ፓትርያርኩ: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን “ቀንደኛ ሌባ” አሉት
- በሕመምተኛ ልጁ ሕክምና ስም በርካታ አጥቢያዎች በ፻ሺሕዎች እያወጡ በሰጡበት ኹኔታ፥ “እኔ ሳላውቅ ስሜን ለማስጠፋት የተሠራ ነው” በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል እየጣረ ነው
- ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው የተወሰነበት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት አስተዳደር ኮሚቴ ውሳኔ ቃለ ጉባኤ፣ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ተሽሮ ውሳኔውን በሚያስተባብል ሌላ ቃለ ጉባኤው እንዲቀየር ሓላፊዎቹን አስገድዶ ነበር
- “ድጋፉን የሰጠነው ተዋቅሮ በተላከ ኮሚቴ በተጠየቅነው መሠረት ነው፤” ያሉት ዐሥር የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት ትእዛዙን ባለመቀበላቸው በየማነ ከሥራና ከደመወዝ ታግደው ነበር
- የእገዳ ርምጃውንና አጠቃላይ ኹኔታውን ከገዳሙ ሓላፊዎች ያዳመጡት ፓትርያርኩ፥ “እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችኹ” ሲሉ ገሥጸው ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ አዘዋል
- በሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ አጥቢያዎችን በማስፈራራት ከብር 3 ሚሊዮን በላይ የሰበሰቡለት አማሳኝ አጋሮቹ፥ “እርሱ አያውቅም፤ ከግል ገንዘባችን ነው የረዳነው” በሚል ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳንና ምዝበራውን ለማስተባበል ልዩ ጽ/ቤታቸውን ደጅ እየጠኑለት ነው
- “እገሌንና የእገሌን ልጅ አሳክመናል፤ ከኪሳችን እንጂ ከሙዳየ ምጽዋት አልነካንም፤” የሚሉት አማሳኞቹ፥ “የቅዱስነታቸውን አእምሮ እንቀይራለን” በሚል ጉዳዩን ለማዳፈን ይንቀሳቀሳሉ
* * *
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፵፭፤ ቅዳሜ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)(ቃለ ጉባኤውን ከዜናው በታች ይመልከቱ)

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ለልጃቸው ሕክምና የገንዘብ ርዳታ የወሰኑላቸውን የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ዐሥር የአስተዳደር ኮሚቴ አባላትን ከሥራና ከደሞዝ ያገዱ ቢኾንም ፓትርያርኩ እግዱን ሽረውታል፡፡
ሥራ አስኪያጁ፣ “ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ” በሚል ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ እንደነበሩ መዘገቡ የሚታወስ ሲኾን፤ ከእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር በገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ እንዲሰጣቸው ቢወሰንም፤ የገዳሙ ሒሳብ ሹም ክፍያውን አልፈጽምም በማለታቸው ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በሥራ አስኪያጁ እግድ ተላልፎባቸው የነበሩት የአስተዳደር ኮሚቴ አባላት፣ ሥራ አስኪያጁ ከትላንት በስቲያ፣ መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽ/ቤታቸው ጠርተዋቸው፣ “ስሜን ለማስጠፋት እኔ ሳላዛችኹ ኾን ብላችሁ የሠራችኹት ነው፤” በሚል ግማሽ ሚሊዮን ብር ለመስጠት የወሰኑበትን ቃለ ጉባኤ ውሳኔውን በሚያስተባብል አስተዳደራዊ ውሳኔ ሽረው ቃለ ጉባኤን እንዲቀየሩ እንዳዘዟቸው ይናገራሉ፡፡
