የማርች ወር የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲታወስ ሞንትጎመሪ ካውንቲ አወጀ:: MARCH AS ADWA VICTORY MONTH IN MONTGOMEY COUNTY , MARYLAND

የማርች ወር የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲታወስ ሞንትጎመሪ ካውንቲ አወጀ::
በሜሪላንድ ግዛት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የማርች ወር የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲታወስ አወጇል

ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለመላው የአፍሪካ ሃገሮች እና ጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ቀንዲል የሆነውን የአድዋ ድል 120ኛ አመት በዓል የሞንትጎመሪ ካውንቲ ወሩን የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲታወስ በተከበሩት የካውንቲው ተወካይ አይሳያ ሌጌት ተፈርሞ የወጣው አዋጅ በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ የተመራው የተባብረው የኢትዮጵያ ወታደር ወራሪውን የኢጣልያ ሃይል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ማርች 01 1896 በአድዋ ላይ ያሸነፈበት ታሪክ የኢትዮጵያውያን አንድነት እና የአፍሪካ ሃገሮች ከአውሮፓ ቅኝ ግዛት ለመውጣት ለሚያደርጉት ትግል መነሻ የሆነ ታሪካዊ ቀን መሆኑን አዋጁ አስታውሷል::

አዋጁ በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን በቁጥር በካውንቲው ከሚኖሩ ከአፍሪካ ከመጡ ነዋሪዎች በሁለተኛነት እንደሚገኙ እና ለካውንቲው የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ አስታውሷል::

ይህ በየአመቱ የሚከበረው ታሪካዊው የአድዋ ድል በዚህ ታላቅ መልክ እንዲታወስ እና በታሪክም እንዲቀመጥ ያደረገው ተቀማጭነቱ በአሜሪካን ሃገር የሆነው የኢትዮጵያውያን ውርስ እና ቅርስ ማህበር በሰሜን አሜሪካ የተባለ ኢትዮጵያውያን ታሪካቸውን እና ባህሎቻቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው::