ታደሰ ሲሳይ ሥልጣነ ክህነቱን ከተገፈፈ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ
የአሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ ሐመረኖህ ኪዳነ ምሕረት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን እንደ ግል ንብረቱ በመያዝ በዕብሪት አብጦ ያሻውን የሚያደርገው ታደሰ ሲሳይ ሥልጣነ ክህነቱን ከተገፈፈና ከተወገዘ ሁለት ዓመታት እንዳለፉት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህ ግለሰብ የፈጸመው ዝሙት በማስረጃ ስለተረጋገጠ ከሁለት ዓመታት በፊት ሥልጣነ ክህነቱን የተገፈፈ ቢሆንም አሁንም ከአውደ ምህረት ላይ አልወርድም ብሎ ሙጭጭ ብሎ ይገኛል። ግለሰቡ ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቀኖና ውጭ በግል ስሙ እንደ ንግድ ተቋም አስመዝግቦ በያዘየው ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያፍሰውን ገንዘብ ካለምንም ተአቅቦና ይሉኝታ የዝሙት ጥማቱን እየተወጣበት እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ። ታደሰ ከጥፋቱ እንዲመለስና ንስሐ እንዲገባ የቀረበለትን ጥሪና መማጸን ከምንም ባለመቁጠር በአሜሪካን አገር ውስጥ ያለውን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን በፓስተሮች ብቸኛ ቁጥጥር የመምራት አሰራር በሐመረኖህ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ በማምጣት እራሱን የማይጠየቅና የማይወቅስ ንጉስ አድርጎ ሾሟል።

በተለይም አንዲት ባለትዳርና የልጆች እናትን በውሽማነት በመያዝ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ከአንድ ካህን የማይጠበቅ ዝሙት መፈጸሙን የሴትየዋ የቀድሞ ህጋዊ ባለቤት የነበሩት ሰው ባቀረቡት ማስረጃ አረጋግጠዋል። ከዚህም በተጨማሪም እንደ ሰፈር ተልከስካሽ ውሻ በፍትወት ስካር ያበደው ታደሰ ሲሳይ ከሌሎችም ሴቶች ጋር ዝሙት እንደሚፈጽም ነቀፋዎችና ትችቶች በተለያየ ጊዜ ሲቀርብበት ቆይቷል።ሆኖም ሰውየው በተደጋጋሚ ተመክሮ ሊመለስና ንስሃ ሊገባ ባለመፈለጉ ምክንያት እንደተወገዘ ይታወሳል። አንዳንድ ሰዎች ሲያወሩ እንደተደመጡት ሰውየው አሜሪካን ከመምጣቱ በፊት ጭራሹን ካህን አልነበረም፣ እንደውም ወያኔ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከመበተኑ በፊት በውትድርና አገልግሎት ላይ የነበረና መጠሪያ ስሙ “ሲሳይ ታደሰ” እንደነበረና አሜሪካ ሲመጣ አዘዋውሮ “ታደሰ ሲሳይ” በማለት መጠራት እንደጀመረ ይናገራሉ።
በአቶ ታደሰ ሲሳይ ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት ውግዘቱን ያወጁት ካህናት የካንሳስ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣የዋሽንግተን ዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሳዬና የቨርጂኒያ የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ኃይለ ሚካኤል ተከለኃይማኖት ናቸው። የውግዘቱ ሥነ ሥርዓት የተካሄደው በሕዝብ ፊት ሲሆን ይህንኑ ጉዳይ እንዲከታተል ከዚህ በፊት የተቋቋመው ኮሚቴ አባላትና ከተለየዩ አድባራት የመጡ ምዕመናንም ተገኝተው የነበረ መሆኑአይዘነጋም።