በሥራ አስኪያጁ ዕውቅና ተዋቅረው ከተላኩት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዎቹ ሦስቱ መጥተው በጠየቁት መሠረት መኾኑን በመጥቀስ በተለይ የገዳሙ አለቃ በስተርጅና እንደማይዋሹና ኹለት ቃል እንደማይናገሩ በማስረዳት፣ የሥራ አስኪያጁን፥ “ውሳኔያችኹን በውሳኔ አስተባብሉ’’ ትእዛዝ ባለመቀበላቸው፤ “በስሜ አጨብርብራችኋዋል፤ እኔ ይሰጠኝ ብዬ አላዘዝኩም፤ ሒሳብ ሹሟ ክፍያውን አልፈጽምም ማለታቸው ትክክል ናቸው፤ ልታግዷቸው አይገባም ነበር፤” በማለት ኹሉንንም ከሥራና ከደመወዝ ማገዳቸውን እንዳሳወቋቸው ገልጸዋል፡፡
“ሥራ አስኪያጁ እገዳውን ካስተላለፉብን በኋላ የታገድንበትን ደብዳቤና የገንዘብ ድጋፉን የወሰንበትን ቃለ ጉባኤ ይዘን ቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በመግባት አስረዳናቸው፤” ያሉት የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት፣ የገንዘብ ድጋፉን ስለሰጡበት ኹኔታና ስለ እግዱ የሚከተለውን ብለዋል፡-
“የሲ.ኤም.ሲ ቅዱስ ሚካኤል አለቃ፣ የሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ጸሐፊዎች መጥተው አዋጡ አሉን፤ ባናዋጣ እንደምንባረር ዛቱብን፤ ትባረራላችሁ፣ ርምጃ እንወስድባችኋለን ሲሉን እኛ ምን እናድርግ? ወደን አይደለም፤ ከሥራችን እንባረራለን፤ ከደረጃችን እንወርዳለን፤ ማን የሚሰማን አለ? ሰበብ ፈጥሮ ነው የሚያግደን፤ ፍትሕ የሚሰጠን አጥተን ነው ይህን ያደረግነው፤ ሒሳብ ሹሟን፥ እነርሱን አግጄ ወደ ሥራ እመልስሻለሁ ብሎ በማለሳሰለስ እኛን ኹላችንን አገደን፡፡”
ፓትርያርኩ፣ “ገንዘቡ በትክክል ወጥቷል ወይ?” ብለው የጠየቋቸው ሲኾን እነርሱም፥ “አዎ፣ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች መጡ፤ አግዙን ብለው ጠየቁን፤ እንዲሰጥ ተፈራርመን ወሰንን፤ እኛ ማወራረድ ስላለብን ቸግሮን በቃለ ጉባኤ ተፈራርመን ሰጠነው እንጂ ሌሎቹ አጥቢያዎች በእጁ አይደለም ወይ ያለሰነድ የሰጡት፤” በማለት ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡
አቤቱታውን ያዳመጡት ፓትርያርኩ፤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና የገንዘብ ርዳታ የወሰኑትን አቤቱታ አቅራቢዎች፣ “እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችሁ፤ እኔ ታምሜአለሁ ብላችሁ 500 ሺሕ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ነው ወይ? ገመናችሁ ባይወጣ ስትሞካከሹ ትኖሩ ነበር፤” በማለት መገሠጻቸው ተነግሯል፡፡
እገዳውን በተመለከተም፣ “ማን ላይ ነው ጨዋታ የሚጫወተው፤ እርሱ ንጹሕ መስሎ እናንተን ሕግ ተላላፊ ለማድረግ አይችልም፤” በማለት በአስቸኳይ እገዳው ተነሥቶላቸው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱና ጉዳዩም እንዲጣራ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ ትእዛዝ መስጠታቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩ የብዙዎች መነጋገርያ ከመኾን አልፎ በፓትርያርኩ ተግሣጽና ውሳኔ ክፉኛ መረበሹ የተነገረለት የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ባለፈው ቅዳሜ ረፋድ አማሳኝ አጋሮቹን በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በመጥራት፣ እርሱ ሳያውቅ ከየግላቸው እንደተሰበሰበና የአጥቢያዎቹ ገንዘብ እንዳልተነካ በማስመሰል የሚያስረዱ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ወደ ፓትርያርኩ መላኩ ተገልጿል፡፡

