ኦሮምያ ውስጥ የተወሰደው እርምጃ “ትክክል እንዳልነበረ ባለሥልጣናቱ አምነዋል” – VOA

ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተወሰደው የኃይል እርምጃ “ስህተት መሆኑን የኢትዮጰያ መንግሥት ባለሥልጣናት አምነዋል” ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አስታውቀዋል