የተሐድሶዎች ዓላማና ግብ ለምን ያደናግረናል? ከሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መማር አቃተን?
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “ተሐድሶ” (ሪፎርሜሽን) ለማካሔድና በእነርሱ እምነት “ተባላሽቷል” የሚሉትን በመቀየር ገሚስ ፕሮቴስታንት ገሚስ ኦርቶዶክስ መሰል እምነት የመፍጠር ዓላማ መኖሩ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነታ ሆኖ “አለ ወይስ የለም?” በሚል ለምን ግር ይለናል? በሃይማኖታቸው ኦርቶዶክሳዊነት የማይጠረጠሩ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ልባቸው ይከፈላል። ለማመንም ለመተውም ይቸግራቸዋል። በሌላ አቀራረብ የሚቃወሙትን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትምህርት ለማስፋፋት የሚጥሩትን ተሐድሶዎቹን ሲረዷቸው ይገኛሉ። ይህ የመደናገርና ግርታ ላይ የመውደቅ አባዜ እጅግ ሥር ከመስደዱ የተነሣ በአገር ቤት ያለችውን ቤተ ክህነት እጅግ እግሯን አስሮ ሊቆጣጠራት ምንም አልቀረውም። ከአገር ቤቱ ተገንጥለን የራሳችን ሲኖዶስ አለን የሚሉትንም አባቶች እንዲሁ መጠቀሚያው አድርጓቸዋል። የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና የሆነው ይህ “ሪፎርሜሽን/Reformation” የተባለ አፈንጋጭ አስተምህሮ ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ለማይታያቸው ምናልባት የዚሁ ችግር ሰለባ የሆነችውን የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በአጭሩ መጥቀስ አብነት ሊሆን ይችል ይሆን?
የሕንድ ኦርቶዶክሶች ከቅ/ቶማስ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚመዘዝ ረዥም ሃይማኖታዊ ታሪክ አላቸው። ልክ እንደኛዋ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በ17ኛው መ/ክፍለ ዘመን ወደ አገራቸው የገቡት ፖርቹጋሎች ባመጡት “ኦርቶዶክሳውያንን ካቶሊክ የማድረግ ዘመቻ” ብዙ መከራ ተቀብለዋል። ግማሽ ሕዝባቸውንም አጥተዋል። በእነርሱ እግር የተተኩት አዲሶቹ የሕንድ ገዢዎች እንግሊዛውያን በበኩላቸው ኦርቶዶክሶችን “አንግሊካን” ለማድረግ በነበራቸው ፍላጎት በገንዘባቸው “የቲዮሎጂ ኮሌጅ በማቋቋምና ራሳቸው ረዳት መስለው በመግባት” ኦርቶዶክስ መምህራንን ሊያፈራ የተቋቋመን መንፈሳዊ ኮሌጅ ለራሳቸው ዓላማ በመቀልበስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውባቸዋል። በዚህም ሰበብ “ማላባር ኢንዲፔንደንት ቸርች፤ ማላንካራ ማር ቶማ ሴሪያን ቸርች እና ሴይንት ቶማስ ኢቫንጄሊካል ቸርች” የተባሉ ሦስት የፕሮቴስታንት እምነት ክፍሎች ሊፈጠሩ ችለዋል።
