ፓትርያርክ አባ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር፣ ለፌዴራል ፖሊስ ከሠሡ !!!
ፓትርያርክ አባ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳን፣ “የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በመጋፋት እና ቤተ ክርስቲያንን በማተራመስ ቀኖና የለሽ ሥርዓት ሲከተል ይስተዋላል፤ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ነው፤” ሲሉ ከሠሡ
ፓትርያርክ አባ ማትያስ ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለሚገኙት ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ መቐለ ለሚገኘው ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአድራሻ በጻፉት ደብዳቤ፤ ማኅበረ ቅዱሳን፣ “የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በመጋፋት እና ቤተ ክርስቲያንን በማተራመስ ቀኖና የለሽ ሥርዓት ሲከተል ይስተዋላል፤ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ነው፤” ሲሉ ከሠሡ፤ የማኅበሩን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘገባ ሰበብ በማድረግ በኮሌጆቹ አንዳንድ አካላት በማኅበሩ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መመሪያ አስተላለፉ፡፡
ፓትርያርኩ በዚኹ የጽሑፍ መመሪያቸው፣ ማኅበሩ ከኦርቶዶክስ ቀኖና ውጭ በመዋቅር ያልታቀፉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እና የተበታተኑ ማኅበራት እንዲፈጠሩ እና ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በየመንደሩ እና በየአዳራሹ እንዲሰበሰቡ በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ ባህልን እንዲለማመዱ፣ እንደዚኹም ከኦርቶዶክስ ቀኖና እንዲያፈነግጡ መጥፎ በር በመክፈት የነገዪቱን ቤተ ክርስቲያን ሰው አልባ የሚያደርግ ኹኔታ ፈጥሯል፤ ሲሉ በርካታ ነጥቦችን ያዘለ ጠንከር ያለ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡
ፓትርያርኩ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር፣ ለፌዴራል ፖሊስ እና ለትግራይ ክልላዊ መንግሥታዊ አካላት ጭምር በግልባጭ ባሳወቁት በዚኹ መመሪያ አዘል ደብዳቤአቸው ማሳረጊያ፣ ለኮሌጆቹ ማሳሰቢያ እና መመሪያ ሰጥተዋል፡- “አኹን እየተከሠተ ያለው ኹኔታ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ስለኾነ የኮሌጆቹን ቀጣይ ህልውና በዘላቂነት ለመጠበቅ የተጠናከረ፣ የተደራጀ እና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራት ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያንና በት/ቤቶቿ ላይ የቀሠራቸውን የጥፋት ጣቶቹን መልሶ ወደ ኪሱ እስኪከትና ለቤተ ክርስቲያን ሉዓላዊ ሕግ ተገዢ እስኪኾን ድረስ የማያቋርጥ ትግል በማድረግ በንቃት መከታተል ይጠበቅባችኋል፡፡ አንድነታችኹን፣ ሃይማኖታችኹንና ሰላማችኹን ከማስጠበቅ ጋር የቤተ ክርስቲያንን አንድነት፣ ሉዓላዊ ክብር እና ህልውና ለማስጠበቅ በምታደርጉት እንቅስቃሴ ኹሉ ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም ከጎናችኹ መኾንዋን በዚኽ አጋጣሚ ልናረጋግጥላችኹ እንወዳለን፤” የተቃውሞ ቅስቀሳ አካሒደውበታል፤ ለእንቅስቃሴውም መጠናከር አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በጉዳዩ ላይ ከሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየቱን ተጠይቆ፣ ዋና ጸሐፊው አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ በሰጡት ምላሽ፤ ፓትርያርኩ ለኮሌጆቹ ጻፉት የተባለው ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ጠቅሰው ነገር ግን በመረጃ ደረጃ ስለ ደብዳቤው መስማታቸውን ገልጸዋል፡፡
