ስደት የፍርሃት ውጤት ነው

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Bewketu Seyoum and Yared Tibebu በእውቀቱ ሥዩም እና ያሬድ ጥበቡ

ከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል። አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ”ነጻነት” የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል። እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም።

ሙሉውን አስነብበኝ …