ሚኒስትሩ የሚመሩትን መ/ቤት የመንግስት ሕንጻ ከነበረበት አስለቅቀው የራሳቸው የግል ሕንጻ እንዲከራይ አደረጉት:: (ሙስና እና ሽሙጥ)

ሚኒስትሩ የሚመሩትን መ/ቤት የመንግስት ሕንጻ ከነበረበት አስለቅቀው የራሳቸው የግል ሕንጻ እንዲከራይ አደረጉት::

[ሙስና እና ሽሙጥ = ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን አስጠሩት]
–    እየተከታተልክ ነው ለመሆኑ?
–    ምኑን ክቡር ሚኒስትር?
–    ቴሌቪዥን ነዋ፡፡
–    በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ምን አሰብክ ታዲያ?
–    በጣም አስፈሪ ነገር ነው፡፡
–    ምኑ ነው የሚያስፈራው?
–    ትራምፕ ነዋ፡፡
–    ትራኩ ነው ያልከኝ?
–    የአሜሪካኑ ትራምፕ ነው ያስጨነቀኝ ስልዎት፡፡
–    እኔ ደግሞ የዩሮ ትራኩ ጉዳይ ነው የሚያስጨንቀኝ፡፡
–    እኔ እኮ ወሬ ብቻ ይመስለኝ ነበር፡፡
–    ምኑ?
–    ክቡር ሚኒስትሩ ዩሮ ትራከር አላቸው ሲባል፡፡
–    ቢኖረኝ ምን ችግር አለው?
–    ያው ከየት ያመጡታል ብዬ ነው?
–    ከብዙ ቦታ ላመጣው እችላለሁ፡፡
–    ለነገሩ እርስዎ ብዙ ቦታ እንዳለዎት አውቃለሁ፡፡
–    ምን አልክ አንተ?
–    ማለቴ ሊያመጡበት የሚችሉበት ብዙ አቅም አለዎት ብዬ ነው፡፡
–    ዛሬ የፈለኩህ እንዴት አየኸው ልልህ ነው?
–    ምኑን ክቡር ሚኒስትር?
–    የሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር፡፡
–    በቴሌቪዥን ነዋ፡፡
–    ቀልዱን ተውና ቁምነገሩን አስቀድም፡፡
–    ሰው በጣም ተገርሟል ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    በምኑ ነው የተገረመው?
–    ኢሕአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋቱን በማመኑ ነዋ፡፡
–    ይኼ ምኑ ነው የሚያስገርመው?
–    ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋቱን ማመኑ ነዋ፡፡
–    እስከዛሬ አምኖ አያውቅም?
–    አዎና ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ለምን አምኖ እንደማያውቅ ታውቃለህ?
–    አላውቅም፡፡
–    አጥፍቶ ስለማያውቅ ነዋ፡፡
–    ምን አሉኝ?
–    አጥፍቶ አያውቅም፡፡
–    ለነገሩ አጥፍቶ የሚያውቀው ሌላ ነገር ነው፡፡
–    ምን?
–    መብራት፡፡
–    እ…
–    ውኃ፡፡
–    እ…
–    ኔትወርክ፡፡
–    ሌላስ?
–    አንዳንዴም የሰው ሕይወት፡፡
–    በል በል ሌላ ፖለቲካ ውስጥ አትግባ፡፡
–    ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ለማንኛውም አሠራራችንን መለወጥ አለብን፡፡
–    እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
–    ሁሉን ነገር በአዲስ መልኩ መጀመር አለብን፡፡
–    በአዲስ ሲሉ?
–    ሕዝቡ በጣም ተማሮብናል፡፡
–    እርሱማ ግልጽ ነው፡፡
–    ስለዚህ ሕዝቡን ማስደሰት አለብን፡፡
–    እኮ በምን እናስደስተው?
–    አዲስ ሕንፃ ውስጥ መግባት አለብን፡፡
–    ለምን ሲባል?
–    ሕዝቡ በደል በደል በሚሸት ሕንፃ ውስጥ ከዚህ በኋላ መገልገል የለበትም፡፡
–    እና ምን ይደረግ?
–    አዲስ ሕንፃ ውስጥ መግባት አለብን ስልህ፡፡
–    የትኛው ሕንፃ ውስጥ ነው የምንገባው?
