መተባበር በተግባር

Ethiopia Oromo students protest addis ababa plan. የኦሮሞ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ያሰሙት ተቃውሞይገረም አለሙ

በሀገር ውስጥም በውጪም ቁጥራው እጅግ የበዛ ተግባራቸው ግን ብዙም የማይታይ ፓርቲዎች አሉ። እነዚህ የሚችሉት ተዋህደው አንድ በመሆን፤ የማይችሉት ተባብረው ትብብርም ይሁን ግንባር በመፍጠር የነጻነት ቀናችንን ለማፋጠን የሚያስችል ትግል ያደርጉ ዘንድ ስንመኝ፣ ስንጠይቅ፣ ስንማጸን፣ ይህን ባለማድረጋቸውም ስንኮንን ወዘተ ዓመታት ተቆጥረዋል። እነርሱ ግን መተባበሩ ቀርቶ መከባበሩ አልሆን ብሎአቸው፣ ተደጋግፎ መቆሙ ቢቀር አንዱ ለአንዱ እንቅፋት ከመሆን መቆጠብ ተስኖአቸው ወያኔ ያሻውን እንዳሻውና ባሰኘው መንገድና ግዜ እየፈጸመ ከዚህ እንዲደርስ አድርገውታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …