“የጋማ ከብቶች” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

“የጋማ ከብቶች”

“የጋማ ከብቶች” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት 

Addis Admass : ያንተ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ቅርስ ስለሆነ ብቻ ዝም ብለህ አትዋጠው፤ አንጥረው፡

፡ ዕውቀት ወደሚባል፣ ማስረጃ ወደሚባል፣ መረጃ ወደሚባል፣ ክርክር ወደሚባል፣
ተጠየቅ ወደሚባል፣ ኅሊና ወደሚባል እሳት ላይ አውጣው፡፡ ይነጥራል፡፡

በቀደም ድሬዳዋ ላይ ዓሣ ዘነበ ብለን ከአንድ ወዳጄ ጋር ስናወራ፤“ባክህ ይሄ እንኳን የጋማ ከብቶች ወሬ ነው” አለኝ፡፡ እኔም አነጋገሩ ገርሞኝ፤“የጋማ ከብቶች ደግሞ እነማን ናቸው” ስል ጠየቅኩት፡፡
“የማያመነዥኩ ናቸዋ” አለና አሳጠረው፡፡
“እኮ ከድሬዳዋ ዓሣ ጋር ምን ያገናኘዋል?”
እኔ ድሬዳዋ እንኳን ዓሣ፣ የዓሣ ፋብሪካ ቢወርድላት ችግር የለብኝም፡፡ ለምን፣ እንዴት፣ መቼ፣ ማን፣ ፊትና ኋላ፣ ቀኝና ግራ የሚባሉ ነገሮች ፋሽናቸው አለፈ እንዴ? አንድ ሚዲያ፤ ‹ዓሣ ዘነበ› ከማለቱ በፊት በጋዜጠኛውና በሚዲያ ኃላፊዎች ላይ ‹ማመዛዘን› የሚባለው ነገር መዝነብ ነበረበት፡፡ ያንን የዘገበ ዘጋቢ ዓሣ ሊያዘንብ የሚችል ታሪካዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ አየር ንብረታዊ፣ ሌላም ምክንያት መኖር አለመኖሩን ሳያጣራ፣ በየቦታው ተዘዋውሮ ሳያረጋግጥ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በኅሊናው መዝኖ ከግምት በላይ ሳያልፍ፣ እንዴት ለዘገባ ያበቃዋል፡፡ ይኼ የጋማ ከብትነት ይባላል፡፡
የጋማ ከብት ይበላል ግን አያመነዥክም፡፡ ያገኘውን መዋጥ ብቻ ነው፡፡ እስኪ የቀንድ ከብቶችን ተመልከት፤ቀን የበሉትን ማታ ጋደም ብለው በጽሞና ሲያመነዥኩት ታዳምጣለህ፡፡ ይፈጩታል፣ ይሰልቁታል፣ ያጣጥሙታል፣ ያወጡታል፣ ያወርዱታል፡፡ አንዴ ገባ ብለው እንዲሁ አይተውትም፡፡ ፊውዝ እንኳን የማይስማማው የኤሌክትሪክ ኃይል ሲመጣ አላሳልፍም ብሎ ራሱ ይቃጠላል፡፡ ብሬከር እንኳን በዐቅሙ የማይሆን ኤሌክትሪክ ሲመጣ ይዘጋል፡፡ እንዴት ሰው እንደ ጋማ ከብት የሰጡትን ሁሉ ይውጣል፡፡
አሁን በየስብሰባውና በየሚዲያው ‹የመለስ ራእይ› ሲባል እንሰማለን፡፡ የመለስ ራእይ ምን እንደሆነ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ብለህ ግለጠው ቢባል ስንቱ ያውቀዋል? የሆነ ቦታ ሲባል ስለሰማ ሳያመነዥክ እርሱም ይለዋል እንጂ፤ እውነት ይሄ ሁሉ ሰው ራእዩን ዐውቆት፣ ከዚያ ገብቶት፣ ከዚያም ተስማምቶበት ነው እያወራ ያለው?
አንዱ፣ እገሌ የተባሉት ባለሥልጣን፣ ሥራ የሚቀጥሩት በዘመድ ነው ሲባል ይሰማል፡፡ ጓደኞቹ ደግሞ ‹የአንተ አገር ሰው’ኮ ናቸው› ይሉታል፡፡ ይሄ ነገር ሲደጋገምበት ‹ለምን አልጠይቃቸውም› ብሎ ቢሯቸው ሄደ፡፡ ምናለ ቢያንስ – የት ሀገር፣ የት ቀበሌ፣ የት መንደር ናቸው የሚለውን እንኳን ቢያጣራ፡፡ ቢሯቸው ገብቶ የሀገራቸው ሰው መሆኑን ይገልጥና ሥራ ይለምናል፡፡ እርሳቸውም በመንደርና በጎጥ የጠበቡ ነበሩና፤ ‹ለመሆኑ ሀገርህ የት ነው?› ይሉታል ‹ከእርስዎ ሀገር› ይላል፡፡ ‹የኔ ሀገር የት ነው?› ሲሉት ‹ከኛ ሀገር› አለ አሉ፡፡
አሁንማ የጋማ ከብቶች ወረሩን’ኮ፡፡ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው፣ ማኅበራዊ ሚዲያው፣ ሥልጣኑ፣ ኪነ ጥበቡ፣ ቤተ እምነቱ፣ ምሁርነቱ፣ ንግዱ፣ ፓርቲው፣ ምኑ ቅጡ– በጋማ ከብቶች እየተሞላ ነው፡፡ እስኪ ከፈለግህ ‹እገሌ ሞተ› በልና ፌስ ቡክ ላይ ለጥፍ፡፡ ምንም ነገር ሳያጣራ ግማሹ ፕሮፋይል ፒክቸሩን ጥቁር ያደርጋል፣ ሌላው ‹አር. አይ. ፒ› ይላል፣ ሌላው ደግሞ ምናልባት ልቅሶ ተቀምጦ የዕድር ብር በልቶ ይሆናል፡፡ ‹በዓሉ ግርማ ዳጋ እስጢፋኖስ ተገኘ› ሲባል በአንድ ጀልባ ሮጦ ሊያጣራ የሚችለው የባሕር ዳር ነዋሪ፣ አብሮ ‹ሼር› እና ‹ላይክ› ካደረገ ከዚህ በላይ የጋማ ከብትነት ምን አለ?
ወዳጄ፣ማመን ማለት ፈጽሞ አእምሮን መነሣት አይደለም፡፡ አእምሮ የፈጠረልህን ፈጣሪ ከሆነ የምታምነው ማመዛዘንን እምነት አይቀማህም፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስን በዓል አከብራለሁ ብሎ የሄደ ምእመን፤‹ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወገረ› ሲሉት ‹እልልልልልል› ብሎ የሚያቀልጠው ከሆነ፣ ዐጸዱ በጋማ ከብቶች ተሞልቷል ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያለው የጋማ ከብትነት ነው ፓስተሮቻችንና አስተማሪዎቻችን ልብሳችሁን አውልቁ፣ ሣር ብሉ፣ መሬት እንዳይነካን አጎንብሱና እንቁምባችሁ ሲሉን ያለማመንዠክ እንድንቀበላቸው ያደረገን፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን እናቱ ትምህርት ቤት ባስገባቺው ጊዜ፣መምህሩ የእብራይስጥን ፊደል ሲያስቆጥረው፤ ‹አሌፍ› በል አለው፡፡ ‹አሌፍ› አለ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ‹ቤት› በል አለው፡፡ ዝም አለ፡፡ መምህሩ ተናደደና፤ ‹ለምን ቤት አትልም?› ሲል ተቆጣው፡፡ ሕጻኑ ክርስቶስም፤ ‹መጀመሪያ የአሌፍን ትርጉም ንገረኝና ከዚያ ቀጥዬ ቤት እላለሁ› አለው ይላል ተአምረ ኢየሱስ፡፡ ታዲያ ምነው የእርሱ ተከታዮች መጠየቅንና መመዘንን ፈሩ? ለምንስ የጋማ ከብትነት በዛ?
