‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ! (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት )

 Addis Admass : ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማህረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ አይሁድ ሀገር ፍለጋ ከሺ ዓመታት በላይ መኳተን አልነበረባቸውም፡፡ በአውሮፓ የሚኖሩት ጂፕሲዎች የታወቀ ማኅበረሰብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሀገር የላቸውም። ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ጂፕሲ የሚባል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ጂፕሲ የሚባል ሀገርም ይኖር ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
በአሜሪካ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ‹በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን› የምትባል ሀገር ግን የለቺም፡፡ 1.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ግሪኮች በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ ‹የአሜሪካ ግሪኮች› የምትባል ሀገር ግን የለችም፡፡ ‹ግሪክ፤ ሲሠራ አሜሪካ ይኖራል፣ ሲያረጅ ግሪክን ይጦራል› የተባለው ሀገር ሰው ብቻ ስላልሆነ ነው።
ሰዎች ተሰብስበው ሀገር ሊመሠርቱ አይችሉም፡፡ በየሀገሩ የተሰበሰቡ ማኅበረሰቦች ‹ኮሙኒቲ› ይባላሉ እንጂ ሀገር አይባሉም፡፡ ሀገር  ሀገር ለመሆንና ለመባል ከሰው በተጨማሪ የምትፈልገው ብዙ ነገር አላትና፡፡ ሀገርን ሀገር ለማስባል መሬትም ያስፈልጋል፤ መሬት ሳይኖርህ ሰው ስለሰበሰብክ ብቻ ሀገር ልትሆን አትችልም፡፡ ያውም የእኔ የምትለው፣ የምትሞትለትና የምትለፋለት ታሪካዊ መሬት ያስፈልግሃል፡፡ አይሁድን በ1930 አካባቢ በኡጋንዳ ኡዋሲን ጊሹ (UasinGishu County) በተባለ ቦታ እንዲሠፍሩና ሀገር እንዲኖራቸው ታስቦ ነበር፡፡ እንደ ቴዎዶር ኸርዝል ያሉ ታላላቅ የጽዮናዊነት መሪዎችም ለጊዜውም ቢሆን  ተስማምተውበት ነበር፡፡ብዙኀኑ አይሁድ ግን ‹ሀገር ማለት የሆነ መሬት አይደለም፡፡ ታሪካዊ መሬት ነው› ብለው ተቃወሙት፡፡ ሀገር ማለት የሆነ መሬት ብቻ ቢሆን ለአይሁድ ከዛሬዋ እሥራኤል ይልቅ በአየር ንብረትና በተፈጥሮ ማዕድን፣ ብሎም በአቀማመጥ ኡጋንዳ ትሻላቸው ነበር፡፡፡፡
ባድሜ ለምትባል ከጦርነቱ በፊት ብዙው ሕዝብ ሰምቷት ለማያውቅ መሬት የተደረገውን ጦርነት የረሳ ሰው ነው ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚል፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለባድሜ የተደረገው ጦርነት ለማን የተደረገ ነው ሊባል ነው፡፡ በሄግ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክርስ የመሬት ክርክር እንጂ የሰው ክርክር ነበር እንዴ?
ሰውስ ስለ ሀገሩ ሲያነሣ ወንዙን፣ ተራራውን፣ ሸለቆውን፣ ሜዳውን፣ ጫካውን እያነሣ ለምን ይዘፍን ነበር ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ፡፡
‹ያገሬ ተራራ ወንዛ ወንዙ ለምለም
እማማ ኢትዮጵያ ኑሪ ለዘላለም› ለምን ይል ነበረ፡፡
ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ይሄ የኔ ክልል፣ ጎጥና መንደር ነው የሚለው ክርክር ከየት ይመጣ ነበር? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ የተለየና የታወቀ የሀገር ድንበርና ካርታ ለምን ያስፈልግ ነበረ? ሰውማ የትም ነው የሚኖረው፡፡ ካርታ አያሻውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለምን የአብዛኞቹ ሀገሮች ብሔራዊ መዝሙር ስለ መሬቱና ስለ ድንበሩ ያወራል? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለሰው ፓስፖርትና ቪዛ ለምን ያስፈልገዋል? ሰው ያለበት ቦታ ሁሉ ሀገሬ ስለሆነ ለምን እንደፈለግኩ አልገባም፡፡ አንድ ሰው ወደ አንድ ሀገር ገባ የሚባለው ወደ መሬቱ ሲገባ እንጂ የሀገሩን ሰው ሲያገኝ ነው እንዴ? ምናልባትም ከአንታርክቲካ በቀር ቪዛ መጠየቅ ያለበት ሀገር አልነበረም፡፡ እርሱ ሰው የለበትምና ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው አይመለከተውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ በሰማይ የሚሄድ አውሮፕላን ‹የአየር ክልሌን ጣሰ› ብሎ መሟገት ምን የሚሉት ሞኝነት ነው? ሰውን አልጣሰ፣ የጣሰው አየር ነው፡፡
ደግሞም አገር ማለት መሬት ብቻ አይደለም፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ አንታርክቲካ ሀገር ይሆን ነበር፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ በዓለም ላይ የሚገኙ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ሰው አልባ ደሴቶች(nonecumene) ‹ሀገር› ተብለው በተባበሩት መንግሥታት ይመዘገቡ ነበር፡፡ ሀገር ማለት መሬት ቢሆን ኖሮ መሬት ያለው ሁሉ ሀገር ይኖረው ነበር፡፡ የአሜሪካ ሕንዶች፣ የአውስትራልያ አቦርጅኖች፣ ከጥንት ጀምሮ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ የራሳቸው የሆነ ሀገር ግን የላቸውም፡፡ ደቡብ ሱዳናውያን የራሳቸው የሆነ የሚኖሩበት መሬት ነበራቸው፤ ሀገር ለመሆን ግን መዋጋት ነበረባቸው፡፡ ደቡብ ሱዳኖችን ያን ሁሉ ዘመን ያዋጋቸው የመሬት ጥያቄ ሳይሆን የሀገርነት ጥያቄ ነው። ያውም የራሳቸው ፖለቲካዊ መሬት አግኝተው እንኳን ሀገር ለመሆን ገና እየተሠሩ ነው፡፡ ፍልስጤማውያን ይብዛም ይነስ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ አገር ግን የላቸውም፡፡
አገር ከዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ሰው፣ ሰው የኖረበትና ታሪክ የሠራበት መሬት፣ ማኅበረሰብ ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከሰው፣ ሰው ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከመሬት፣ ሰው ከአራዊት፣ ሰው ከተፈጥሮ፣ ሰው ከወራሪ ጋር የነበረው ትግል፣ ውጊያና ወዳጅነት፤ የተረተው ተረት፣ ያወጋው ወግ፣ የፈጠረው አፈ ታሪክ፣ ያከማቸው ትዝታ፣ ሰው ለመሬቱ፣ ለወገኑና ለእምነቱ የከፈለው መሥዋዕትነት፤ የዘፈነው ዘፈን፣ ያቅራራው ቀረርቶ፣ የፎከረው ፉከራ፤ ያገኘው ድልና የተሸከመው ሽንፈት፤ ያደረሰው በደልና የደረሰበት በደል ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡
መገለጫው ቅርስ፣ መዋሐጃው ባህል፣ መታያው ልብስና መዋቢያው ጌጣጌጥ፣ መገናኛው ቋንቋ፣ መዝናኛው ጭፈራ፤ ማስተማሪያው ተረት፣ መክበሪያው ዓመት ባል፣ መጠበቢያው ምግብ፣ መቆዘሚያው እንጉርጉሮ፣ መተከዣው ልቅሶ፣ መተኪያው ልደት፣ ማሳረጊያው ቀብር፤ መገምገሚያው ምግባር፣ ማነወሪያው ነውር፤ መኩሪያ ጀግንነቱ፣ ማፈሪያ ገመናው፤ መደበቂያ ቤቱ፣ መመረሪያ ጫካው፤ ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡ ታሽቶ ተገርኝቶ ያመጣው አንድነት፣ ተጣልቶ ተባልቶ ያመጣው ልዩነት፣ እንደ ዘሐ ዘጊ የተጠላለፈው፣ እንደ እግር ሠንሠለት የተቆላለፈው፣ ሲፈተል፣ ሲገመድ፤ ሲባዘት፣ ሲዳወር፤ ሲከካ፣ ሲሰለቅ፤ ሲጣላ፣ ሲታረቅ፤ ሲያውቅና ሲማይም፤ ሲሠለጥንና ሲደኸይ፤ ሲሰፋና ሲጠብ፤ የኖረውና የኖረበት፣ የኖረለትም ነው ሀገር፡፡
ሀገር ትዝታ ነው፡፡ የትም ቦታ ስትሄድ ጠምዶ የሚያመጣህ፡፡ ምንም ሥጋ ብትቆርጥ ከብቱ ትዝ ይልሃል፤ ምንም ቢች ዳር ብትዝናና ወንዙ ትዝ ይልሃል፤ ምን በሽቱ ብትታጠን አፈሩ ይሸትሃል፤ ምን በሥጋጃ ላይ ብትሄድ ጉዝጓዙ ይመጣብሃል፡፡ በኮምፒውተር እየሠራህ ያቦካኸው ጭቃ ይናፍቅሃል፤ በጄት እየበረርክ አህያና በቅሎው ያምርሃል፤ ማንሐተን ተቀምጠህ ሰባተኛ፣ ሎንደን ተቀምጠህ ቂርቆስ፣ ኖርዌይ ሆነህ ጅግጅጋ፣ ካናዳ ሆነህ ሐረር ይወዘውዝሃል፡፡ ሀገር ማለት ትዝታ ነው፡፡
ሀገር ማለት ከምትገልጠው ብታስበው፣ ከምትኖርበት ብትሞትበት፤ ከምትስቅለት ብታለቅስለት የምትመርጥለት ነገር ነው፤ ሀገር ማለት ትተኸው ብትሄድ ትቶህ የማይሄድ፣ በራቅከው ቁጥር ልብህ ውስጥ የሚቀር፣ ባወቅከው ቁጥር የምትንገበገብለት፤ በተረዳኸው ቁጥር የምትሳሳለት፣ አንተን እርሱ ውስጥ እንደምታገኘው ሁሉእርሱንም አንተ ውስጥ የምታገኘው፤ የተሠራህበት ውሑድ፤ የተቀረጽክበት ማንነት ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመድ የሌለው ሰው ወደ ሀገሩ ለመምጣት ባልናፈቀ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመዶቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር ውጭ የሚኖሩለት ሰው ‹ሀገሬን ሀገሬን› እያለ መከራ ባላየ ነበር። ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰዎች በየዘመናቱ የበደሉት ሰው ሀገሬ በደለችኝ ባለ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰው ስለ ሀገሩ ሲያስብ ተራራውና ወንዙ፣ አዕዋፉና አራዊቱ፣ ማሳውና ቀየው ለምን ትዝ ይለው ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ያሸነፈ አትሌት፣ ድል ያደረገ ኳስ ተጨዋች ባንዴራው ሲሰቀል ለምን ያለቅስ ነበር?
‹አዙረሀ አዙረህ ሀገሬ መልሰኝ
በሹም ታዘዘ አፈር አታልብሰኝ› ብሎ ለምን ያንጎራጉር ነበር፡፡ ዐጽሙ በአፈሩ እንዲያርፍ ለምን ይናዘዝ ነበር፡፡ ለምን ሙሾውን፣ የሠርግ ዘፈኑን፣ ወጉን ማዕረጉን ይፈልገው ነበር፡፡
ሀገር በአርምሞ እንጂ በንግግር፣ በተግባር እንጂ በዝርዝር ሊናገሩለት የማይቻል ነገር ነው፡፡ ውጥንቅጥ ሰበዞች የሰፉት ሞሰብ፣ ዓይነተ ብዙ  ድርና ማጎች የሸመኑት ጋቢ፣ ልዩ ልዩ ቅመሞች የሠሩት ወጥ፣ ብዙ ገባሮች የፈጠሩት ዓባይ፣ ብዙ ትውልዶች የከመሩት ተራራ፣ ከአራቱ አቅጣጫ ተሰብስቦ በአንድ ወፍጮ የተፈጨ እህል፣ ከየአበባው ተቀስሞ በአንድ ቀፎ የተሠራ ማር፣  ከየእህሉ ወጥቶ በአንድ ማድጋ የተጠመቀ ጠላ፣ ከየ እንጨቱ ተለቅሞ በአንድ ጽንሐ የታጠነ ዕጣን ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ነው? እስኪ ሙት በለኝ!

