ከኦሮሞ ማዕበል ማግስት …
ተስፋዬ ገብረአብ
በዓለማችን ላይ ወጣቶች በአንድ ልብ የተሳተፉበት ያልተሳካ የአብዮት ታሪክ አናውቅም። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። ይህችን እየፃፍኩ ሳለ የማያቋርጥ፣ የተቀናጀ የአመፅ ዜና ከኢትዮ-ኦሮሚያ እየሰማሁ ነበር። ዝምታው ማብቃቱ ግልፅ ነበር። የኦሮሚያ ወጣቶች የሥርዓቱን ታጣቂ ኃይል በጦርና በጠመንጃ ይፋለሙት ይዘዋል። ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ መንገድ ተዘግቶአል። ልማደኛዋ ኮፈሌ ጦር ሜዳ ሆናለች። ብረት ለበስ ጦር ኮፈሌና ሻሸመኔ ገብቷል። በጥቅሉ ወለጋና ሐረርጌ ፀጥታ የለም። ሱሉልታ ብሶበታል። ጭራሽ ገበሬዎቹ ያስለቀቁትን መሬት መከፋፈል ጀምረዋል። ደራ ነፃ ነው።