በደርግ ዘመን፤ ‹ጓድ መንግሥቱ እንዳሉት› እየተባሉ የሚነገሩት ጥቅሶች ሁሉ ብዙዎቹ መንግሥቱ ኃይለማርያም ራሳቸው የማያውቋቸው እንደሆኑ በኋላ ታውቋል፡፡ እንዲያውም በአንድ ስብሰባ ላይ ‹ሰውን ሰው ያደረገው ሥራ ነው› ብለዋል ጓድ መንግሥቱ ብሎ አንዱ ካድሬ ይጠቅሳል፡፡ ያውም ራሳቸው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ባሉበት፡፡ እርሳቸው ራሳቸው ገርሟቸው፤ ‹ኧረ ይሄን ነገር እኔ አልተናገርኩም› ይሉና ከስብሰባው በኋላ ያስጠሩታል፡፡ ‹ይህ ንግግር የኔ መሆኑን ከየት አገኘኸው?› ሲሉት ‹መቼም እንዲህ ያለ ንግግር ከእርስዎ አፍ ካልሆነ በቀር ከአድኃሪያን አፍ አይወጣም ብዬ ነው› አለ አሉ፡፡ ካድሬ ምን አለበት፤ ‹ነው› ከተባለ ነው፣ ‹አይደለም› ከተባለ፣ አይደለም ብሎ ይኖራል፡፡
በወዲህም ሆነ በወዲያ ቆመው ሚዲያውን የተቆጣጠሩት ወገኖቻችን ጥቂት ማመንዠክ ቢችሉ ኖሮ እኛን የአህያ ሆድ አድርገው አይቆጥሩንም ነበር፡፡ የሚበሉት እህል ይለያያል እንጂ ሁለቱም አያመነዥኩም፡፡ ሁለቱም ወዳጆቻቸው የነገሯቸውን ሳያመሰኩ ይውጣሉ፤ ሁለቱም ጠላት ከሚሏቸው የሚመጣውን አይቀበሉም፡፡ እነርሱን እስከ ደገፈና ጠላቶቻቸውን እስከ ተቃወመ ድረስ ሁለቱም ማንጠሪያ የላቸውም፡፡
በተለይ ደግሞ ዘረኝነትና ማይምነት ሲጨመሩበት፣የጋማ ከብትነት የከፋ ይሆናል፡፡ ዘረኞች ከራሳቸው ወገን የሚመጣውን ሁሉ እንዳለ ይውጡታል፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው ሁሉ ሊያጠፋቸው፣ ሊቀማቸው፣ ሊያንቋሽሻቸው የሚመጣ አድርገው ስለሚመለከቱት ከወገናቸው ውጭ ማንንም አያምኑም፡፡ በባለሞያ ያልተቃኙ፣ በገለልተኝነት ያልተበየኑ፣ በማስረጃ የማይበጠሩ፣ ስሜትና እውነትን ያልለዩ፣ የታሪክ ድርሳናት በየቦታው ሲታተሙና ‹ለብሔረሰቡ› ሲሠራጩ ሃይ ባይ የላቸውም፡፡ ዘረኞች እውነትን በዘር መነጽር ነው የሚያዩዋት፡፡ ምን ተነገረ? ሳይሆን ማን ተናገረ? ነው ቁም ነገሩ? ቀጥሎ ደግሞ የኛ ወገን ነው ወይስ የነዚያ? ይባላል፡፡ የራስህ ወገን የነገረህን ዝም ብለህ መጋት ነው፡፡ ቢቻል ቢቻል ጀግና ነህ፣ ማራኪ ነህ፣ የሠለጠንክ ነህ፣ የዚህና የዚያ ምንጭ ነህ፣ ድንቅ ባህልና ምርጥ ታሪክ አለህ ይበልህ፡፡ ሳታመነዥክ ትጋተዋለህ፡፡ ይኼ ካልሆነ ደግሞ ተጨቁነህ፣ ተረግጠህ፣ ማንነትህ ተረስቶ፣ ከሰው በታች ሆነህ ነበር፤ እነ እገሌና እነ እገሊት ጠላቶችህ ናቸው ብሎ ሙሾ ያውርድልህ አሁንም ትጋተዋለህ፡፡ ማንጠር የሚባል ነገር የለም፡፡
