በካድሬዎች ስር የወደቀችው ቤተ ክርስትያን (አምዶም ገብረስላሴ)
ከአምዶም ገብረስላሴ
ኣቶ መኮነን ኣስፋው በምርጫ 2007 ዓ/ም በተካሄደው ምርጫ ዓረና-መድረክን ወክለው በኣላማጣ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ህወሓትን ኣምበርክከዋል ዳሩ ድምፃቸው ተዘረፉ እንጂ።
ኣቶ መኮንን በ1974 ዓም ወደ በረሃ ወጥቶ ያታገሉ ሲሆኑ ከነ ሓየሎም ኣርኣያና ገብሩ ኣስራት ጎን ተሰልፈው ደርግ በመደምሰስ ታላቅ ድርሻ የተጫወቱ የህዝብ ልጅ ናቸው።
ኣቶ መኮነን በህወሓት ካድሬዎች ከግድያ ዛቻ ጀምሮ እስከ የሃይማኖት ኣባቶችና የኣገር ሽማግሌዎች ሽምግልና የሚደርሱ ተፅእኖዎች ሲደርስባቸው ነበር።
ኣቶ መኮነን ኣስፋው ግን ሁሉንም ዓይነት የዓፈና መንገዶች ተቋቁመው በዓረና_መድረክ ስር ሆነው እየታገሉ መጥተዋል።
በመጋቢት ወር ያጋጠማቸው ገጠመኝ ግን ለራሳቸውም እጅግ ያስደነገጠና ያስገረማቸው ነበር። ገጠመኙ የማርያም ባላ ኣስተዳዳሪ ቄስ ኣፅበሃ ኣሰፋ ያሳወቋቸው ጉዳይ ነው።
ቄስ ኣፅበሃ ኣሰፋ ለታላቅ ጉዳይ እፈልገሃለው ብለው ቀጠሮ ያዙላቸው።
በቀጠረው መሰረት ሲገናኙ የሰሙት ንግግር ግን በፍፁም ለማመን ኣልቻሉም።
ቄስ ኣፅበሃ “… ኣንተ ኣሁን እየሰራኸው ያለው ስራ ሰው፣ መንግስትና ቤተ ክርስትያን የማይቀበሉት ተግባር ነው። ከዚህ በፊትም የክርስትናና የሙስሊም ሃይማኖት መሪዎችና ያገር ሽማግሌዎች ምክርና ተግሳፅ ኣልሰማ ብለሃል። ይሄ ዓረና የሚል የጠላት ኣላማ ይዘህ በቤተ ክርስትያናችን መቆየት ኣትችልም። ከዓረና የማትወጣ ከሆነ፣ ብትወልድ ኣናስጠምቅህም፣ ብትሞት ኣናስፈታህም፣ በቤተ ክርስትያናችንም ኣናስቀብርህም፣ ከቤተ ክርስትያንም እንደወጣህ ይቆጠራል።…” በማለት ከዓረና ኣባልነቱ ካልወጣ ክርስትያናዊ መብቱን እንደሚነጥቁት ተነግሯቸዋል።
“……ኣንተ የቤተ ክርስትያን ኣገልጋይ ነህ። ማገልገል ያለብህ ለቤተክርስትያን ብቻ መሆን ነበረበት። ኣሁን ያንተ ተግባር ግን የህወሓት ካድሬ እንጂ የቤተ ክርስትያን ኣገልጋይ እንዳልሆንክ ያመላክታል። እኔ እማውቀው ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ መሆናቸው ነበር።
ቤተ ክርስትያንዋ በህወሓት ካድሬዎች የምትመራ ከሆነች ግን ከስርዋ ኣይደለሁምና እናንተም ሙቼ መቃብር ከልክሉኝ እኔም የምሰራውን ራሴ እወስናለው……” በማለት ራሳቸው ዓፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ ሂደው ወደ እስልምና ሃይማኖት ተከታይነት መቀየራቸው በይፋ ኣሳውቀዋል።
የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በከፍተኛ ደረጃ የህወሓት ተፅእኖ ስር ወድቃ ትገኛለች።
በየ ደብሩ የሚገኙ የህወሓት ቄስ ካድሬዎች በዓረና ኣባላት ላይ ከዓረና ኣባልነታቸው እንዲወጡ የግዝት፣ለልጆቻቸው የጥምቀት ክልከላ፣ የኣባት ንስሃ ክልከላና ከሞቱ በኋላ የፍትሃትና የቀብር ስርዓት እንደማይፈፀምላቸው ከፍተኛ ሃይማኖታዊ ተፅእኖ በማድረስ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ተፅእኖ ጥልቅ የሃይማኖት ተከታይ የሆነው የትግራይ ህዝብ ላይ የፖለቲካዊ ተፅእኖ ስር እንዲወድቅና ስጋት ውስጥ እንዲወድቅ የሚያስገድድ ነው።
ቤተ ክርስትያንዋ ከህወሃት ቀጥተኛ ተፅእኖ ካልወጣች ኣማኝዋ እያስከፋችና ሞራሉ እያዳከመች ከሄደች ህልውናዋ ላይ ኣደጋ ማስከተሉ ኣይቀረውም።
የትግራይ የገጠር ኣብያተ ክርስትያን የህወሓት የስብሰባ ማካሄጃ ሁነዋል፣ ቄሶች በኣንድ ለ ኣምስት ተደራጅተው የህወሓት የፕሮፓጋንዳ መሳርያ ሁነዋል፣ የተቃዋሚ ድርጅት ዓረና ኣባላት ጥምቀት መከልከል፣ ኣባት ንስሃ መቋረጥ፣ መገዘት፣ ኣንቀብርም ማለት፣ የቤተ ክርስትያንዋ መሪዎች በታጋዮች ቁጥጥር መውደቅ ወዘተ የሚጠቀሱ ጥሰቶች ይፈፀማሉ።
