ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን / ቢንያም ሙልጌታ ( ከኖርዌይ )

ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን / ቢንያም ሙልጌታ ( ከኖርዌይ )

ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ታሪክ ናት፡፡ይህም በዜጎችዋ አንደበት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እውቅና በመስጠት የሚናገሩት ነው። ጥንታዊና ታሪካዊነቷ ለጉብኚዎቿ አይን መስህብ የሚሆኑ ዘመናትን ያለፉት ቅርሳ ቅርሶች ብቻ ሳይሆኑ ህዝቧ በራሱ የተለየ ስብዕና ባለቤት ነውና ብዙዎች ይደነቁበታል። ፍቅሩ፣ ደግነቱ፣ መከባበሩ፣ ችሮታው፣ ወኔው፣ ጀግንነቱ፣ያለውን ተካፍሎ መኖሩ እና ከሌላው ትውልድ ለየት የሚያደርገው ብዙ ብዙ ተፈጥሮው ወ ዘ ተ . . . ያስደምማል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገር ወዳድ የሆኑ ጀግኖች የፈለቁበት ሀገር በመሆን፤እንኳን ዳር ድንበርን አፍሩ እንዳይቆነጠር የታገሉ ሴት እና ወንድ ታጋዩች የሞሉባት ሀገር ናት። በአገራችን ረጅም ታሪክ ውስጥ ህዝቦቿ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያለፉና ዘውዳዊው ተሽሮ ወታደራዊ አገዛዝ ሲተካ የሚደርስበትን የተለያየ እንግልት እና በደል ዋጥ ስልቅጥ አድርጎ የእርስ በእርስ የነገድ እና የብሔር ብሎም የሀይማኖት ልዩነቶች ሳይበግሩት እና ሳይከፈፍሉት የኖረ ህዝብ ነው።