“እኛ የኃይሌን[ኃይሌ ኣብርሃ] ልጅ ሌላም አሳክመናል፤ ግን ከራሳችን ከግል ገንዘብ ነው፤ ለእርሱም ያደረግነው ይኼን ነው፤ እርሱ ግን አያውቅም፤” በማለት፣ ሕጋዊነት ሳይኖራቸው ቁጥጥር የማይደረግበትን ገንዘብ በሕክምና ድጋፍ ስም በማሰባሰባቸው ከሚከተላቸው ተጠያቂነት ራሳቸውን ለማዳንና ሥራ አስኪያጁም በሚሊዮኖች የመዘበረበትን አካሔድ ለማስተባበል የፓትርያርኩን ልዩ ጽ/ቤት ደጅ በመጥናት ላይ መኾናቸው ተመልክቷል፡፡ “ከኪሳችን የመርዳት ልምድ ስላለን ቅዱስነታቸውን አግኝተን አእምሯቸውንና አመለካከታቸውን ማስተካከል አለብን፤” በሚል ተግሣጻቸውን ለመመለስና ለመቀየር ማቀዳቸው ታውቋል፡፡
ከአሰባሳቢ ኮሚቴው አባላት፡- የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የሲ.ኤም.ሲ ቅዱስ ሚካኤል፣ የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል፣ የሳሪስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ የጀሞ ቅድስት ሥላሴ፣ የገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የጻድቁ አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ፣ የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ አለቆች፤ የሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም አለቃና ጸሐፊ፤ የብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም አለቃና ሒሳብ ሹም፤ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አለቃና ተቆጣጣሪ፤ የብሥራተ ገብርኤል ጸሐፊና ሒሳብ ሹም፤ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም፣ የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤልና የደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሐፊዎች ይገኙበታል፡፡
* * *

የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አስተዳደር ኮሚቴ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ
የስብሰባ ቀን፡- 25/06/2008 ዓ.ም.
የስብሰባ ቦታ፡- በገዳሙ አስተዳደር ቢሮ
የስብሰባ ሰዓት፡- ከቀኑ 3፡00 ጀምሮ
ተሰብሳቢ አባላት፤
- ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል – የገዳሙ አስተዳዳሪና የጉባኤው ዋና ሰብሳቢ
- ክቡር በኵረ ትጉሃን ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር – የገዳሙ ምክትል አስተዳዳሪና የጉባኤው ምክትል ሰብሳቢ
- መልአከ ፀሐይ አባ ቀለመ ወርቅ አዳሙ – የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
- መ/ር አባ ማቴዎስ ከፍያለው – የገዳሙ አስተዳዳር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
- አባ ገብረ ትንሣኤ ብሬ – የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
- ሊቀ ጠበብት ተከሥተ ብርሃኑ – የገዳሙ አስተዳደር ጉባኤ አባል – የጉባኤው አባል
- መሪጌታ ፍሬ ስብሐት አለነ – የገዳሙ አስተዳደር ጉባኤ አባል – የጉባኤው አባል
- መሪጌታ አክሎግ ደሴ – የገዳሙ አስተዳደር ጉባኤ አባል – የጉባኤው አባል
- መዘምር አብርሃም አንዳርጌ – የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
- ቀሲስ ዘነበ ብርሃኑ – የገዳሙ ዋና ጸሐፊ – የገዳሙ ጸሐፊ ኾነው በተገኙበት ስብሰባ ተደርጓል፡፡
የዕለቱ ጉባኤ በጸሎት ተከፈተ፡፡ የዕለቱን ስብሰባ አጀንዳ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል የገዳሙ አስተዳዳሪና የጉባኤውም ሰብሳቢ ለጉባኤው አባላት ሲያስረዱ፤ ክቡር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ልጃቸውን ለማሳከም ይችሉ ዘንድ ቀደም ሲል ለዚኽ ዓላማ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች መጥተው ድጋፍ እንድናደርግ ጠይቀውን ሳለ እስከ አኹን በኛ በኩል የአዎንታም ኾነ የአሉታ መልስ ያልሰጠን ሲኾን ሌሎች ገዳማትና አድባራት ግን ቀድመውን ለዚኽ ዓላማ የተቻላቸውን የሰጡ ስለኾነ እኛም ይህንኑ መሠረት አድርገን ከሌሎች ገዳማትና አድባራት መለየት የሌለብን በመኾኑ በዚኽ ዙሪያ በጋራ ተመካክረን የተቻለንን ድጋፍ ለክቡር ሥራ አስኪያጅ ለልጃቸው ማሳከሚያ የሚውል ድጋፍ ማድረግ በምንችልበት ዙሪያ በጋራ መክረን አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ እንድንችል የተደረገ ስብሰባ ነው፤ ሲሉ ሰብሳቢው ለጉባኤው አባላት በማስረዳት ጉባኤያቸውን አጠቃለዋል፡፡
የጉባኤው አባላትም ከክቡር ሰብሳቢው የተሰጠውን አጀንዳ ገለጻ በጽሞና ከማድመጥ በመነሣት በመሠረተ ሐሳቡ ዙሪያ ጉባኤው ሲመክር፣ አኹን ላይ የቀረበው አጀንዳ ተገቢነት ያለው መኾኑ ቢታመንም ከተጠየቀበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አኹን መዘግየቱ ተገቢ አለመኾኑን ጉባኤው የተቸ ሲኾን ያም ኾነ ይህ አነሰ በዛ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በወቅቱ ይደረግ እንኳ ቢባል በሰዎች እጅ መላኩ ጥርጣሬ ውስጥ በመገባቱ የተነሣ ነገ ዛሬ ሲባል ሊዘገይ እንደቻለ የጋራ ግንዛቤ ተወስዶ ያም ኾነ ይህ አኹንም ቢኾን ድጋፍ ካደረጉ ከሌሎች ገዳማትና አድባራት እኛ መዘግየታችን ቢታመንም ድጋፍ ማድረጉ የረፈደ ስለማያሰኝ የገዳማችን ታላቅነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ታይቶ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅ በጉባኤው አጠያያቂ ኾኖ አልተገኘም፡፡
ስለኾነም ለዚኽ ለተቀደሰ በጎ ዓላማ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ የተገባ መኾኑ ታምኖ ለክቡር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ ይረዳቸው ዘንድ ዓላማውም የሰውን ፍጡር የማዳን በጎ ምግባር ስለኾነ ከገዳሙ ገቢ ላይ ብር 500‚000(አምስት መቶ ሺሕ) ወጪ እንዲመደብ ኾኖ ከዚኹ ውስጥ ብር 300‚000(ሦስት መቶ ሺሕ) በገዳሙ ስም፤ ቀሪው ብር 200‚000(ኹለት መቶ ሺሕ ብር) ደግሞ በገዳሙ ሠራተኞች ስም ተሰይሞ ለክቡር ሥራ አስኪያጅ በክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪና የጉባኤው ሰብሳቢ እጅ እንዲያደርሱ ሲል ጉባኤው ሙሉ ሓላፊነት በመስጠት ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስኖ የዕለቱን ስብሰባ 4፡30 ሰዓት በጸሎት ዘግቶ ፈጽሞ ተነሣ፡፡
የዋና እና የምክትል ሰብሳቢውን ጨምሮ የዐሥር የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት የማይነበብ ፊርማ አለው
አህያ ለአህያ ቢራገጥ…
Fata says:
March 26, 2016 at 9:58 pm
የዳግም አደዎ ዘመቻ
ቁጥር 7 መመሪያ
ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። ይሁን ና የነብዪን ቃል የፈረሱት አገሮች ተቀጥተዎል ለምሳሌ ሱማሊያ፣ኢራቅ፣ግብፅ፣ሊቢያ፣የመን፣ሰውዲ ፣አራን አሁን ደግም በቅርብ ቀን አልበሽር ተረኛ ነው። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
1ኛ፣ ኢሕአዴግ ስላዬቸን ኤርትራዊ ናቸው እያላቸው እንደ ስደተኞቹ ለሌላው አላም በችግራችን ግዜ ደረሶቹን ወንድም ኤርትራዊያን ስም ማጥፋት ቀጥሏል። መረጃ ለወድ ኩሩ ለሆነው አቶ ኦባንግ መቶ አስተላልፈ፣ ትክክለኛ ስደተኞችን መርዳት ሲገባ የባለሥልጣናት ልጆች ስራቸውን ስለሚያቁ እየጎረፈ ነው።
2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣል።
3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ፣ ጠ/ሚ፣ የስውር ተሐድሶ መሪዎች በጋሻው፣ከቤተ ክህነት ወስጥ ባሉት ሰንሰለት ሌሎችን አባቶችን፣ ማሕበራትን፣ ጥሩ አገልጋዮችን በማግለል በአለፈው ሳምንት በብዙ ሚሊዮን ለመሸጥ እና አስመሳዩን ታቦት ለማስቀመጥ በስውር የጋኔን አምላኪዎች ጋር ተማምሏል። ባዶ ቀፎ ይዞ መጓዝ አይቻልም? ኢትዮጵያዊ ሁለ በግዜህ ተነስ፣ በቃ በቁመና ሞተናል ወሬ በቃኝ።
አቡነ መርቆርዮስ እራሳቹን ወደ ውስጥ መመልከቻቹ አሁን ነው። የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን ለአንድነት ጥሪ መድረግ አለቦት። አለበለዚያ የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል!!!
4ኛ፣ ማንም አስከ ዛሬ ያልቻለው የትግሉ አቀናጅ ማነው ብለው በአምቦ ክተ ት ላይ ነች። እኔ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ሰው አንዴ በዘር ፓለቲካ ይታለላል ግን ሁለተኛ ከደገመው ግራ የገባው ነው።
5ኛ፣ ግራ የሚያጋቡትን የታሪክ አዎራዎችን አትመለከቱ ጊዜ የለም ህዝባችን እየተገደሉ እና ረሐብ ላይ
ነን። የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ከዚያ በአዲሱ ህጉ መስረት ቋሚ መንግሥት ቢበዛ ለ 10 የሚያገለግል ይመረጣል። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር ተጠንቅቃቹ ጠብቁ። ወላ ዋይ ትውልድ መሆንን አቁማችሁ ፣ በአገር ወስጥ ከ10ኛ ክፍል ኢሐዲግ ተስፈህን ያጨለመብህ መሰደድን አቁመህ በአገርህ የትግሉ ወስጥ ተሳታፊ ሆነህ ቀጥል። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። በመተዛዘን ፣ በፍቅር፣ በአንድነት እንነሳ!!! ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው የሚያስፈልገው ለ1000 ኢሕአዴጎች ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ የአምቦ ንኡስ ኮር።
[Reply]
Reply
Fekeru Tolcha says:
March 26, 2016 at 10:47 pm
Hero proud of u!!!!!!!!!!!!!!! we stand together Mote Lewyeana ena Le Faku Aba Mathis
ABUNE MATHIAS THE WORST DEVIL AND HE LOST HIS SPRITUAL POWER. HE IS A CHAIR PERSON ON EVERY FRIDAY DEVIL SECRET MEETINGS.
Be sudan 17 asmateñoch ahyawoch yizew.
Asmat mibal yelem.
