ዕርቅ፤ የሚነገር – የማይተገበር
ይገረም አለሙ

በአቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመራው ድርጅት አዘጋጅነት በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ስብሰባቸውን ያጠናቀቁት በሀገራችን ዕርቅ አስፈላጊ መሆኑ ላይ በመተማመንና ለዚህም ተግባራዊነት ዕርቅን ከራስ መጀመር እንደሚገባ አጽንኦት በመሰጠት መሆኑን ሰምተናል። የእስከዛሬው ተሞክሮአችን ተግባራዊነቱን እንድንጠራጠር ቢያደርገንም የአሰባሳቢዎቹ ተግባርም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የደረሱበት ድምዳሜ የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ ድጋፍ ሊቸረው የሚገባ ነው።