ ኣልሆነም። ኣቶ መለስ በደባዳቤ ኣስገነጠልዋት፤ የህዝብ ማንዴት ሳይኖራቸው እውቅና መስጠት ብሉሹነታቸው ነው። ሰለዚህ መነሻው፣ ሂደቱ፣ መድረሻው ግልጽ መሆን ዘላቂ ተቀባይነት ይኖረዋል። ነካ ነካ የትም ኣያደርስም።

  6. Assab be Shabiya
    Ije indtewdk yaderegut ye ginbot 7 founding fathers
    Kassa Kebede ena
    Ye Neamin Zeleken
    teyik .

  7. ባጫ : – ያ ሁሉ እንደከብት እየተነዳ ከሻብያ ጎን ሲዋጋ ህይወቱን ለኤርትራ ናፅነት የሰጠውን ባንዳ ትግሬ የት ረሳኸው!!!

  8. @tola, thank you. This idiotic young woyannes think Eritrea get independent because of derge. Ya band lij,anbeta balita blood Suker tigere fought ethiopian troops for shabiya. @USA decline you faggot woyanne cadre, Chinese cock sucker. You miget dead cunt sold ethiopian port to shabiya. Now you blame everything on USA and western countries for your short comings. Person like should be violated by Arab kuala just like your sister and your cousins in north.wergate cheap banda

  9. ^^^^^^^^^^^^^^

    Anchi milasam shabia (or are you “selam” ?),
    minew indih qinTrishin qolash ?

    Imiyaberdilish aTash inde, italian dk sucker ? 😉

  10. ye ginbot 7 barriawoch indaysemueh
    ine Yohannes sile Assab bitanesa
    yegeluhal . iski Bete Tsefet Eritrea
    hid bemulu ye ginbot 7 Majerat Mechiwoch
    tagegnachwalh .

  11. ‘USA Decline’ is a Chinese dk sucker Banda from Adwa/Adi Abun. Ethiopia will be free from China and the Adwa Bandas. Ethiopia will be ruled by her Patriots and true tigrean Ethiopians will rise over again.

    Death to Adwa bandas
    Death to the evil empire of China
    Long leave democracy
    Long leave Ethiopia

  12. Please read as ‘long live democracy’ and ‘long live Ethiopia’.

    Death to the Adwa bandas again.

  13. To USA decline: please stop such type of politics. Especially, don’t go around this country, the greatest country in the world, USA, an open minded world, under any circumstances, if they find their wrong, they can correct it. But it isn’t the way you think. Stop such type of politics because it can’t help for that poor country. This is my personal comment.

  14. Ethiopia was supposed to be put 3 times on the list above !

    * Ethiopia 1960, 1974 *, 1991 *

    The list is no doubt not complete. Only the obvious and hard to deny cases are listed.

  15. Yealekah yene
    Neamin Zeleke abat
    nachew be fake Dollar le Shabia yasrekbut. Moltewal
    be DC ena akababiw.
    sile Assab kanesah
    ginbotoch yegaluhal. Meles men yadregh yante sheto yehiedwun.

  16. The biggest mission of Melase Zenawi is killing the generation. Don’t divert our struggle. Even TPLF start crying about Asset .Tears of crocodile.

  17. With all its weakness we Ethiopians Prefers
    to be ruled by EPRDF than these power thirsty bunches of treasoners of MAMMA Ethiopia. The coming 50 years would be a time for
    full democratic transition. ISHE
    Allah !!!

  18. mr. usa decline….? it looks like you are thre only one who held the truth…you are a sad ass…

  19. again mr know it all…what the heck are you writing…you did not told things we did not know …plz tell us something we don’t know…

  20. Whats up retarded dirty mouth ?
    How long since you washed your mouth, a year ?

    Better take a point and ask, so we can know what you want. Speaking in general terms is retarded.

    ” the observrer says: April 16, 2016 at 1:42 pm

    mr. usa decline….? it looks like you are thre only one who held the truth…you are a sad ass…”

  21. Oh, you knew everything ?

    So, then you know when the letter of De Gaulle was written, please tell us the year.