በደብዳቤው ስለ ቀረቡት ክሦችም፣ ፓትርያርኩ ማኅበሩን በየጊዜው በሚከሡባቸው ጉዳዮች አመራሩን አቅርበው እንዲያነጋግሩ በተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፤ ነገር ግን እኒኽን ክሦች ለተለያዩ አካላት ማቅረባቸውን ከመቀጠላቸውም አልፈው ማኅበሩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ሥልጣን እንደሚጋፋና ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ እንደሚገኝ፣ መጥቀሳቸው በቅዱስነታቸው ደረጃ የማንጠብቀውና በእጅጉ ያሳዘነን ጉዳይ ነው፤ ብለዋል፡፡
በቅዱስ ሲኖዶስ በ1994 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎና ጸድቆ የተሰጠው መተዳደርያ ደንብ እንዲሻሻልለት ማኅበሩ መጠየቁን ያስታወሱት ዋና ጸሐፊው፤ ቅዱስ ሲኖዶስም በግንቦት 2004 ዓ.ም. ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሕግ ባለሞያዎች እና የማኅበሩ ተወካዮች ያሉበት ኮሚቴ በማቋቋም እንዲሻሻል ወስኖ የማሻሻል ሥራው ተሠርቶ በ2006 ዓ.ም. ተጠናቅቆ ነበር፤ ይኹንና የማኅበሩ አባላት ለምን በኮሚቴ ውስጥ ተካተቱ በሚል ረቂቁ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሳይቀርብ በዚኹ ዓመት ሒደቱ እንዲቆም ተደርጎ የማኅበሩ ተወካዮች ያልተካተቱበት ሌላ ኮሚቴ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. ተቋቁሞ ማሻሻያውን እየሠራ መኾኑን እንደሚያውቁና መረጃውም እንዳላቸው አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
የማኅበሩ ደንብ ተሻሽሎ እስኪጸድቅ ድረስ ማኅበሩ ቀደም ብሎ በነበረው ደንብ የመመራት መብት እንዳለውና ግዴታም እንዳለበት አቶ ተስፋዬ አስገንዝበዋል፡፡ አዲስ በተቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ የማኅበሩ ተወካዮች በሌሉበትና አንዳችም ዕንቅፋት ባልፈጠሩበት ኹኔታ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ማኅበሩ የማሻሻያውን ሒደት ኾን ብሎ ያሰናክላል መባሉ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም፤ ሲሉም አስረድተዋል፡፡
በመተዳደርያ ደንቡ መሠረት ማኅበሩ፣ የአባላቱንና የበጎ አድራጊዎችን የሞያ እና የገንዘብ አስተዋፅኦ በማስተባበር ቅዱሳት መካናት እና የአብነት ት/ቤቶች እንዲደገፉ የማድረግ ተግባር ተሰጥቶት ሳለ፣ ከቤተ ክርስቲያን ሳይጠየቅ እና ሳይፈቀድለት በጣልቃ ገብነት፣ የአብነት መምህራንን፣ ገዳማውያንንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለድብቅ ዓላማው መሣርያ እንዲኾኑ ያታልላል፤ በሚል በፓትርያርኩ ደብዳቤ የቀረበው ክሥ የማኅበሩን አገልግሎት የሚገልጸው አይደለም፤ በማለት አቶ ተስፋዬ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ፣ በፓትርያርኩ በሥራ አስኪያጅነት በተሾመበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በየሰበቡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያካበተ ይገኛል፤ ልጄን በውጭ ሀገር ለማሳከም በሚል ብቻ እንኳ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ከየአድባራቱ ሰብስቧል፤ ይህንንም እስከ 7 ሚሊዮን ብር የማድረስ ውጥን ይዞ እየሠራ ነው፤ ቀደም ሲል፣ ከሥራ አስኪያጅነቱ ጋር ደርቦ በያዘው የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ዋና ጸሐፊነቱም ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ልዩነት በታየበት የሕንፃ ዲዛይን ማሻሻያ ስም ሚሊዮኖችን መዝብሯል፤ ቋሚ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ በመጣስ በደብሩ ከሕንፃ ግንባታ ጋራ በተያያዘ በልማታዊነት ስም የሚፈጽመው አንቃዥነትም በፓትርያርኩ ቡራኬ ጭምር ቀጥሏል፤ ይህም ኾኖ በሀገረ ስብከቱ መልካም አስተዳደር ሰፍኗል በሚል ባለፈው ሰኞ ከፓትርያርኩ ጋራ ተሸላልሟል፤ በዚኹ ዕለትም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የፓትርያርኩ የክሥ እና የቅስቀሳ መመሪያ የተላለፈበትን ደብዳቤ ከኮሌጆቹ ግብረ አበር ሓላፊዎች ጋር አዘጋጅቶ ያቀረበው እርሱ ነው – በተለያዩ ግርዶሾች የከፋ የሙስና ወንጀሉን በመሸፈን የዘረፋና የምዝበራ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ!