አቶ ታደሰ ሲሳይ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. (ማርች 9, 2014) ስልጣነ ክህነቱ የተሰረዘና ወደ ተራ ምዕመንነት የወረደ መሆኑ ቢገለጽም በማን አለብኝነትና በዕብሪት አሁንም ቤተክርስቲያንን ማርከሱን ቀጥሎበታል። ታደሰ ሲሳይ እንደግል ንብረቱ የፈለገውን የሚያደርግባት የቨርጂኒያ ሐመረኖህ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ ከምዕመናን የሚመነትፈውን ገንዘብ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመርጨት ጉቦ ከፍሎ በገዛው የምንኩስና ማዕረግ አሁንም ውንብድናውን ሳያፍርና ሳይሸማቀቅ ቀጥሎበታል።ይህንን ለትውልድ ሲያስጠይቅ የሚኖር በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ የተሰራ ወንጀል ኢትዮጵያ ድረስ ሰንሰለት በመዘርጋት በግምባር ቀደምትነት ተባባሪ የሆኑት በቀላማጅነታቸውና በአወናባጅነታቸው የሚታወቁት አባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) ናቸው።
በአቡነ ማትያስ የሚመራው “ሲኖዶስ” ቢያንስ ሚስቱን በአቶ ታደሰ የተነጠቀውንና ልጆቹ ካለ እናት እንዲያድጉ የተፈረደባቸውን ልጆች የእምባ ድምጽ በመስማት ትክክለኛ ፍርድ መስጠት ሲገባው ቀድሞ በሌሎች ሶስት ካህናት በምዕመናን ፊት የተወሰነውን ውግዘት እንኳ ለማጽናት ወኔው ከከዳው ሁለት ዓመታት አለፉ። የአቡነ ማትያስ ሲኖዶስ በዚህም ምክንያት በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 20 ቁጥር 28-30 የተጻፈው እየመሰከረባቸው እንደሆነ ለመገንዘብ አያዳግትም። “……..በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና

ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።…”

የታደሰን ጉዳይ ጠንቅቃችሁ እያወቃችሁ አባ መላኩንና ወያኔን ላለማስቀየም ወይም ኢትዮጵያ ከመመላለስ ያግደናል ብላችሁ እውነተኛውን ነገር ከመመስከር የተለጎማችሁ ካህናት አሁንም አልመሸባችሁምና የውግዘትና የተቃውሞ ድምጻችሁን አሰሙ እየተባላችሁ ነው። ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን በሊቢያ በረሃ ስለ ክርስቶስ ፍቅር መራራውን የሞት ፅዋ በጸጋ ሰማዕት ሆነው ለመላው ዓለም ሲመሰክሩና የክርስትናን ሰንደቅ ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ እያያችሁ እናንተ ግን በጣም ትንሹን መስዋዕትነት እውነቱን መመስከር እንዳትችሉ የስጋችሁ ገመድ አስሯችሁ እስከ መቼ ነው የምትቀጥሉት??? ክርስትና የማይጨበጥና የማይዳሰስ ፅንሰ-ሀሳብ አይደለም። ክርስትና በሁሉም መንገድ የሚገለጽና ጽናትን የሚጠይቅ እንዲሁም መስዋዕትነትንና ተግባርን የሚጠይቅ ሐይማኖት ነው። ክርስትና እውነቱን ተናግሮ የመጣውን የሚቀበሉበት እንጅ ተመሳስሎና ተቀላቅሎ የሚኖሩበት ዓለማዊ ገበያ አይደለም። ስለሆነም ከሁለት ሽህ ዓመታት አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ታላቅ መስዋዕትነቶች እየተከፈሉባት ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ ቁርጠኛና ጠንካራ አባቶችን የምትፈልግበት ሰዓት አሁን ነው። ለቤተክርስቲያኒቷ መደረግ ያለባቸው አስተዋጽኦዎች ገቢራዊ መሆን የሚገባቸው አሁን እንጅ ይዋሉ፣ ይደሩ የሚባሉ አይደሉም። ከሁለት ዓምታት በፊት የታወጀውን ውግዘት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የቀድሞው ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ ሥልጣነ ክህነታቸውን ተገፈፉ
egzio meharene kiristos !!!!!
ABETU Hizbihin adin ristihin bark
amen
Why don’t people boycott this con man? People who go to him and give him money are responsible for aiding and abetting a criminal. In my opinion people who go to this disgraceful person are irresponsible and can not call themselves Christians.
