በደሴ እና በአቅራቢያ ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::

በደሴ እና በአቅራቢያ ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Dessie‬ ‪#‎TaxiDriversStrike‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከወሎ ክፍለሃገር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በደሴ እና አከባቢው ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::የወያኔ ፖሊሶች እና ካድሬዎች ታርጋ እየፈቱ ቢገኙም ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው::በዚህም መሰረት ደሴ ከ4 መቶ የማያንሱ ታክሲ እና ከ 3 መቶ በላይ ባጃጆች አሏት ዛሬ ጥቂቶች ናቸው የሰሩት አድማው ከሰአት ቡሀላ ተተናክሮ ይቀጥላል ተብሏል በሚሰሩ መኪኖች ላይ እርምጃም እንወስዳለን ብሏል ህዝቡ::

ከአሽከርካሪዎች ጋር በመተባባር እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነጻነት የናፈቀው የደሴ የወልዲያ እና የአከባቢው ከተሞች ሕዝብ ከአሽከርካሪዎች ጎን መቆሙን በተግባር አሳይቷል::በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ የወያኔ አገዛዝ ከፍተኛ የሆነ የመብት ገፈፋ እንደሚያካሂድ የታወቀ ሲሆን የትራፊክ ፖሊሶች በዘረፋ ላይ መሰማራታቸው በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል:: የአዲስ አበባ የታክሲዎችን አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ከፍተኛ የሆነ መተባበሮች እና አድማዎች ቀጥለዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.