በዚህች ጥንታዊና ታሪካዊ አገር ብሶት የወለደው ብሎ ለአንድ ብሔር የታገለው አምባገነን ቡድን ከሀያ አምስት አመት በፊት ምሊኒክ ቤተ መንግስት ሲከትም ለዜጎች በእናስብላችኋለንና እናውቅላችኋለን ማስመሰያ ተሸብቦ ከጊዜ ወደጊዜ ለአፍሪቃ እንኳን ምሳሌ በመሆን አንድነቷን እና ድንበሯን በማስጠበቅ የተፈራችውን ሀገር ሊመዘብራት ተነሳ። አሁን ላይ የአገዛዙ ሌብነት እና በደል በጉልህ በሁሉ ዘንድ ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዝብ መብት እና ነፃነት ክፉኛ ተደፍጥጦ ህዝባችን ወሳኝ ሳይሆን ውሳኔ ተሸካሚ ብቻ በመሆን በፈላጭ ቆራጭ ዘረኛ ስር በመውደቅ ምድሪቷ የመከራ በትር እየደቆሳት እንደሆነ ከሁላችንም የተደበቀ አይደለም፡፡ ወያኔ ወደ ስልጣን ከመጣበት ከ ሀያ አምስት አመት በፊት የነበረውን ስርዓት ብንመዝነው እነዛ ዘመናት ለአገራችን ጭቁን ህዝቦች በመሪርነታቸው ፍፁም የማይረሱና አገራችንን ወደ ኋላ የጎተቱ በሁሉም ልብ ተፅፈው የሚገኙ የቁጭት ዘመናት ቢሆኑም የአሁኑ ዘመን ጭቆና እና በህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ከየትኛውም የማይገጥም ነው። ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ በየግዜው መልኩን እና ግፋዊ ስርዓቱን በተለያየ ቅርፅ እየቀያየረ በሀገሪቷ ላይ ከቶውንም ያልታየ ፋሺስታዊ ድርጊቱን አቀላጥፎታል።
በኢትዮጵያ ምድር ላይ ህዝብን ከህዝብ፣ወገንን ከወገንን፣ሀይማኖትን ከሀይማኖት አንዱን ብሔር ከሌላው ብሔር በማናቆር እና በቂም በቀል ህዝብ እንዲጠላላ የሚያደርግበት የወያኔ ቫይረስ በሀገሪቱ ዳር እስከመሀል ድረስ በሁሉ ዘንድ ተውሳኩ ተዛምቷል። ቫይረሱንም ለማምከን ኢትዩጵያዊነት በትውልዱ ስብዕና ላይ እንደገና ይገነባ ዘንድ ማንም ሳያፈገፍግ ሊስማማበት የሚገባ አንገብጋቢ መፍትሔ ነው። ለኦሮሞው መበደል አማራው ካልጮኸ ለአኝዋኩ ጉራጌው ካልተነሳ ወያኔ ወደ ግቡ ወደ ስኬቱ ይገሰግሳል ይፈጥናል። ኢትዩጵያዊነትን የማጥፋት ስኬት እና ጉዞ። የቂም በቀልና የዘረኝነት ደመና አገሪቷን በሸፈነበት በዚያን ወቅት፣ በጎንደር ክፍለ ሃገር ጭካኔ በተሞላው አካሔድ የወያኔ አጋዚ ታጣቂዎች ህዝብን በማፈን እና በማፈናቀል እና በዘራቸዉ ምክንያት ዜጎች ይጠቁ ዘንድ የሚገፋፋ ርካሽ ቅስቀሳ በስፋት እየተገበሩ ነው። ኢትዮጵያዊው ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ በአንክሮ ሲታይ ሆን ተብሎ በገዢው ክፍል አንድን ብሔር ከማጉላት አንፃር የሚደረግ መሆኑን ማንም ሊስተውም አይገባም። የሚያስደንቀዉ ነገር ግን በኦሮሚያ ክልልሎች እና በአማራው ክልል የሚኖሩ አበዉና ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችን ተሰብስበዉ … ለዘመናት አብረን ኖረናል። ተዋልደናል። ተጋብተናል። የነርሱ ልጆች የኛ ልጆች ናቸዉ። እነርሱን ማጥፋት እኛን ማጥፋት ነዉ… ብለዉ ፍቅርንና አንድነትን እንዳይሰብኩ የወያኔ ቫይረስ ከትውልዱ ላይ ኢትዮጵያዊነትን እያሳሳው ለሀገር ሳይሆን ለብሔር ዘብ መቆምን እያስተማረ ይገኛል።
በተለያዩ የአለም ህብረተሰብ ዘንድ ከዘረኝነት አልፎ በጋራ መሥራት በተጀመረበት በዚህ የስልጣኔ ወቅት፣ በአገራችን ባሉ ዜጎች መሀል የሀይማኖት መሪዎችንም በሚያካትት ሁኔታ ይህ አይነት ከዘር ጋር የተገናኙ ችግሮች መፈጠራቸዉ እጅግ የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነዉ። ይህም ወደ አስከፊ ደረጃ ላይ እየደርሰ ይገኛል። በተለያየ የትምህርት ተቋም ውስጥ የሚማሩትን ሳይቀር ይኸው የወያኔ የዘረኝነት ተውሳክ ትውልዱን ለሀገር ቀናኢ መሆኑን እየሰረቀው ይገኛል። የተማረው ወገን የበለጠ መብሰልና ማገናዘብ ሲገባው፣ በሰይጣን መንፈስ የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸዉ የሚያናፍሱትንና የሚቆሰቁሱትን የጥላቻና የዘረኝነት ፖለቲካን በማስተናገድ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለጥቂቶች መጠቀሚያ እስክንሆን ድርስ ማስተዋል መጥፋቱ እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑም ባሻገር ትልቅ የሆነ በስልጣን ላይ መባለግን እና እንዲሁም ደግሞ ወያኔ የኢትዩጵያ ጠላት እና አጥፊዋ እንጂ ገንቢዋ እንዳለሆነ በግላጭ የታየበትም ሆኗል።