Be qoraT Tnu tgl dl emenu.
the so called papas himself is a thief he is unlawful pop. therefore if the other guy didn’t take the money the pop will. there is no different from one thief to the other.
ሌባ ያልሆነ አለ እንዴ ከነሱ? አንድ አማራ መቀሌ ሄዶ እንደው ከተማው በሙሉ ጭር ይልበትና እንደው መንገድ ላይ ያገኛቸውን ትግሬ አሮጊት ጠጋ ብሎ ኧረ እንደው ህዝቡ የት ሄደ ብሎ ሲጠይቃቸው እሳቸውም ጉልበት ያለው በሙሉ እናተጋ ለዘረፋ ሄደዋል እኔም ጉልበት አጥቼ ነው እንጅ ሃሳቡ ነበረኝ ብለው መለሱለት። ጉልበት በማጣት ሌባ ያልሆኑ አንድ ትግሬ እኝህ ሴትዮ ብቻ ናቸው!!!!
እግዚኦ ማለት የለንም ጊዜ ላይ ነን ከመሪ የራሳችን ዜጎች አረመኔ ዲያቢሎስ ሆነው ይገሉናል። በሐይማኖትም ያልታደልን ታጋይ አባ ጳውሎስ ሲሄድ ታጋይ ማትያስ በመለስ ሰም እየማሉ ሐይማኖቱን በተሐድሶ አመሰው፣ እግዚኦ የለህም እንዳልል የ365 ቀናት ፓውዛህ ኢትዮጵያ ላይ በቃልህ ስታበራ አይተናል ግን አምላክዬ ትግስትህ በዛ አንድ በል በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ??? በሥልጣን ላይ በህይወት ያሉትን አቡነ መርቆርዩስ አልናገርም እሳቸው ለ ቡራኬ እንኳን ዝም ብለዎል፣ አንተ አንደበታቸውን ክፈትልን!!! እሳቸው ዝም በማለታቸው ሐይማኖት እናድስው ብለው አርጋንና በፍልስፈረና አጅበው ያልተለመደ ጉዞ እነ አባ መልከ ፀደቅ፣ አባ ወ/ትንሣኤ ፣ አባ መላኩ፣ ልኡለቃል ሕዝብ በተሐድሶ መንገድ ኢትዮጵያዊን ጋራ እያጋቡ ነው። ስርአቱን ጠብቀው ህዝብን በአንዲት ቤተክርስቲያን መሰብሰብ አልቻሉም። እባካችሁ የአገራችን ፈተና ለይ ነች፣ ይቅርታ ህዝቡን ጠይቃችሁ፣ ህዝቡን እንደገና አሰባስቡ፣ የጥላቻ ቤተክርስቲያን በዛ ፍቅር ከሌለ በመሀከላችሁ እግዚያብሔር የለም ባዶ ባዶ!!! እርስ በእርስ በሁለቱም ጎራ ዲየቢሎስ በረሱ መንገድ እየመራችሁ ነው ቆም ብላችሁ በአሰቸኳይ አስቡ። ስሙኝ እኔን ዛሬ የወደቁ ሐጥያተኛውን እኔ እንደ እናንተ አልሆንም ኤኔን ሐጥያተኛውን ስማኝ ብዬ እፀልይላቸዎለሁ። እባካቹ የማህበሩ ቅዱሳን ተግባር አትኮኑኑ ፈራጅ ያያል በአንፃሩ አንዳንዱቩም ከኔ በላይ ክርስትያን የለም የሚሉትን ለይቶ ማስተማር ይበጃል።
አንድ የወያኔ ሬድዬ ጣቢያ የሚሰራ ተራ ግለሰብ እንዴት ብሎነው መሪ የሚሆነው እሥኪ ወያኔ ሾሞት ነው እንጂ
‘እስመ ሥሙ ይመርሖ ኀበ ግብሩ’
ከአህያ የዋለች በቅሎ….