–    የምንገባበትን ሕንፃ እኔ እጨርሰዋለሁ፡፡
–    የመንግሥት ሕንፃ ነው?
–    የግል ነው እንጂ፡፡
–    በኪራይ ክቡር ሚኒስትር?
–    አዎና የግል ሴክተሩን እኮ ማበረታታት አለብን፡፡
–    እና ከመንግሥት ሕንፃ ወጥተን ወደ ኪራይ እንግባ እያሉ ነው?
–    ለሕዝቡ ሲባል የማይደረግ ምንም ነገር የለም፡፡
–    ለማን አሉኝ?
–    ለሕዝቡ፡፡
–    ለእርስዎ ማለትዎ ነው?
[ክቡር ሚኒስትሩ ለምሳ ቤታቸው ሲሄዱ ሚስታቸውን አገኟቸው]
–    ምነው ደስ ያለህ ትመስላለህ?
–    እንዴት አልደሰት?
–    እኮ ምን ተገኘ?
–    ያው አፉን ከፍቶ የነበረው ሕንፃችን ተከራይ ተገኘለት፡፡
–    ማን ሊከራየው ነው?
–    እኛ ነና፡፡
–    እናንተ ማን ናችሁ?
–    የእኛ መሥሪያ ቤት፡፡
–    ምን?
–    አዎን ሁሉን ነገር ጨርሼዋለሁ፡፡
–    ለምንድን ነው ቢሮ የምትቀይሩት?
–    በአዲስ መንፈስ ሥራ መጀመር አለብና፡፡
–    ያላችሁበት የመንግሥት ሕንፃ አይደል እንዴ?
–    ቢሆንስ?
–    ታዲያ ከዛ ወጥታችሁ ወደ ግለሰብ ሕንፃ ልትገቡ?
–    ምን አለበት?
–    ለነገሩ ከመንግሥት ሕንፃ ወደ መንግሥት ባለሥልጣን ሕንፃ ነው የገባችሁት፡፡
–    አመጣሽው ጨዋታውን፡፡
–    ያን ያህል ልዩነት ያለው አይመስለኝም፡፡
–    ያው ነው ስልሽ፡፡
–    የእኔ ሥራ ብቻ ተቀዛቅዟል፡፡
–    የትኛው ሥራሽ?
–    የፈርኒቸሩ ሥራ ነዋ፡፡
–    ለእሱም ቢዝነስ ሥራ አግቼልሻለሁ፡፡
–    ምን ተገኘ?
–    አዲሱ ሕንፃ ውስጥ ስንገባ አዲስ ፈርኒቸር ያስፈልገናል፡፡
–    የድሮዎቹ ምን ሆኑ?
–    ወንበሮቹ ራሳቸው ግፍ ግፍ ይሸታሉ፡፡
–    ታዲያ ወንበሮቹ ሳይሆኑ ወንበሮቹ ላይ የተቀመጡት እኮ ናቸው ግፈኞቹ፡፡
–    ቢሆንም ሕዝቡ በእነዚህ ግፈኛ ወንበሮች ከዚህ በኋላ መገልገል የለበትም፡፡
–    እኔማ ደስ ነው የሚለኝ፤ ቢዝነስ አገኘሁ፡፡
–    ስለዚህ ተዘጋጂ፡፡
–    ስለእሱ አታስብ፡፡
[ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ሲገቡ አማካሪያቸውን አስጠሩት]
–    አቤት ክቡር ሚኒስትት፡፡
–    አንድ ሐሳብ መጥቶልኝ ነው፡፡
–    የምን ሐሳብ?
–    አዲሱ ቢሮ ስንገባ አዲስ ፈርኒቸር መግዛት አለብን፡፡
–    ምን?
–    ሁሉን ነገር በአዲስ መንፈስ መጀመር አለብን ስልህ፡፡
–    ፈርኒቸሮቹ ከተገዙ እኮ ስድስት ወራቸው ነው፡፡
–    ስማ ቢሆኑም ሕዝቡ በእነዚህ ግፈኛ ወንበሮች መገልገል የለበትም፤ መቀየር አለባቸው፡፡
–    መቀየርማ ያለባቸው ሰዎቹ ናቸው፡፡
–    ሰዎቹን መቀየር ከባድ ስለሆነ ወንበሮቹን ብንቀይራቸው ይሻላል፡፡
–    ሕዝቡ እኮ የተማረረው በወንበሮቹ ሳይሆን በሰዎቹ ነው፡፡
–    አየህ በወንበሮቹ ጀምረን በሰዎቹ እንቀጥላለን፡፡
–    ለማንኛውም የሰዎቹን ቅያሬ ስንጠብቅ ቀኑ እንዳይደርስብን፡፡
–    የምኑ ቀን?
–    የምፅዓት ቀን!
[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ቢሯቸው ገባች]
–    ጠዋት የት ሄደሽ ነው?
–    አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ታዲያ አታስፈቅጂም እንዴ?
–    ስልክዎትን ብለው ብለው አልሠራ አለኝ፡፡
–    ሞክረሽልኝ ነበር?
–    በጣም ብዙ ጊዜ ነው የሞከርኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    አየሽ ሌላም ሰው ቢፈልገኝ አልገኝም ማለት ነው፡፡