በምድራችን ላይ ፍቅርና ሰላም ቢኖር ኖሮማ፣ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነን ባለሥልጣናት በጋዜጠኞች በብሎገሮች እና ጦማሮች እንዲሁም ግፉና ጭቆናው ይብቃ ድምፃችንም ይሰማ በሚሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያራምዱትን የእልህና የግፍ ፖለቲካ ባስወገዱ ነበር፣ በጥያቄ የተሞላውን ህዝብ በመጠጋት ከሁሉ ኢትዮጵያዊ ጋርም በትህትና የአገራችንን ችግር ለመፍታት ቢነጋገሩ ፣ በውጭ ሀገር በተለያየ ምክንያት በስደት የሚኖረውን ዜጋ እንደ “ሰይጣን” ከማየትና ከማጥላላት ይል ቅንነት ያለበት ንግግር ቢጀመሩ እና የምዕራባውያንን ፍርፋሪ ንቀው ዲያስፖራውን ዉጭ አገር ከሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የዉጭ ምንዛሪ መሰብሰብ ይቻል ነበር። እጅግ አያሌ መልካም እና ለሀገር የሚበጅ ነገራት በጋራና በአንድነት ማከናወን ይቻል ነበር።ዳሩ ወያኔ ከደደቢት ጀምሮ የተለከፈበት አጋንንት የሚገድል የሚሰርቅ የሚያጠፋ ሆነና ለኢትዮጵያችን መርገም ሆነ። የበረሐው ልክፍት ለሚያስተዳድረው ህዝብ፣ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲያሟላ አላስቻለውም ገና ከጥንስሱ በሀገር ልማት አልተመሰረትም እና ህዝብ የሚኖረው ኑሮ ከበረሐ ተለይቶ ሊታይ አይችልም። የህዝብን ኑሮ ባዶ በረሐ። የሚያቃጥል፣ የሚያነድ በረሐ ሆኗ – ኃለፊነቱን ያልተወጣ መንግስት ደግሞ ህዝብን ለእንግልት ለስቃይ እና ለሞት አሳልፎ ይሰጣል። እየሰጠም ነው።
በተለይም በአሁን ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ብሔር እና ጎሳዎች ትልቅ በደል እየተፈፀመባቸው ባለበት በዚህ ከባድ ወቅት የሚከተለውን ማጤን አስፈላጊ እንድሆነ ተናግሬ ሀሳቤን ለዛሬው ልደምድም። በሀገራችን ላይ የተበደለው እና የተጠቃው አንድ ብሔር አይደለም፣ የተፈናቀለውም አማራው አሊያም ኦሮሞው አይደለም ቤጌምድር ለትግራይ ሲሸነሸን ወልቃይቶች ተሰደዱ ተሰቃዩ የሚለው መገለጫ ሊሆንም ከቶ አይገባም። ኢትዩጵያዊው ወገን ነው በጨቋኝ አገዛዝ እየተሰቃየ ያለው። ስናብር በእርግጥ የምናስረው ነገር አለ ኢትዩጵያዊነት በሁሉ ዜጋ ላይ ይታተም!
ሀገራችንን እና ትውልዳችንን በመለያየት ቫይረስ በመበከል በዜግነታችን ለትውልድ እንዳንታገል ያደረገንን የወያኔን ተውሳክ አምክነን ሰሜኑ ለደቡቡ ምስራቁ ለምዕራቡ ይጮህ የሚገባበት ስልጣኔ እና እውቀት ላይ እንድረስ። በተለያዩ ውብ እና ማራኪ ባህል የተላበስን ኢትዩጵያዊ ህዝቦች ነን። ተከብራ የኖረች ሀገራችን ለተተኪው ትውልድ ተላልፋ ዜጋው የሚለማባት እና በሰላም የሚኖርባት ሀገር እንድትሆን እንደ ኢትዮጵያዊ የምንወስደው አማራጭ አንድ እና አንድ ነው፤ የሀገራችን ምድራዊ አቀማመጥ አመቺ በመሆኑ ከወደ አሥመራም ሆነ ከወደ ካይሮ የሚያስመሽገን ምንም ምክንያት የለም ወቅታዊው የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታም የሚያሳየን ይህኑኑ ዕውነታ ነው። ወያኔን በሁለገብ ትግል አንድነትን አጠናክሮ ለህዝብ ከቆሙና ታግሎ ከሚያታግሉ እንደ ኢህአፓ ያሉ ሕብረ ቤሄርና የብዙ ትግል ተሞክሮና በቆመለት ዓላማና በአገራችን ቤሄራዊ ጥቅም አይደራደሬ በመሆናቸው ልንደገፋቸውና በየቦታው የተበተታተነውንና መሪ ያጣውን ትግል እንዲመሩና ሕዝባዊውን ትግሉእንዲያጥናክሩትና እንዲያፋፍሙት በያለንበት ሆነን ጥሪ ልናቀርብላችውና እንዲሁም ከጎናቸው በመቆምና በማጠናከር እና እንደዚሁም ደግሞ ለህዝብ ነፃ መውጣት መስዋዕት ለመሆን ከቆረጡና በኢትዮጵያ ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ ምንም ብዥታ ከሌላቸው የተለያዩ የህዝብ ክፍሎች ጋር በማበር እና በመያያዝ የወያኔን ሀገር በታኝ ቫይረስ ለማምከን በኢትዩጵያዊነት ስሜት እና ሞራል እንነሳ! እንደራጅ! ኢትዮጵያ ከወያኔበቀር ሌላ ጠላት የላትም። አንዱን ጠላት በተባበረ ክንዳችን እናድቀው!!!
እናቸንፋለን!!! ቢንያም ሙሉጌታ
[email protected]
 http://ethfreedomfighter.blogspot.no/2016/04/blog-post_6.html

12 Comments on “ሀገር በታኙን ቫይረስ ለማምከን / ቢንያም ሙልጌታ ( ከኖርዌይ )”

  1. I think you are suggested a very good new idea and the road map or the other way of the strategy . What are they said EPRP AND Former and Recent Members? My suggestion is with out any condition all EPRP members together discuss it and now a days they must have to be leadership of Ethiopian politics because this party is still now to live in Ethiopian heart and they know deeply this grouping government. Finally who is collected and discuss this issue? I suggested ” YA TEWLED” or …. thank you.

  2. The meaning of Racism :-The unfair treatment of people who belong to a different race. with in Ethiopia context I can’t explain because that not the writer(Biniam’S)Topics or issues. Thanks.

  3. Why EPRP at this time? you know clearly the people who you afried to mention in your text is much better to save the so calld “Ethiopia” and even if they pushed like enemy in thier own land, they still belive that they can live with peace and harmony with others. What you must have to understand is, who ever came on power in that empire, this people never axept without true democrats. This people said enough.

    You guys live in democratic country, but you don`t learn the meaning of democracy. before crying for unity, try to understand the question of your people, respect the voice of the oppressed, try to be voice for voiceless. Do you know the constitution of Norway? do you know how the Norwegian law respect the people who live in northern Norway? They have thier own parlament and thier own flag. Nobody criticize them for their decision. Just they are Norwegians evn if they use flag or own parlament.

    Before criticizing TPLF who are you? I think those they call themselves ” ተቃዋሚ” are oppressors than TPLF, becouse they are telling us what they gonna be do if they have a chance. But allready they uses their chance to sell Djibouti and Ertreria. N o M o r e chance to sell what we have.

  4. No no speak the truth. you said the heros our grand fathers. but they solds eritrea and jdibouti.so speak the truth do not blame woyane.why you guys afraid minilik?no one king sold his land except minilik.this is the truth.

  5. Twenty five years means half a century, but it has reflected that peoples are not okay with such type of government. To govern the people they must be free of corruption, and they must represent the entire Ethiopian and not just from one ethinic group. If they continue in that aspect, it will be dangerous. This tension between the people and the one party will keep on moving, and there is a break point at the end.
    Is twenty five years not enough to create stabilized Ethiopia???