ዘረኝነት ማንጠር የሚባለውን ሞያ አጥፍቶብናል፡፡ ቅቤን ከአንጉላው የሚለየው ማንጠር ነው፡፡ ሲነጠር ቅቤው ለብቻው፣ አንጉላው ለብቻው ተለይቶ ቁጭ ይላል፡፡ ለአንጉላ ተብሎ ቅቤ አይጣልም፤ ለቅቤም ተብሎ አንጉላ አይበላም፡፡ ይነጠራል እንጂ፡፡ ያንተ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ቅርስ ስለሆነ ብቻ ዝም ብለህ አትዋጠው፤ አንጥረው፡፡ ዕውቀት ወደሚባል፣ ማስረጃ ወደሚባል፣ መረጃ ወደሚባል፣ ክርክር ወደሚባል፣ ተጠየቅ ወደሚባል፣ ኅሊና ወደሚባል፣ እሳት ላይ አውጣው፡፡ ይነጥራል፡፡ አንጉላው ከቅቤው ይለያል፡፡ ካልሆነ ግን በተለይ የማያመነዥኩ ሰዎች ሆድ ውስጥ ከገባ አደጋ ነው፡፡
እንክርዳድ እክርደድ የተንከረደደ
ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ፤ የተባለው ለዚህ አይደል፡፡
ማይምነትን በእናቶቻችን ቋንቋ ለመተርጎም ‹የማይለቅም፣ የማያነፍስ፣ የማያበጥር፣ የማይነፋ፤ እንዲሁ የሚያስፈጭና የሚበላ› ማለት ነው፡፡ እናቶቻችን እህሉን ከቆሻሻው ለመለየት የቻሉትን በእጅ ይለቅማሉ፣ ያልተቻለውን በሰፌድ ያነፍሳሉ፣ የተረፈውን በማበጠሪያ ወንፊት ያበጥራሉ፡፡ ተፈጭቶ ከመጣ በኋላ ደግሞ በጥቅጥቅ ወንፊት ይነፉታል፡፡ ይኼ ሁሉ ልፋት ዓይነተኛውን እህል ለማግኘት ነው፡፡ ዓይነተኛውን እውነት ለማግኘትም በመረጃና በማስረጃ፣ በዕውቀትና በብስለት፣ በተጠየቅና በመጠንቀቅ መልቀም፣ ማንፈስ፣ ማበጠርና መንፋት ያስፈልጋል፡፡
ምሁራኑ እንኳን በየዐውደ ጥናቱ፣ ጥናታዊ ጽሑፍ ብለው የሚያቀርቡት ተዘጋጅቶና ተሰናድቶ የመጣውን ‹ዳታ›፣ ለበዓሉ የሚስማማውን ቀለም፣አየሩና ነፋሱ ሲለው የከረመውን እንጂ ዘወር ያለ፣ የተመዘነ፣የነጠረና፣የተመረመረ ነገር አይናገሩም፡፡ በዜና የሰማነውን በጥናታዊ ጽሑፍ ቅርጽ ያቀርቡታል፡፡ ሳያመነዥኩ ያቀርባሉ፤ ሳናመነዥክ እንበላለን፡፡
በድሬዳዋ የተጀመረውን ነገር ድሬዳዋ ላይ በተፈጸመ የጋማ ከብትነት እንዝጋው፡፡ መምህሩ ውጭ ቁጭ ብሎ ተማሪውን ይጠራውና፤ ‹እዚያ ክፍል ሄደህ እኔ መኖሬንና አለመኖሬን አይተህ ንገረኝ› ይለዋል፡፡ ተማሪውም ቀጥ ብሎ ሄዶ በመስኮት ያይና ተመልሶ መጥቶ ‹የሉም› ይለዋል፡፡ ይሄኔ መምህሩ በጥፊ ተማሪውን መታው፡፡ ተማሪው የደረሰበትን ይናገርና አባቱን ይዞት ይመጣል፡፡ አባትዬውም እንደመጡ፤ ‹እንዴት ልጄን ትመታለህ!› ብለው ይፎክራሉ፡፡ መምህሩም፤ ‹ታዲያ ለምን ከክፍል ውስጥ የለም ይለኛል› አላቸው፡፡ አባት መለስ ይሉና ልጃቸውን፤ ‹እንደዚህ ብለሃል› ይሉታል፡፡ ‹አዎ› ይላል ተማሪው፡፡ ‹መምህሩን ከክፍል ውስጥ የሉም አልክ› አባት አጽንተው ጠየቁ፡፡ ‹አዎ ብያለሁ› ይላል ልጅ፡፡ አባትም ተናድደው፤ ‹ታድያ እርሳቸው ከሌሉ ማን እያስተማረህ ነው ተምሬ መጣሁ የምትለው› ብለው ልጃቸውን ጥፊ ደገሙት ይባላል፡፡ እንዲህ ነው የጋማ ከብትነት የመጣልህን መዋጥ፡፡