    ” the observrer says: April 16, 2016 at 1:50 pm

    again mr know it all…what the heck are you writing…you did not told things we did not know …plz tell us something we don’t know… “

  22. Indie beka Doctors and Professors qewesu indie ? Betam sira yefetu yemeslegnal woyalawun ena Mehurun meleyit altechalm

  23. አማረ= ማለት አንተ የባንዳ ዘር ጣሊያን ሰሀጢ በረሃላይ መቶ በከረሚላ እያታለለ አስመራ ድረስ አምጥቶ ያስቀመጠ እዛው ያንተ የባንዳ አባቶች ትግሪ እንጂ ሚሊሊክ ከሸዋ መቶነው ጣሊያንን የተስማማው እናት ባንዳዎች እንካን ለሚሊሊክ አይደለም አጺ ዮሃንስን የካዳችሁ አገር ለስልጣን ስትሉ ያስረከባችሁ ናችሁ የፈረጅ አሽከርነት ለናተ ክብርንው :: የአድዋ ባንዳዎች እንካን አይደለም ኢርትሪያን ኢትዮፒያን ለጣሊያን ለማስረከብ ሚሊሊክን ለመጣል አንዲ ከጣሊያን አንዲ ከሚሊሊክ እያላችሁ ስታምታቱና ዛሪ ኢትዮፒያን ሸጣችሁ ደም እየመጠጣችሁ ያሰባችሁትን ህልም ሚሊሊክ ኩሩ ኢትዮፒያዊ ነቂ ብሎ ለዘመናት የኢትዮፒያን ህዝብ በባንዳ ትግሪ እንዳይጭበረበር እና ኢትዮፒያዊነቱን ማንነቱን አሳልፎ እንዳይሰጥ በማድረጉ አድዋላይ የባንዳ አባቶችን እና ፋሺስቶችን በጀግና ኢትዮፒያኖች በማዋረዱ ትልቅ የታሪክ ውርደት ስላለባችሁ ልጆቻችሁን ለማጭበርበር ኢርትሪያን ሚሊሊክ ሸጦ የትግሪን ዘር ለ2 ከፈለ በማለት ኢርትራና ትግሪ በፋሺስት ህልም ውስጥ ሆናችሁ ኢትዮፒያን አፍርሳችሁ ታላቃን ትግሪ ትግረ ለመመስረት በናተ በጎባጣ አሽከሮች የዘር ልሂቃኖች የኢትዮፒያን ህዝቦች አገኛችሁ:: ሚሊሊክ ቢተመንግስት ገባችሁ አለፈላችሁ ኢርትሪያን እና ትግሪን ይዛችሁ አምሃራ ኦሮሞ ደቡብ ሱማሊ …ሸጣችሁ ወደብ ለወደፊቱ የትግሪና የኢርትሪያ እንዲሆን በኢርትሪያ አስቀመጣችሁ ህወሃት ባንዳ ደግሞ ኢትዮፒያዊያንን በዘር ከፋፍሎ ለማጥፋት ለመውረር ጠላቶቺ የሚላቸውን የኢትዮፒያ ህዝቦች አምሃራውን እና ኦሮሞውን እንዲሁም ሊላው ሲስተማቲክ አጥፍተን ኢትዮፒያዊነታቸውን ሰርዘን በዘር ማንነታቸውም እንዳይነሱ አድርገን የትግሪን ትግረ ነጻነት ህልውና እስከምናረጋግጥ ጠላቶቻችን መጥፋታቸውን እስከምናረጋግጥ ድረስ ኢርትሪያኖች ጠብቁን የትግሪው ነጻ አውጭ ህወሃት ኢትዮፒያን ቀብረንላችሁ እኛ የምንገናኝባት ግዚ አለች በትግስት ጠብቁ ኢሳያስ የትግሪን እና የኢርትሪያን ጠላት ኢትዮፒያኖችን አማራዎችን ኦሮሞዎችን እንዳያስጠጋ ተቃወሙ ጠብቁ :: የመለስ እራይ ወደብ ለኢርትሪያ ትግሪ ከኢትዮፒያ በዘረፋ ነጻ ሲወጣ በጋራ ወደቡን ለመጠቀም ያስቀመጣት ነች:: ኢትዮፒያ በጠላቶቻ ቁትጥር ስር በፋሺስት ሲስተም ወደቀች እንጂ ህወሃት እና መለስ ህልማቸው ታላቃ ትግሪነች ይህ ያልተገለጸለት ህዝብ ወይም ዚጋ ህወሃትን 25 አመት ያላወቀ መቺም አያውቀውም ::

  24. MELES MALET BERASU MENGED SETANAWI TEGIBARUN FETSIMO AYIMOTU MOT MOTOWAL.ZARE YEBASUT AGANINTOCH NEGISEWAL. Tadiya yihinin betigil mekeyer yasifeligal. “meles!yederek wedeb balebet adirigewin yele ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*