13 Comments on “‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ! (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት )”

  1. Dani , weyane fet nesah ende ?

    ANTE ALNEBERK QEGN EJACHEW ?

    WEDET TEGA;TEGA ?

    TALAQU YE WEYANE CADRE MAN HONENA ?

    YANTE YE MENDER TUMERA AYASHANIM ABO ZOR BEL !!!

  2. አቶ ክብረት ሃገር ማለት ትዝታ ነው ያልካትን አባባል አልጋራም፣ “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚለውን የወያኔ አባባል እንደ መጋራት ነው። ሃገር ትዝታ ከሆነ ጂፕሲዎች በየሃገሩ ያላችው ትዝታቸው አገራቸው በሆነ ነበር፣ አራቅቃለሁ ብለው ከድጡ ወደማጡ ገብተዋልና ያርሙት። መቼም ይህ ገንቢ ሂስ ነውና እርማቶን መቀበሎን እንደሚያሳዉቁን በቀርቡ እጠባበቃለሁ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ! መይሳው

  3. betam yemigermew comment yesetachihut ke tsihufu antsar sayhon daniel kemewded ena kemetlat antsar new enam atitbebu.endewm rezmobachu yanebebachihut aymeslegnim.

  4. Dani be Memhir Girma lay

    yecharkew kibret ayntenim lefejih new

    weyane yehedal qerew Hizb new

    yemetal qen !!!

  5. የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 7 መመሪያ
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። ይሁን ና የነብዪን ቃል የፈረሱት አገሮች ተቀጥተዎል ለምሳሌ ሱማሊያ፣ኢራቅ፣ግብፅ፣ሊቢያ፣የመን፣ሰውዲ ፣አራን አሁን ደግም በቅርብ ቀን አልበሽር ተረኛ ነው። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
    1ኛ፣ ኢሕአዴግ ስላዬቸን ኤርትራዊ ናቸው እያላቸው እንደ ስደተኞቹ ለሌላው አላም በችግራችን ግዜ ደረሶቹን ወንድም ኤርትራዊያን ስም ማጥፋት ቀጥሏል። መረጃ ለወድ ኩሩ ለሆነው አቶ ኦባንግ መቶ አስተላልፈ፣ ትክክለኛ ስደተኞችን መርዳት ሲገባ የባለሥልጣናት ልጆች ስራቸውን ስለሚያቁ እየጎረፈ ነው።
    2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣል።
    3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ፣ ጠ/ሚ፣ የስውር ተሐድሶ መሪዎች በጋሻው፣ከቤተ ክህነት ወስጥ ባሉት ሰንሰለት ሌሎችን አባቶችን፣ ማሕበራትን፣ ጥሩ አገልጋዮችን በማግለል በአለፈው ሳምንት በብዙ ሚሊዮን ለመሸጥ እና አስመሳዩን ታቦት ለማስቀመጥ በስውር የጋኔን አምላኪዎች ጋር ተማምሏል። ባዶ ቀፎ ይዞ መጓዝ አይቻልም? ኢትዮጵያዊ ሁለ በግዜህ ተነስ፣ በቃ በቁመና ሞተናል ወሬ በቃኝ።
    አቡነ መርቆርዮስ እራሳቹን ወደ ውስጥ መመልከቻቹ አሁን ነው። የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን ለአንድነት ጥሪ መድረግ አለቦት። አለበለዚያ የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል!!!
    4ኛ፣ ማንም አስከ ዛሬ ያልቻለው የትግሉ አቀናጅ ማነው ብለው በአምቦ ክተ ት ላይ ነች። እኔ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ሰው አንዴ በዘር ፓለቲካ ይታለላል ግን ሁለተኛ ከደገመው ግራ የገባው ነው።
    5ኛ፣ ግራ የሚያጋቡትን የታሪክ አዎራዎችን አትመለከቱ ጊዜ የለም ህዝባችን እየተገደሉ እና ረሐብ ላይ
    ነን። የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ከዚያ በአዲሱ ህጉ መስረት ቋሚ መንግሥት ቢበዛ ለ 10 የሚያገለግል ይመረጣል። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር ተጠንቅቃቹ ጠብቁ። ወላ ዋይ ትውልድ መሆንን አቁማችሁ ፣ በአገር ወስጥ ከ10ኛ ክፍል ኢሐዲግ ተስፈህን ያጨለመብህ መሰደድን አቁመህ በአገርህ የትግሉ ወስጥ ተሳታፊ ሆነህ ቀጥል። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። በመተዛዘን ፣ በፍቅር፣ በአንድነት እንነሳ!!! ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው የሚያስፈልገው ለ1000 ኢሕአዴጎች ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ የአምቦ ንኡስ ኮር።