–    ለእኔ አልሠራልኝም ነበር፡፡
–    ሕዝቡ የሚማረረው እኮ እንደዚህ እየሆነ ነው፡፡
–    እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
–    ስልኬ በአዲስ መቀየር እንዳለበት ገብቶኛል፡፡
–    እ…
–    አዲስ አይፎን ያስፈልገኛል፡፡
[ክቡር ሚኒስትሩ የአይቲ ክፍል ኃላፊውን አስጠሩት]
–    አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
–    ሕዝቡ ምን ያህል እየተማረረ እንደሆነ ታውቃለህ አይደል?
–    በጣም ተማሯል፡፡
–    ሕዝቡን እኔን ሊያገኘኝ አልቻለም፡፡
–    ቢሮ መቼ ተቀምጠው ያውቃሉ?
–    ቢሮ ባልቀመጥም ቢያንስ በስልክ ሊያገኘኝ ይገባል፡፡
–    ስልክዎትን የሚያውቀውማ ይደውልልዎታል፡፡
–    የማያውቀውም ቢሆን ቢያንስ በኢሜይል ሊያገኘኝ ይገባል፡፡
–    ታዲያ ለምን አያገኝዎትም?
–    አየህ ኮምፒዩተሮቻችን አሮጌ ናቸው፡፡
–    እ…
–    አሁን አዲስ ሕንፃ ውስጥ ስለምንገባ ሁሉንም በአዲስ ኮምፒዩተር መተካት አለብን፡፡
–    ክቡር ሚኒስትር አሁን ያሉት ኮምፒውተሮች እኮ ከተገዙ ገና ስድስት ወራቸው ነው፡፡
–    ስማ ቴክኖሎጂው እኮ በየጊዜው ነው የሚቀያየረው፡፡
–    እ…
–    ስልኮቻችንም በአዲስ መቀየር አለባቸው፡፡
–    ጨረታ ይውጣ?
–    ቢሮክራሲ አያስፈልግም፡፡
–    ምን?
–    እኔ እጨርሰዋለሁ፡፡
[ክቡር ሚኒስትሩ የኮምፒዩተር ቢዝነስ የሚሠራው ወንድማቸው ጋ ደወሉ]
–    አቤት ጋሼ፡፡
–    የት ነው ያለኸው?
–    ካርታ እየተጫወትኩ ነው፡፡
–    አንተ ልጅ ይኼ ካርታ ሱስ ሆነብህ አይደል?
–    ያው በዘር እኮ ነው ሱስ የሆነብን ጋሼ፡፡
–    እኔ የት ነው ካርታ ስጫወት ያየኸው?
–    ያው አንተ በመሬት ካርታ ነዋ የምትጫወተው፡፡
–    ለማንኛውም አሁን ሥራ አግኝቼልሃለሁ፡፡
–    የምን ሥራ ጋሼ?
–    ለቢሯችን ሙሉ ኮምፒዩተር እንድታቀርብ፡፡
–    እየቀለድክ ነው ጋሼ?
–    የምን ቀልድ ነው? እውነቴን ነው፡፡
–    ከስድስት ወር በፊት ነው እኮ ለሙሉ ቢሮው ኮምፒዩተር ያቀረብኩት፡፡
–    እና ይኼኛውን አትፈልገውም?
–    ኧረ እንደሱ ማለቴ አይደለም፤ በጣም ደስ ብሎኝ ነው፡፡
–    ምኑ ነው ደስ ያለህ?
–    በቃ በዚህ ሥራ ሕንፃዬን እጨርሰዋለሁ ብዬ ነዋ፡፡
–    ሕንፃህንም ተጨማሪ ቦታ ስለሚያስፈልገን መከራየታችን አይቀርም፡፡
–    አንጀት አርስ ነህ ጋሼ፡፡
[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ ስብሰባ ተጠርተው ሄዱ፤ ሳያስቡት መገምገም ጀመሩ]
–    ክቡር ሚኒስትር ከብልሹ አሠራርዎት ሊታቀቡ አልቻሉም፡፡
–    እናንተ ከእኔ ውጪ ሰው አይታያችሁም እንዴ?
–    ይኸው ባለፈው ተገምግመው አሁንም ያው ነዎት፡፡
–    ምን አደረግኩ?
–    ይኸው አዲስ ሕንፃ ውስጥ ካልገባን እያሉ ነው፡፡
–    በአዲስ መልክ ሥራ መጀመር ስላለብን ነዋ፡፡
–    ደግሞ ሕንፃው የእርስዎ ነው አሉ?
–    በተመጣጣኝ ዋጋ እስካከራየሁት ድረስ ምን ችግር አለው?
–    እ…
–    ፈርኒቸሮቹንም ቢሆን በአገር ዋጋ ነው የምናቀርበው፡፡
–    ሌላስ?
–    ኮምፒዩተሮቹም ቢሆኑ ሌተስት የሆኑት እኛ ጋ ስላሉ ነው፡፡
–    ወይ ቅሌት፡፡
–    ይህንንም ያደረግነው ሥራችንን በአዲስ መንፈስ ለመጀመር ነው፡፡
–    እርስዎም በአዲስ መልክ ጀምረውልኛላ፡፡
–    ምኑን?
–    ሌብነቱን!

