አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ስለማይሰማ እንደነቀነቅነው ልንነቅለው ይገባል::
አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ስለማይሰማ እንደነቀነቅነው ልንነቅለው ይገባል::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
#Ethiopia #Oromoprotests #EthiopianOppositionParties #Miniliksalsawi #EPRDF
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ተቀጣጥሎ የሚገኘው የሕዝብ ተቃውሞ ለአገዛዙ ከባድ ፈተና ሆኖበታል:: የወያኔ አገዛዝ በአንድ ብሄር የበላይነት ሌሎች የኢትዮጵያ አካላት ብሄሮችን እያባሉ ለመኖር ለመግዛት ለመበዝበዝ ያደረገው ሂደት ተነቅቶበታል::ሕዝብ ሁሉን እያወቅን ዝም ስንል ሞኞች አይደለንም ጠላታችን አብሮን የኖረ ሕዝብ ሳይሆን አገዛዙ ነው በማለት ወያኔን ለመንቀል በተቃውሞ መነቅነቁ ላለፉት ሶስት ወራት እያየነው ሲሆን ትግሉ ላይቆም ቀጥሏል::
የወያኔ ስርኣት እስካልተወገደ ድረስ ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንደማይመለስ አስረግጦ ተናግሯል::የተነቃነቀ ይወልቃል ይነቀላል::ሕዝቡን ማበረታታት ሁሉም በጋራ ለቀጣዩ ትግል እዲቆም ማድረግ የለውጥ ሃይሉ ግዴታ ነው::በኦሮሚያ ክልል የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግሉን ሊቀላቀል ይገባል::የፖለቲካ ጫናው የኢኮኖሚው ተዘራፊ አካል መሆኑን መዘንጋት የለበትም::የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በኦሮሚያ ያሉ ነዋሪዎች የወያኔ ጭቆና ቀንበር በላያቸው ላይ የተጫነ እስከሆነ ድረስ በጋራ ከተቃውሞው በመቀላቀል የተጀመረው ትግል በእርከን ማደጉን እና ፍሬ ማፍራቱን በተግባር ማሳየት አለባቸው::በሃገር ቤት ይሁን በውጪ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አካል እና አስተባባሪ ሊሆኑ ይገባል::የተገኙት አጋጣሚዎች ወያኤን ለመጣል የማንጠቀምባቸው ከሆነ የሕዝብ እኩልነት እንደተደፈጠጥ አምባገነኖች እድሜያቸው እንደረዘመ ይኖራሉ::
የወያኔ ስርኣት የሕዝብን ተቃውሞ አትኩሮት እንዳያገኝ ለማድረግ ቢሞክርም አልተሳካለትም::የለውጥ ሃይሉ ደግሞ ትግሉ እንዲያድግ ማድረግ አለበት::የሕዝብ ልጆች ካለምንም መሪ ብሶታቸውን ይዘው አደባባይ በመውጣት መስዋትነት እየከፈሉ ይገኛል::የኦሮሞ ሕዝብ በሚከፍለው መስዋትነት ጥቂት ፖለቲከኞች እና ባለምላስ ታክቲክኞች ስልጣን ላይ ለመንጠልጠል ሲያሰፈስፉ ማየት ያማል::እንዲሁመስከመቼ ባለንበት እንቀጥላለ የሚለውን ልናስብበት ይገባል::ለነጻነት እና ልመብት እንታገላለን እስካልን ድረስ ስለ መቻቻል እና ስለ ሃገራዊ አጀንዳ ስንል ራሳችንን ምስበር አለብን::ካልሆነ ለጠላት ክፍተት መስጠት ነው::ወያኔ ይህን ክፍተት ስለሚያውቅ በአጀንዳ ጡዘቶች ሌላውን ወጥሮ በሃሰት እየተናጠ ድምጹን ያጠፋል::አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ስለማይሰማ እንደነቀነቅነው ልንነቅለው ይገባል:: #ምንሊክሳልሳዊ