ከሕንድ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው “ተሐድሶው” የተጀመረው በአንግሊካን እንግሊዞች እርዳታ፣ ቄስ ያውም የቲዎሎጂ መምህር በነበረ ሰው አማካኝነት ነው። ይህ “አብርሃም ማፕላን” የተባለ ግለሰብ ዘመዱ የሆነን ዲያቆን መንበረ ፕትርክናው ወደሚገኘው ወደ ሶሪያ የሐሰት ደብዳቤ አስይዞ በመላክ እና ጵጵስና እንዲቀበል በማድረግ ሐሳቡን ከግብ ለማድረስ ችሏል። ጵጵስናውን ተሳስተው የሰጡት ፓትርያርክ ነገሩ ስሕተት መሆኑን ዘግይተው ቢገነዘቡም የደረሰውን ጥፋት እና ስብራት ለመጠገን ሳይቻላቸው ቀርቷል። ችግሩን ለመፍታት ሕንድ ድረስ ቢጓዙም “የፈሰሰ አይታፈስ” ሆኖባቸው አልፏል።
ዛሬ ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያናችን በሁሉም ዘርፍ ተንሰራፍተው ተቀምጠዋል። በአገር ቤትም በውጪውም ሲኖዶሶች አይነኬ ከመሆን ደረጃ ደርሰዋል። የሚያራምዱት እምነት ተሐድሶ መሆኑ በሰፊው እየተነገረ ዲቁናም ቅስናም የሚሰጣቸው ጳጳስ አላጡም። ምንኩስናን እየተቃወሙ ለጊዜው የመነኩሴ ቆብ የደፉትም ጵጵስና ለመቀበል በአገር ውስጡም በውጪውም ተራ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ ሰዎች እንደሚፈራው እስከ ጵጵስናው ማዕረግ ለመድረስ ከቻሉ በሕንድ የደረሰው በእኛም ላይ እንደማይደርስ ምንም ማስተማመኛ ማግኘት አይቻልም። የሕንዱ ተሐድሶ (“የማር ቶማ ቸርች”) በእምነት ከአንግሊካኖች ጋር አንድ መሆኑን አውጆ የራሱን ጎጆ እንደቀለሰው ሁሉ የኛዎቹም የራሳቸውን ጎጆ የማይቀልሱበት ምንም ምክንያት የለም። በሕንዶች ከ1880ዎቹ ጀምሮ የተከሰተውን ታሪክ ከ150 ዓመት በኋላ የተፈጠርን ሰዎች ተመልክተን ችግሩን መገንዘብ ለምን ያቅተናል?
የሶሪያው ፓትርያርክ ለተሐድሶዎቹ የመጀመሪያ ጳጳስ ማዕረጉን ተሳስተው እንደሰጡት ሁሉ ዛሬም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ መናፍቃኑን ማዕረግ በማዕረግ አድርገው በመንጋው ላይ በእረኛ ፈንታ ተኩላ የሚልኩባቸው ሰዎች ከፍ ያለ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባቸው ነበር።
በዚህ ወቅት የተሐድሶዎች ክፍል በቤተ ክህነቱ የተፈጠረው የአባቶች መከፋፈል ሰርግና ምላሽ ሆኖት ከዚህ ሲሉት ከዚያ፣ ከዚያ ሲሉት ከዚህ እያጣቀሰ ስሩን እያስፋፋ ሲሆን የአባቶች መከፋፈል እውነት የመሰለው ኦርቶዶክሱ ክፍል በዚህም በዚያም ወገን እየተጎዳ ከሁለት ያጣች ጎመን ሆኖ ተዘልሎ ተቀምጧል። የተሐድሶው ክፍል አገር ቤት ሲገባ ኢሕዴግን፤ ውጪ ሲወጣ ተቃዋሚውን እየመሰለ ዋና ዓላማው የሆነውን የኑፋቄ ስራ በሰፊው ያስፋፋል። “ፓትርያርካችን አቡነ መርቆርዮስ ናቸው” ሲል ይቆይና አቡነ ማትያስ የደገፉት ሲመስለው ተቀልብሶ ሲያመሰግናቸው ያመሻል። “አቡነ ማትያስ ፓትርያርኬ” ሲል የቆየው አገር ቤት ያለው ክንፋቸው ሲመቸው ደግሞ ውጪ ያሉት አባቶች ጋር ራት ሲበላ ይገኛል። በዚህም በዚያም ግን ቤተ ክርስቲያን እየደማች ነው። ይህ አዚም የሚለቀን መቼ ነው? የምንደናገረውስ እስመቼ ነው?
በዚህ ረገድ ፓትርያርክ አባ ማትያስ ቀደምቶቻቸው አድርገውት በማያውቁት መጠን እና ስፋት ቤተ ክርስቲያኒቱን ጅብ እያስበሏት ነው። አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት የተሐድሶዎችና የዚሁ ዓላማ መጋቢ የሆኑ ግብረ በላ ወዳጆቻቸው መጠቀሚያ ሆነዋል። በቤተ ክህነቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያስብል ደረጃ ከቅ/ሲኖዶስ ተነጥለው፣ ሲኖዶሳዊቱን ቤተ ክርስቲያን ኢ-ሶኖዶሳዊ አስተዳደር ተክለውባታል። ብዙ ሚሊዮን ሕዝቧ በረሃብና በችጋር የዓለም መሳቂያ መሳለቂያ በሆነበት ዘመን፤ የኑሮ ምሬት ያንገሸገሸው ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ግዛቶች ምሬቱን በሚያሰማበትና በዚሁ ሰበብ የሚያልቀው ምእመን የቀብሩን ስፍራ ባጣበበት በዚህ ወቅት “አስረሽ ምቺው” የቅንጦትና የዘረፋ ሰደድ ቤተ ክህነቱን አቀጣጥሎታል። ይህ ሁሉ ሰርግና ምላሽ የሆነው ግን ለተሐድሶው ኑፋቄ ነው። ይህ ሁሉ ነገር እንዴት ያደናግረናል? ለምንስ አንነቃም?
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን።
i think this is time to work with the people and officially declare this fact to he christian public
God bless Ethiopia and our church
Tehadeso/reforem is a wright way we have to follow them what the new thing hay !!
ተሐድሶ ማለት በራሳቸው ፈልስፈና በገንዘብ አስክሮአቸው ዲያቢሎስ ከጣፈጩ የተዎህዶ እምነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነጥሎ ያወጣቸው ማለት ነው። የሚያሳዝነው ነገር እነ አባ አመለከተ ፀዲቅ፣ አባ ወለደ ትንሳኤ ፣ አባ መላኩ፣ መምህር ሉለቃል የውጪ አባቶችን አሳስተው ኦርጋኖ በቤተክርስቲያን ውስጥ አስገብተው ዳንኪራ አሰረገጡ። አረ ምን ነካቹ ኦርጋኖ እኮ የሙዚቃ እንጂ የመንፈስ አይደለም። እባካችሁ ይህንን የተከፋፈለ ህዝብ በውጭ ስኒዶስ የአባቶቻችን ሰርአቱን ሳትቀይሩ መስብሰብ በቀላሉ በፍቅር ጊዜ እስከሚያልፍ መሰብሰብ ስትችሉ እባካችሁ ተመለስ። አቡነ መርቆረዎስ እና ሌሎች ጥሩ አባቶች አላችሁ ይቺ ቀጥተኛ ተወህዶ እምነት ነች ተናገሩ የራሳችሁ ክህናት እያወቁ እንዴት በግራ ለመቆም ይቸኩላሉ። እኔ 30 ቀን እሰጣቸዎከሁ ኦረጋኖን ለመጣል እና ስርአት ቤተ ክርስቲያኗን መልሳችሁ የቺ ጊዜ አልፎ ለ አገራችን እስክንበቃ። እግዚአብሔር የርዳን ተመለሱ ፍቅር ጥሩ ነው ፈጣሪም ይረዳናል። እባካችሁ በአይኔ እያየሁ ዲያቢሎስ በግራ በኩል እንዳየቆማቹ በእግዚአብሔር ሰም አለምናችሀለሁ። ጐበዝ በአይኔ እያየሁ እናንተን የመሰለ ሰው ዲያቢሉስ ይውሰዳችሁ??? አይሆንም ቆም ብላችሁ አድኑ። No No No in English back to real normal!!!
በተለይም እኛ ኢትዮጽያውያኖች በእምነት ረገድ አግዚአብሔር በአለም ላይ በእራሱ አምሳል ከፈጠራቸው ልጆቹ መካከል እኛ ብቻ የተለየን ጻድቃኖች በቅስትም ሀገር ያለን እስቈከሚመስለን ድረስ የኛን መንገድ ያልሄደ ወገን ሁሉ ስም እያወጣን ነአንዴ መናነፍቅ እያልን ኦግዚአብሔር የፈጠረውን ክቡር ሰው ስንኮን ግነዜ በመውነሰድ የመዳንን ህይወትም የሚሆነውን የአምላካችን ቃል ሳናስተምርበት ልዩነትን በመፍጠርና በማነስፋትም ወገን ከወገኑ ጋር ህብረት ፈጥሮ ልዩነትን ተቀሪርቦ ከመወያየት ይልቅ ለመለያየትና ለመጣጣል የምናደርገው ርኩነሴዊዉን ስሬችንን ጨርሶ ያስተዋልነው አይደለንም፡፡ይልቂንም በተለይም ሪሱን ያለምንም ምስክር ሪሱን ማህበረ ቅዱሳን ብሎ የነሰየመው ወገን ራሱን የቅዲሳነ ቦታ አስቀምጦ ከእርሱ በብቃትም በማስተወልም የተለየዉን ሁሉ ዐገን መናፍቅ ራሱን ደግሞ ቅድስ ሲያደርግና ሲኮንነን ሌላዉን ወገኑን ጨርሶ በእግዚብሔር አምላክ እንዳልተፈጠረ ሲያወግዝ እግዚአብሔርን ባለመፍራት ነውና እናንተ ማቅ ቢያንስ እንደ እናንተ የተቀረው ወገናችሁ የሚያስብ የሚያስተውል የኦርቶዶክስ ተዎህዶ ልጆች መሆናችንና የእናንተን ምነስክርነትንም የማያሻን መሆኑን ብታውቁትና ልየነት ባኖርም እንሿን አይኖርም እንጂ ለባለቤቱም ጉዳዩን ሲኖዶሱ የሚመለከተው ነውና እባካችሁ እራሳችሁን ትልቅ የተቀደሰ ተሪሪ ላይ አስቀምጣቾሁ አትመልከቱ፡፡ትል አፍሬሽ ቈስራ እየሰሪችሁ መሆኑን አስተውሉ፡፡ስማችሁን በስሪ አነሳዩ ፡፡አልያም ቀይሩ፡፡አልያም እስቲ መሰናክልና መጥፊያ ከምትሆኑ ገለል አሁንም ገለለ በሉ
The propoganda of childish & gambler Mahibere Kidusan! MK trading in the name of EOTC. MK axion in the name of EOTC . The camp of hiypocratic, know nothing!
I AM SAYING PLEAE BACK TO NORMAL KEEP UP YOUR FATHERS SPRIT OF LAW. PLEASE STOP ADDING YOUR MODERN PHILOSPHY IN TO OURFOUNDERS FATHERS ORTHODOX TEWHEDO SPIRIT OF LAW. STOP PIANO IN CHURCH LIKE NIGHT CLUB. STOP MODERN WEDDING IN CHURCH. I AM TELLING YOU THAT IF YOU DO ALL OF THOSE THINGS MEANS YOU ARE OUT OF THE CIRCLE OF THE RELGION LAW. IT IS CLEAR DON’T MISLEAD CHILDERN BORN IN AMERICA, CANADA OR EUROPE. ORTHODOX MEANS YOU CAN NOT CHANGE ANY LAW BECAUSE OF YOU LOVE TECHNOLOGY. Please refer Psalm 150 and piano is not there. EVEN FOR THAT MATTER WHITE PEOPLE RESPECT YOU IF YOU SHOW YOUR UNIQUE IDENTITY. OVERALL, THOSE GROUP PLEASE YOU LIVE ONLY ONCE AND BACK TO NORMAL FROM WRONG EVENGLICAL 16th CENTURY PHILOSPHY. MEHABERE KEDUSAN HAS GREAT CONTRIBUTION FOR OUR CHURCH PRACTICALLY IF YOU OPPOSE OF ALL THAT THINK TWICE. I DISAGREE THOUGH WITH SOME OF THE MEMBERS PUT THEM SELVES AS THE ONLY SUPER CHRISTIAN THAT IS RIGHT IN THE EYES OF God!