ከማኅበሩ የንብረት እና የገንዘብ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ፣ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው ሀብት ያለካርኒ እየሰበሰበና እያደለበ እንደሚገኝ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ተጠቅሷል፡፡ አቶ ተስፋዬ በሰጡት ምላሽ፣ ይህ ክሥ የማኅበሩ የሒሳብ እና የንብረት እንቅስቃሴ ሪፖርት በሚቀርብለት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካል ያልቀረበ፣ ከእውነታው ጋር የሚጋጭ እና ተጨባጭነት የሌለው ነው፤ ብለዋል፡፡ ማኅበሩ በዚኽ ረገድ በሚከተለው ደንባዊ አሠራሩም÷ የአገልግሎት ዕቅዱን በየዓመቱ፣ ክንውኑንም በየመንፈቁ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በማሳወቅ በተሻሻለው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሞዴላሞዴሎች እየተጠቀመ፣ በሕጋዊ ኦዲተር እያስመረመረና ይህንንም ሪፖርት እያደረገ እንደሚገኝ በስፋት አብራርተዋል፡፡
ለፓትርያርኩ ክሥ እና መመሪያ በዋናነት መነሻ የኾነው፣ የስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ የኅዳር አጋማሽ 2008 ዓ.ም. እትም ዘገባ ሲኾን፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ኮሌጆች ውስጥ ከኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በተፃራሪ የሚካሔዱ የኑፋቄ እንቅስቃሴዎችን በማጋለጥ እና በማሳወቅ ላይ ያተኮረ ዘገባ እንደነበር አቶ ተስፋዬ አስታውሰዋል፡፡
ይህ ዘገባ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባዎች በተላለፉ ውሳኔዎች እና የአቋም መግለጫዎች፣ ለማኅበሩም በደንቡ በተሰጠው ድርሻ መሠረት የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ፣ ሥርዓት እና ትውፊት ለመጠበቅ የቀረበ የዕቅበተ እምነት ተግባር እንጂ ኮሌጆቹን በጅምላ በሃይማኖት ሕጸጽ ለመክሠሥ ያለመ እንዳልኾነ፤ ዋና ጸሐፊው ያስረዳሉ፡፡
ማኅበሩ ከአብዛኞቹ የኮሌጆቹ ሓላፊዎች እና መምህራን ጋር ያለው ተቋማዊ ግንኙነት መልካም እንደኾነ የሚገልጹት አቶ ተስፋዬ፣ ልዩነትም ካለ በሃይማኖት አቋም ባለ አሰላለፍ እንደኾነ በአጽንዖት አስቀምጠዋል፡፡ በዘገባው የኮሌጆቹን ስም የሚያጠፋው፣ የራሱን ት/ቤት ሊያስፋፋ ነው፤ ለተባለውም፣ ማኅበረ ቅዱሳን ገዳማትንና የአብነት ት/ቤቶችን ባሉበት፣ እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የነፃ ትምህርት ዕድል ያሉ ፐሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን እየቀረጸ ማኅበራዊ ኑሯቸውን ከመደገፍ በስተቀር እነርሱን የሚያስተምረው ትምህርት የለውም፤ ሲሉ ውንጀላውን ተከላክለዋል፡፡
በአጠቃላይ የስምዓ ጽድቅን ዘገባ መነሻ በማድረግ በማኅበሩ ላይ የቀረቡ ክሦች መሠረተ ቢስ ናቸው ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ ማኅበረ ቅዱሳን፥ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመፈጸም፣ የአባቶችን መመሪያ በመቀበል እና ለአባቶች በመታዘዝ ፣ ቅዱሳት መካናትንና የአብነት ት/ቤቶችን በመደገፍ እና በመጠበቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን ማእከል ያደረገ ጥናትና ምርምር በማካሔድ፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት እንዲኹም በመንግሥት እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግቢ ጉባኤያት ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን አሰባስቦ በሃይማኖት በማነፅ እና በሥነ ምግባር በመቅረፅ ለሀገር እና ለትውልድ የሚተርፍ ታሪክ እየሠራ እንጂ በፓትርያርኩ መመሪያ እንደሰፈረው፣ “ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ” እንዳልኾነ፤ አበክረው ተናግረዋል፡፡