ቤተ ክርስትያንዋ ነፃነትዋ በህወሓት ካድሬዎች እየተረገጠ፣ ኣማኞች ሳይወዱ በግድ እንዲርቋት እየተደረገ፣ ህወሓት እንደ የፖለቲካ መሳርያ እየተጠቀመችባት እስከ መቼ ነው? እንደ ተቋም ለምእመናን ኣገልግሎት ታላቅ ትኩረት መስጠት ኣላባት።
ሃይማኖት ከፖለቲካ፤ ፖለቲካ ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንደሚለዩ የሚሰብከው ህገ መንግስትስ የት ገባ?
የሃይማኖት ነፃነት ይከበር…!
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
Reply
Haylome Andi says:
April 14, 2016 at 7:25 pm
ንጉሡ ሞቱማ says:
April 14, 2016 at 1:21 pm
የዳግም አደዎ ዘመቻ
ቁጥር 10 አሰቸኳይ መመሪያ
+-+++++++++++++++
ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ባንዲራችን ላይ በጋኔኑ አስገዳጅነት የጋኔን ምልክት አርገው ሕዝባችንን የእኩልነት ብሔር ብለው ጅል አረጉን። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራትን። የአገራችን ህዝቦች አገራችን በየአቅጣጫው መከራ ተደቅኖባታል ሰለዚህ ሁሉም እንደእምነቱ ወደ ፈጣሪ ከልብ የሚያለቅስበት ጊዜ ላይ ነን። ተራማጅ የአገር ውስጥ አሮሞ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጠላታችን ጋኔኗ ኢሕአዴግ ብቻ ነች ብለን ከሌሎች ወድ ኢትዮጵያዊያን ጋር የዱሮ ፈቅራችንን መልሰን በጋራ ለሁላችን ብለን የምንተሰብበት ደረጃ ላይ ደርሰን በማንዴላን አርእያ አና ገድል የዘርን ፓለቲካ እጥፈተን ወደ ዋናው ድህነታችን ወግያ በጋራ ቀጥታ እንገባለን። የአገር ውስጥ ኦሮሞዎች የዘር ፓለቲካ ነቃንብሸ ኢሐዲግዬ ብለውታል። አደዎዎቹ ሌላውን የትግራይ ህዝብ አፉን አፍነው የተሰወረ ግፍ ሲያደርሱበት ቆይተዋል አይ እንዳይናገር ሌሎች ብሔሮች ይሰሙናል እያሉ በጀርባው ሲሳለቁበት ኖረዋል፣ በየአንዳንዱ ከተማ ሠራዊታችን ገብቷል እና ለቆረጣ ወግያ 30 ሚሊዬን ኢሕአዴግ ከ10ኘ ከፈል ያባረራቸው ወጣቶች በትንሹ ተዘጋጅተዎል። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ለ ሕዝባችን።
1ኛ፣ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ጦሩን አብዛኛውን ሰለ ስራ አስመስለው ለወገናቻችን እና ለአገራቸው እንዲስሩ ታዘዎል። በሰሞኑ የጦር ግምገማ እርቃናቸውን እንደቀሩ አዩት።
2ኛ ኢህአዲግ አስከ አሁን ኢሳትን ላማፈን $26 ሚሊዬን፣ ዜጎችን ለማፈን $48 ሚሊዩን ከፈሏል፣ ሰሞኑን ደግም ቫይበር እና ጓደኛውን ለማፈን $10 ሚሊዬን ቅድሚያ ክፍያ አደርጓል። የውስጥ አርበኞቻችን እንዲሁም በቴሌ ውስጥ ያላችሁ የማፈኛ ቦታዎችን ለአባሎቻችን መረጃ ስጡ። ለኢሳት ባንክ በስውር አሳውቁ።
3ኛ አቡነ ማቲያስ ከግበረአበሮቹ ተሐድሶዎች ጋር አንድ ያለህን እምነትህን ሊያጠፈብህ ነው። ፈረንጅ አንተ ስትጎብዝ ነው የሚያከብርህ። ወሬ በቃን ሰው እየሞተ ነው። እርምጃ ዶ/ር ብርሀኑ/ ጀነራል ከማል። ኢሳትን፣ግንቦት7፣የተራበውን ወገናቹን ፣ ወድ የአቶ ኦባንግን ድርጅት እርዱ አደራ በተጨቆነው ኢትዮጵያዊ ስም እንለምናችሃለን።
4ኛ የወንድም ፓሮስቴንታንት እምነት እንደ አሸን የቸርች ቢዝነስ የከፈታቹ እነ ፓስተር ዳንኤል እና ሁለት ፓስተሮች መርዝ ህዝባችን ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሌላ በጭፈራ እየአደነጋገራችሁ ስለ ኢትዮጵያ አታስቡ አሮሚያ ለኢትዮጵያ ይጨነቅ?። ሰለዚህ በእምነቱ ስም የግል አላማችሁን ለኢሐዲግ ከፋፋይነተት አትጠቀሙ።