እግዚኦ ማለት የለብን ጊዜ ላይ ነን ከመሪ የራሳችን ዜጎች አረመኔ ጋኔን እና ዲያቢሎስ ሆነው ይገሉናል። በሐይማኖትም ያልታደልን ሆን ታጋይ አባ ጳውሎስ ሲሄዱ ታጋይ ማትያስ በመለስ ሰም እየማሉ ይገኛሉ ሐይማኖቱን ከተሐድሶ ሰዎች ጋር አመሰት፣ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ የለህም እንዳልል የ365 ቀናት ፓውዛህ መብራት ኢትዮጵያ ላይ በቃልህ ስታበራ አይተናል፣ ግን አምላክዬ ትግስትህ በዛ አንድ በል በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይብቃህ ዝምታ? በሥልጣን ላይ በህይወት ያሉትን አቡነ መርቆርዩስ አልናገርም እሳቸው ለ ቡራኬ እንኳን ዝም ብለዎል፣ አንተ አንደበታቸውን ክፈትልን!!! እሳቸው ዝም በማለታቸው ሐይማኖቱን እናድስው ብለው ኦርጋን ና የግዜውን ፍልስፍና ጨምረው፣አጅበው ከሐይማኖቱ ታሪክ ጋር ያልተለመደ ጉዞ እነ አባ መልከ ፀደቅ፣ አባ ወ/ትንሣኤ ፣ አባ መላኩ፣ ልኡለቃል ሕዝቡን በተሐድሶ መንገድ ኢትዮጵያዊውን ጋራ እያጋቡ ነው። ተው ተብለው ሲመክሩ ያለመታደል ከእኔ በላይ ከፈጣሪ የቀረበ የለም ይሉናል። ብዞዎቹ በጎንደርነት ያከብሯቸዎል ማክበር ጥሩ ነው ሲሰታቱ ከለነገራቹ ግን እነሱን ገደለ ውስጥ ከታችሁ ማለት ነው። አባቶቻችን ያስረከቡንን ዶግማ እና ቀኖና አንዲት ነገር ሳትቀየር፣ ስርአቱን ጠብቀው ህዝብን በአንዲት ቤተክርስቲያን መሰብሰብ አልቻሉም እባካችሁ ስህተት ጎዳና ላይ ናቹ ተመለሱ። እባካችሁ የአገራችን ፈተና ለይ ነች፣ ይቅርታ ህዝቡን ጠይቃችሁ፣ ህዝቡን እንደገና አሰባስቡ፣ የጥላቻ ቤተክርስቲያን በዛ ፍቅር ከሌለ በመሀከላችሁ እግዚያብሔር የለም ማለት ነው ባዶ ባዶ ባዶ ከደመና በታች ስጋን ለማስደስት ይሆንባቸዎል!!! እርስ በእርስ በሁለቱም ጎራ ዲየቢሎስ በረሱ መንገድ እየመራችሁ፣ እያረሰረባችሁ ነው ቆም ብላችሁ ሁለቴ በአሰቸኳይ ዛሬ አስቡ ነገ ፈራጅ ይመጣል። ስሙኝ እኔን ዛሬ የወደቁ ሐጥያተኛውን እኔ እንደ እናንተ አልሆንም ኤኔን ሐጥያተኛውን ስማኝ አምላኬ ብዬ እፀልይላቸዎለሁ። እባካቹ የማህበሩ ቅዱሳን ተግባር አትኮኑኑ ፈራጅ ያያል በአንፃሩ አንዳንዱቹ ከኔ በላይ ክርስትያን የለም ብለው የሚታበዩ አሉ እነሱን ቀጥታ ለይቶ ማስተማር እና ወደ ስርአቱ መመለስ ይበጃል ደካማው ወገኔ ብዙ ደም የተከፈለበት ነው።
Ethiopia in all dricion, the corporation of narrow nationalist Tigerians. Yelunta Yelelachew Woshoch