የወያኔው አገዛዝ ሻእቢያ አፍኖብኛል ያለችውን 85 ማእድን ፈላላጊዎች እንዲለቅላት ሱዳንን አማላጅ ላከ::
የወያኔው አገዛዝ ሻእቢያ አፍኖብኛል ያለችውን 85 ማእድን ፈላላጊዎች እንዲለቅላት ሱዳንን አማላጅ ላከ::
ለጦርነት አይደለም ለፕሮፓጋንዳ ዝግጁ ያልሆነ የማይተማመንበት ሰራዊት ያለው የወያኔው መንግስት ባለፈው ሳምንት ታፍነዋል የተባሉትን 85 የማእድን ቆፋሪ ኢትዮጵያውያንን ሻእቢያ እንዲለቅለት በሱዳን በኩል የተማጽኖ ሽምግልና መላኩ የታወቀ ሲሆን እስካሁን ድረስ በድንበር አከባቢ ታስረው የሚገኙ ማእድን ቆፋሪዎች ለመልቀቅ ሻእቢያ የተስማማ ያልተስማማ መሆኑ ከሻኢቢያ ወገን ባይረጋገጥም ከወያኔ ወገን ደግሞ ታጋቾቹ ሱዳን ተረክባ ልታስረክበት ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው::
የወያኔ ቀረርቶ በሃገር ቤት ያለውን ትግል አትኩሮት ለመንፈግ የተደረገ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ወያኔ ሱዳንን አማጽኚኝ ማለቱ አስተማማኝ ጦር እንደሌለው እና በራሱ እንደማይተማመት በግልጽ ያሳየ ስለሆነ ተቃዋሚ ሃይሎች ተጠናክረው ትግላቸውን በመቀጠል ስርኣቱን እንዲገረሰሱ ይናገራሉ::ከትግራይ ክልል በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ላይ የወርቅ ቁፋሮ ሲያደርጉ የታፈኑ 85 ሰዎች በአረና ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት በኩል መረጃው ይፋ መጣቱ ይታወሳል::