48 Comments on ““የጋማ ከብቶች” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት”

  1. yeGizew bale gize Deyakom kibret

    bel esti endametalih afihen kifet

    anten belo deyakon kkkk

    Hodam ye weyane cadre sebaqi

    alubaltegna kibret !!! Miqegna !!

  2. እግዜር ይስጥህ ወንድሜ ዳነኤል ። ይህን ሁሉ የጋማ ከብት ልክልኩን ነገርከው ከገባው ። የሚገርመው ከብቶች የት ጋ ጥሩ ግጦሽ እንኳ እንዳለ ፈልገው ማግኘት አለመቻላቸው ነው ። ከላይ የተቹት ሁሉ ከብቶች ናቸው ለማለት ያስደፍራል ። ትችታቸው ስለፃፍከው ጉዳይ ሳይሆን ፤ የራሳቸውን መጋዣነት የሚገልፅ ነው ። መመርመር ማሰብ ማስተዋል የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም ።

  3. ዉሸትና ኩሸት ለኢትዮዽያዉ አዶልፍ ሂትለር/ወያኔ/ አይነተኛ መገለጫዉ ነዉ

  4. አንባ ገነን መለስ የኢትዮ ህዝብ በቀን 3 ጊዜ እንመግበዋለን ያሉት በምግብ ሳይሆን በዉሸትና በኩሸት ቁንጣን አስያዙን! አይ መለስ ነብስህን ይማግደዉ ከሳት! በአለም ታይቶ የማይታወቅ አንባ ገነን ወሮበላ ያገሩን መሬት እየሸጠ የሚበላ ዱሩየ አረ በገንኩ!

  5. Senu,
    I don’t see any thing in the writing that makes Daniel a woyane cadre. He didn’t also mention anyone or group by name. If you see yourself in the analogie and think your thinking process parallels the mules that don’t chew the cud, then that is what you are.

    Sidib min ametaw?

  6. የግጦሽ መሬቱ ድንበሩ እየተሸጠ ያለውን ማህበረሰብ ዝም ካለ ያው የጋማ ከብት መባል ያንሰዋል ባይ ነኝ።

  7. Selam and senu both of you are ye andnet wegenoch nachuh
    so be respectful each other. Here is where tolerance is required.
    Regarding daniel if he is or not woyanie’s cadre share us facts.

  8. I don’t expect this writing from “Deacon”. Who think himself as GOD servant.Human being is always human being even they have different ideology. i don’t see humanity respect in you,why for? I don’t think you are believer if you were,you wouldn’t compare incomparable.Just talk couldn’t make you anything? first know that don’t driven emotionally

  9. ዉድ ወንድማችን ዳንኤል ክብረት የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን።ምድረ ከሃድያን(ፕሮቴስታንት)ምን መልስ አለሽ ስድብ ብቻ

  10. አንዳንድ ሰዎች አራሳቸውን በፅሁፉ ዉስጥ በደንብ አገኙት፡ አዩት በመስታዉት ሰው እራሱን እንደሚያይ፡፡ እና ያዪት መልካቸዉ ለራሳቸው ሲዘገንናቸው መስታዉቱን መራገምና መሳደብ ጀመሩ፡፡ ገራሚ ህብረተሰብ!!

  11. ወዳጄ አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን ስትሰማም ሆነ ሰታነብ፡ መጀመሪያ እራስህን መዝንበት እራስህን እይበት፡፡ ሁሌ ይህ ለእገሌ ነው እያልክ ከሰማህና ካነበብክ ትጠፋለህ፡፡ በአይኑ ምሰሶ ተሸክሞ የሰውን ጉድፍ ላውጣ እንደሚለዉ ሰዉ እነዳትሆን፡፡

  12. ከዚህ ዘመን ሰው ገዳይ ዘረኛ አስመሳይ ጋማከት
    ስንት አገልግሎት የሰጣሉ ውሸታም አስመሳይ

  13. በልዓም ያላየውን አህያ አይታለች ጌታንም
    አጋጉዛለች ዛሬ እኛ ከምንሰራው የባሰ ስህተት
    የለም

  14. እንሰሳን ለሰው እንዲታዘዙ ስላደረጋቸው ለመጥፎ ምሳሌ መሆን የለባቸውም
    እንደሚመቻቸው በሉ አለቀ ሰውም እንደዚያው

  15. Thank you Gelagay,

    I do agree that we all should be respectful to each other.