    [Reply]

    Reply

    Fekeru Tolcha says:

    March 26, 2016 at 10:47 pm

    Hero proud of u!!!!!!!!!!!!!!! we stand together Mote Lewyeana ena Le Faku Aba Mathis

  6. እጅግ ከባድ ሃሳብ ነው ያነሳኸው፡፡
    እውን ሀገር ማለት ምን ማለት ነው?
    ለእኔ ሀገር ማለት ህዝብ ማለት ነው፡፡
    ለእኔ ሀገር ማለት ወንዝ ተራራ መሬት ማለት አይደለም አለን መለስ ዜናዊ፡፡
    ከዚያም ጉደኛው መለስና ወያኔ ኢትዮጵያውያንን ሀገር አልባ አድርገው መሬቱን የባህር በሩን ታሪኩን ባህሉን ወዘተ ለባእድ ቸበቸቡት፡፡ምን ይህ ብቻ መለስ ከኢሳያስ ጋር ተመሳጥረው ለባድሜ መሬት ሲሉ ሊበቀሉት የፈለጉትን አማራ ከፊት አሰልፈው ከ70 ሺህ በላይ አስጨረሱት፡፡መለስና ወያኔ በሰው ፍቅር እንጂ በመሬት ፍቅር መቼ ይታሙና ነው፡፡አንድ ዌብ-ሳይት ላይ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ ወደ ታላቂቷ አዲስ አበባ እየተቀየረች ነው የሚል አነበብኩኝ፡፡እውነት ይመስላል፡፡ከእያንዳንዱ ሀብት ጀርባ ወንጀል አለ የሚባለው ለካ እውነት ነው፡፡ይህ አባባል ከምንጊዜም በላይ በዘመነ ወያኔ ግልፅ የሆነ አባባል ነው፡፡ዛሬ ግን ከእያንዳንዱ ወንጅል ጀርባም ሀብት አለ ለማለት ያስደፍራል፡፡ወያኔ በ17 ዓመት የነፃ-አውጪ ጦርነት ዘመኑ የሰው ህይወት ቸበቸበ ኤርትራን ቸበቸበ የባህር በራችንን ቸበቸበ መሬታችንን ቸበቸበ ታሪካችንን ቸበቸበ ቅርሳችንን ቸበቸበ ሃይማኖታችንን ቸበቸበ ኢትዮጵያውያን ሴቶቻችንን ለዘመናዊ ባርነት(ግርድና) አረብ ሀገር ቸበቸበ በጉዲፈቻ ሽፋን ህፃናትን ለውጪ ሀገራት ካኒባሊስቶችና ለፔዶፊሊያ ሳታኒስቶች ቸበቸበ በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን እንደ ጉድ ቸበቸበ፡፡በዘመነ ወያኔ ምን ያልተቸበቸበ ነገር አለ፡፡ከዚያም ኢትዮጵያዊ ሀገር አልባ እንዲሆን ተደርጎ በስደት በድህነት በርሃብ በበሽታ በድንቁርና በአደንዛዥ-ዕፅ በጫት በግብረሰዶም በዝሙትና በአጠቃላይ በሞራል ውድቀት ትውልዱ ተኮላሽቶ ተስፋ ቢስ ሆኖ እንዲሰቃይ ተደረገ፡፡ሀገር የውክልና ቅኝ ግዛት ውስጥ ወደቀች፡፡ከዚያም የሀገርና የህዝብ ችብቸባው የውጪ እርዳታና ብድር ተጨምሮበት አዲስ አበባ ላይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መቀሌ ውስጥ ደግሞ ፎቅና ፋብሪካ ተገነባ፡፡ወያኔም ታላቂቷን ኢትዮጵያን በዘር ክልል ከፋፍሎና እርስ በርስ አናክሶ ሲያበቃና ወደ ታላቂቷ አዲስ አበባ ቀይሮ እንካችሁ አዲስቷን ኢትዮጵያን እዩልኝ አለን፡፡ገበያ ሲደራ የሚባለው ለካ እንደዚህ ነው፡፡ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ የቃብድ ብር እየተቀበሉ የሚጠፉ ነጋዴዎች በርክተዋል አሉ፡፡ወያኔም ኢትዮጵያን ቃብድ ተቀብሎባት ሸጧት እንዳይሄድ ቦሌ ላይ ጥበቃው ቢጠናከር ጥሩ ነው፡፡እንግዲህ የ11 በመቶው የኢኮኖሚ እድገት ውጤት ይህ ነው፡፡ከ20 ሚሊዬን ህዝብ በላይ በርሃብ እየተሰቃየ እንደ ቅጠል የሚረግፍባት የጉድ ሀገር፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አዲስ አበባ ውስጥ ቤትና ቦታ ከመግዛት ይልቅ ገነት ወይንም መንግስተ-ሰማያት ውስጥ ቦታ መግዛት ይቀላል ነው የሚባለው፡፡ሀገርና ሰው እረከሰ መሬት ተወደደ፡፡ለካ ሀገር ሲረክስ ሰውም ይረክሳል ማለት ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ አያት ቅድማያቶቹ መስዋእትነት የከፈሉበትን መሬትና ሀገር ተቀምቷል፡፡እድሜ ለወያኔዎች ሀገር የሚባለውን ትልቅ ፅንሰ-ሃሳብ አጥፍተውታል፡፡ዛሬ ሀገር ማለት መንገድ ፎቅ ባቡር መኪና ሸቀጣ-ሸቀጥ አርሰናል ማንቸስተር ወዘተ ሻል ካለ ደግሞ ሀገር ማለት ብሄር-ብሄረሰብ ወይንም ዲሞክራሲ ማለት ነው፡፡በዘመነ ወያኔ ለብዙሃኑ ሀገር ማለት ትርጉሙና ፋይዳው ከዚህ የዘለለ አይደለም፡፡ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የሀገርንና የነፃነትን ትርጉምና ፋይዳ ላለፉት 25 ዓመታት ያክል ብዙም አያውቁትም ነበር፡፡ብኩርናውን ለምስር ወጥ እንደሸጠው ኤሳው እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገርንና ነፃነትን ለሸቀጥና ለሌላም ሌላም የማይረባ ነገር ለውጠነዋል፡፡የሀገርና የነፃነት ትርጉምና ፋይዳው የሚገባን ስናጣው ብቻ ነው፡፡ምክንያቱም ጦርነትን ያላየ የሰላምን ዋጋ አያውቃትምና፡፡ስለዚህም ሀገራችንን እና ነፃነታችንን መልሰን ለማግኘት ውድ ዋጋ መክፈል አለብን፡፡በቀላሉ ሊገኝ አይችልም፡፡አያት ቅድመ-አያቶቻችን ለሀገርና ለነፃነት ሲሉ የከፈሉትን ውድ የህይወትና ሌላም መስዋእትነት ዋጋ አቃለነዋል፡፡ዛሬ ለእኛ ሀገር ማለት ከምንዝናናበት ሆቴልና ካፍቴርያ ወይንም ከምንነዳው አውቶሞቢል የተለየ ነገር አይደለም፡፡አሳፋሪ ዘመን ነው፡፡
    ይህ ትውልድ ሀገርና ነፃነት አይገባውም፡፡ደግሞም ሀገርና ነፃነትን ይገባኛል ካለ በውድ ዋጋ ይግዛት፡፡ዝም ብሎ በነፃ የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ከውጪ የፈረንጅ እርዳታ ማግኘት እንደ መብት የሚቆጠርበት ዘመን፡፡ለምንድን ነው ከውጪ እርዳታ ማግኘትን እንደ መብት የቆጠርነው?ፈረንጆቹ የሚረዱንስ እውን ለምንድን ነው? እውን ለእኛ ብለው ነው? ነው ወይንስ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ በርካሽና በነፃ የሚሰጥ ነገር ይወዳል ማለት ነው?ወያኔዎች ከውጪ ባገኙት እርዳታና ብድር አዲስ አበባ ላይ ፎቅ ገነቡበት መቀሌ ላይ ፋብሪካ ገነቡበት የቢሊዬን ዶላር ካምፓኒ ኢፈርትን ገነቡበት ሌላም-ሌላም ነገር አደረጉበት የተቀረው ኢትዮጵያዊ ግን ማንነቱን ክብሩን ሀገሩንና ነፃነቱን ተቀማ፡፡በዘመነ ወያኔ ያለው እድገት ከወጪ ቀሪ ሂሳቡ ሲወራረድ ይህንን ይመስላል፡፡ወያኔ የኢትዮጵያን ገበሬ በሴፍቲ ኔት እንደ ራሱ የውጪ እርዳታ ጥገኛና ለማኝ አደረገው፡፡ዛሬ የኢትዮጵያ ገበሬ በርሃብ እንዲያልቅ የተደረገው ሆነኝ ተብሎ ነው፡፡
    የኢትዮጵያ ገበሬ ሀገሩን የሚመግብ የሰብል እህል ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መንገድ ጫት ቡና ወዘተ ብቻ የንግድ ምርት እንዲያመርት ተደረገ፡፡ግብርናው የተዋቀረው ለወያኔ ዝርፊያና አፈና በሚመች መንገድ ሆነ፡፡በአጠቃላይ ሀገርና ነፃነት የሚባለው ትልቅ ቁም-ነገር ቢዝነስ በሚባል ነገር እየተተካ የመጣ ይመስላል፡፡በእርግጥ ለተራ ቢዝነስ የሸጥነውን ሀገርና ነፃነት ምን ያህል ቢዝነስ ሰርተን መልሰን እንደምናገኘው አላውቅም፡፡እውን ሀገር ማለት ሰው ነው?ብሄር በሄረሰብ ማለት ነው? ዲሞክራሲ ማለት ነው?የፖለቲካ ፓርቲ ማለት ነው? ሃይማኖት ታሪክና ባህል ነው?እቁብ እድር ሰርግ ማህበር ሰንበቴ ተዝካር ለቅሶ?እናት አባት እህት ወንድም ባል ሚስት ልጅ ነው?አርሰናል ማንቸስተር ጊዮርጊስ ቡና ማለት ነው ?ወይንስ ግኡዝ የሆነ መሬት ወንዝ ተራራ ሸለቆ ፎቅ መንገድ መኪና ባቡር? ነው ወይንስ ነፍስ ወይንም መንፈስ ያለው ነገር ነው?በእውነት ሀገር ማለት ምን ማለት ነው?ምናልባት ሀገር የሚባለው ትርጉሙ በደንብ የሚገባን ስናጣው ይመስለኛል፡፡ስለዚህም ትርጉሙ እንዲገባን ከእጃችን ወጥቶ እንጣውና ትርጉሙ ሲገባን መልሰን ውድ ዋጋ ከፍለን እናግኘው፡፡ጨረስኩ፡፡