አቶ ታደሰ በሽታ ሆኖበት ነው የሚያሳዝነው የጳጳስ ተብየው ነው ክርስትናውን በገንዘብ እየቸረቸረ ያለው እነሱም እንደሰው መሞታቸው ቀርቶ መቀመቅ መውረዳቸው አይቀርም። ታደስ በዚህ ብቻ አላቆመም ንስሀ አባት ሁነኝ ብላ የተጠጋችውንም ሴት እንደለመደው ደፍሮአት አገር ይያዝልኝ ስትል በድንጋጤ ፈርጥጦ ኢትዮጵያ ሄዶ ተደብቆ ከጥቅም ተካፋዮችዋ አንድዋ የወያኔዋ ተላላኪ ቅድስት ተብዬዋ እና መቅደስዋ የአዝማሪው ሚስት ሁሉም ነገር በቁጥጥራችን ስር አድርገናል መምጣት ትችላለህ ስላሉት መጥቶ ይኸው እንደለመደው አውደምህረቱን መቀለጃ አድርጎታል መቼም ምን እንደሚያስነካችው ባይታወቅም ጎነተለኝ የማትል ሴት የለችም ለመሸፈኛ ግን ኪዳነምህረትን ብለን ነው የምንሄደው ታደስ እንደሆነ በብልግናው ቆሞስ ሆኖአል አሁንም እየደጋገመ የሚዘሙተው ጽጽስናን አላጣም ፋኑኤል እንደሆነ። ገንዘብ እስከሰጠሁት ድረስ ጽጽስና ያሰጠኛል ብሎ ያስባል። በነገራችን ላይ ተደፈርኩ ብላ ልታጋልጠው የነበረችውም ቀላማጅና አልያስ የድሮ ተሳዳቢው የታደሰ ሲሳይ አፍቀላጤ ገንዘብ ካልሰጠኸን እናጋልጥሀለን እያሉ ሲያስፈራሩት ነበር አሉ ከፍሎእቸው ይሆን እንዴ ድምጻችው የጠፋው የገንዘብ ችግር እንደሆን የለበት ሞኝ እያለ እሚጠራው ምእመን እስካለለት ድረስ እስቲ የምታውቁት ንገሩን። በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጽሁፍ ያቀረበውን በጣም መስገን እወዳለሁ ክርስትና ማለት እውነትን መመስከር ነው። ከዚህ በዝሙት ከሰከረ ሰው እጅ ሰጋ ወደሙ የምትቀበሉ ሰዎች እራሳችሁ የዝሙት ተባባሪ መሆናችሁን ልታውቁት ይገባል አብራችሁም አውደምህረት ላይ የምትቆሙና መቅደስ የምትገቡ ካሳሁን ወርቅነህና ሌሎችም ወዮላችሁ እንደ ውንብዴው ኤልያስ ቀን እየተጠበቀላችሁ ነው።
እግዚኦ የሚያሰኝ ነው ምነው የሚጠይቅም የለም እንዴ ወይ አሜሪካ እንዲህ ሃይማኖት የሚቀለድበት አገር ይሁን ዳሩ ቄሶቹ ምን ያድርጉ ህዝቡ እንደከብት እየተነዳላቸው የዘረፋው አይነት እኮ እሚደንቅ ነው እውነት ህዝቡ በዚህ ጽድቅ የሚገኝ መስሎት ይሆን? አገር አጥፊ ካድሬ ሁሉ ቀሚስ አጥልቆ መስቀል ይዞ ካህን ነኝ እያለ በሚዘርፈው ገንዘብ አትዮጽያ ፎቁን ይገነባል ሞኙ ሁለት ሶስት ሰራ እየሰራ ለፍቶ ያገኘውን ገንዘብ ከቤተሰቡ አፍ ነጥቆ ወስዶ ይገብራል።
http://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2014/12/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%89%A3-%E1%8D%8B%E1%8A%91%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%8C%A0-%E1%88%98%E1%8C%8D%E1%88%88%E1%8C%AB-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%A8%E1%88%A8%E1%88%BB-formated.pdf
የእብድ ገላጋይ ዱላ ያቀብላል አሁን ማን ይሙት የተወገዘው ቄስ ነኝ ባዩ አስተራየና በዲሲ ማርያም አስተዳዳሪ የነበረው በተለምዶ ዣን ቤዴል ቦካሳ እያሉ የሚጠሩት ቄስ ሆነው የካህን ስልጣን ወሳጅ እና ሰጭ የሆኑት እንዲያው ስው ሁሉ ነውሩን ሽጦ በልቶ የለም እንዴ!አረ እናንተ ማን ናችሁ ጳ
ጳሳት? ስለሰውዬው ሐጥያት አዋቂው እግዚአብሄር ነውና አጥፍቶም ከሆነም ይዘገይ ይሆን እንጅ ፍርድ አይቀርም።