    What do you mean by Andinet?

    Other than reading a couple of his writings, I don’t know Daniel’s background nor do I want to research about it. I read what is presented to me, evaluate it and comment on it without any bias and prejudice.

    Based on this piece of writing, I see only truth, wit and wisdom in Daniel. If his background speaks otherwise, let people criticize him on that in a separate line.

    I really doubt if some of the critics finish reading the entire article and attempt to first question whether there is any truth in the writing or not. They just rush to stereotype and trash the person. It frustrates and baffles me.

  16. I think Daniel is not a Deacon. He is so disrespectful to himself and humans. He is disrespectful to himself because he pulls out his ink to write without any clue to choice of words. I’m sure an Ethiopian mom has taught what to say in public. But also he exposed himself that he doesn’t have any spiritual upbringing. He vomits this and gets into betemekdes with a priest. Secondly, no human being is a gamakebt. Humans are humans however diverse their thoughts. Hope you won’t come out nacked again.

  17. ማይምነትን በእናቶቻችን ቋንቋ ለመተርጎም ‹የማይለቅም፣ የማያነፍስ፣ የማያበጥር፣ የማይነፋ፤ እንዲሁ የሚያስፈጭና የሚበላ› ማለት ነው፡፡

  18. Mului,
    Daniel rightly compared the lack of critical thinking with the digestive system of unclean animals that don’t chew the cud. It seems to me that he used the correct analogy to describe our ignirance and wickedness. I don’t think the descriptive writing is intended to broadly offend or disrespect humanity. The bible itself contains many parables and verses in which sinners are compared to beasts, loathsome spiders or venomous serpents.
    Here are some examples:

    Psalm 58:4
    They have venom like the venom of a serpent; Like a deaf cobra that stops up its ear.

    Matthew 23:33
    You serpents, you brood of vipers, how will you escape the sentence of hell.

  19. ሞሰብ ብናጣ በአንድ በላን ይባላል!!That is all! ያልገባዉ ለምን ሀሳብ ይሰጣል???

  20. ዲ/ን ዳንኤል በህብረተሰባችን ውስጥ ያለውን ያስተሳሰብ ችግር በትከከል አስቀምጠውታል።ለዚህ ያበቃው ግን
    ሥርዐቱ ነወ።

  21. God create human being different from other animal in many ways, I am not trying to list the human, animal different part in this short writing because there are so many different in their DNA beside the holy bible thought. Even it is not clear who you refer or target. Any way it is not a good compression to animal which are doing differently due to anatomical nature of their organ within them. These abdominal organs difference do not make their brain smarter than others to check out you need to be refer your animal biology. So your analog just shows hate some group the society because they have different view from your view but it does not help anybody including you.
    In fact it is back word and it is not fit in 21 century. Some people using their only analysis by their own reference which is far from the reality. How they pass their message by using realigns venue or community meeting to label some group intentional or unintentional even biologically unacceptable human nature. Example in north west Ethiopia one group of people to other people say that group of people their ancestor came from the son of wood still some people believe that including the victims of the society. I do not mention the ethnics groups because it does not help any of us. So when you write please focus for the mutual benefit of each group to save the union.

  22. May be Daniel himself is tegamakebt. He doesn’t seem to regurgitate his words when spilling dirt on public media. Did you think about that Dan?

    Don’t come again you rubbish!

  23. Gama kebitoch ahunim sayagniku eybelu new! Lezih new Yeminchachut. I respect you and your innovative ideas D/n Dani.

  24. I don’t have the capacity to criticize what is written by Danel. What I can say is we need a lot of people like him, Mesfin Negash, Temesgen Desalegn, Eskinder Nega and so on. They teach us how we should behave and remain rational.

  25. Comrade workers:
    Thank you for coming and
    listening my discourse on
    socialism – communism of karl
    marx, markeshaw.
    Socialism is nationalization =
    consfication of all the means of
    production = of all income
    generating properties, services,
    resources by the government of
    the workers for the common and
    equal use of society.
    Socialism wealth distribution
    principles are:
    1st stage socialism for each
    according to each ability
    2nd stage communism for each
    according to each need.
    Upto now no pure, real socialism
    exists due to u.sa, uk, and other
    capitalist-imperialists fight against
    it, because it is anti- exploitation
    and oppression, e.i., against
    capitalism-imperialism.
    Socialism is equality, justice,
    peace. Humanity, cooperation,
    internationalism, Friendship,
    comradeship, heaven in earth.
    Soon socialism will replace
    capitalism as an unenvitable necessity of human historical development.
    Currently Cuba and north korea
    are relatively near good socialists.

  26. Dani derom achir sew tenkolegna new!

    BANTE BET WEYANE ZELALEMAWI mengist meslohal kk

    enkezaw eyaqaterk bila

    hulun awqalehu kengideh ayseram !

    ZELALEMAWIW EGZEYABHER ; ETHIOPIAN be mihretu yegobgnal

    dane yan qen ke Hizb fet teqerbaleh !!!!!

  27. ተውኝ ወንድሞች ብአዴን የሚባል ድርጅት የለም!
    ቢኖርማ ራሳደጄን ተራራ ወደትግራይ ክልል ሲከለል ለምን የሚል ጥያቄ ያስነሳና መፍትሄ ይፈልግ ነበር
    አማራ አከርካሪው ተመትቶል ኦርቶደክስም፣እስልምናንም ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ በወያኔ ሃይል ተመትቶል
    የብአድን አባላት የሚባሉት ሃይሎች ሆዳሞችና ከርስ አደሮች እና ከዚያ ውጭ ያለ ካለ አርካሪውን በተደጋጋሚ የተመታበት መሆኑን ይታወቃል፡፡
    ሰ.አ

  28. Emebetee titebkh, MEDIHANIALEM Abzto ybarkh.Sintochachn melktun endeteredanw alawkm.Yegama kebt bahri aynurachihu lemn tebaln blo sdb minmalet nw? Sew kalgebaw ategebu kale sew teyko ayredam? Enee D.Daniel betsafew neger ejig tedeschalew.ewnetun lemenager setan enkuan yezih aynet mikr bimekregn salameseginew alalfm.

  29. አፍንጫህ ስር ሁኖ ‘የኢ/ያ በሬ’ ወለደ የሚለዉን ‘ልማታዊ’ ሚዲያ ትተህ ብዙሃንን በደፈናው መተቸት አህያውን ፈርቶ ዳውላዉን … እንደማለት ነው!

  30. ድንቅ አገላለጽ ነው። እስከዛሬ ስፈልገው ነበር። አሁን አገኘሁት። በጣም አመሰግናለሁ። የጋማ ከበት አስተሳሰብ ያለው ምሳሌ፦ የወያኔ ኢህአደግ ካድሬዎች፣ ሀይሌ ገብረስላሴ ፣ ልደቱ አያሌው፣ ስብሀት ነጋ፣ ተፈራ ዋለዋ ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ሚሚ ስብሀቱ፣ ሰይፋ ፋንታሁን ወዘተ ።

  31. Dani- Thank you.
    But, when I see the ideas of people like Mului, et.al, Daniel should have third category of people i.e. Inferior to nonruminants. I know how Daniel cares..

  32. ጉድ ነው ወንድሞች! ሃይሌ ገ/ስላሴ አበደ መሰለኝ? ምን ነካው? ከማንስ ጋር ዋለ ይህ ሰው ሃብት አሳበደው እንደ መቼም ከዘመኑ ሰዎች ጋር አብሮ መዶለት ጀመረ ወይም የማሰቢያው ሶፍትዎር ቀየሩለት
    ለአፍሪካ ድሞክራሲ አያስፈልግም ዋይ !ተው ሃይሌ እንደሰው አስብ አማካሪህንም ምን እየሰራሁ ነው በለው?
    አላህ እንደሰው ያድርግህ ከቻልክ ማሰብ ካልቻልክ ተዎው
    ሰ.አ

  33. ካድሬ ምን አለበት፤ ‹ነው› ከተባለ ነው፣ ‹አይደለም› ከተባለ፣ አይደለም ብሎ ይኖራል

  34. teru eyeta new memeher daniel,zeregnenet ahun ye ethiopia helewena segat new.weyanem sebeke sebekena ahun ራሱ የተከለው በርበረ ኣደገና ኣቃጠለው፡፡endeweyane sra esey yemiasbel neger bihonem,yehager guday selehone gin asasabi new.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*