  6. Motiman(loot man)and ali(Hagos) take it is easy. Minilik was 19 century king unlike woyanne. Minilik didn’t fight Ethiopians to sell Djbouti unlike woyyane fought ethiopian for independent of Eritrea. You guys need treatment for hating Ethiopia and it’s people’s. After 25 years of looting still not ready to stop your revenge toward other Ethiopians. Mercy less thugs.

  7. 1. HagosAbreha says:
    April 5, 2016 at 8:21 pm
    Negussu Motoma says:
    April 5, 2016 at 8:13 pm
    የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 8 አሰቸኳይ መመሪያ
    +-+++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ላለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። አበው እንደሚሉት ይቺን የመከራ ጊዜ ካለፈን ኢትዬጰያዊ መሆን እንደ ሎተሪ የሚታይበት ቀን በቅርቡ ይደርሳል። የአገር ውስጥ ኦርሞዎች የዘር ፓለቲካ ነቃንብሸ ኢሐዲግዬ ብለውታል። የተደራጅው ንኡስ ኮር በወልቃይት፣ በትግራይ፣ በሐረ ር ፣ በአምቦ እና በመተከል ኮሩን ዘርግቶ በየአንዳንዱ ከተማ ሠራዊታችን ገብቷል። ሕዝባችን አየሞተ ነው በኢሕአዴግ አጋዚ እና በረሐብ እርዳታ የሚሰጠው ቅድሚያ ለሆዳሞች ብቻ ከዚያ በሚድያቸው ረዥሙን ይሉኝታ የሌለውን ምላስ ይለቁብናል። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
    1ኛ፣ እኛ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ከታች ያለውን አብዛኛውን ፈሸካው ሲነፈ የአገር ግዴታ የሚሰሩትን አዘጋጅተን ጨርሰናል። ለምሳሌ በመተማ የሰፈረውን ጦር እንደቋንቋው መረጃውን አግኝቶ ከወገኔ ጋር ብሎ ኢትዬጰያዊነቱን አስቀድሞ በተጠንቀቅ ይጠብቃል። የጦር መሪዎች ስንት የሰረቁት ዶላር አስቀምጠው ጦር ሜዳአይሞክሩትም።
    2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን ከዘር ነፃ የሆነ ተራማጅ አትዬጰያን የሚያሰቀድም በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣሉ።
    እኛ አሁን ለወሬ እና ለዘር ፓለቲካ ጊዜ የለንም የፈለገ መሪ በቋሚ ሰርአትን ተከትሉ እኩል ማስተዳደር የሚችል ብቻ ነው የምንፈልገው ከዚህ ውጭ የሆናችሁ የራሳችሁን ሙያ ቀጥሉ እንጂ የማይሁን ቃላት አቁሙ እና ተራማጅ የለውጥ ሐዋሪያዎችን እንድትደግፍ እናሳስባለን።
    3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የ አክሱም ትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ሌሎችን ጳጳሳት ጉባኤ በማግለል ከገንዘብ አፍቃሪ ተሐድሶዎች ጋር በመሆን የውሸት ተቦት አስቀምጠው፣ ትክክለኛውን ለመሸጥ ውሉን ጨርሰዎል ከዚህ ቀን ጀምሮ አቡነ ማቲያስ እንቅልፍ የላቸውም፣ የሚሰሩትን ምንም አያቁም። የግፍ ወንበር በተራው እንደዚህ ያረጋል።
    4ኛ አቡነ መርቆርዮስ በሕገ ወንበር ላይ ስላሉ፣ የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን አንድነት ቡራኬ እና ጥሪ እንዲያደርጉልን በማክበር እንጠይቃለን። ይህንን ስንል የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል ማለታችን ነው!!!
    የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር እንወጠዋለን። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ አምቦ ኮር
    [Reply]
    Reply
    2. አብርሃም ተወልደ says:
    April 6, 2016 at 6:22 pm
    አብርሃም ተወልደ says:
    April 6, 2016 at 6:02 pm
    ጀግኖች ናቹ የሚያሳዝነው ነገር እንደ ተባለውእንደ አህያዋ በድን ሆኖ ስለ አገሩ ቅንጣት እንኳን የማይሰማው
    ብዞች አሉ። በስደቱ አለም ላይ የተዋረደውን ኢትዮጵያዊ አስቡት። ነገ ጠዋት በፍቅር የምንሰባሰበት አገር አለችኝ ግን እኔ ይህንን የጥላቻ አጥር ልበጣጥሰውብለን ዛሬ እርምጃ መወሰድ አለብን። የትም አገር በስደት ያለህው አገርህን እንዳይረሳ። በቅርብ ቀን ኢሐዲጎች በእራት ላይ ተሰባስበው እኛ በየጨቅጣጫው 25 አመት ሙሉ የሐይማኖት ታጋይ አንበሶች ኮራንባችሁ አንድም ቀን መንግሥትን አላወገዛሁም። በቁመና እያላችሁ ይችን ሸልማትአዘገጅተናላችሃለን ብለው ጠቅልለው አንድ አንድ ሽጉጥ አርገው አቦይ ስብሐት፣አባዬች ሆነው ሸለሟቸው። እንዲያውም የሉት በስተመጨረሻ የሚያስደስት ነገር ስላጣን ነው ይህንን ያበረከትናችሁ። የ25 አመት ታሪካችን ቀድመን ከሲቪል ኮሌጅ ለሲኦል የሚሆን ስለሆነ እወቁት ግን አሁን በእስር ቤት ያሉትን ጨካኝ ገራፈዎችን የዘን አንሄድም እዛው ያለው የሱዳኑ ጋኔን ይሻለናሉ አሉ እየሳቁ። አሰቡት እናንተ ስላላቹ ኦርቶዶክስ፣መስሊሙን ልናጣላ ሙከራን አልሆነም ግን ሰሰነጣጥቅናቸው። እና ፓስተር ዳንኤልን ሱቃችሁን አብዝታቹ ወንጌልና ትታዘቹ ይህንን ግራ የገባውን ህዝብ ቢዚይ አርፋችሁ ቸርቹ ውስጥ ታስረግጡታላችሁ አሉን ። እነዚህ ናቸው እንግዲ የአገር እና ሐይማኖትን መሪዎች። አይ 8ኛ ሺየመጨረሻ ሰአት።
    [Reply]
    [Reply]