የሚያሳዝነው ግን እኔ ምን እያደረግሁ ነው ብሎ ራስን ማየት አለመቻል ነው። ይልቁንስ ይህ ዓለም አላፊ ነው እኛ የምንሳሳለት የዘላለም ሰልጣን እና ማን አለብኝነትን በሕይወትና ሞት የምናጣው ስለሆነ ወደ ንስሀ ተመልሰን መኖርን የመሰለ ነገር የለም። ሰው ሆኖ ሁልጊዜ ስህተት አይጠፋምና።በተለይ በዲሲ ማርያም ያለው ሁኔታ በቅርብም ባልሆን አሳዝኖኛል በተቻለ ወደ ህሊናችን እንመለስ ። የሚጠፋው ገንዘብ ድሀዋ እንጀራ ሽጣ ታክሲ ሻንጣ ተሽክሞ ለማርያም የሰጠውን ገንዘብ እያሳዝናችሁም በርግጥ ምንም ላላወጣበት ምንም አይመስለውም ስለዚህ እባካችሁ ወደ ህሊናችን እንመለስ ጊዜው አሁን ነውና።
እግዚአብሔር የዕውነት አምላክ ይፍረድ።ቀሲስ አስቴርየ ፅየን በጣም የማከብራቸው አባት ናቸው።ብሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍርድ በዝች ምድር ሲፈጸም ይታያል።አንዳንድ ዚዜ ግን መሰሪ እና ቀጣፊ ሳይጋለጥ ከዚች ምድር ይሽኛል።ለማነኛውም የእግዚአብሔርን ፍርድ እንጠብቅ።የሚዘገንን ዓለም ውስጥ ነን ጎበዝ ! ! ! ! “በሰው የታመነ እርጉም ይሁን” የሚለውን አስታውሱ።አለዚያ ውስጣችሁን ትጎድላችሁ።
Jara = tesfa gebreb/tefa gebrebab
Please do some thing this stupid assole guys we are believer we should do some thing according to our religion if we have really proof
Mergerefee alebetee koshasha.
In fact this is Ksis Asteraye Tsige & Amare Kassaye propoganda and slandering strategy based on presonal interest however I do not apricated Abba Melaku reaction as if like the patriarch, I think he is excited and dreaming day and night to be the Patriarch. As fare as I know this man even the arcbishop is too much for him, he do not deserved to be honest. He is not educated enough even he doesn’t know daily WODASEMARIAM. I do not understand why people wanted to what actually they are not, this is pure Hiypocratic. this is 21st centrury the new generation can find out who is who by only reading our body laguage, look at Abba Melaku he is exactly wanted to be look like Abuna Palose, it is really shameless act. It is the matter of time we can not hid ourseves from the reality forever it is only temporary why that day come we have no where to go. Ever body knows Abba Melaku why he wanted pretended like that.
Amare Kasaye used to pretended like “Komos” , Doctor in Law and the all knowing preson in this world, at the end of the day what happened? he found an empty & nothing in his mind but all about money hiding himself in the shadow of so called Independant chuch.