7 Comments on “ሚኒስትሩ የሚመሩትን መ/ቤት የመንግስት ሕንጻ ከነበረበት አስለቅቀው የራሳቸው የግል ሕንጻ እንዲከራይ አደረጉት:: (ሙስና እና ሽሙጥ)”

  1. ይህን መሰል ዝርፊያ በተለይ ቁጥር አንድ ዘራፊ ህንፃዎችን በመከራየት ጉምሩክ ገቢዎች ኢትዬ ቴሎኮም ግንባር ቀደም ናቸው።

  2. No news about jawar siraj mehamod al abyssinia, ajrie he may be gathering arms from turky in somali as his grand father gragn ahmed.
    The silence may grow into big storm that wipeout tgrai woyane from abyssinia-habasha.

  3. No news about jawar siraj mehamod al-abyssinia, yhienie ajrie, he may be gathering arms from turky in somali as his grand father gragn ahmed.
    The silence may grow into big storm that wipesout tgrai woyane from abyssinia-habasha.

  4. አዳሜ ወያኔ እንዲህ በቀላሉ ይወርድልናል ብላችሁ በማሰብ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ይቅርታ ንግግር ገርሟችሁ ብት ዝናኑ፣ ወዮላችሁ፣ ያኔ ወያኔ የፈታውን ቀበቶ እያጠበቀ እንደሆነ ማን በነገራችሁ።
    የኦሮሞ ህዝብ ሞቶልን እኛ ነጻ እንወጣለን ከሆነ ተሳስታችኋል፣ እያንዳንዱ የድርሻውን ማበርከት ወቅታዊና ሃገራዊ ግዴታው መሆኑን ማወቅ አለበት።
    ወያኔን ፋታ እንዲያገኝ ማድረግ የመከራ ዱላን ማብዛት መሆኑን ተገንዝበን ኃይላችንን አንድ ላይ እናንሳ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*