  8. አይ መተማመን ወንድም አለም እንዳንተማመን የጎሳ ቨይረስ ከገባ 50 አመታት አስቆጠረ
    አሁን መተማመን ያለው በስርቆት፣በሌብነት፣በግድያ፣በዘረፋ፣ሰውን ገድለው ትክክል ነን የሚባልበት መተማመን አይደለ የምንሰማው የምናየው የኦሮሚያ ክልል ፕሩዚዳንት ምን እንዳለ አልሰማህም ወንድም አለም አነጣጥሮ ተኮሸች የሰሩት ስራ/ተግባር/ ትክክል ነው አዎን በእሱ አስተሳሰብ ሰውን መግደል ያኮራል፣ስልጣንንም ያስተማምናል ማን ነክቶን/ነክቶቸው እይ ይች መተማመን
    ሕዝብ አብረህ አትኖርም እናባላሃለን/እንበላሃለን፣እናስበላሃለን ሰውን ሰውን እየበላው ነው መተማመኑ
    ሰ.አ

  9. Sanjaw: your response is tell me who you are. To back to the reality, history can never change. Yes Menilik was a king, but he wasn`t creat Ethiopia by love and peace. Try to read before insult others. Yes he was the king who sold Dejbouti to France in Ethiopian history. Even if your historians trying to cover this shamedull work, but this is the part of our history you like it or not. Don`t follow the past blindly.

    Was Minilik our king? yes he was. Yes he create the so called Ethiopian empeire, yes he killed innocents, But we can`t deny the part of our history

    Adios

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*