  7. ሀገር በአርምሞ እንጂ በንግግር፣ በተግባር እንጂ በዝርዝር
    ሊናገሩለት የማይቻል ነገር ነው፡፡ ውጥንቅጥ ሰበዞች የሰፉት
    ሞሰብ፣ ዓይነተ ብዙ ድርና ማጎች የሸመኑት ጋቢ፣ ልዩ ልዩ
    ቅመሞች የሠሩት ወጥ፣ ብዙ ገባሮች የፈጠሩት ዓባይ፣ ብዙ
    ትውልዶች የከመሩት ተራራ፣ ከአራቱ አቅጣጫ ተሰብስቦ በአንድ
    ወፍጮ የተፈጨ እህል፣ ከየአበባው ተቀስሞ በአንድ ቀፎ የተሠራ
    ማር፣ ከየእህሉ ወጥቶ በአንድ ማድጋ የተጠመቀ ጠላ፣ ከየ
    እንጨቱ ተለቅሞ በአንድ ጽንሐ የታጠነ ዕጣን ነው ሀገር፡፡
    ሀገር ማለት ሰው ነው? እስኪ ሙት በለኝ! በርታ!!!

  8. Dn Daniel, you are a very good writer. I do appreciate what you’re doing to our country and these people.Please keep it up.

  9. Dani Ene ye aniten tsifoch benabebiku kutur hulu menfase yitadesal ewunete nw milih Geta abizito ewuketunina tibebun yisitih kelali ayidelam sila ager guday gize satito yihen hulu tsihuf mesehaf
    Tnk you Dani may God Bless u more .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*