አንጋፋው የሳክስፎን ተጫዋች አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ አረፈ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. April 4, 2016):- በ1927 ዓ.ም. የተወለደው አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ ጥበብን የተቀላቀላት በመንገድ ላይ ታንቡር መቺ በመሆን ነው። ይህ የሆነው በ1940 ዓ.ም. ነበር ። በኋላም ጥበብን እየተከተላት እሷም ወዳለችበት እየጠራችው በ1948 ዓ.ም. በመዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በፊት ከሚያደንቃቸው በኋላም ለረጅም ዓመታት አብረውት ከሠሩት ከአርቲስት ተፈራ አቡነወልድና ከአርቲስት ወዳጄነህ ፍልፍሉ ጋር ተቀላቀለ።