የጋምቤላ ልዩ ኃይል ትጥቅ ፈታ – VOA

ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ ናቸው የሚባሉት የልዩ ኃይሉ አባላት በክልልሉ ዋና ዋና በሚባሉት አኝዋክና ኝዌር ጎሣቸው ተከፋፍለው መጋጨታቸው የተገለፀ ሲሆን ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ገብተው ሁኔታውን መቆጣጠራቸውን እነዚሁ የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል፡፡
በልዩ አባላት መካከል በተነሣው ግጭት የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ባይኖረንም በግጭቶቹ መካከል ግን ሰሞኑን የአንዲት ጎልማሣ ሴት እና የአንድ አምስት ዓመት ሕፃን ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል፡፡ እስከአሁንም ከዘጠኝ መቶ በላይ የሚሆኑ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ካምፕ መግባታቸውና ቀሪዎቹም አየተፈለጉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ጋምቤላ ክልል ውስጥ ከሰማንያ ሺህ በላይ ስደተኞች በተጠለሉበት ፑኝዶ የስደተኞች ሠፈር ውስጥ በስደተኞች መካከል የተፈጠረ ጎራ የለየ ግጭት እንደነበር ተገልጿል፡፡
ስደተኞቹ በአኝዋክና በኝዌር ጎሣዎች ሠፈሮች የተከፋፈሉ እንደሆኑና ባለፈው ሣምንት ውስጥ ደርሷል ከተባለው ብጥብጥ በኋላ ብዙ ስደተኞች ሠፈሮቻቸውን እየጣሉ ከነዋሪው ጋር ተቀላቅለው እንደነበረ በአካባቢው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀውልናል፡፡
በኢታንግ እና በፑኝዶ ሕዝባዊ የሰላም ስብሰባዎች እየተደረጉ ሲሆን ሁኔታው አሁን ወደ መረጋጋት እየተመለሰና ስደተኞቹም ወደ ሠፈሮቻቸው እየገቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ስለስደተኞቹ ሁኔታ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ቢሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን እንገኛለን፡፡
አትዮጵያ ጋምቤላ ውስጥ ባሉ የስደተኞች ሠፈሮች ከ250 ሺህ በላይ ስደተኞችን አስጠልላ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ ዝርዝሩን ያድምጡ። listen
Laura continua!!!
ነገሩ ቆየ ኢትዮጵያን ከማዳከም አልፈው ዛሬ አማራ፣ኦሮሞ ፣ጋምቤላ ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ሁሉ ሃገር የለውም ከየት እንድመጣ አይተወቅም በትውልድ ሃገሩ እየገደሉት፣እያሰሩት፣እየቀበሩት ይገኛሉ
ለመሆኑ ወያኔ ለምን የኢትዮጵያ ጠላት ሆነ?
ኢትዮጵያን አጥፍተው ፣ሃገር አስገንጥለው ሃብትም ለመሆን ፎቅ ለመስራት አላማቸው ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ለማጥፋት የቤት ስራቸው ከሆነ ሰንብቷ!
1- በአለፈው ገና ሰሞን በዲባይ ከተቃጠለው ሆቴል ውስጥ አንድ የወያኔ ዘራፊ በሆቴሉ ውስጥ ያስቀመጠው 400 000ዶላር(አራት መቶ ሺህ ዶላር) መቃጠሉ ብትሰሙ ይደንቃችሁ ይሆን! የተዘረፈው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰረቀና የተዘረፈ አያጠራጥርም
ሁሉም ይወቀው እላለሁ
ሳ.አ
ወንድም ጅሃር መሃመድ
ጤና ትሆን ዘንድ በአላህ ስም እመኝልሃለሁ!
የኦሮሞ መሬት የኦሮሞ ነው ያልከው አይ አንተ ይች ጉደኛ መሬት ኢትዪጵያ የምተባል እንዳው ዝም እንዳው ዝም ነው ይላል ዘፋኙ
አዎን ኢትዮጵያ የኦሮሞ ናት! ዛሬ ግን አይደለችም ምክንያቱም ሰዎች ሃገራች ከሆነ እናት ከነልጆቾ ስትገደል፣የ7 አመት ሕጻን በቅልብ ወታደር ስትገደል /ሲገደሉ/ እኮ የኦሮማይ ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ሙክታር ከድር ምን እንዳሉ ሰምተህ ከሆነ አላውቅም ለማኝኛውም አንተ በርቀት ስላለህ በኦሮሚያ ወንድሞችና አባቶች፣እህቶች ላይ የተኮሱት ወታደሮች ትክክል ናቸው ነበር ያሉት ገብቶሃል ተጨማሪ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደስአለኝ ፈረንሳ ሃገር ስብሰባ ሂደው በፈረንሳይ የተገደሉትን የፈረንሳይ ዜጎች ሃዘናቸውን ገለጽ እንደ ሰው ሃዘን መግለጽ ትክክል ነው እላለሁ የሚያሳዝነው ወንድም ጅሃር መሃመድ በኦሮሚያ ለተገደሉት ሃዘን መግለጽ አይደለም ወታደሩን በማሞገስ እሰየው ነበር ያሉት እንኮንስ ለኦሮሞ ዜጎች ሃዘናቸውን ሲገልጽ (የኦሮሞ ዜጎች ያልኩት ለአንተ ነው እንጅ ኢትዮጵያዊያን ናቸው በእኔ እምነት ምክንያቱም በአገዚ ወታደር የተገደሉት ወንድሞች እህቶች ነገ የኢትዮጵያ መሪዎች ሃገር አስተዳዳሪዎች ሳይንቲስቶች የሚሆኑትን ታዳጊዎች ተቀጠፉ) ለመጥቀስ ይቻላል
ተጨማሪ አንተ ለአበበ ገላው መልስ መስጠትህ ከሆነ የጸፍከው ስተትህን መረዳት ያንተ ፋንታ ሲሆን አማራ ሲገደል፣ሲባረር፣ ሲጨፈጨፍ፣ሲፈናቀል በአንድ ስብሰባ ላይ የሰማሁትን ልንገርህ የአንድ ድርጅት ስራአስኪያጅ ስም መጥቀስ አያስፈልግም በሌላ ወቅት በዝርዝር እመጣበታለሁ አማራ አለ ሰውየው ከሌሎች ክልሎች የተፈናቀሉት አለ በክብር በመኪና ተዘጋጁቶላቸው ነበር ያለው ይህ ሰው ነገ ወደሕዝብ ይቀላቀላል በወቅቱ የተናገር ወያኔ በል ያለው ለማስተላለፍ አፉ አርቶ/ቀዝኖ/ ነው ሰውየው የኦህደድ አባል ነው ማወቅ ካስፈለገ
ሰ.አ