* * *
ፓትርያርኩ፥ የማኅበረ ቅዱሳንን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሚዲያዊ ዘገባ ምክንያት በማድረግ የቀረበበት ክሥና ውንጀላ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ደንባዊ ህልውናውን ክደው የቅስቀሳ መመሪያ ያስተላለፉበትና ለእንቀስቃሴውም አጋርነታቸውን ያረጋገጡበት ደብዳቤ፤
ሰንደቅ ጋዜጣ
የተከበሩ ብጹእ አቡነ ማቲያስ
በዚህ ጉዳይ መሃይምናን የሆን ሶስት የተዋህዶ ልጆች የሆን ሺትዮጵያውያን ስንነጋገር ደብዳቤው ከርስዎ መሆኑን የተጠራጠረም ነበር። ያቀረበውም ምክንያት በሳቸው ስም የሚጠቅሙ ሊኖሩ ይችላሉ እንጂ እንዳንድ ተራ አማኝ እንኳን የማያደርገውን አያደርጉም; ቢያንስ ቢያንስ እንዲህ ባለው ጉዳይ የፖለቲካ አምባገነን መሪ እንኳን ቢሆን በዚህ መልክ አያደርገውም። ቢያንስ ከእምነት የውጣ ተግባር ተፈጽሞ ከሆነ እኮ ሲኖዶሱ ጋር እንጂ ከግለሰብ ጋር መክሮ ወስኖ እንደ መንደር ደብዳቤ መመሪያ የሚሰጥበት አይደለም። ስለዚህ የሳቸው ከሆነም መንግስት ጥንቃቄ ማድረግ ያለበት ይመስለኛል። ማለቴ እንደ ህገ መንግስቱም እንደ ህገ ቤተክርስቲያኑም። የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርንም ለእግዚአብሄር ነውና ።
ሌላው አስተያየት ሲሰጥ አቡኑ በኔ በኩል የጃጁ ይመስልኛል እንጂ ሊስከትለው የሚችለውን አደጋ ሳያጠኑ ይህንን ባላደረጉ ነበር አድርገውት ከሆነ፡ ስለዚህ አሁንም መንግስት ሊጠነቀቅ ይገባዋል። ምናልባት ቢሆን የሚሻለው ሲኖዶሱ እንዳለ የሚግኝበት ኮንፈረንስ የሚመለከታቸው ባሉበት ተክሂዶ በዚህ ጉዳይ ላይ ሲኖዶሱ ቢወስኑበት። ግልጽ ውይይትም በሰፊው በጋዜጦችም ቢካሄድ። የኮንፈረንሱንም ተሳታፊዎች ማህበራቱ ነነጻነት መርጠው የሚልኳችሀው እንጂ በሹማምንት ጥቅሻ ብቻ የሚጋበዙ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ቢደረግ። አለበለዚያ መዘዙ ቀላል ላይሆን ይችላል። ሰዉ በሃይማኖቱ ቀልድ አያውቅምና።
የሶስተኛው ሃሳብ ግን ይለያል። የመንፈሳዊ ኮሌጆቹ ዘመናዊነትን በሃይማኖቱ ሊያሰርጹ ሲፈልጉ ማህበረ ቅዱሳን እንቅፋት እየሆነ ነውና ሃይ ሊባል ይገባል በመንግስትም ቢሆን ይላል።
ለማንኛውም ግን እንደዚህ ባለ ከባድ ጉዳይ የፓትሪያርኩ ወይም በዙሪያቸው ካሉ ጋር ተማክረው የሚያደርጉት ሊሆን አይገባውም። ይህ የያንዳንዱ መእምን እንዲያም ሲል የሲኖዶሱ ጉዳይ ስለሆነ በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባዋል። በህገ ቤተ ክርስቲያኗና በራሷ መእምናን እንጂ ሃይማኖቱን የማይወክል አካል ጣልቃ ገብቶበት የሚያልቅ አይደለም። ለነገሩ ፓትሪያርኩ ተጠሪነታቸው ለሲኖዶሱ መሆኑን እንዴት ይዘነጋሉ።
ነቃ እንበል ጎበዝ። እዚያ ጋ የሆን ነገር ይሸታል።
መሃይምኑ
Please don’t mention the name of other religions institutions, totally it’s internal problem. Ethiopian evangelical Christians are not the cause of disagreement rather it’s corruption!! Do your own job, if you are preaching wrong gospel, people’s are gone.
it is the strategy of TPLF “divide and rule” be aware of that men!!
Targeting Mahibere Kidusan Association as an enemy of the Ethiopian Tewahido Church could be one of the most dangerous moves that the Patriarchate and the politicians will be taking in the history of the country.
It is true that the Association has created a lot of wealth legally that will be deployed for needy Ethiopians. We do not have to forget that the Association has done by way of preserving church antiques, maintaining dilapidated ancient church buildings, etc. everywhere in Ethiopia. Incriminating an association with million membership is a crime by itself. As the head of the patriarchate, Aba Mathias should have defended instead of becoming a government instrument to dissolve the association. I have watched on the Ethiopian TV that some individuals within the church establishment were agitating for the confiscation of the Association’s property. The question will be: who is going to own the property that is estimated to be that is worth billions of birr? the church, the government or high placed politicians…?….?
ብንያም ከዳላስ እንዳሉት ይሄ ይራስ ችግር ነው ንቅዘቱና የመልካም አስተዳደር ችግሩን እንጂ የምልኮውን ጉዳይ ግን ለባለቤቶቹ መተው ይገባል እንላለን ከአኢትዮጵያ።። ንትርክ አያስፈልግም። ግን ማንም ይሁን ማን በማያገባው ከገባ በሳት መጫወት ነው።
ሌላው ግን ሁሉም ባግባቡና በተገቢው አካል እንጂ መእምኑን ያላገለለ በህጉ ካልተፈጸመ አስችጋሪ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል። መእምናን እኮ ለሃይማኖታችን እንጂ ለማንም ጀሌዎች አይደለንም።
ይህች ነገር ተደጋገመች
ክርሥትናውንም እሥልምናውንም እየበጠበጠ ያለው የወያኔ ሥርአት ነው ቄሥ ለመሆን መሥፈርቱ ብሄር መጅሊሥም ለመሆን ብሄር የሚጠየቅበት ሀገር ሆናለች እንኳን ድሥ አላችሁ።
….any way ad news either it is true or fake. on one in orthodox christian will never give up to fight this kind of emotional distraction of millions of followers…. the POP & his synod should think & rethink his decision…
if in case some one or interest group is behind this letter they will enjoy the consequences ….. GOD knows every thing…
የጥቅም ትግል ያለበት መሆኑን ያወቀው ሰይጣኑ ይሁዳ ወያኔ በ39 ብር እየከፋፋለ መሀላችሁ ገብቶ ዳኛ ለመሆን በመብቃቱ ደሥተኛ ነው ይህን የህዝብ ንዋይ ምንጩ ያልታወቀ ብሎ ወያኔ የማህበረ ቅዱሣንን አካውንት ለማሥበርበር ያለመድከም እነሆ አሥር አመታትን ሲያበጣብጥ ያለው ወያኔ ጭራሽ ተሀድሶ ብሎ የካድሬዎች መፈልፈያ ተቋማትና የስላም ትብብር የሚል መፅሀፈ እርኩስ ማሣተሙን አይተናል፥ይህም በዲህ ሣለ 50% በላይ የሚሆኑ አድባራት ንዋዩ ወደ ወያኔ ካዝና እንዳይገባ ፍላጎቱ አላቸው ራሣችንን እናሥተዳድር ነው ይህም በቅድሥት በልደታው የዛሬ 10 አመት አካባቢ የነበረውን ውዥንብር ማሥታወሥ ግድ ይላል ታድያ ማን ነው ለእግዚያብሄር የቆመው? እንዲሁም ማን ነው ለወያኔ የቆመው? ፍርዱን ለእግዚያብሄር ትቼዋለሁ በግሌ ሀለተኛው ካዝና ወያኔ ለሀገር አድን እንቅሥቃሴ እንዳይውል በሚል ማበጣበጡን በሁለቱም ሀይማኖቶች እያየን ነን።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ፖትሪያሊኩ ተጠሪነታቸው ለማን ነው?
Le arba amet le and afta
sayaqom Telatachn yetgrai
woyanie eñan eyegedele
ena agerachn eyaTefat
ygeñal.
Lemedan and bcha mrcha
alen.
Esum: woyanien megdel
new.
Jegnoch, beyalenbet
beyegiziew wedaj meslen
bemeqreb, lemanm
sanasawq bedbq yetgrai
woyanien engdel.
woyaniewochn sngelachew
yeterefut sisheshu weym
siyalqu bcha neTanet ygeñal.
MiTeqmun mesariyana
sltoch. Tyt, bomb, slu
mesariya (goradie, seyf,
meTrebiya, bilawa, Tor,
ankasie), bebox, qomeT,
dngay, merz, maqaTel,
maneq, mafen, wede gedel,
gudguad megefter, kewha
masmeT, bebeshta maslekef
etc new.
Zm blen mawelawel lemaleq
new.
Saichersun qedmen mawdem aleben.
https://youtu.be/VtdumyqQgcs
Mahibere Kidusan – as much as I know it – is the strongest part of the Ethiopian Orthodox Church. The enemies of the church – led by the political elite – won’t sleep until they destroy our church for reasons mentioned in the book written by Ermias Legesse – former cadre and Minister. When you are in to destroying something you focus on the strongest part. That is what is happening. I declined membership so many times. Now, I will do whatever it takes to be a member. I am really sorry to witness such stupidity nonetheless!!!
Mdre menafk mahbere Kdusan ayfersm ! Rasachu yfresna .le enante esat nacew yangebegbuwachal . M.KDUSAN Egziabher ytebkachu .ayzoachu hzbu ke enante gar new .
ፍርድ ለእግዚአብሔር ነው የሚተወው ወይስ ምድራዊ ለሆነ መንግሥት ? ፓትርያሪኩ እውነት ለቤተክርስቲያን ተቆርቁረው ነው? ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተዋለን። ግን አጠገባቸው ያሉትን የመስቀል ሥር ቁማርተኞችን አይከሱም ወይ? እግዚአብሔር የፍትህ አምላክ ነው። አይዘገይም፨
ምንም እንኳ ፓትሪያርኩም አጭበርባሪ ቢሆንም ከፓትሪያርኩ በላይ ማህበረ ቅዱሳን በብዝሃነት ያማያምኑ ለሃጋር ጠንክ ስለሆኑ መክሰሳቸው ተገቢ ነው።
http://www.ethiopiandj.com/2016/01/29/the-ethiopian-government-continues-to-kill-dissidents-dictatorial-already-killed-more-than-150-demonstrators-in-oromo/
These are Weyanes mouth pieces. Remember what SITETA NEGA said “we brock the back bones of AMHARA & ETHIOPIAN ORTHODOX church” so the head of the church & his cares are taking like any weyane officials, the church has its own way of addressing a problem.
But, the monk has been talking like typical weyane cadre “eskedem tebita” I hope
the outcome this mess will expose the so called Aba Mathias.
GOD BLESS OUR CHURCH
ፓትርያርኩ ምን አይነት ስልጣን አለውና ነው በሃይማኖት ጣልቃ ገብቶ የሚከሰው እራሱ ጳጳሱ የኦርቶዶክስን ህግ ተከትሎ ነወይ ስልጣን ላይ የተኮፈሰው ለምን መጀመሪያ እራሳችሁን አታውቁም ለብነት መሆኑንስ እንደት አትረዱም ቁሻሾች ይሀ ሞጥማጣ ቄስ ደግሞ ዝም ብሎ ይወሻክታል ሌባ
ፈጣሪ ይቅር የማይለው ሀጣያት እየሰራ ያለው ማን ይሆን!!!!!!????
Shame on our spiritual leaders. They are politicians and trying to do things not in Christanity way but rather through TPLF Force.
በእርግጥ ቆብ የደፋ የጠለቀ ሁሉ ህገ እግዚአብሔርን ተከትሎአል ማለት አይደለም በተለይም ኤንደ ምቱር አባ ማትያስ ያለ ይሁዳም ከደቀመዝምርቱ ጋር ተቆጥሮነአልና አንድ ናቸው፡፡ኃይላቸው አድርገዉ ያመኑት የፈጠሩአቸውን አባ ፀሀዬን ነውና እኛም ኃይላችን መከታችን መድኃኒአለም እየሱስ ክርነስቶስ ነዉና የዳዊትን ወንጭፍና ጠጠር ይዘን እንጠብቃቸዋለን፡፡የሚያደርግ ፉከራ አያበዛምና ምቱር አባ ማትያስ ኃይላችንን የእምነታችን ፅናት መለኪያ ነውና ስራችን ለትውል አብነት ነውና እባክዎትን አጋዚን ይዘው ይነሱ፣ የዬዳት ጉዲትን ፡የሙሴን ታሪክ ያንብቡ ያስተውሉ ጥቂት ግዜአልዎት ሁላችንም የማህበረ ቅዱሳን ልጆቾች ለመስዋእትነት ስግጁ ነን የአባቶች አደሪም አለብን፡፡ወኔዎ የአጏነዚ ጦር ነውና ይሞጡ፡፡የሚሰራዉን የሚያቅ ወሬ አያበዛም፡፡ ምቲር ምቲር አባ ማትያስ የዘመኑ ዮዲት ጉዲት አልያም ግራኝ አህመድ፡፡
Let’s have God intervene on this, God has an answer for everything. Mehabera Kidusen is stronger than Tahadeso’s Propaganda. God bless you Mehabera Kidusen, my prayer is with you. You will go through it like everything else.
One of your supporter from North America,
ወያኔና ተሃድሶ ብር ወዳጆች ናቸው ጥፋትን እንጂ እድገትን እውነትን አይወዱም ኮሌጁ ካድሬዎችን ስለሚያስመርቅ ስለተነቃባቸው ነው የአብነት ትምህርት ቤቶቹን ታዲያ ቤተክህነት ካላቀናች ሊላ የሚያቀናው ሲመጣ ምነው ተናደዱ እነሱ ያልሰሩትን የሚሰራ ሲገኝ ተናደው ነው የተሃድሶንም አከርካሪ እየመታ ያለው ማሃበሩ ስለሆነ ጠልተዋቸው ነው ማሃበሩ እኮ ዛሬ አልተፈጠረም ዝም ብለው ምናለ እየዘረፉ ቢኖሩ ማሃበሩን ለቀቅ ያርጉት ኦርቶዶክስን እያንዳችንን መንካት ማለት ነው ገዳማትን ማፍረስ፣ ስርአትን ማጥፋት መናፍቅን ማስፋፋት፣ ግብረሶዶምን ማምጣትና በጠቅላላው ኢትዮዽያን ማጥፋት ፈልገው ነውና እንንቃ እሄን ሁሉ ደብዳቤ ማደል ምን ይባላል መንግስትስ ምን አገባው? ስለዚህ በሀይማኖታች ነፃነት ሊነፍጉን ነው አዲሱስ ትውልድ ምን ይማር ነውስ እንደዚህ አገር ባህል መናር ይሻለናል? ቀጥሎ ሳር መጋጥ መፈንገል እረስንቱ ብቻ የመጣውን መአት አምላክ ይመልሰው እንፀልይ እኔን አይመለከተኝም አንበል ተዋህዶን ሊያጠፉ ነው የተነሱት በረሮዎቹ!!!!
ወያኔና ተሃድሶ ብር ወዳጆች ናቸው ጥፋትን እንጂ እድገትን እውነትን አይወዱም ኮሌጁ ካድሬዎችን ስለሚያስመርቅ ስለተነቃባቸው ነው የአብነት ትምህርት ቤቶቹን ታዲያ ቤተክህነት ካላቀናች ሊላ የሚያቀናው ሲመጣ ምነው ተናደዱ እነሱ ያልሰሩትን የሚሰራ ሲገኝ ተናደው ነው የተሃድሶንም አከርካሪ እየመታ ያለው ማሃበሩ ስለሆነ ጠልተዋቸው ነው ማሃበሩ እኮ ዛሬ አልተፈጠረም ዝም ብለው ምናለ እየዘረፉ ቢኖሩ ማሃበሩን ለቀቅ ያርጉት ኦርቶዶክስን እያንዳችንን መንካት ማለት ነው ገዳማትን ማፍረስ፣ ስርአትን ማጥፋት መናፍቅን ማስፋፋት፣ ግብረሶዶምን ማምጣትና በጠቅላላው ኢትዮዽያን ማጥፋት ፈልገው ነውና እንንቃ እሄን ሁሉ ደብዳቤ ማደል ምን ይባላል መንግስትስ ምን አገባው? ስለዚህ በሀይማኖታች ነፃነት ሊነፍጉን ነው አዲሱስ ትውልድ ምን ይማር ነውስ እንደዚህ አገር ባህል መናር ይሻለናል? ቀጥሎ ሳር መጋጥ መፈንገል እረስንቱ ብቻ የመጣውን መአት አምላክ ይመልሰው እንፀልይ እኔን አይመለከተኝም አንበል ተዋህዶን ሊያጠፉ ነው የተነሱት በረሮዎቹ።
MK is the day light group of teft and unti orthodox in the name of EOTC . His holiness is 100% right. This illegal organisation stealing the asset of the church illegaly for the interest of one particular group must be stop! MK is drivel mement!!