Asteray Tsige no dout his well educated he can express what we are believing but he always used his knowledge wrong direction nither for the followers of the church nor for himself, non stop screamed like made Doge all his life pointless.
I salute Kesis Astreay Tsege, Abba Haile Mickaeal Tekle Haimanot and Kesis Amare Kassaye for taking this strong stand against Taddese Sisay. They are my heroes. They are taking the heat for doing the correct thing. However, Abbune Fanuel is covering and helping Taddese.
ሁሉም የ10ቱን ቃላት ህግ ያፈረሱ ናቸው አይደለም የሀይማኖት አባት በሀይማኖት የቆዩም አይመስሉም የሰሩት ስራ ዝሙትና ሌብነት አንድ ናቸው ወገኖቼ እኛ ግን በዝህ በጾም ሰአት ህዝባችንን እያሰብን ልንጸልይ ልናለቅስ ይገባናል እንጅ የእነሱን ሀጥያት እያሰብን በነሱ ሀጥያት የራሳችንን ነፍስ ባናጎድፍ ይሻላል ።
Please at least you guys respect each other don’t use bad words. God bless every body!
“ክርስትና” ብለው የጻፉ ሰው የተናገፉት በሙሉ ጸረ ክርስትና ነው። ትክክል የሚሰሩ አባቶችን መከተል አለብን ግን አጥፊዎችን መኮነንና ማወገዝ ይገባናል። በወንጌል ክፉውን ተጸየፉት ይላል። “..የእነሱን ሀጥያት እያሰብን በነሱ ሀጥያት የራሳችንን ነፍስ ባናጎድፍ ይሻላል” ያሉት በጣም አደገኛና ሃላፊነት የጎደለው አባባል ነው። ይህ አይነት አባባል ነው ለታደሰና መሰሎቹ የልብ ልብ የሰጣቸውና በወንጀላቸው እንዲቀጥሉ ሽፋን የሆነላቸው። የታደሰ ሲሳይን ሃጠአት ያሰበ ያለ አይመስለኝም። ዋናው ቁም ነገር ግን ታደሰ የካህንነት አገልግሎት ለማካሄድ ስልጣኑ ስለተሰረዘበት መወገድ አለበት ነው እየተባለ ያለው። ከቤተክርስቲያን እራሱን ቢያገል ማንም ስለሱ የሚያወራና እንቅልፍ ያጣ የለም። ታደሰ አሁንም ሴቶችን እያባለገና ቤተክርስቲያናችንን እያቆሸሸ ስለሆነ ይወገድ ነው እየተባለ ያለው። ይህ ደግሞ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ሃላፊነትና ግዴታ ነው የምለው።
Be yalachuhbet Tere-tgrai woyanie hunachuh tagelu, yechigrochachn mensea slehonetablen medemses alebn .
I’d like to see the proof. I listened to a cd that was distributed on the alleged accusations but only one person can be heard on the recorded cd. If the accused voice can be heard on the CD, it would be a solid proof but that is not the case. So, unless there is another proof that can be brought to light, that recording is useless. Yes he is divorced and now is a monk.
ይህ ብቻ አይደለም በየቤተክርስትያኑ የውስጥ በችግር የተወታተበ ነው ቀሲስ የታደሰ ብቻአይደለም
ቦካሳ:
Do agree that Tadesse divorced his wife in the state of North Carolina? If you have not read the divorce parers, it is available (it is public record).
I second Semu, does ቦካሳ agree that a divorced person could not be serving as a priest? In particular, if the priest got divorced not because of death or the wife has done immoral thing.