5ኛ በውጭ አገር ምሁራኖቻችን በአቶ አባንግ አሰተባባረነት ለተደረገው ሀሳብ እናመሰግናለን። የኛዎች የቀድሞው ኦነግ ኦሮሞዎች መሪዎች ጥሩ እርምጃ ተራምደዎል እናመስግናለን። አሁን አገር ውስጥ ያለው በተግባር የተራማጅ ማንዴላ አርእያ ቀይረነው ከአስመራ ትእዛዝ ደ/ር ብርሐኑ/ ጀ°ከማል ጅምሮ አገር ውስጥ በኮር ሰንሰለት ተገናኝቷል። ግን ዋናው አሁን ኢትዮጵያ የምትፈልገው በእኩል የሚያስዳድር ብቻ ነው። ያለፉትን መሪዎችን መውቀስ ማቆም አለብን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር። ንጉሡ ሞቱማ ተራማጅ የኦሮሞ ማህበር የታጋዮች ኮር አዛዥ ከአምቦ።
[Reply]
Reply
Gebra Gebru says:
April 14, 2016 at 1:31 pm
Gebra Gebru says:
April 14, 2016 at 1:28 pm
You are hero Negussu and you brought us together. We shall make it!!!!!!!!!!
[Reply]
[Reply]
I don\’t know every body in Ethiopia in every region hates Tigray. Why? TPLF has given freedom for all Ethiopian People. Ethiopian people don\’t beleive in democracy you can do any business, you can participate in any politics but you hate us.
TPLF is a pieces of devil. From devil, no one expects good things . So, at anytime any religious followers do not give up for Devils. Keep your religion and fight woyanes at the end of your life.
The Weyane under cover Papas Mathias is responsible for all Ethiopian Orthodox crisis. He is terrorizing our innocent Orthodox fathers and priests Guiding by Weyane cadres. Abune Matias banes the known God blessed father Memhir Girma not to heal People who are suffering by demons in the country and outside. Is this Papas the follower of God? I’m in doubt. At this time the church has a big problem created by its lavish church leaders. The symbol Synodose is like the symbol Weyane Parliament. God bless Ethiopia and its people. Amen!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ አሁን በትልቅ አደጋ ላይ እንደምትገኝ ሁላችንም የምንረዳው ይመስለኛል። ሉዓላዊነቷን ለመንግስት ካስረከበችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ራሷን ችላ ቀኖናዋን አክብራ፣ በኅገ እግዚአብሄር መመራቱን አቁማ ለጊዝያዊ ስልጣን በሚሯሯጡ አባቶች በመመራት፣ የካድሬነት ስራ እየሰራች ከመጣች ቆይታለች። ይህ ሲባል ግን ሁሉንም አባቶች በደምሳሳው እየወቀስኩ አለመሆኔን ተገንዘቡልኝ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ በካድሬዎች እጅ ተነድተው ይኸውና አገር እየጠፋ አንድም የተግሳጽ መልዕክት ሲያስተላልፉ አልሰማሁም።
ይህ ሁሉ የሚያሳየን ለምድራዊው ዓለም ተገዢ ሆነው ለስጋቸው ማደራቸውን ነው።
ስለዚህ ይህቺ ማስፈራርያቸው ግዝት፣ እኛው ራሳችን ወስደን እነርሱን እንገዝት እንደሁ እንጂ ከነርሱ ምንም የምንጠብቀው ነገር የለም።
ወገኖቼ፣ አንድ ማወቅ የሚገባን ያለ ነገር ቢኖር ግን ወያኔ ቤተክርስትያኗን ለማጥፋት የተሰጠውን የባእዳን ተልዕኮ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ እየተጠቀመበት መሆኑን ተረድተን ይህንን አደጋ ለመቀልበስ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ አደራ እላለሁ።