የ“ቲያንስ” ኔትዎርክ መሪዎች እየታሰሩ ነው

• 11 ዋና አከፋፋዮች ታስረዋል፤ የዋስትና ጥያቄያቸው በፍ/ቤት ተቀባይነት አላገኘም
• በርካታ ሺ ሰዎች በአባልነት ተመዝግበዋል መግቢያ 4ሺ ብር ይከፈላል
• ቲያንስ 700 ገፅ ደብዳቤ፣ የ15ሺህ ሰዎች የድጋፍ ፊርማ ለጠ/ሚ ቢሮ አስገብቻለሁ ብሏል

የቻይናው ኩባንያ ቲያንስ፤ ሰፊ የምልመላ ዘመቻ በርካታ ሺ ሰዎችን ያስተሳሰረ መረብ መዘርጋት አለመዘርጋቱ አይደለም አከራካሪው ጉዳይ፡፡ የመረቡ አሰራርና አላማ ነው አወዛጋቢው ጥያቄ። የቪታሚንና የሚኒራል ክኒኖችን እንዲሁም ቅባቶችን እንደሚሸጥ የሚገልፀው ቲያንስ፤ ለዚህም “የኔትዎርክ ግብይት”ን እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡
አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ የድርጅቱ አላማ ሸቀጣሸቀጥን መሸጥ ሳይሆን፣ በዚሁ ሽፋን የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ መሰብሰብ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ የተዘረጋው መረብም፣ በፒራሚድ ቅርጽ የተሸረበ ነው ብሏል – አቃቤ ህግ፡፡ ኩባንያው የፒራሚዱ የላይኛውን ጫፍ በመያዝ ይመለምላል፡፡ አስር ሰዎችን ቢመለምል የፒራሚዱ 2ኛ ደረጃ ረድፍ ተፈጠረ ማለት ነው፡፡ ተመልማዮቹ በተራቸው፤ እያንዳንዳቸው አስር አስር ሰው መልምለው በአባልነት እየመዘገቡ ለኩባንያው ያስተላልፋሉ፤ እነሱም ኮሚሽን ያገኛሉ፡፡ መቶ አዳዲስ አባላት ተፈጠሩ ማለት ነው – የፒራሚዱ ሶስተኛ ረድፍ፡፡ እነዚህም  የከፈሉትን 4ሺ ብር ለማካካስ አዳዲስ አባላትን መመልመል አለባቸው፡፡
መቶዎቹ አባላት አስር አስር ሰዎችን ሲመለምሉ፣ ለራሳቸው ኮሚሽን ያገኛሉ፤ ከነሱ በላይ ላሉት ቀደምት መልማዮችም ክፍያ ይደረግላቸዋል፡፡ ከታች ደግሞ አራተኛ ረድፍ ተፈጥሯል – አንድ ሺ አባላትን ያሳለፈ፡፡
እነዚህም በተራቸው፤ ኮሚሽን ለማግኘት 10ሺ አዳዲስ አባላትን መመልመል ሊኖርባቸው ነው – ከታች አምስተኛ ረድፍ በመፍጠር፡፡ እነዚህም እንዲሁ፣ ለአባልነት የከፈሉት ገንዘብ ቀልጦ እንዳይቀር 100ሺ አባላትን መመልመል የግድ ይሆንባቸዋል፡፡ እነዚህም ከኪሳራ ሊድኑ የሚችሉት አንድ ሚሊዮን አባላትን መልምለው ክፍያ ከተቀበሉ ብቻ ነው፡፡
እነዚህ ግን ለምዝገባ የከፈሉት ገንዘብ ቀልጦ ይቀራል፤ አዲስ አበባ ውስጥ አዲስ አባል ሆኖ ሊመለመል የሚችል 10 ሚሊዮን ሰው የለም፡፡
ከፒራሚዱ የላይኛው ጫፍ ላይ ያለው አውራ፣ ከስሩ ያሉት አስር ሰዎች፣ ምናልባትም ቀጥለው ያሉት መቶ ሰዎች፣ ብዙ ገንዘብ ይሰበስባሉ፤ ከታች ያሉት መቶ ሰዎች፤ ብዙ ገንዘብ ይሰበስባሉ፤ ከታች ያሉት ብዙ ሺ ሰዎች ግን ገንዘባቸው የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል፡፡ ቲያንስ እንዲህ አይነት በፒራሚድ ቅርጽ የተሸረበ ኔትዎርክ ይጠቀማል ይላል አቃቤ ህግ፡፡ የቲያንስ ሃላፊዎች ግን ያስተባብላሉ፡፡ ጥራት ያለውን ምርት ለመሸጥ የኔትዎርክ ግብይትን አከናውናለሁ በማለትም ይከራከራል፡፡  የኔትዎርክ ግብይትን የሚደግፍም ሆነ የሚከለክል ህግ ስለሌለ፣ የንግድ ፈቃድ የተሰረዘብኝ አላግባብ ነው ብሏል ድርጅቱ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት 700 ገፅ ደብዳቤ፣ ከ15 ሺህ የድጋፍ ፊርማ ጋር አያይዤ አስገብቻለሁ ይላል፡
አቃቤ ህግ በበኩሉ፣ ቲያንስ በሸቀጥ ሽያጭ ሳይሆን በአዲስ አበባ አስር ክፍለ ከተሞች፣ የአባልነት ክፍያ እየጠየቀ ብዙ ገንዘብ ሰብስቧል ብሏል፡፡ በዚሁ መረብ አቀናባሪና አስፈፃሚ ሆነዋል ያላቸውን 11 ሰዎችንም ያሰረ ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎች ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርበው በዋስ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ ይህን እንደሚቃወም የገለፀው አቃቤ ህግ፣ ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡ ፍ/ቤቱ የሁለት ሳምንት ጊዜ በመፍቀዱ ተጠርጣሪዎቹ በእስር ይቆያሉ ተብሏል፡፡

Addis Admass

9 Comments on “የ“ቲያንስ” ኔትዎርክ መሪዎች እየታሰሩ ነው”

  1. Chainim yehinin Yenetwork lebinet teyayizachewalech
    Keman Temar Aqabi higum biyaqitegn biyaqiteng chainine Ayaqitegnem new bertu!

  2. ህዝቡን ሲልሱት የነበሩት የኔትዎርክ አባላት የወያኔ ካድሬዎች አሉበት።

  3. Amareña be englizeña fidel
    siTaf ende amareñanetu
    ynebeb lemiyaqut slehone.
    he hu hi — hie h ho
    le lu li la lie l lo
    red color = qey qelem
    goodness = chernet
    only = bcha
    salt = Cew = chew
    student = temari
    breast = Tut
    monday = seño = seNo
    one = and
    oozo = uzo
    ethiopia = itiyopiya
    = etiopia
    tortoise = ieli = eli
    mother = enat = ènat
    buyer =gex
    brave = jegna
    start = mejemer
    page = geT
    poet = gTm geTami
    drink = meTeT
    study = Tnat
    correct = right = tkkl
    patience = tgst
    but = gn
    orange = brtukan
    ethiopian bir=yeitiyopiya br
    pen = b-er = eskrbito
    picture = s-el
    duke = luul= lu-ul
    your pencil = ersas-h
    = ersassh
    your mattress = frashish
    = frashih

    miyadenagerun aswegdu:
    consonant plus e = le geez yemejemeriya fideloch
    consonant plus i= li sals
    3 ña biet fideloch
    malet brhan new, aybal birhan weym berhan,
    mkniyat ox = berie, aybal bere mkniyat helper = redat

  4. Wdera :- ይህንን ሁሉ ከመቀበጣጠር አንደኛህን ኮምፒዩተርህን ወይም I phoneን የአማርኛ font ጭነኸው በአማርኛ ብትፅፍ አይሻልምን?

  5. Woyane and Chinese exploiting those fool fortune hunters.Believe me the criminals will be acquitted free right tomorrow. Because the chain stretches from bottom up to Abaya tsehye,Sibhat Nega and other woyane core members.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*