“ክርስትና” ና ‘ቦካሳ’ ያቀረቡት ደንበኛ የወያኔያው አገላለፅ ነው። ለምን ብትሉኝ: “ተደጋግሞ እንደተገነዘብነው ሁሉንም ካህናት የማይረቡና የተበላሹ አስመስሎ በማቅረብ፣ እንደውም እንያንዳንዳችን የተበላሸን ስለሆነ ዝም እንበል።” የሚል ድምዳሜ ነው።
ይህ ባጭሩ የሕብረተሰባችን የመከባበር ባህልና የፈርሀ እግዚአብሔር አስተሳሳብ ጨርሶ እንዲጠፋ አድርገዋል። ለዚህ ነው ታደሰ ስሳይም ሆነ ማንኛውም ሰው ችግር አለትና ቢያንስ ወያኔ ገንዘብ ያከፋፍላል። ተከተሉት” የሚል ነው።
ታደሰ ስሳይ ሚስቱን መፍታቱን የሚያውቀ ነው። አባ ፋኑኤል ቆሞስ ብለው የሾሙት ሳይመለኩስ ለ 8 ዓመት ያህል ሲቀድስ የነበር ።
ኮንዶሚኒያም ለሃብታም ወይስ ለድሃ? ማህበረሰብ ተው ወዳጄ እባክህ እራስህን አታታል በአንድ ኮንዶሚኒያም እንዳለ አንድ ባለሃብት ገዝቶት ነገር ግን አንዱ እድለኛ አልሽጥም ሲለው ባለሃብቱን በየቀኑ ከፍተኛ ገንዘብ በመጨመር ለማታለል እየሞከረ ነው
ሌላው የዐዲስ አበባ ኮንዶሚኒያም 35 በመቶውን ለኤትራዊያን በትዕዛዝ ተሰጥቶል ይሕን ያምናሉ በላስልጣኖች እድል የሚገባው ኢትዮጵያዊያን ወይስ ኤትራዊያን የውጭ ዜጋ የቤት ተጠቃሚ ያደረጋል በሕግ አምላክ ተውን ተውን ሲበሉ ሲያስበሉ ሲያሳድዱን እስከ መቼ?
ሃይሉ
(Maheder) Kesis Astray Tsega : You yourself were deferocked by His Holines Abuna Matias before he be came the patriarch, still you are performing your priesthood with no excuse. You and Amare in what authority able to defreocked Kesis Tadess? Priest do not have a mandate to defrocked a priest in the first place, of course if you have factual evidence you should have to reported to the Arcbishop or the patriarch only. If the arc bishop and the patriarch do not take action the only thing you can do is stopped performing service with that preson pariod.
Even if any priest defrocked by the arcbishop, no arcbishop allowed to reinstated his priesthood because they have balanced or equal mandate and authority, however if the priest appeal to the Patriarch or the Holy Synod with evidence Yes of course! the priest may can get back his priesthood depend the evidence he appealed with.
In my View you Kesis Asteray Tige and aka Amare Kassaye deserved to be defrocked more than Kesis Tadess because your are abolished the canonical church and established un canonical independant church instade in the name of EOTC called franchising trading, you are misleaded and misguided innocent believers for only presonal satisfactions. you are committed the worst crime in the history of EOTC than any others, You are encuraging devision and segerigation inside the Church by calling yourself stupied independent.
If Kesis Tadess divorced his wife or she left him in any presonal reason of course nothing protect him to be became a Monck. regarding about sexual relationship complinet with married or any other women, no one have any factual evidence against him and to prove exactly what happened, it is only exaggerated unintruptedly by Kesis Asteray & aka Amare Kassaye sound like presonal haters.
First of all who you are blaming some one live alone him God is justice!
Taddsess please, please enough is enough leave the church and go to a monastery and confess your sins and live as a layman not as a priest, because you no longer are a priest. When you divorced your wife and continued serving in the church for many years until you were excommunicated and your status a priest revoked you were tarnishing our church.
What we learn from you guys sepacalley this holly days all a time complain each other rise your hands to some one is that the right way? This is Renaissance time .God bless every body!
People who go to Taddesse’s church are lazy at best or impostors at worst. Why do you go to a church where a criminal presides and controls? Your very presence and financial contribution is behind Taddesse’s adulterous behavior.
Hulum kesoch and be and limeremeru yigebal
ቀላማጅ በፖለቲካው በሀይመኖቱ ሽብር መንዛት ይህችን ሀገር ለመበተን ቆርጣችሁ ተነስታችል ባፕሳካላችሁም ሥም ማጥፋት የቦዘኔ መገለጫው ነው።